Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ – ዮሐንስ አማረ

$
0
0

ሰሞኑን ከቆሼ ዘግናኝ አደጋ ጋር ተያይዞ አጋጣሚው የፖለቲካ ሰርግና ምላሽ የሆነላቸው የኦሮሞ ብሄርተኞች እንደተለመደው የአዲስ አበባን የባለቤትነት ጥያቄ በማንሳት አዲስ አበባ የኦሮሞ እንደሆነችና ወደ ኦሮሚያ ብትጠቃለል የቆሻሻ መድፊያ ችግር እንደማይኖር ብሎም አደጋውም ላይደርስ ይችል እንደነበር ሊነግሩን እየሞከሩ ነው። ይህ ትንኮሳቸው አዲስ ነገር ባይሆንም አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ አንድ ነገር በተነሳ ቁጥር በየጊዜው የውሸት የባለቤትነት ጥያቄ እያነሱ የመነታረኪያ መንገድ ማድረጋቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ግራ እንዲጋቡ ምክንያት መሆኑ አልቀረም። የዚህ ጽሁፍ አላማ የአዲስ አበባን የሸዋ አማራነት ከህጋዊ እና ታሪካዊ መስፈርቶች አንጻር ቀናኢ ለሆኑ ጥቂት ኦሮሞዎች (ካሉ ማለቴ ነው) እና ለሰፊው የአማራ ህዝብ ማስረዳት ሲሆን እያንዳንዱ አማራ የራሱን ህዝብ፤ መሬት እና እሴት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ጥቆማ በመስጠት ለሚመጣው በጎም ሆነ ክፉ ነገር ራሱን እንዲያዘጋጅ ለማስገንዘብ ያክል ነው!

አዲስ አበባ ከተማ ከጥንትም ጀምሮ የሸዋ አማራ መሆኗ ጸሃይ የሞቀው ሃገር ያወቀው እውነታ ነው። አዲስ አበባ የአማራ ናት ስንል መሰረታዊ ማሳያዎቻችን ሞራላዊ፤ ህጋዊ እና ታሪካዊ ኩነቶችን ናቸው እንጂ የቀን ህልም እያለምን አሊያም በስሜት ተነስተን አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እሮሮ የሚሰማውከላይ እንደናገርኩት ከ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን ጋር በሚደረግ ክርክር ሲሆን ዋና መከራከሪያ ሃሳባቸውም አዲስ አበባ የ’ኦሮሞ’ እንጂ የማንም አይደለችም፤ አዲስ አበባ የአማራ የሆነችውም ከአጼሚኒሊክ ‘ቅኝ ግዛት በኋላ ነው’ የሚል ነው። በዚህ እና በሌሎች ጉዳይ ላይ ከ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን ጋ ተነጋግሮ መግባባት የማይቻለው በሁለት ዋና ዋና አበይት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው ቅድመ – ሚኒሊክ ታሪካዊ ክስተቶችን መስማትም ሆነ ማየት አይፈልጉም፤ ሁለተኛ ህዋሃት ያመጣውን የብሄር ፌድራሊዝም ግዛት አከላለልን እንደ አለምአቀፍ ህግ አድርገው መቀበላቸው ነው። እስኪ ሁለቱን ነጥቦች አንድ በአንድ እንያቸው።

የመጀመሪያው እና ከ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን ጋር መግባባት የሚያስቸግረው ምንጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያ ታሪክ የ100 አመት በመሆኑ ቅድመ ሚኒሊክ ታሪክን ለዛሬው ማህበረ-ፖለቲካዊ መስተጋብራችን መጠቀም ፋይዳ የለውም የሚል ነው። በእነሱ አባባል ከአጼ ሚኒሊክ ሃገር ግንባታ ዘመቻ በፊት (ከ1890ዎቹ በፊት) ‘ኦሮሚያ’ ራሷን የቻለች እና መና የሚታፈስባት እንዲሁም በገዳ ዲሞክራሲ የአለም ቁንጮ የነበረችበት ወቅት ነው የሚል ነጭ ውሸት ለትውልዱ በማስተማር ሌላውን ‘አቢሲኒያ እና መጤ’ አድርጎ የመሳል አባዜ ነው። ይህ አዲስ የፖለቲካ መቀስቀሻ መንገድ የቁቤ ትውልድ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ማህበረ-ፖለቲካ ኩነት አባቶቻቸው በ’ኦሮሞ’ ወረራ /Oromo invasion/ ወቅት በነባር ህዝቦች ላይ የፈጸሙትን ወረራ እና እልቂት በመካድ የባእድነት እና የወራሪነት ስሜት እንዳይሰማው ብሎም የባለቤትነት እና የነባርነት ስነልቦናን እንዲገነባ ለማድረግ ነው።

እውነታው ግን ከ1520ዎች በፊት ‘ኦሮሞ” የሚባል ህዝብ በኢትዮጵያ ምድር አለመኖሩ እና አለመታወቁ ነው (ከታች ያለውን ምስል ይመልከቱ)። ሲጀመር ‘ኦሮሞ’ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በጀርመኑ ፕሮቴስታንት ቄስ በJohann Ludwig Krapf አማካኝነት ለስብከት በመጣበት ወቅት ነው። ታሪካዊ እና እውነተኛ ስያሜያቸው ዛሬ ሊጠሩበት የማይፈልጉት ጋላ ነው። ይህንን ታሪካዊ እውነታ የምንናገረው በደንብ የተሰነዱ መዛግብትን አገላብጠን እንጂ ጠንቁለን አይደለም። Greater Ethiopia: The Evolution of a Multiethnic Society በሚለው መጻሃፋቸው በገጽ 78 ላይ አሜሪካዊው ተመራማሪ ዶናልድ ሌቪን እንዲህ ይላሉ “የመጀመሪያው ‘የጋላ’ እንቅስቃሴ የተጀመረው በ1520ዎች ሲሆን መጀመሪያ ላይ ባሌን ወረሩ፤ ቀጥለው ዋቢሸበሌን ተሻግረው ዳዋሮን ወረሩ። በ1540ዎቹ እና 50ዎቹ ደግሞ ፋጢጋር እና ሸዋን ወረሩ። በ1567 በሃረር ‘ከፍተኛ ወረራ ወይንም devastating raid’ አካሄዱ። ሌሎቹ የ’ኦሮሞ’ ጎሳዎች ደግሞ ወደ ሰሜን በመግፋት አማራን በተለይም አንጎት/ራያ/ እና ቤጌምድርን ወረሩ። በ16ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ላይም ወደ ቤጌምድር፤ ደምቢያን እና ጎጃም ተስፋፉ። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ጎሳዎቻቸው ወደ ትልቁ ስምጥ ሸለቆ፤ ዋጂ፤ ጊቤ ወንዝ፤ ዳሞት እና ጎጃም ከፍተኛ ወረራ ፈጸሙ ” ይላሉ። ስለዚህም ኦሮሞዎች መሃል አዲስ አበባ ይቅርና የራሳችን ነው የሚሉት ባሌ እና ወለጋ እንኳ የነባር ህዝቦች ምድር እንደነበረ መረዳት ያሻል። እና ይህንን ታሪካዊ እውነታ እየካዱ ሌላውን በወራሪነት በመፈረጅ አዲስ አበባ የእኔ ናት ማለት በየትኛው የሞራል ልእልና፤ የህግ አግባብ እና የታሪክ ማስረጃ ይሆን?

ሁለተኛው የ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን ስህተት ህዋሃት የከለለላቸውን የብሄር ፌድራሊዝምን ግዛት እንደ አለም አቀፍ ህግ አምነው መቀበላቸው ነው። ህዋሃት ለአስተዳደር እንዲመቸው የህዝብን ፍላጎት፤ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥን እና ታሪካዊ ጉዳዮችን ወደ ጎን በማለት በፖለቲካዊ ውሳኔዎች ህዝብን የሚያስቆጣ ድርጊት ማድረጉ አዲስ ነገር አይደለም። በተለይም ይህ የፖለቲካ ቁማር አማራ ላይ ሲሆን ይበረታል። የአማራ ግዛቶችን ወልቃይት ጠገዴን እና ራያን ወደ ትግራይ እንዲሁም መተከልን ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ የከለለው ታሪካዊ ሁነቶችን እና የህዝብን ፍላጎት አክብሮ ሳይሆን ወቅቱ በፈቀደለት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስልጣን አማራን የማዳከም ስትራቴጂ ነው። የአዲስ አበባ ሁኔታም የተለየ አይደለም። በታሪክ የሸዋ ግዛት እንደሆነ እየታወቀ እና ከ50% በላይ የከተማዋ ነዋሪ ምንም ቅልቅል የሌለበት ንጹህ አማራ እንደሆነ እየታወቀ ኢህጋዊ በሆነ መንገድ ከተማዋ የኦሮሞ ናት ማለት ህመም እንጂ ጤነኝነት አይደለም። ይህ ደግሞ ፖለቲካዊ ውሳኔ መሆኑን የምንረዳው ህዋሃት በ1997ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ በምርጫ በተሸነፈበት ወቅት በአንድ ጀምበር የኦሮሚያ ዋና ከተማን ከአዲስ አበባ ወደ ናዝሬት ያደረገበት መንገድን መረዳት በቂ ነው። መልእክቱ አዲስ አበባን ለእናንተ የሰጠኋችሁ ከአማራ የስልጣን ሽሚያ እንድትጠብቁኝ እንጂ ዋና ከተማችሁማ ናዝሬት ነው ለማለት ነበር። የዚያ ድርጊት ዋና አላማም በአማራ እና ‘ኦሮሞ’ መካከል ግጭት በመፍጠር ገላጋይ ሆኖ መሃል ላይ ስልጣን ወንበሩን ማደላደል ነበር።

ህዋሃት ራሱ ህገመንግስት ላይ የጻፈውን የብሄር ፌድራሊዝም አከላለል መስፈርቶችን ማለትም ስነልቦና፤ ታሪክ፤ ባህል እንዲሁም ቋንቋን ወደ ጎን በመተው ነው እንግዲህ አዲስ አበባ የ’ኦሮሞ’ ናት ብሎ የወሰነው። ቀደም ብየ እንደገለጽኩት በታሪካዊ ሰነዶች አዲስ አበባ የአማራ እንጂ የ’ኦሮሞ’ እንዳልሆነች እየታወቀ፤ ስነልቦናው አማራዊ እንጂ ‘ኦሮሞ’ እንዳልሆነ እየታወቀ፤ ባህሉ ሙሉ በሙሉ አማራዊ እንጂ የ’ኦሮሞ’ እንዳልሆነ እየታወቀ እና የከተማዋ ቋንቋ መሉ በሙሉ አማርኛ ሆኖ ሳለ ከተማዋ የ’ኦሮሞ’ ናት ማለት ከፖለቲካዊ ስሜት ውጭ ምንም አይነት ህዝባዊም ሆነ ታሪካዊ አምክንዮ የለውም። ሃገር ማለት ህዝብ ነው ብሎ የሚደሰኩሩ የህዋሃትም ሆነ የ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን የአዲስ አበባ ህዝብ ፍላጎትን እና ስሜትን ግን የማንበብ ፍላጎት ሆነ ችሎታው ያላቸው አይመስልም።

ለማጠቃለል ያክል
ነባሩ የአማራ ትውልድ የኢትዮጵያዊነት አቀንቃኝ ስለነበር አዲስ አበባ ቀርቶ ባህርዳርም ሆነ ደብረማርቆስ የ’ኦሮሞ’ አልያ የትግሬ ቢሆኑ ግድ አልነበረውም። ይህም ከዘር በላይ ሰብአዊነትን ስለሚያስቀድም እና መርሁ አድርጎ ስለሚኖር ነበር። አዲስ አበባም የ’ኦሮሚያ’ ናት ሲባል ብዙሃኑ አማራ ከምንም ያልቆጠረው ‘ኦሮሚያም’ ኢትዮጵያ ናት በሚል ሆደሰፊነት ነበር። ይህንን ሆደሰፊነት ግን በተሳሳተ መልክ በመረዳት የ’ኦሮሞ’ ሊሂቃን ትውልዳቸውን አዲስ አበባ የ’ኦሮሚያ’ መሆኗን በመንገር ታሪካዊ ውሸቱን ወቅታዊ እውነት ለማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል። ነገር ግን አዲሱ የአማራ ትውልድ ይህንን ፈጽሞ አይቀበልም። ታሪኩን እና ህግን ጠንቅቆ ለሚረዳው አዲሱ የአማራ ትውልድ ይህ ያረጀ ያፈጀ የኢትዮጵያዊነት አካሄድ እና የኦነግ ብልጠት የትም እንደማያዳረስ በደንብ ይገነዘባል። የአዲስ አበባ አማራነትም ነገም እንደ ትላንቱ ለዘላለም ተረጋግጦ ይኖራል!

ማስታወሻ
(የመጀመሪያው ገጽ’ኦሮሞዎች’ ወደ መሃል ኢትዮጵያ ከመፍለሳቸው በፊት በመላው ሸዋ እና አጎራባች ክፍለሃገሮች ይኖሩ የነበሩ ነባር ህዝቦችን ያመላክታል። ሁለተኛው ደግሞ የኦሮሞን የወረራ ታሪክ)

አማራዊ ብሄርተኝነት የሰፊው አማራ ህዝብ ፈውስ ነው!

(YohannesAmhara የሳምንቱን የኦነግ ግርግር ውሃ ቸለስክበት።እዙዚአብሄር ይባብክህ)

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265