በጥር ወር 22/2012 እንቆሳዛና ድላሚኒ ዙማ( Nkosazana Dlamini zuma ) የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነዉ ነበር፡ በተመሳሳይ ቀን ግዜና ወቅት የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ቢሮ የግድያ ሙከራ እንደሚደረግ መረጃ ማግኘቱን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ፍንጭ ሰጠ ከዚያም በፍጥነት በኢትዮጵያ የሚገኘዉ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ለድላሚኒ ዙማ የጥበቃ ለዉጥ እንደሚደረግ አስታወቀ።
የደቡብ አፍሪካ የደህንነት መረብ የደረሰዉ መረጃ በሁለት ቀናት ዉስጥ የግድያ ሙከራ ሊደረግ እንደሚችል የሚያሳይ በመሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ የስለላ መረብ አናት ለኢትዮጵያ የደህንነት ሐላፊ መልእክት አስተላለፈ ከሰሐታት ቆይታ በኃላ ተመላሽ መልእክት ከኢትዮጵያ የደህነት ክንፍ ወደ ደቡብ አፍሪካዉ ተወረወረ በዚህም መሰረት አራት ተጨማሪ የግል ጠባቂዎችን ወደ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበሯ ሆቴል ተላከላት።
በጠዋቱ የተጀመረዉ ከባድ ጥበቃ ተጠናክሮ ቀጠለ የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ክንፍ የበላይ ወደ ከሰሐቱ አካባቢ የሐገሪቱን ወታደራዊ ደህንነት ክንፍ ጄኔራል ቲ. ኘየቤን ( general T.Nyaembe ) አካቶ ስብሰባ ተቀመጠ በስብሰባዉም ዉስጥ ስሙ ያልተጠቀሰ ሐገር ከግድያ ሙከራዉ ጀርባ መኖሩን ለመወያያ ሲቀርብ የግድያ ሙከራዉ በጥንቃቄ እንዲታይ ጥሪ ተላለፈ።
በመቀጠል የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ክንፍ በአፍሪካ ህብረቱ ሊቀምነበር ዙሪያ ላይ በሚደረገዉ የጥበቃ እና የደህንነት ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ ላይ እምነት እንዳጣ አረጋገጠ።
እለቱ እንደተገመተዉ አደጋ ሳይፈጸምበት አለፈ በሚቀጥለዉ ቀን ጠዋት የኢትዮጵያ እና የደቡብ አፍሪካ አቻዎች ተገናኝተዉ ተወያዩ በኢትዮጵያ በኩል ሱዳን ከግድያ ሙከራዉ ጀርባ መኖርዋን ለደቡብ አፍሪካ አቻ ፍንጭ ተሰጠ።
የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ዳይሬክተር የደህንነት ክፍል ( Ethiopia’s National Intelligence And Security Service) NISS. ዳይሬክተር ሃድራ አበራ የግድያ ሙከራዉ በሱዳን መግቢያዎች በኩል የተደረገን ከፍተኛ ክትትል ተንተርሶ ምንም አይነት ፍንጭ እንዳልተገኘ ስትገለጽ ከዚህ ቀደም በሆስኒ ሙባረክ ላይ እ.ኢ.አ በ1987/ እ.ኤ.አ በ1995 የተደረገዉን ሙከራ በምሳሌነት አስቀመጠች በደቡብ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ በኩል በሐድራ አበራ የቀን አቀመማጥ ላይ አለመስማምት ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን አሁን በድጋሚ ነገሮችን በጥንቃቄ መመልከት የሚያስችሉ ሁኔታዎች እየጎሉ ይገኛሉ።
ከላይ የቀረበዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በኢትዮጵያ በኩል ጎረቤት ሐገራትን ለማጥቃት ሆን ተብለዉ ለተለያዩ ሐገር የደህንነት ክፍሎች በዲፕሎማቶች ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ ፍንጭ የመስጠትና ከኢትዮጵያ ጋር በአመለካከት የተለያዩ ሐገራትን ተጠርጣሪነት በአለም አቀፍ ደረጃ የማብዛት ሴራ መኖሩን የሚያመላክት ሲሆን ጉዳዩ እንደ አዲስ በጥንቃቄና በከፍተኛ የአፍሪካ ህብረት ደህንነቶች ተይዞ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ የዉስጥ ምንጫችን ጠቁመዋል።
ይህንን አስመልክቶ በከፊሉ በ25/የካቲት/2015 አል-ጀዚራ የዘገበ መሆኑ የሚታወስ ነዉ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
↧
መረጃ –የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ላይ የግድያ ሙከራ! (spy cable revel) – ሉኡል አለሜ
↧