Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all 2265 articles
Browse latest View live

የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ስርጭት ሆን ተብሎ እየታፈነ ነው

$
0
0

የዶይቼ ቬለ የአማርኛው ስርጭት መታፈን

ኢትዮጵያ | DW.COM | 29.09.2016

የዶይቼ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ  ሆን ተብሎ እየታፈነ ወይም እየታወከ መሆኑ  ተገለጸ። የመሥሪያ ቤቱ የቴክኒክ ባለሙያዎች እንደረሱበት፣ ስርጭቱ የሚታወክበት ቦታ እና የጊዜ ርዝመት የተለያየ መልክ አለው።
dw-amharic-satenaw-news ስርጭቱ ቀደም ባሉ ዓመታት ተመሳሳይ እወካ ደርሶበት የነበረ ሲሆን፣ የመብት ተሟጋቾች እወካውን የሚፈጽመው የኢትዮጵያ መንግሥት ነው በሚል መክሰሳቸው አይዘነጋም። ዶይቸ ቬለ ይህን ችግር በተመለከተ ቅሬታውን ለኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያቀርብ ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
የዶይቼ ቬለ የአማርኛ ስርጭት ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ  የድምፅ መታፈን/መታወክ ወይም ጃሚንግ እንዳገጠመው የቴክኒክ ክፍል ኃላፊዎች አስታውቀዋል። እወካው መኖሩንም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ አድማጮቻችንም በሚልኩልን መልዕክቶች አረጋግጠውልናል። የአማርኛዉ ዝግጅት በሚሰራጩባቸዉ የአጭር ሞገድ መስመሮች ላይ እየደረሰ ያለው መታወክ ወይም ጃሚንጉ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሳይሆን እንዳልቀረ የስርጭቱን ጥራት እና ሽፋንን የሚከታተሉት የዶይቸ ቬለ የቴክኒክ ባለሙያው ሁበርት ቻያ ገልጸዋል።

«  ከተሞክሮ ለመናገር የምንችለው፣ ይህ ረባሽ ድምፅ ወይም እወካ በተወሰነ የስርጭቱ ወቅት ስለሆነ የሚሰማው፣ ሆን ተብሎ የሚደረግ ነው ብለን እናስባለን። ይህ እወካ በተለይ፣ ለምሳሌ ዜናን ወይም እንዲሰሙ የማይፈለጉ ዘገባዎችን ይመለከታል። »

የእወካው ዓይነት የተለያየ መልክ እንዳለው ብሎም ፣ አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ፣ ሌላ ጊዜ አለፍ አለፍ ብሎ እንደሚቋረጥ ወይም ስርጭቱን የሚረብሽ ድምፅ እንደሚሰማበት ነው ባለሙያው ያስታወቁት። ለዚህም ባለሙያው የሚሰጡት ምክንያት፣

« የሚያውክው ወገን ስርጭቱን በጠቅላላ ወይም የተወሰነውን ክፍሉን ማወክ የሚያስችለው በቂ አቅም የለውም። ስለዚህ በርግጠኝነት ውጤታማ ለመሆን የተወሰኑ ይዘቶችን ለተወሰኑ ደቂቃዎች እየመረጠ  ያውካል። »
የመታፈን ወይም የመታወክ እጣ ሲገጥመው የመጀመሪያው ጊዜ ያልሆነው የዶይቸ ቬለ የአማርኛው ስርጭት ካሁን ቀደም ለገጠመው አፈና ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግሥት ሳይሆን እንዳልቀረ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት  «ሂውመን ራይትስ ዎች» ያወጣቸው ዘገባዎችም ይህንኑ  ይጠቁማሉ

ለተወሰነ ጊዜ ከአፈና ነፃ ሆኖ ከቆየው በኋላ አሁን  እንደገና ለገጠመው የመታፈን ችግር  ለስርጭቱ መታፈኑ ምክንያቱ በርግጠኝነት ይህ ነው ብሎ ለመናገር ባይቻልም፣  እንደ ዶይቸ ቬለ የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ሚስተር ክላውስ ሽቴከር ግምት፣ ከጥቂት ወራት ወዲህ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተነሳው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

« የኢትዮጵያ ባለስልጣን መሥሪያ ቤት ስርጭቱን እንዲያፍን ያነሳሳውን ምክንያት በተመለከተ ግምት ብቻ ነው ልንሰጥ የምንችለው። ይሁንና፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ከተነሳው እና ከ400 የሚበልጡ ሰዎች ሕይወት ካለፈበት ግጭት በኋላ የጃሚንግ እና ሆን ተብሎ የሚደረገው የማወክ ተግባር ጨምሮዋል። እና  የስርጭቱ መታወክ በመንግሥት ጭቆና ፣ እንዲሁም፣ ተጓድሎ በሚገኘው ፖለቲካዊ ተሀድሶ ሰበብ በተለይ በወጣቱ ዘንድ ስለሚታየው ቅሬታ ከምናቀርባቸው ዘገባዎች ጋር የተያያዘ ነው ብለን እንጠረጥራለን። መንግሥት በዘገባዎቹ ደስተኛ አይደለም። ነገር ግን ይህ ሚዛናዊ የሆነ የዘገባ አቀራረብ ሥራችን አንድ አካል ነው። »
ዶይቸ ቬለ የሰሞኑን የስርጭት መታወክ/ ጃሚንግን በተመለከተ፣ ካሁን ቀደም ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው እንዳደረገው ሁሉ፣ አሁንም ቅሬታውን  ለኢትዮጵያ መንግሥት የማቅረብ እቅድ እንዳለው ሚስተር ክላውስ ሽቴከር ገልጸዋል።
« በአዲስ አበባ የጀርመን አምባሳደር በተገኙበት አንድ ስብሰባ ወቅት የስርጭት አፈና ጃሚንግ ድጋሚ ሥራ ላይ እንደማይውል ከኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሚንስቴር ዋስትና አግኝተን ነበር። እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለ ጃሚንግ እንዲህ በግልጽ ሲነገር ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር። እና በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የሚሰራበት ዘዴ በዚሁ አብቅቷል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። ግን ይህ ቃላቸው/ዋስት አለመከበሩን ነው አሁን ያየነው። በዚህም የተነሳ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት፣ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝታቸው ወቅት ስለዚሁ ጉዳይ  ከከፍተኞቹ ባለስልጣናት ጋር አንስተው እንዲወያዩበት የመራሒተ መንግሥቷን ጽሕፈት ቤት እንጠይቃለን። የስርጭት አፈና/እወካ ከጊዜው ጋር የሚሄድ አይደለም። እኛ የኢትዮጵያንም መንግሥት ሆነ ሕዝብ ለመጉዳት አንፈልግም። ሚዛናዊ  የሆነ መረጃ ማቅረብ ብቻ ነው የምንፈልገው። እና በዚሁ ሥራችንም ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ወደፊት እንደማያውከን ተስፋ እናደርጋለን።
»አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ

የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ወያኔ በኮሚቴዎች ላይ የሽብር ክስ መስርቷል

$
0
0

የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ወያኔ በኮሚቴዎች ላይ የሽብር ክስ መስርቷል። የአማራ ተጋድሎ ወያኔን ካላጠፋ የማይቆም ነበልባል እሳት መሆኑን አላወቁቱም!!

#የአማራተጋድሎ

14502828_1318610204830256_4850974451050126063_n

“አባታችን ስንለው ልጆቼ የሚለን እረኛ አግኝተናል” [መልካሙ በየነ]

$
0
0

© መልካሙ በየነ
መስከረም 18/ 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
===============================

abune-abrham-satenaw-news

እረኛ እንደመሆን ከባድ አደራ የለም፡፡ አደራው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ያከብደዋል፡፡ ለጴጥሮስ የተሠጠው የእረኝነት ሥልጣን በጎችን እንዲጠብቅ ብቻ ሳይሆን በሚገባ እንዲያሰማራ ጭምር ነበር፡፡ መጠበቅ ቀላል ነው ማሰማራት ግን ከባድ ነው፡፡ የለመለመ ሣር በሌለበት፣ የእረፍት ውኃ በማይገኝበት ቦታ መጠበቅ ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን በጎቹ ይከሳሉ፣ ይጠቁራሉ፣ ይደክማሉ፣ ይራባሉ፣ ይጠማሉ በመጨረሻም ይሞታሉ፡፡ ይህ እረኝነት ችግር አለበት፡፡ ተኩላ ሊነጥቃቸው ቢመጣ ስለበጎቹ ራሱን አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ስለዚህ ነው ይህን እረኝነት ችግር አለበት የምንለው፡፡ እረኝነት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን በአግባቡ ማሰማራትንም ይጠይቃል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የበጎቹን ባሕርይ በሚገባ ማዎቅ ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም የምናሰማራበትን ቦታ ለመምረጥ የበጎቹን ፍላጎት መረዳት ግድ ይላል፡፡ ውኃ የጠማቸውን በጎች ከለመለመ ሳር ውስጥ፣ የተራቡ በጎችን ደግሞ በእረፍት ውኃ ዘንድ ብናሰማራቸው ምንም ዋጋ የለውም፡፡ ምክንያቱም ለጠማው ውኃ፤ ለራበው ደግሞ ሳር እንጅ ሌላ ፍላጎት እንደማይኖራቸው የታወቀ ነውና፡፡ ስለዚህ ነው እንግዲህ እረኝነት ከባድ አደራ ነው የምንለው፡፡ እውነተኛው እረኛ ስለበጎቹ ራሱን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ተኩላ ሊነጥቃቸው ቢመጣ በመጀመሪያ እረኛው ከተኩላው ጋር ይታገላል፡፡ እረኛው በትግሉ ከተሸነፈ ከዚያ በኋላ ነው እንግዲህ በጎቹን ተኩላ ሊነጥቃቸው የሚችለው፡፡ ከዚያ ውጭ ግን በጎቹ በማንም አይነጠቁም፡፡ እረኝነት ይህ ነው ከእግዚአብሔር ስንቀበለው ደግሞ እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡

በዚህ አስከፊ ዘመን እርስ በርሳችን ደም ስንፋሰስ ሰላም ስትርቀን ወንድሞቻችን ሲሞቱ፣ ሕጻናት ሳይቀር ሲጨፈጨፉ፣ እናቶች በልጆቻቸው አስከሬን ላይ ቁጭ በሉ እየተባሉ ሲደበደቡ የሚያጽናናን አባት ማጣታችን ልባችንን ሰብሮት ነበር፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ ፓትርያርኩ ከምእመናን በተሰበሰበ ሽራፊ ሳንቲም በሚንቀሳቀሰው የቤተክርስቲያናችን ቴሌቪዥን ላይ ብቅ እያሉ ማን የጻፈላቸውን እንደሆነ ባናውቅም ከአንድ እረኛ የማይጠበቅ መግለጫ መሰል ንግግራቸውን ሲያነበንቡብን በጣም እጅግ አዝነን ነበር፡፡ ኤልያስ ስለ ናቡቴ ከንጉሡ አክአብና ንግሥት ኤልዛቤል ጋር የተጋጨው፣ ዮሐንስ መጥምቅ የወንድምህን ሚስት ልታገባት ህግ አይፈቅድልህም በማለት ከንጉሥ ሔሮድስ ጋር የተጋፈጠው፣ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ አንዲት ደሃ መበለት ከንግሥት አውዶክስያ ጋር የተከራከረው እና መከራን የተቀበለው፣ አቡነ ጴጥሮስ ኢትዮጵያ ለፋሽስት ባህል እምነት እንዳትገዛ በማውገዛቸው በጥይት የተገደሉ እረኝነታቸው እውነተኛ ስለነበር ነው፡፡ ዛሬ ግን ፓትርያርኩ የሚሰጡት መግለጫ እረኝነታቸውን የማያሳይ ምእመናንን ይበልጥ ውስጣቸውን እየጎዳቸው ያለ ነገር ነው፡፡ እረኝነት የሞቱ በጎቹን እየፈታ መቅበር ከዚያም ነፍሳቸውን ማርልን ብሎ ማስተጋባት ብቻ አይደለም እንዳይሞቱ መጠበቅ ጭምር እንጅ፡፡

ለብዙ ዘመናት አባት የሌለን ልጆች ነን ስንል ነበር፡፡ ፓትርያርኩ የሚሰጡት መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶሱ እየመሰለን አባቶቻችንን ስንጠላቸው ኖረናል፡፡ ግን አይደለም፡፡ አባት አለን ልጆች መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡ በደመራ በዓል ላይ የምእራብ ጎጃም፣ የአዊ እና የመተከል አህጉረ ስብከቶች ሊቀጳጳስ የሆኑት አቡነ አብርሃም የብዙ ንጹሐን ወገኖቻችን ደም በፈሰሰባት በባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ላይ ተገኝተው ከአንድ መልካም እረኛ የምንጠብቀውን ስንናፍቀው የኖርነውን የተመኘነውን የአባት ፍቅር ሰጥተውን ተመለከትን እና በጣም ደስ አለን፡፡ አባታችን እንደሚከተለው ነበር በህዝብና በመንግሥት መካከል በመሆን የሰላም ንግግር ያደረጉት፡፡ «ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለበት፤ እኛ አባቶች የምንናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም ፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?፤ መንግስት የተሸከመው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዪ የእርሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍስሱ» በማለት ነበር እውነትን በአደባባይ የገለጡት። ከዚህ የተረዳነው ትልቁ ነገር የፓትርያርኩ መግለጫ የቤተክርስቲያናችን አለመሆኑን ነው፡፡ እርሳቸውንማ ግማደ መስቀሉ ያለው ግሸን መሆኑን ዘንግተው አዲግራት ላይ አየናቸው እኮ፡፡ አዲግራት መገኘታቸው ማንንም አያስከፋም የተናገሩት መርዝ ንግግር ግን ሁሉን ያስከፋል።

የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደሚባለው ከአንድ ማኅጸን ተወልደው በአንድ ቤት አድገው የዚህ የእኛው የምሥራቅ ጎጃሙ ሊቀጳጳስ አቡነ ማርቆስ ከአሜሪካ ስልክ መትተው “መስቀል አብርሃ” ከሚለው መዝሙር ውጭ ሌላ እንዳይዘመር ሰንበት ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቁ አሉን፡፡ “አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሔር ነው የእኛ ኃይላችን፤ መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንእነ መስቀል ቤዛነ” እየተባለ እንዳይዘመር አስጠነቀቁ ተባልን እኛም “መስቀል አብርሃ” ስንል ዋልን፡፡ አቡነ አብርሃም ደግሞ “ወታደሮች ከተሸከሙት መሣሪያ ይልቅ መስቀል ይበልጣል” በማለት በከበቧቸው ወታደርች መካከል ቆመው እውነቱን መሰከሩ፡፡ ልጆቼ ከቤታቸው በሰላም ሲገቡ ሳላይ ወደ መንበሬ አልሄድም ብለው ልጆቻቸው በሰላም መግባታቸውን አይተው በእግራቸው ወደ መንበራቸው ገቡ አሉን ደስ አለን፡፡

በዘመናችን መራራ የሆነውን እውነት ተጋፋጭ አቡነ አብርሃም ዳግማዊ አቡነ ጴጥሮስ ብላቸው እንዴት ደስ ባለኝ ነበር ዳሩ ግን እኔ ስም የማውጣት መብቱ የለኝም፡፡ ለአባታችን ረዥም ዕድሜ ዘመንን ይስጥልን፡፡ አባታችን ስንለው ልጆቼ የሚለን በማግኘታችንም ሁላችንም ኮርተናል ደስም ብሎናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ንግግራቸው መከራ እና ስቃይ ሊደርስባቸው እንደሚችል የታመነ ነው፡፡ በርግጥ እርሳቸው ለዚህ እንደማይበገሩ እናምናለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ህዝቡን እንዲጠብቁ አደራ ሰጥቷቸዋልና፡፡ ሆኖም ግን ጠባቂው እግዚአብሔር እንደሆነ ብናውቅም የአባታችንን ጉዳይ ግነ በቅርበት መከታተል እንደሚገባን አሳስባለሁ፡፡

 

 

አገር ማለት፤ የኔ ልጅ – ግጥም በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

$
0
0

አገር ማለት፤ የኔ ልጅ – ግጥም በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

አገር ማለት፤ የኔ ልጅ – ግጥም በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ

የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል….. (መርሐጥበብ ከባህር ዳር)

$
0
0

መርሐጥበብ
ከባህር ዳር

tigist-satenawnews-6
ዲንቢጧ የሕወአት ተላላኪና የተላላው ደርጅት ብአዴን አባል ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/ኢየሱስ

እኔማ ዘንድሮ በግርምት መሞቴ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚያውቀውም ሆነ በማያውቀው እየገባ መዘባረቁ የግርምቴ መነሻ ነው፡፡ የሻይ ማንኪያ ያህል መረጃ ይዞ ጭልፋ ሙሉ ወግ ማውጋት ምን የሚሉት በሽታ ነው፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ በትንሽ ነገር ሲነኩ እንደ ቆሌ ዶሮ መርገፍገፉ የሰሞኑ የአገሪቱ ካብኔ ተብየዎች ባህርይ በመሆኑ ከመደነቅ ይልቅ መገረም ነው የዕለት ቀለቤ፡፡

ሰሞኑን የአማራ ክልል ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በኃላፊነት የምትመራው ዲንቢጧ የሕወአት ተላላኪና የተላላው ደርጅት ብአዴን አባል ገነት ገ/እግዚአብሔር ገ/ኢየሱስ በምትፈጽመው ድርጊት በመላው አማራ ክልል የሕዝብ ጥላቻ ከማትረፏ በላይ አመኔታ የሌላት ደካማ ፍጡር መሆኗን በምትመራው ተቋምና በተለያዩ መድረኮች ሲነገራት የማትሰማና ከወድቀት የማትማር የባህር ዳር ከተማ ወጣት እያሳደነች የምታሳስርና የምታስገድል እንዲሁም በአማራ ክልል ሕዝብ ስም የምትነግድ ትውልድና ዘመን የማይረሳት ጠላት መሆኗ እየታወቀ የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ ተብየው ንጉሱ ጥላሁን ለክልሉ መንግስት ቃል ማቀበሉን ትቶ ለወ/ሮዋ ጥብቅና መቆሙን በራሱ የማኅበራዊ ድረ ገጽ በለቀቀው መረጃ መታዘብ ችያለሁ፡፡

የጠሉትን ማስጠላት ምን ያደርጋል በሚል ርዕስ የለቀቀው መረጃ “ወ/ሮ ገነት ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆን እና የቅንጦት ኑሮ ከማንም የኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ለመሆን ሲባል ይህች ሴት የምትጠላውን ኪራይ ሰብሳቢነት ስለሚሰሩ ሴትነቷ ሳይገድባት ትታገላቸዋለች፣ ከስራ ታግዳለች፤ ለአብነት በቅርቡ የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሽህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ስራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ነገር ግን ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው፡፡ ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” የሚል ነው፡፡

እንደ ቃል አቀባዩ ዲስኩር ሙሰኞችን አጥብቃ የምትታገል ምርጥ የሴት አመራር መሆኗን መመስከር እፈልጋለሁ ማለቱ “የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል” የሚለውን አባባል ለጽሁፌ በርዕስነት እንድመርጥ አስገደደኝ፡፡ ለምን ቢሉ ከጌታው ከፍ ብሎ ላለመታየትና ጌታውን ላለማሳጣት ነው የሚለው አባባል ትዝ አለኝ፡፡ የንጉሱ ጠበቃነት በመረጃ ያልተደገፈ ነው፡፡

በሶማሌ አንድ አባባል አለ ልንገራችሁ። አባባሏን የሰመኋት ይህን ጦማር ስሞነጫጭር ነው፡፡ አንዲት ሶማሌ ሴት ነበረች። በሶማሌ ባህል ጋብቻ በግልጽ ካልሆነ አይፈጸምም። አንዲት ሶማሌ ከባህሉ ውጭ በድብቅ የወደደችውን ባል አገባች። ሁለቱ ተጋቢዎች  ከጊዜ በኋላ እንናገራለን በሚል ስምምነት የተጋቢ ቤተሰቦች ሳያውቁ አብረው መኖር እንደጀመሩ ባል በድንገት በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያልፋል። ሚስት እንዴት ብላ ታልቅስ፤ ምክንያት አጣች። ‘ባሌ ነበረ’ ብላ ካለቀሰች፣ ሕጋዊ ባል አይደለም፤ ስለዚህ ‘ብልግና ነበር የምትሰሩት፤ መቼ ነው የተጋባችሁት?’ ሊባል ነው። ስለዚህ ልጅቷ ተጨንቃ ዝም አለች። በዚህ አጋጣሚ ከነበራቸው ፍየሎች አንዱ በቀበሮ ተበላና ሞተ የሚባል ወሬ በእረኛው መልዕክት ይደርሳል፡፡ ‘የኛ ፍየል እኮ በቀበሮ ተበላ ይላታል። ሚስቲቱም ምክንያት አግኝታ በዛ አለቀሰች። የልቅሶ ደረጃውን በመገንዘብ ይህን ያዩ አባትም “ልጄ ይሄ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነው!” አላት። ይባላል፡፡ የንጉሱ ወግም ከገነት ትግል ጀርባ ያለውን ድርጊት አለመገንዘቡን ያስታውሳል፡፡

በቅድሚያ ገነት ተብየዋን ግለሰብ በሚገባ አያውቃትም፡፡ የቀን እንጂ የሰው ጀግና እንደሌለውና በአንድ ድርጅት መሰባሰብ የግለሰቦች ማንነት መገለጫ እንደማይሆን እንኳን የመንግስት ቃል አቀባይ በሌላም ሙያ የተሰማራ ይዘነጋዋል የሚል ህሳቤ የለኝም፡፡ የንጉሱ ሀሳብ አላዋቂ ሳሚ ….. ነው የሆነብኝ፡፡

ግለሰቡ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች በአጭር ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው ሃብት በማካበት መኪና መግዛት፣ የቤት ባለቤት መሆንና የቅንጦት ኑሮ እየኖሩ ያሉትን ጾታዋ ሳይገድባት ትታገላለች ያለው ሀሳብ ጅምላ አስተያየት በመሆኑ ብዙም ባልቀበለውም ድክመቱንና ሀቁን ጉዳይ ለማሳየት እሻለሁ፡፡ አቶ ንጉሱ ቆርጦ ቀጥል አመለካከትህ ብዙም ርቀት አያስጉዝህም፡፡ የአማራ ክልል አመራር ስሙ በተነሳ ቁጥር የምትሰነዝረው አስተያየት ለስልጣንህ ማቆያ የምትጠቀምበት ስትራቴጂ እንደሆነ ማስረጃ መጥቀስ አያስፈልግም፡፡ የጎንደር ቅዳሜ ገበያ በእሳት ሲጋይ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ላይ ሆነህ በቪኦኤ የአማረኛ ቋንቋ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጠኸው መግለጫ ተጠቃሽ ነው፡፡ በሌለህበትና በማታውቀው ጉዳይ መዘባረቅ በክራሞት የተላበስከው የሙያ ካባ ስለሆነ ብዙም  አይደንቀኝም፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ ግለሰቧ የሰጠኸው አስተያየት ብዕሬን ከወረቀት ጋር እንዳዋድድ አስገደድከኝ፡፡ ምክንያቱም ነገ ደግሞ ሌላ ላለማለትህ ዕምነት ስላጣሁብህ ነው፡፡

በእኛ አገር የጋዜጠኝነት ሙያ  የአንድ ወገን መረጃ ዜና እየሆነ አገር ማመስ ከተጀመረ ሩብ ዓመት እንዳለፈው ላንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆንብኝ፡፡ ሴትየዋ ብቻ የነገረችህን ተቀብለህ በቢሮው ውስጥ ያሉ መሃንዲሶች ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው ማለትህ አዘንኩልህ ይህ ቀን እንዲህ ሆኖ የሚቀር መስሎህ ሁሉንም መሃንዲሶች በኪራይ ሰብሳቢዎች ቅርጫት ማስቀመጥህ ዘንግተኸው እንደሆነ እንጃ እንጂ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚመራውም ኃላፊ መሃንዲስ ነው፡፡ ዳሩ ከመንግስት ቃል አቀባይ ምን ይጠበቃል፡፡

አቶ ንጉሱ ከሰጠኸው አስተያየት ተነስቼ ለአብነት ብለህ ያቀረብከው ሀሳብ “ጅል አይሙት እንዲያጫውት” የሚያሰኝ ነው፡፡ ቢሮው የኮንትራክተሮችን የደረጃ ማሳደግ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከአንድ ኮንትራክተር እስከ 20 ሺህ ብር በመቀበል ህጉና መመሪያው የሚጠይቀውን መረጃ ሳያሟሉ ደረጃ የማሳደግ ሥራ የሰሩ 4 ባለሙያዎችን ማንም ወንድ ያልደፈራቸውን እሷ ከስራ አግዳቸዋለች ያልከው ጉዳይ ጫፍ ይዘህ መሮጥህን ያሳያል፡፡ በቅድሚያ ምነው ዛሬ ይህን ሀሳብ ይዘህ ወጣህ ጃል? ከነገረ ቀደም በዚህ ዘርፍ ከሥራ የታገደ አይደለም አራት አንድም ባለሙያ የለም፡፡ በሥራ ተቋራጮች የደረጃ ማሳደግ ተግባር ከመመሪያ ውጭ ተደራድረዋል በሚል ተብለው የተጠረጠሩ በተለያየ የሥራ መደብና ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች ከነበሩበት የሥራ መደብ አንተ እንዳወራኸው ታግደው ሳይሆን በሌላ የሥራ መደብ ተዛውረው እየሠሩ እንዳሉና እስካሁንም የተጠረጠሩበት ጉዳይ አስካሁን ዳር ሳይደርስ ባለሙያዎችም በተመደቡበት የሥራ መደብ እያገለገሉ እንደሚገኙ ልብ ትለው ይገባል፡፡

“ወዳጄ” አለ አጎቴ ታየር ወዳጄ ንጉሱ የወግህን ብዕር አልወደድኩትም፡፡ በደብዛዛ አመለካከት የወጣ ሀሳብ ከማደናቆር ውጭ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ታዲያ ይህችን ሴት ከዚህ በላይ ብትባልም አይገርመኝም ያልከው ነገር አልገባኝም ለምን አትነግረንም ቃል አቀባይነትህን ዘነጋኸው፡፡

ደሃው የአማራ ህዝብ ነገ እለወጣለሁ እያለ የሚከፍለውን ግብር ሙሰኞች ሲዘርፋት ዝም ብዬ አላይም በማለቷ እንድትሸማቀቅ የሚያደርጉ የፌስ ቡክ ጀግኖች የገባችሁም ያልገባችሁም ከዚች ጀግና ሴት ራስ ላይ ብትወርዱ ጥሩ ነው ያልከው ጉዳይ እጅግ አስጋራሚና እስስታም ባህርይን የሚያንፀባርቅ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ርካሽ ተወዳጅነት የሚፈጥረው ስሜት በመሆኑ አልተቀየምኩህም፡፡ ግለሰቧ ልውደድህ ብትልህስ በምን ቀልቧ ትወዳሃለች ጊዜውንና ቦታውን ማየት ነው እንጂ፡፡

ካቀረብከው ሀሳብ ሌላው ያስገረመኝ ጉዳይ “…ከሚፃፈው ነገር ስነሳም ወ/ሮ ገነት ተወልዳ ያደገችው ባህር ዳር ቀበሌ 11 ሆኖ ሳለ ሌላ ታርጋ በመስጠት በሴትነት አታሸማቋት ኪራይ ሰብሳቢው ትታገልበት ይህ እውነታ ታሪክ ነው፡፡” ያልከው ነው፡፡ ይህ ሀሳብ ጤንነትህን ሁሉ እንድጠራጠር ነው ያደረገረኸው

በቅድሚያ ምነው ስሟን ብቻ ጠርተህ ተውካት? ብዕርህ የፍርሃት ቀለም ለምን ይተፋል? ሌላው ትውልድ በማን ይገለጻል? በወላጅ ወይስ በቦታ? ደግሞም የግለሰቧን የትውልድ ቦታ ለማወቅ የግል ማኅደሯ ከሚገኝበት ተቋም ፈትሽ፡፡ እያሸማቀቃት እያለው ጾታዋ ሳይሆን ተግባሯ ነውና በመጀመሪያ ኪራይ ሰብሳቢነት ከመታገሏ በፊት ራሷን ከኪራይ ሰብሳቢነት ታጽዳ ያኔ የቃል አቀባይነትህ ተግባር ትፈጽማለህ፡፡ ዘመዴ ጫፍ ይዘህ አትባዝን- አበቃሁ፡፡

 

ዓመተ ፍዳ ዘነገደ አማራ! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኩዳን]

$
0
0
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ቤተክርስቲያን “ዓመተ ፍዳ” የሚለውን ቃል ዓለም ከተፈጠረ አንሥቶ ከክርስቶስ መወለድ በፊት ያለውን የሰው ልጆች በነፍስና በሥጋችን በአጋንንት አስከፊ የፍዳ፣ የመከራ፣ የሰቆቃ፣ ግዞት የነበርንበትን ዘመን ለማመልከት የምትጠቅሰው ቃል ነው፡፡

በቅርቡ “የጥፋት ዘመን” በሚል ርእስ በዋናነት በጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የተዘጋጀ በ25 ዓመታቱ የወያኔ አገዛዝ ዘመን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአማራው ሕዝብ ላይ አጋንንት በተዋሐዷቸው በወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማፅዳት እልቂት የሚያትት ጥናታዊ መጽሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን መቅረቡ ይታወቃል፡፡

አስቀድሜ ከጅማሬው አንሥቶ ይህ መጽሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን እስኪደርስ ባለው ሒደት የተሳተፉ ወገኖችን በሙሉ በግሌ እጅግ አድርጌ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ተባረኩ!

ከዓመታት በፊት ቀደም ሲል በዚህ ጉዳይ ላይ የጻፍኩትን “የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሒደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!” የሚለውን ረዘም ያለ ጽሑፍ በማካተት እንዲህ ዓይነት መጽሐፍ ለማዘጋጀት አስቤ ለዚህ እነ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ላዘጋጁት መጽሐፍ መዘጋጀት እስፖንሰር (ደጋፊ) የሆነው ሞረሽ ወገኔ እንደተመሠረተ ሰሞን ለአንደኛቸው የድጋፍ (የስፖንሰር) ጥያቄ አቅርቤ ነበር፡፡ ሰውየው እንደሚያቀርበው ከነገረኝ በኋላ ምን ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ሳይነግረኝ በመቅረቱና በእኔም ላይ ታች አምና ኦነግ ያሳሳታቸው የጅማ ዩኒቨርስቲ (መካነ ትምህርት) ተማሪዎች ተገንብቶ ሊመረቅ በነበረው በአኖሌ ሐውልትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መጽሔት ላይ የጻፍኩትን ጽሑፍ ምክንያት በማድረግ ቁጥሩ ያልተወቀ ሰው የሞተበትን ዐመፅ አስነሥተው በእኔና በመጽሔቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሲጠይቁ (በጥቂት ቀናት ውስጥም ዐመፁ ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲቀጣጠል የኦሕዴድ ሰዎች “አሃ! ሕዝባችን በዚህ ደረጃ መነሣሣት የሚችል ከሆነማ!” በማለት አጋጣሚውን ለመጠቀም በማሰብ እጃቸውን አስገቡበትና የተማሪዎቹን ጥያቄ የአዲስ አበባን ዐቢይ የማስፋፊያ አቅድ ወደ መቃወም እንዲዞር አደረጉት)

እናም በዚህ መልኩ በእኔና በመጽሔቱ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ሲጠይቁና በግልም የተለያየ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲደርስብኝ ጊዜ ወያኔና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች ኦሮሚያ ሲሉ በሚጠሩት የሀገራችን ክፍል በነጻነት ተዘዋውሬ በአማራ ኅብረተሰብ ላይ የተፈጸመውን አረመኔያዊ ኢሰብአዊ ዘር የማጥፋትና የማጽዳት ግፍ የማጥናት የማጣራትና የመዘገብ ዕድሌ እንደተበላሸብኝ ሲገባኝ ለሞረሽ ወገኔም ሆነ ለሌላ አካል ጥያቄውን ደግሜ ሳላቀርብ ቀረሁ፡፡

ይሁንና ይህ መሠራት መከወን የነበረበት ሥራ በእኔ ባይሠራም በእነ ሙሉቀን ተስፋው ተሠርቷልና ዋናው ጉዳይም መሠራቱ ነውና ምንም ዓይነት ቅሬታ አላደረብኝም፡፡ ከዚህ በፊት በዚህና ተያያዥ ጉዳይ ላይ በጻፍኳቸው ጽሑፎች ላይ ያነሣኋቸው ሐሰቦች እዚህ መጽሐፍ ላይ በመንጸባረቃቸውም አልተከፋሁም ጉዳዩ የሀገርና የወገን ነውና፡፡

እነ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሁኔታው የፈቀደላቸውንና መድረስ የቻሉትን ያህል በመድረስ ነፍሳቸውን ለአደጋ በማጋለጥ ጭምር በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የመጨረሻ ወንጀል ለመዘገብ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ያልደረሷቸው አካባቢዎችና የፍጅት ኩነቶች ቢኖሩም መጽሐፉ  ግን በሀገራችን በ21ኛው መቶ ክ/ዘ በፍጹም በፍጹም ይፈጸማል አይደለም ይታሰባል እንኳን የማይባል አረመኔያዊ ድርጊት ምናልባት አጋንንት ይሆናሉ እንጅ ሰው መሆናቸው በእጅጉ በሚያጠራጥሩ አራዊት የተፈጸመውንና አሁንም እየተፈጸመ ያለውን የግፍ ደረጃና ክብደት ለመረዳት ከበቂ በላይ መረጃና ግንዛቤ ሰጪ ነው፡፡

እነኝህን እጅግ ኢሰብአዊ የአውሬዎችን ድርጊቶች ድርጊቶቹ ለተፈጸመባቸው አካባቢዎች ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ለብዙዎቻችን ጭምጭምታውን ካልሰማን ወገኖች መሀል ግን በሌላው የዓለም ክፍል በፍጹም ተሞክረው የማያውቁ ዘግናኝና አረመኔያዊ ግፎች በአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ላይ በብዛት መፈጸማቸውን የሚያውቅ እንደሌለ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

የዚህ ምክንያቶቹ  ደግሞ አንደኛ፦ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ወገኖቻችን የተፈጸመባቸውንና እየተፈጸመባቸው ያለውን ግፍ ማውራታቸው ወይም መናገራቸው ለተጨማሪ ጥቃት የሚያጋልጣቸው መሆኑ ሲሆን፡፡ ሌላው ደግሞ “አማራ እንደ ሕዝብ የአጋንንቱ ኢላማ ሆኖ እየተጠቃ መሆኑ በይፋ ቢታወቅ ይህ ግፍ የዘነበበት ሕዝብ ተገዶ በሚወስደው የመከላከል እርምጃ እንዳለ ብሔረሰቡን ብሎም ሀገሪቱን ችግር ላይ መጣል ይሆናልና በእኛው ቢቀር ዋጥ አድርገነው ብንጠፋ ይሻላል!” ከሚል ከፍተኛ ኃላፊነት የተሞላበት አስተሳሰብ ነገር ግን የተሳሳተ አቋም የተነሣ ነው፡፡

ብዙዎቻችን በተለይም መረጃው የሌለን ወገኖች ለመረጃው ሩቅ ከመሆናችን የተነሣ ከፊሉ የተፈጸመው  የግፍ ዓይነት ለማመን እጅግ የምንቸገርበት ነገር ቢሆንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በተለይም የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ይሄንን መጽሐፍ ማንበብና ያለንበትን ሁኔታ መረዳት ይኖርበታል፡፡

ለሰብአዊ መብቶች መከበርና መጠበቅ የጸና አቋም ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተለይም የጥቃቱ ኢላማና ሰለባ የሆነው ዘር አባል የአማራ ተወላጅ  የሆነ ሁሉ ይሄንን መጽሐፍ አንብቦ ያ ግፍ የተፈጸመባቸው ወገኖች ሰቆቃና ሕመም አጥንቱ ድረስ ዘልቆ ካልተሰማው፣ ካልተንገበገበ፣ ቁጭት ካላቃጠለው፣ ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ የፈጸሙና እየፈጸሙ ያሉ አራዊትን የመታገልና የመደምሰስ የትግል ስሜት ከውስጡ ካልተቀጣጠለበት ካልነደደበት እሱ በድን፣ እሬሳ፣ ጤና በእጅጉ የተጓደለው ወይም  የተሟላ የስሜት ሕዋሳት የሌለው መሆኑን እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በዚህ የራሱ ጉዳይ በሆነ ነገር ያልተነሣሣ ያልተቀሰቀሰ ያልተቃጠለ በሌላ በምንም ሊቀሰቀስ አይችልምና፡፡

አርጀንቲኒያዊው ቸ ጉቬራ በዘርና በቀለም ለማይመስሉት ግፉአን ጥቁር አፍሪካውያን ሲል ለነጻነታቸው ለህልውናቸው አንዲት ነፍሱን መሥዋዕት እስከማድረግ ድረስ ቆርጦ መሰለፉን እያወቅን፣ የእኛም አባቶች በኮሪያ በሊቢያ በኮንጎ ወዘተርፈ ለሌሎች ሕልውና ነጻነትና ደኅንነት አንዲት መተኪያ የሌላት ነፍሳቸውን መሥዋዕት ለማድረግ ቆርጠው በመሰለፍ ዋጋ መክፈላቸውን እያወቅን፤ እኛ ይሄ ግፍ እየተፈጸመብን ለራሳችን ህልውና ነጻነትና ደኅንነት ዋጋ ለመክፈል ካመነታን ወደኋላ ካልን ይሄ በድን ሬሳ ካላስባለ ሌላ ምን ሊያስብል ይችላል? ለሆድህ ስትል ሆድህ አምላክህ ሆኖብህ የምትሸሽ ካለህ መብላት የምትችለው ስትኖር ነውና እንዳትኖርም ደግሞ አማራ በመሆንህ ምክንያት ብቻ እየታደንክ እንድትጠፋ ተፈርዶብሀልና ሆዳም ሆይ! እባክህን ሆድህን ምክንያት አታድርግ፡፡

ጥቂት የማንባል የአማራ ተወላጆች አጋንንቶቹ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የፈጸሙትንና እየፈጸሙት ያሉትን አረመኔያዊ ጥፋት አለመስማታችን አማራ በመሆን ብቻ እየተፈጸመ ካለው መጠነ ሰፊ አረመኔያዊ ጥቃት ሰለባነት ወይም ተጠቂ ከመሆን ያድነን ይታደገን ይመስል ጉዳዩ ሲወራ ላለመስማት እንሸሻለን እንጅ የራሳችኑ ጉዳይ እንደመሆኑ በንቃት ትኩረት ሰጥተን የት ቦታ ምን እየተደረገ እንዳለ በመከታተል ለመፍትሔው አንታትርም፡፡ ብዙዎቹም ይሄንን አደጋ ለመቀልበስ ከመታገል ይልቅ አማራነታቸውን መካድ መፍትሔ አድርገውታል፡፡ ይሁንና እነኝህ አማራነታቸውን የካዱ ወገኖች በአንድም በሌላም መንገድ አማራ ወይም የአማራ ደም ያለባቸው መሆኑ እየታወቀባቸው ለጥቃት ሲዳረጉ ዓየን እንጅ አማራነታቸውን መካዳቸው ከጥቃት ሲታደጋቸው ዓላየንም፡፡ ምንም ይምጣ ምን ማንነትን መካድ እራሱ እጅግ ወራዳና ነውረኛ የለፈስፋሶች ተግባር ነው፡፡

በመሆኑን መፍትሔው ወገብን አስሮ በቁርጠኝነት በጋለ ወኔና ጀግንነት አራዊቶቹን ታግሎ መጣልና መቅጣት ነው እንጅ ክህደት አይደለምና ለዚሁ ቆራጥ እርምጃ የበርካቶችን ነፍስ የሚያስበላ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ሳናባክን አጋንንቶቹን በተለያየ የትግል ስልት ለመታገል  በፍጥነት ቆርጠን እንነሣ!!!

ከዚህ ቀደም አነኚህ ሁሉ በ21ኛው መቶ ክ/ዘ ፈጽሞ የማይጠበቁ አረመኔያዊ ግፎች ሲፈጸሙ ፈተናው በሚጠይቀው ጥንካሬና ቁርጠኝነት በመነሣሣት ተገቢውን የተጠናከረ ተቃውሞ አለማሰማታችን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በግድ እንዲያውቀው ዐውቆም እንዲያወግዘውና እርምጃ እንዲወስድበት አለማድረጋችን ይህ አረመኔያዊ ግፍ እስከአሁንም እንዲቀጥል ምቹ ዕድል ሰጥቷል፡፡

ወገን ሆይ! ስለ ዲሞክራሲ (መስፍነ ሕዝብ) ሥርዓት መመሥረት መታገሉን ምንንትስ እርሱት፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄ ዓይነት ትግል ለአማራ ሕዝብ ሲበዛ ቅንጦት ነውና፡፡ መጀመሪያ በገዛ ሀገርህ አማራ በመሆንህ ብቻ እንደ አውሬ በየትም ቦታ እየታደንክ ከመታረድ ከመቃጠል ከመሳደድ ወጥተህ እንደሰው የመኖር መብትህን አረጋግጥ!!

በዚህ መጽሐፍ የተዘረዘሩ ግፎችን ስንመለከት ወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች እንደ አኖሌ ያሉ የፈጠራ ስም የማጥፋት ክሶችን እውነት እያስመሰሉ ለምን እየፈጠሩ እንደሚያናፍሱና እንደሚያራግቡ በሚገባ ግልጽ ይሆንለታል፣ የጥፋት ኃይሎቹ እጅግ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ በምን ያህል ደረጃ ደንቆሮዎች, የማሰብ ችሎታቸው እጅግ የተገደበና ኃላፊነት የሚባል ነገር ቅንጣት ታክል እንኳ የማይሰማቸው መሆናቸውን  ይረዳል፡፡ ምክንያቱም ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ በዚህን ያህል ስፋትና ጥልቀት በደል በሌለባቸው ወገኖች ላይ አማራ መሆናቸውን ብቻ ወንጀል አድርገው ጥቃቱን ሲፈጽሙ ወደፊት እነሱን ምንም ዓይነት ዋጋ ሳያስከፍላቸው የአንድ ሰሞን ተራ ወሬ ሆኖ የሚቀር ተራ ነገር እንደሆነ አድርገው ያስባሉና ነው፡፡

ይሄንን ባለፉት 25 ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን በመጽሐፉም ውስጥ የተገለጸውን በታሪክ ጨካኝና አረመኔያዊ ግፍ በሕዝባችን ላይ ፈጽመዋል የተባሉት ፋሺስት ጣሊያን፣ ግራኝ አሕመድና ዮዲት ጉዲት እንኳን ፈጽሞ ያልሞከሩትን ሰው የአንድ ዘር አባል (አማራ) በመሆኑ ብቻ ሰብአዊና የዜግነት ክብሩን እጅግ ከተዳፈረው፣ ሥነልቡናን እጅግ ከሚያውከው፣ ጭንቅላትን እጅግ ከሚያደማው በርካታ የበደል ዓይነቶች አንሥቶ ፈጽሞ ለማመን በማይቻል ደረጃ እንደበግ ታርዶ ኩላሊቱና ጉበቱ በሚጥሚጣ እየተጠቀሰ እስከመበላት ድረስ በሰው ልጆች ታሪክ ታይተውና ተሰምተው የማያውቁ የግፍ ዓይነቶች መፈጸሙን ስመለከት እጅግ ግርም የሚሉኝ ሰባት ነገሮች አሉ፡፡

1ኛ. ይህ አማራን ከሀገር መንጥሮ የማጥፋት እርምጃ ወያኔ ክልል ብሎ በሚጠራቸው የሀገሪቱ የግዛት አሥተዳደሮች ሁሉ በሱ ትዕዛዝ ይህ ሁሉ ግፍ በአማራ ማኅበረሰብ ላይ ሲፈጸም በወያኔና ግብረ አበሮቹ ቀስቃሽነት አነሣሽነት ገፋፊነት አቀነባባሪነት አደራጅነት ካልሆነ በስተቀር በእየአካባቢው  ሕዝብ የራስ ተነሣሽነት የተፈጸመ አለመሆኑ፡፡

2ኛ. በእነዚያ ወያኔ ክልል በማለት በሚጠራቸው የሀገራችን ክፍሎች ያለቀው የአማራ ማኅበረሰብ ሊያርዱት፣ ገደል ሊወረውሩት፣ ሊረሽኑት፣ ሊያቃጥሉት እየወሰዱት ወይም እያጎሩት እንደሆነ እያወቀ ሦስትና አራት ቦታዎች ላይ ከተደረገው በስተቀር በአልሞት ባይ ተጋዳይነት መንፈስ ወይም “ሞቴ ካልቀረ ጠላቴን ይዠው ልሙት!” በሚል መንፈስ አንገቱን እያነቁም ይዘውት አብረው ገደል እየተወረወሩም መሞት ሲገባቸው ለመሥዋዕት እንደሚነዳ በግ ዝም ብለው መታረዳቸው፣ ገደል መወርወራቸው፣ መረሸናቸው፣ መቃጠላቸው፡፡

3ኛ. ይሄ ሁሉ ሕዝብ “አማራ ነህ!” ከሚለው ምክንያት በተጨማሪ በክርስቲያንነቱ ከነ አብያተክርስቲያናቱ እየተቃጠለ፣ እየታረደ፣ እየተሠየፈ ሲፈጅ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንደተጠቂነቷና ጉዳዩ በቀጥታ እንደሚመለከተው አካል ለአንድም ጊዜ እንኳ ጠንካራ የአቋምና የኃዘን መግለጫ አሰምታ አለማወቋ ጉዳዩንም አለመከታተሏ፡፡

እርግጥ ነው በዚህ 25 ዓመታት የቤተክርስቲያኗን የሥልጣን ቦታዎች በየእርከኑ የወያኔ የውሸት ካህናት ተቆጣጥረው እንደያዙት ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ይህን ዓይነት እርምጃ ቤተክርስቲያን ትወስዳለች ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይታሰብ የማይጠበቅም ነው፡፡ ይሁን እንጅ የወሳኝነት የሥልጣን ቦታ አይሁን እንጅ የአገልግሎት የሥልጣን ቦታ ላይ ከጵጵስና እስከ ዲቁና ያሉ በርካታ የአማራ ተወላጆች አሉ አይደለም ወይ? (ጉዳዩ በቀጥታ የአማራ ተወላጆችን ይመለከታል ለማለት ነው እንጅ ይሄንን አረመኔያዊ ግፍ ማውገዝስ የሁሉም ሰው ግዴታ ነበር፡፡)

እናም እነኝህ ሰዎች እንደእረኝነታቸው በግልም  ይሁን በቡድን ምን ያደረጉት ነገር ነበር? “ስለበጎችህ ቤዛ እራሴን አሳልፌ እሰጣለሁ!” ብለው በክርስቶስ ፊት ቃል ገብተው የእረኝነትን ሥልጣን ከተቀበሉ በተለይም “መነኮስኩ ነገንዠ ሞትኩ!” ካሉ በኋላ ምን የሚያስፈራቸውና ወደኋላ የሚስባቸው ነገር ኖሮ ነው ለክርስቶስ የገቡትን ቃልና ክርስቶስ የጣለባቸውን አደራ እየበሉ ጭጭ ያሉት?

“ምእመናን በአብያተክርስቲያናት ውስጥ እየታጎሩ ተቃጠሉ፣ ተመንጥረው በመጨፍጨፋቸው ይኖሩበት የነበረው ሀገር ወና ሆነ አብያተክርስቲያናቱንም አሕዛቡ አረማዊያኑ ከመዘበሯቸው በኋላ ጫት ማመንዠኪያቸው አደረጓቸው!” የሚለው ለሚሰማው ሁሉ ጆሮዎቹን ጭው የሚያደርግ የቤተክርስቲያን ታላቅ መርዶ ያልገደደው፣ ያልተሰማው፣ ኃላፊነቱንና ግዴታውንም ለመወጣት ያልቻለ እረኛ “እረኛ ነኝ!” ብሎ አፉን ሞልቶ ያወራል??? አደራቹህን! ሥራቹህ ቁልጭ አድርጎ እንደሚመሰክርባቹህ እናንተ ምንደኞች እንጅ እረኞች አይደላቹህምና ተሳስታቹህም እንኳ ቢሆን “የመንጋው እረኞች፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ነን!” እንዳትሉ! የምታመልኩትም የምታገለግሉትም ሆዳቹህን እንጅ እግዚአብሔርን አይደለምና ይሄን ትሉ ዘንድ በፍጹም በፍጹም የተገባቹህ አይደላቹህም!

4ኛ. ምንም እንኳን ብአዴን ትግሬ ተሰግስጎ የሞላበት የወያኔ አሻንጉሊት ድርጅት ቢሆንም ያሉትንም ያህል ቢሆን የአማራ ተወላጅ የሆኑ ወይም ነን የሚሉም በሽዎች የሚቆጠሩ አሉና እነኝህ ሁሉ እያሉና ድርጅቱ “ለአማራ ሕዝብ መብት ነፃነት ህልውናና ጥቅም የቆምኩ ነኝ!” ብሎ እየለፈፈ እያለ በተባባሪነትና በቀጥታ ተሳታፊነት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም በቆየውና እየተፈጸመም ባለው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ከፍተኛ ወንጀል ውስጥ መገኘታቸው፡፡

መቸስ ትንግርት ነው! ሰው ራሱን ይበላል? እጅግ የሚያስገርመው ነገር ደግሞ ብአዴን ይሄንን እያደረገ ያለው ወያኔ ሌት ተቀን ለሚደክምለት ለትግሬ ሕዝብ ጥቅም መሆኑ ነው፡፡ “የብአዴን አማሮች የገዛ ሕዝባቸውን ለትግሬ ጥቅም ሲሉ ይፈጃሉ ያስፈጃሉ!” ሲባል እንዴት ሊሆን እንደቻለ በጣም ግራ አይገባቹህም? እጅግ አይደንቃቹህም? አሁን እነዚህ ብአዴን ውስጥ ያሉ አማሮች ሰው ነን ብለው ሳያፍሩ ከሰው ፊት ይቀርባሉ? እንደሚቀርቡማ ዕለት ዕለት ዕያየናቸውም አይደል! ግን ምን ጉድ ፍጥረቶች ቢሆኑ ነው? እውነት ግን እንደኛ ሰዎች ናቸው? ምንድን ነው እንደዚህ ተናጋሪ ዕቃ ወይም ተናጋሪ እንስሳ ሊያደርጋቸው የቻለው? ዕቃ ወይም እንስሳ ብቻ ነው ለምን? እንዴት? ሳይል እንዲያደርግ ያስደረጉትን ነገር ዝም ብሎ የሚያደርገው፡፡

ከዚህ ቀደም የብአዴኑ አቶ ታምራት ለዓይኔ ምን ብሎ ቀስቅሶ የአማራን ሕዝብ እንዳስፈጀው እናውቃለን፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ደግሞ ሌላኛው የብአዴን ባለሥልጣን የዛሬው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን 1983/84ዓ.ም. ላይ መንታ ውኃ አካባቢ ሰዎችን አደራጅቶ በአብዛኞቹ የመተከል ሰፋፊ ጫካዎች ውስጥ ከ50 እስከ መቶ እርምጃ ልከ እምብርት (ራዲየስ) ርቀት ውስጥ ሲያንስ በአንድ ሲበዛ በበርካታ የአማራ ተወላጆች አስከሬን እንዲሞሉ ያደረገ፣ 1986ዓ.ም. ፓዊ በገበያ ቀን ሀገር ሰላም ብሎ በደራ ገበያ ሲገበያይ የነበረን በሽዎች የሚቆጠርን የአማራ ሕዝብ በድንገት ዙሪያውን አስከብቦ በመትረጊስ እርምት አድርጎ በማስፈጀት ገበያ የነበረውን ሜዳ ወደ የሰው ቄራነት በመቀየር በአስከሬን ቁልልና በሕዝብ ደም ኩሬ ማጥለቅለቁ በድፍን የመተከል የቻዌ ነዋሪ ይታወቃል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን አማራ ነው ይባላል፡፡ ከሆነ እሱና ያንን እልቂት የፈጸሙት ጓዶቹ እንዴት በገዛ ወገናቸው ላይ ምንም በደል ሳይኖርበት የእነሱን አማራነት የት ጥለውት ነው አማራነቱን ወንጀል አድርገው እንዲህ ሊፈጁት የቻሉት? ዘር ደም ከሆነ ብአዴኖች የአማራነት ደማቸውን እንዴት አድርገው ቀድተው ደፍተው ቀይረውት ነው አማራነትን ወንጀል አድርገው እንዲህ ሕዝብ ለመፍጀት የበቁት? በገዛ ወገናቸው ላይ እንዲህ ዓይነት ክሕደት ፈጽመው የፈጁ ሰዎች በደም ለማይዘመዳቸው ለማይመስላቸው ለራሱ ለወያኔ (ለትግሬ) እንዴት ነው ታማኝ ሊሆኑ የቻሉት??? ይሄ የሆነው በአንዳች መተት ወይም አጋንንታዊ ኃይል ካልሆነ በስተቀር አንድን ሰው ለራሱ ለሥጋው ለወገኑ ያለውንና ሊኖረውም የሚገባውን አግባብነት ያለው ተቆርቋሪነትን አጥፍቶ፣ ሚዛናዊ አመለካከቱን አዛብቶ እንደ ዕቃ ወይም ሮቦት (ምስለ ፍጡር) እንደፈለጉ እያሽከረከሩ “ለምን? እንዴት?” ሳይል እንዲህ ዓይነት አረመኔያዊ ድርጊት በገዛ ወገኑ ላይ በግፍ እንዲፈጽም ማድረግ እንዴት ነው የቻሉት???

ብዙዎቻቹህ “ኧረ ባክህ! የምን መተት ነው ደግሞ? ሰዎቹ ከልክ በላይ ራሳቸውን ስለሚወዱ ለግል ጥቅማቸው ብቻ ስለሚያስቡ ነው!” ትሉኝ ይሆናል፡፡ ለእኔ ግን ይሄ አሳማኝ ምክንያት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሀገርና ወገን በሌሉበት ሁኔታ እኮ “እኔ” ማለትና የግል ጥቅም የሚባል ነገር እኮ ሊኖር አይችልም! በእርግጥ ይሄው በሰዎቹ ላይ እያየን እንዳለነው ለጊዜው ሊመስል ይችላል፡፡ ስር መሠረትና ዘለቄታዊነት ግን አይኖረውም፡፡

“የሰው ልጅ ማኅበራዊ ፍጡር ነው!” ይባላል፡፡ ትክክልም ነው፡፡ የሰው ልጅ “እኛ” ማለት ካልቻለ “እኔ” ብሎ መኖር ፈጽሞ አይችልም! እኛ ሲል ደግሞ እኛ ሊል የሚገባው ሀገርንና ሕዝብን በፍትሐዊነት ተጠቃሚ ማድረግን መሠረት በማድረግ ካልሆነ በስተቀርና “እኛ” የሚለው ሰው የሱን ቢጤዎች አራዊት ሰብስቦ እነሱን እያሰበ ከሆነ ገና “እኛ” ማለት አልጀመረም፡፡ “እኛ” የሚሉ መሰላቸው እንጅ “እኔ” ነው እያሉ ያሉት፡፡

የሰው ልጅ “እኛ” ማለት ካልቻለ በስተቀር ለአንዲት ነፍሱ ሳይሳሳ የሚሠዋላት የጋራ ሀገር ሊኖረው አይችልም! የሰው ልጅ ራሱን ሲወድ ጥሩ ነው፡፡ ያኔ ነውና “እኛ” ማለት የሚችለው፡፡ “እኛ” ማለት ሳይችል ያለሥጋትና አደጋ የሚወደውን እራሱን ተጠቃሚ ማድረግ እንደማይችል ጠንቅቆ ያውቃልና ነው ማኅበራዊ ሰላሙ “እኔ” በሚሉ ከመታወኩ ነጻ ሆኖ ባያውቅም “እኛ” በማለት የጋራ ሀገር መሥርቶ አብሮ ለመኖር የቻለው፡፡

በመሆኑም ይህ የብአዴን ሰዎች ችግር የራስ ወዳድነት ችግር አይደለም፡፡ ምንድነው ታዲያ? ካላቹህኝ፦ ሌላ ምንም ሳይሆን በሆዳምነታቸው ላይ እጅግ ከባድ የሆነ  የአእምሮ፣ የአስተሳሰብ፣ የሥነ ልቡና መታወክና መዛባት ችግር (Mental & Psychological disorder) ያለባቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ነው ባደረጉትና በሚያደርጉት ኢሰብአዊ ግፍ ሁሉ እንደ ሰው ቅንጣት ታክል እንኳ የማይሰማቸው፣ የማያሳስባቸው፣ የማይገዳቸው፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው ሊሆኑ የቻሉት፡፡ ራሳቸው፣ የሚያገለግሉት ወያኔ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ ተጠቃሚ የማይሆኑበትን ተግባር ታጥቀው እየፈጸሙ ያሉት፡፡

5ኛ. ይህ ሁሉ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በዚህ ክ/ዘ ይፈጸማል አይደለም ይታሰባል እንኳ የማይባል እጅግ አደገኛው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም ወንጀል እራሱን “የኢትዮጵያ መንግሥት ነኝ!” ባለ ኃይል አደራጅና አቀነባባሪነት ያለማሰለስ በስፋት ላለፉት 25 ዓመታት ያህል ሲፈጸም ምሁራኑ በተለይም የአማራ ምሁራን በግልም ይሁን በመደራጀት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማጋለጥንና ጉዳዩ የሚገባውን ትኩረት እንዲያገኝ ማድረግን ጨምሮ ሊያደርጉት የሚገባቸውን ሁሉ አለማድረጋቸው፡፡

እርግጥ ነው የቀድሞው ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ላስተማራቸው ሕዝብና ሀገር የሚጠበቅባቸውን ለማበርከት የሚጥሩ ምሁራን ፍሬዎች መሆናቸውን እረዳለሁ፡፡ ይሁንና ግን እነኝህ ድርጅቶች ያለብንን ፈተና በሚመጥን ጥንካሬ ትጋትና ቁርጠኝነት ነው ወይ እየሠሩ እየታገሉ ያሉት? እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡

አሁንም እርግጥ ነው መጽሐፍ በመጻፍ፣ ይህን የዘር ፍጅት የPHD (የሊቀ ጥብና) ትምህርታቸው የመመረቂያ ጽሑፍ ርእሰ ጉዳይ በማድረግና በሌሎችም መድረኮች ሦስት አራት የሚሆኑ ምሁራን ይሄንን የወያኔን አረመኔያዊ ተግባር ያጋለጡ አሉ፡፡ ሊመሰገኑም ይገባል፡፡

ነገር ግን ይሄ ሕዝብ ያስተማረውና ኃለፊነቱም ያለባቸው እነዚህ ብቻ ናቸው ወይ? የተቀረውስ? በእውነት በእውነት ምሁሩ ክፍል በዚህ ጊዜ የማይሰጥና አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበትን ርብርብ አለማድረጉና ዝም ጭጭ በማለቱ የወገኑ ደም ዕዳ አለበት! ለምንስ ጭጭ አላቹህ? እንዴት ነው ታዲያ እናንተ ያዳፈናቹህትን ያልተናገራቹህትን ባዕዳኑ እንዲጮሁት እንዲያስተጋቡት ልንጠብቅ የምንችለው? ከቶ እንዴትስ አስቻላቹህ? እንቅልፉስ እንዴት ተተኛላቹህ? እህልስ እንዴት ተበላላቹህ? ይሄ ድሀ ሕዝብ በድህነት አቅሙ ሳይማር እናንተን አስተምሮ ለዚህ ካበቃበት ዐበይት ምክንያቶች አንዱ ለእንደዚህ ዓይነቱ ክፉ ቀን እንድትደርሱለት ነበር እንጅ ወደ አደጉ ሀገራት ጣጥላቹህት እየሔዳቹህ እራሳቹህን በምቾት እያኖራቹህ እንድትረሱት ወይም ከንፈር እንድትመጡለት ነው ወይ???

6ኛ. የተባበሩት መንግሥታት፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ኃያላን መንግሥታት ይህ በዚህ ዘመን ይሆናል ተብሎ በፍጹም የማይታሰብ አረመኔያዊ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸም የመጨረሻ ወንጀል መንግሥት ነኝ በሚል አካልና አጋሮቹ በተለያዩ ቦታዎች ትናንትና እስከሸኘነው 2008ዓ.ም. ድረስ በአማራ ሕዝብ ላይ በስፋት ሲፈጸም እንደቆየና እየተፈጸመም እንዳለ እያወቁ መረጃዎች በሚገባ እያሏቸው ለእንዲት ጊዜም እንኳ ቢሆን መግለጫ አውጥተው አለማውገዛቸው፡፡

መረጃው ስለሌላቸው ስላልሰሙ እንዳይመስሏቹህ እንዳላዩና እንዳልሰሙ ሆነው ዝም ጭጭ ያሉት፡፡ እነኝህ ዓለም አቀፍ አካላት በወያኔና በሌሎቹ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ዘር ላይ ለተፈጸመችው ለእያንዳንዷ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል መረጃው በሚገባ እንዳላቸው መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እነሱ እንኳንና በብዙኃን መገናኛዎች ሳይቀር በተደጋጋሚ የተዘገበባቸውን የአደባባይ ምሥጢሮች ይቅርና ወያኔ ተቃዋሚዎችን ለመወንጀል እያጠመደ ያፈነዳቸውንና ንጹሐንን የፈጀባቸውን የፈንጅ ጥቃቶች ሳይቀር ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ እኛ ዜጎች በሀገራችንና በራሳችን ላይ መፈጸሙን ፈጽሞ የማናውቀውን ስንት የተሠወረ ጉድ ሁሉ በሚገባ ያውቃሉ፡፡

እነሱ ሰሜን ኮሪያ፣ ኤርትራ፣ ሶሪያ፣ ቻይና፣ ኢራን ምንትስ እያሉ “በዓለማችን ላይ የሰብአዊ መብቶች እጅግ የሚጣስባቸው ሀገራት!” እያሉ ያብጠለጥላሉ እንጅ የሁሉም ግፍ ቢደመር ወያኔ የፈጸመውን ቅንጣት እንደማያክል በሚገባ ያውቃሉ፡፡ እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ሀገራት ፈጸሙ የተባሉት ወንጀል የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ወያኔ ግን የፈጸመውና እየፈጸመው ያለው በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻ ወንጀል የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀልን ነው፡፡ በመሆኑም በዚህች ዓለም ላይ ፍትሕና ርትዕ ቢኖር ኖሮ በዚህች ዓለም የወያኔን ያክል የሚወገዝና እርምጃ የሚወሰድበት አገዛዝ ከቶውንም ባልነበረ፡፡

“እና ታዲያ እነዚህ ምዕራባውያን መንግሥታት በተለይም የተባበሩት መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለሰብአዊ መብቶች መጠበቅ ቆመናል! እያሉ በዚህ ዘመን ፈጽሞ የማይጠበቀውን የወያኔን አረመኔያዊ ወንጀል ካወቁ ለምንድነው የማያወግዙትና እርምጃስ የማይወስዱበት?” ካላቹህኝ ኃያላኑ ሀገራት እስከዛሬ በወያኔና አጋሮቹ በይፋ የሚደረገውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል አለማውገዛቸውንና ለማውገዝም አለመፈለጋቸውን በምናይበት ጊዜና ወያኔም በአቶ አቦይ ስብሐት በኩል ያለአንዳች የተጠያቂነት ስሜትና ፍርሐት በአደባባይ “የአማራንና የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርገን ሠብረናል!” ብሎ መናገሩን ስንመለከት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየታተሙ በሚወጡ መጻሕፍት ላይ “ኃያላኑ ሀገራትና ወያኔ በአውሬው 666 የዲያብሎስ መንፈስ እየታዘዙና እየተመሩ ይሄንን ወንጀል በሀገራችንና በሃይማኖታችን ለመፈጸም በርትተው እየሠሩ ነው!” በማለት የሚያቀርቡትን ክስ እንድናምን ያስገድደናል፡፡

ይህ የመጻሕፍቱ ክስ እውነት ሆነም አልሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት የጀርባ አጥንት የሆነው የአማራ ሕዝብ ጉልበቱን እግዚአብሔርን አድርጎ ውጊያውን መዋጋት ግዱ መሆኑን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ምንም ዓይነት መዘናጋት እንዳይኖር እጅግ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ እርግጥ ነው በእርኩሰት ተዳድፈን ለይስሙላ በዘልማድ ካልሆነ በስተቀር እንደቀድሞው ከልብ በንጽሕናና ቅድስና በሚደረግ አገልግሎትና አምልኮ ከእግዚአብሔር በመራቃችን እግዚአብሔር ለዚህ ውርደት ስብራትና ጥፋት አጋልጦናል፡፡ እነኛ አብያተክርስቲያናት በአረማውያኑ ሲቃጠሉ ሲፈርሱና አሕዛብ አረማውያኑ የጫት ማመንዠኪያ ስፍራቸው ሲያደርጓቸው የተደፈረው ክብር የእሱም መሆኑን እግዚአብሔር አጥቶት አይደለም እንደማያይና እንደማይሰማ በዝምታ እየተመለከተ ያለው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን አሕዛብ አረማውያኑን በደል እንደፈጸሙ እንዲቀስፍ እንዲበቀላቸው ወይም ደግሞ ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብሎ እንዲመለከት የሚያደርገው የእኛው ሥራ ነው፡፡

የካህኑን የዔሊንና የልጆቹን የአፍኒንና የፊንሐስን ሥራ አስታውሱ፡፡ 1ኛ ሳሙ. ከም. 2-4 የእነሱ መበደል ታቦተ ጽዮን በአሕዛብ እጅ እንድትማረክ፤ ወስደውም እንደምናምንቴ በጣኦት ቤታቸው ከጣኦታቸው ስር እንዲወረውሯት፣ እስራኤላውያንም በጦርነቱ እንዲሸነፉና እንዲዋረዱ እንዲደቆሱም እንደዳረጋቸው አስታውሱ፡፡

እኛም በራሳችን ላይ እየደጋገምነው ያለነው ይሄንን ታሪክ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ንጹሕ እኛነታችን ነው እንጅ ከረከሱ እጆች የሚበረከት ገንዘባችንን አይደለም፡፡ እራሳችንን ሳንቀድስ እያሳመፅንና እያረከስን ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን በግንብ አይደለም በዕንቁ እንኳ ብንሠራለት ለእሱ ምኑም አይደለም! አይደሰትበትምም፡፡ እንዲያውም አጥፊ ያዝበታል፡፡ ነገር ግን እንዳስቻለን መጠን እራሳችንን ቀድሰን ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን ወይም የእግዚአብሔርን ቤት በጭራሮ እንኳን ብንሠራው ለእሱ በዕንቁ ከተሠራም በላይ ነው፡፡ ይሄንን ልብ ልንል ይገባል፡፡

ካልሆነ ግን እሱ ምንጊዜም ቢሆን የዐመፃን ዋጋ ከመክፈል ወደ ኋላ አይልም፡፡ ቃሉም እንደሚል “እሽ ብትሉ ለኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹህ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላቹሀል” ትን.ኢሳ. 1፤19-20 እንዳለው ይህ ሁሉ ጉድ የመጣብንና የተሰበርነው እንቢ በማለታችን በማመፃችን መሆኑን መገንዘብ ይገባናል፡፡

መቀጣታችን ሌላም ዐቢይ ምክንያት አለው ቃሉ እንዲህ ይላል “ልጀ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታቹሀል፡፡ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋቹሀልና፡፡ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኗልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጅ ልጆች አይደላቹህም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይዎት ልንኖር በተገባን? እነሱ መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” ይላል ቃሉ ዕብ. 12:5-11፡፡

“የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን? ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ. 9፤7 በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ልጆች እንጅ ዲቃሎች አይደለንምና ምንም ቢበድሉ የቱንም ያህል ቢረክሱ ቢያምፁበትም ምንም እንደማይላቸው እንደ ሌሎች ሀገራትና ሕዝቦች ዝም አይለንም፡፡ እሽ እስክንልና እስክንመለስ ድረስ ይቀጣናል እንጅ፡፡ ስለሆነም ትቶ ላይተወን ነገር እሱን “እሽ!” ካለማለት በስተቀር ሌላ ምንም መፍትሔ የለንምና እሽ እንበል! ንስሐ እንግባ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! ከዚያ እንደ እናት አባቶቻችን ለእግዚአብሔር ታምነን ስሙን ጋሻና ጦራችን አድርገን ያለብንን ውጊያ እንዋጋ በእኛና በጠላቶቻችን መሀከል ያለው የኃይል አሰላለፍ ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ርቀት ቢኖረውም እንኳ ያለጥርጥር እናሸንፋለን!!!

7ኛ. የወያኔ የኦነግና የሌሎች የጥፋት ኃይሎች ድንቁርና፡፡ እነኝህን ሰዎች ሳስብ ዓለም እንደዛሬው አንድ መንደር ሆና በአንደኛው የዓለም ጫፍ የተደረገው በሌላኛው የዓለም ጫፍ ላለው ምን እየተደረገ እንዳለ በዓይን ቅጽበት በሚታወቅበት ዘመን ሳይሆን ጥንት ሥልጣኔ ባልነበረበትና አንዱ ስለሌላው መረጃ በማያገኝበት ዘመን ላይ ይሄንን ሥልጣን የያዙ ሆነው ቢሆን ኖሮ ምን ሊያደርጉን ይችሉ እንደነበር ሳስብ በጣም ያስፈራኛል፡፡ እርግጥ ነው ወያኔ “መረጃ በዓይን ቅጽበት ከአንዱ የዓለም ጫፍ ወደሌላው በሚደርስበት ዘመን ላይ ነው ያለሁትና” ብሎ ምንም ነገር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ ይሁንና ግን ይሄንን ሁሉ ጉድ ስናይ “በዚህ ዘመን ይሄንን ያደረገ በዚያ ዘመን ቢሆን ኖሮስ ምን ሊያደርግ ይችል ነበር?” ያሰኛል፡፡ አንድ ሰው ወይም ቡድን ኃላፊነት ተጠያቂነት ሰብአዊነት የማይሰማው፣ ነገን የማያስብ ሆኖ ካገኛቹህት ምንም ስለሆነ እንዳይመስላቹህ! ደንቆሮ ስለሆነ ብቻና ብቻ ነው፡፡ የድንቁርናቸው ድድርናና ጥልቀት እንደየሚሠሩት አውሬአዊ ተግባሮቻቸው ይወሰናል፡፡

ወያኔ ኦነግና ሌሎች የጥፋት ኃይሎች ይሄንን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙ በየቦታው የሚሰጡት ምክንያት የተለያየ ነው፡፡

ወያኔ ኦሮሚያ ብሎ በከለለው አካባቢ የሚጠቀሰው ምክንያት፦ “እናንተ የምኒልክ ዘሮች ናቹህ! ምኒልክ አሩሲ ሔጦሳ ላይ የወገኖቻችንን እጅና ጡት ቆርጧል!” የሚል ምንም ዓይነት መረጃ የሌለው ፋሽስት ጣሊያን “ልመሠርተው ያሰብኩትን ቅኝ አገዛዝ ያከሽፍብኛል!” ብሎ የፈራውን አማራን ለማስጠቃትና የሕዝቡን አንድነት ፈረካክሶ ለማዳከም ሆን ብሎ ፈጥኖ ያወራውን በጊዜውም ተሳክቶለት በአማራ ላይ ብዙ ግፍ እንዲፈጸምበት ለማድረግ አስችሎት የነበረውን የፈጠራ ወሬ ይዘው “እንበቀላቹሀለን!” በማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁንና አሁን አሁን እንኳ ይህ ወሬ ነጭ ውሸትና ፈጠራ መሆኑንና ወያኔና ኦነግ ለተመሳሳይ ዓላማ ከፋሺስት ጣሊያን ተውሰው ያመጡት የፈጠራ ወሬ መሆኑን እኛ ብቻ ሳንሆን የኦሮሞ ምሁራንም ሳይቀሩ ያረጋገጡት ሀቅ በመሆኑ ይሄንን ፈጠራ ምክንያት ማድረግ አይቻልም፡፡

ሌላኛው ወያኔ ኦሮሚያ ሲል በከለለው የሀገራችን አካባቢ የሚጠቀሰው ምክንያት ደሞ “አኛ የሀገሩ ሰዎች ደሀ ሆነን እያለ እናንተ ያለሀገራቹህ መጥታቹህ በእኛ ላይ ሀብታም ሆናቹህብን!” የሚል ነው፡፡ የገጠሩ ሰው ብዙ የሚያውቀው ነገር የለምና ወያኔና ኦነግ እውነት አስመስለው ለጥቃት ሲያነሳሡት የሚነግሩትን ነገር እንዳለች ይተፋታል፡፡ ሀቁ ግን ማን የመሬቱ ባለቤት፣ ማን ደግሞ በወረራና በመስፋፋት ይሄንን መሬት ከመቸ ጀምሮ ማንን አፈናቅሎ አሰድዶና አጥፍቶ ይሄንን መሬት እንደያዘ በግልጽ ይታወቃልና ወደ ሐተታ መግባት አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ወያኔ በገዛ ሕገመንግሥቱ ላይ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ በየትኛውም አካባቢ በነጻ የመዘዋወር፣ ኑሮን የመመሥረት፣ ሀብት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ ነው!” እያለ በጎን ደግሞ ለየ ክልል ለሚለው አሥተዳደር የዚህን ተቃራኒ መልዕክት እየረጨ አማራን መጨፍጨፍ ማስጨፍጨፍ ማፈናቀሉ ደንቆሮነቱን፣ ኃላፊነት የማይሰማው የወሮበላ ቡድንነቱን፣ አርቆ ማሰብ አለመቻሉን እንጅ ሌላ የሚያረጋግጠው ነገር የለም፡፡

ወያኔ “የደቡብ ክልል” ሲል በሚጠራው የሀገሪቱ ክፍል የሚጠቀሱት ምክንያቶች ደግሞ፦ ደን ያቃጥላሉ!፣ ሕገወጥ ሰፋሪ ናቸው!፣ ከተወላጁ ጋር ተስማምተው መኖር አይችሉም! ፣ ሀገራቹህ አይደለም ከሀገራችን ውጡልን! የሚሉ ናቸው፡፡

እያንዳቸውን ዕንይ፦ ደን ያቃጥላሉ! ያ አካባቢ ከብት አርቢ ማኅበረሰብ ያለበት አካባቢ ነው፡፡ ደርግ በሰፈራ “ውጡልን!” የተባሉትን ወገኖች እዚያ ከማስፈሩም በፊት ከብት አርቢዎቹ ለከብቶቻቸው መሬቱ በየዓመቱ አዳዲስ ሳር እንዲያበቅልላቸው የግጦሽ መሬቱን የማቃጠል ልማድ እንዳላቸው እየታወቀ  ራሳቸው በሚለኩሱት እሳት ሁሌም ጠተያቂ የሚያደርጉት አማራውን ነው፡፡ መረጃ ተገኝቶ ደን ሲያቃጥል የተያዘ ሰው ኖሮ ያ ሰው በሕጋዊ መንገድ ቢቀጣ ምንም ባልነበረ ተገቢም ነው፡፡ የሚሆነው ይህ አይደለም፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ምክንያቱ የሚጠቀሰው ሆን ብሎ ለማጥቂያ ሰበብ ለመፍጠር ነው እንጅ በትክክል ስለተፈጸመ አይደለምና፡፡

ሕገወጥ ሰፋሪ ናቹህ! ወደሚሉት ምክንያት ስንሔድ እንዲህ እያሉ የሚያፈናቅሏቸው በሙሉ በደርግ መንግሥት የሰፈራ መርሐ ግብር የሠፈሩ ከዚያም በኋላ የገቡትም የእርሻ መሬት ተሰጥቷቸው ሕጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተሰጥቷቸው ግብር ሲከፍሉ የኖሩ ስለሆኑ ይሄኛው ምክንያትም አይሠራም፡፡

ከተወለለጁ ጋር ተስማምተው መኖር አይችሉም፦ በዚህ የሚወነጀል ካለ ያልተስማማው በምን ጉዳይ ነው? እንደ ዜጋ መብትና ግዴታውን በመተላለፉ ነው ወይ እንዲህ ሊባል የቻለው? ከሆነም ወንጀል የሠራ ሰው በሚጠየቅበት ሕግ ተጠይቆ በአግባቡ ማስቀጣት ነው እንጅ ሕጋዊው አሠራር ዛሬ ዜጎች ባሕር ተሻግረው በባዕዳን ሀገራት በነጻነት ሠርተው መኖር ኑሮን መመሥረት በተቻለበት ዘመን በገዛ ሀገራቸው ወንጀላቸው ምን እንደሆነ ሳይጠቀስ “ከተወላጁ ጋር ተስማምታቹህ መኖር አትችሉምና!” ብሎ ዜጎችን በጅምላ ማፈናቀል፣ መዝረፍ፣ መፍጀት፣ ማቃጠል የትኛው የወንጀል ሕግ የደነገገው ድንጋጌ ነው?

እጅግ እጅግ የሚያሳዝነው የሚያስደነግጠውና የሚያስገርመው ደግሞ  “ከተወላጁ ጋር ተስማምታቹህ መኖር አትችሉም!” የሚለው ክስ ትርጉም አባዎራዎች ዋልጌና ውርጋጦች እቤታቹህ እደገቡ ባለቤቶቻቹህንና ልጆቻቹህን ሲደፍሩባቹህ፣ ከብቶቻችሁን ከበረትና ከመስክ እንደፈለጉ ነድተው ሲወስዱባቹህ፣ ከሱቆቻቹህ ያለክፍያ ዕቃ ያሻቸውን ያህል እያነሱ ሲወስዱባቹህ፣ በፀብ የሚተናኮላቹህ ጥጋበኛ ሲኖር ወዘተረፈ. ወዘተረፈ. ሲሆን ምንም እንዳልሆናቹህ ምናቹህም እንዳልተነካ በዝምታና በጸጋ ተቀበሉ! ማለት መሆኑን በደሉ ለተፈጸመባቸው ዜጎች ይህ ቃል የሚጠቀስላቸው እነኝህ በደሎች ተፈጽመውባቸው ፍትሕ ይሰጣቸው፣ የሚደርስባቸው ገደብ የለሽ ግፍ ይቆምላቸው ዘንድ ወደ ሕግ አካላት አቤት! ባሉ ጊዜ ሕግ ያስከብራሉ ከተባሉ ወንጀሉን ከሚፈጽሙት የባሱ እንስሳ ሕግ ያስከብራሉ ተብለው በኃላፊነት ከተቀመጡ ከሕግ አካላት ዘወትር የሚጠቀስላቸው ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡ መቸስ በጣም የሚገርምና እጅግም የሚያሳፍር ነገር ነው፡፡

ሀገራቹህ አይደለም ከሀገራችን ውጡልን! ወደሚለው ስንሔድ፦ ይሄንን ችግር የበለጠ ከባድና የተወሳሰበ የሚያደርገው ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ? ጥቃት ፈጻሚዎቹ የበሰለ ንቃተ ኅሊና ደረጃ ላይ ያሉ አለመሆናቸው ነው፡፡ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ሀገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ይህች ሀገር እንደሌሎቹ ሀገራትና ሕዝቦች በቅኝ ተይዛ ሕዝቧ እንዴት በባርነት ተቀጥቅጦ እንዳልጠፋ፣ የሀገሪቱ የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ሀብቷ እንዴት ሳይቦጠቦጥ ሳይዘረፍ ሳይወሰድ እንደቀረ፣ ማን ምን ዓይነት መራራ መሥዋዕትነት ለሽዎች ዓመታት ሲከፍል ስለኖረ የሀገሪቱ መሬት እንደተፈጠረ ድንግል መሬት ሊሆን የቻለው፣ የተለያዩ ጎሳዎችም እንዳሉ ሳይበረዙ ሳይከለሱ እንደተፈጠሩ ለሥነ ሰብእ (ለአንትሮፖሎጂ) ጥናቶች  ምቹ መሆናቸው እስኪመሠከርላቸው ድረስ የተጠበቁ ሆነው ሊገኙ እንዴትና በምን ምክንያት እንደቻሉ ቢያውቁ ኖሮ አማራን “ሀገራቹህ አይደለም! ሀገራችንን ለቃቹህ ውጡልን!” ሊሉ አይደለም ለውለታው ምንም ቢያደርጉ ቢከፍሉት የማይጨርሱት እጅግ የበዛ ዕዳ እንዳለባቸው ተረድተው አክብረውት አድንቀውት አመስግነውት ወደውት ባልጠገቡት ባልረኩ ውለታው ባስጨነቃቸው ነበር፡፡

ግን ምን ያደርጋል ድንቁርናና አለማሰብ አለማስተዋል የሚባል አውሬ በወገኖቻችን ላይ ሠልጥኖ በባለውለታው በአማራ ሕዝብ ላይ በማነሣሣት እንዲህ ዓይነት ግፍ እያስፈጸመበት ይገኛል፡፡ ምን ማድረግ ይቻላል? ዕውቀት እንደ ክትባት በመርፌ አይሰጥ!

ለማንኛውም ወያኔ ደቡብ ሲል በከለለው የሀገራችን ክፍል ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የሚጠቀሱ ምክንያቶች እነኝህን ይመስላሉ፡፡

ወያኔ ቤንሻንጉል ጉምዝ ሲል ወደሚጠራው የሀገራችን ክፍል ለጭፍጨፋው ወደሚጠቀሰው ምክንያት ስናልፍ ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን፦ “የክልላቹህ መንግሥት በማዳበሪያ ዕዳ ስለሚፈልጋቹህ ለቃቹህ ሒዱ!” የሚል ነው፡፡ የሚሉት እኮ ቢያጡ ነው! ለሚያይ ለሚሰማ “አማራ ስለሆኑና አማራ እንዲጠፋ ስለምንፈልግ ነው የምንጨፈጭፋቸው!” ላለማለት እኮ ነው እንጅ ሰዎቹ እዚያ ቦታ ላይ ያሠፈራቸው ደርግ በመላ ሀገሪቱ ይዞት በነበረው ሰፊ መርሐ ግብር ሳቢያ ነው፡፡

ስንት ችግርና ፈተናን አሳልፈው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች ሁሉ ከአራዊቱ ከእባቡ ከጊንጡ ጋር ታግለው መሬቱን ሲያለሙትና ከዓመታት በኋላ የድካማቸውን ፍሬ መቅመስ ማጣጣም ሲጀምሩ “ብርቱና አርአያ አርሶ አደር!” እየተባሉ በየ የወያኔ ክልሉ የሚሸለሙት እነሱው ሲሆኑ ሰይጣን ያደረበት ሁሉ በቅናት ተቃጠለ “እኔ መጥፋቱን  እፈልጋለሁ እሱ ጭራሽ ይፋፋልኛል? በል በልልኝ!” እያለ ይፈጀው ያዘ፡፡ እንጅ እውነቱማ እዚያ ቦታ ላይ የሠፈሩት በደርግ ዘመን ሆኖ ወያኔ ገብቶ “የአማራ ክልል” ብሎ ከሠየመው አሥተዳደር ዕዳ ሊኖርባቸው የሚችልበት አንዳችም መንገድ ሊኖር እንደማይችል ሁሉም ሊረዳው የሚችለው ነገር ነው፡፡

ወልቃይት ላይ ለሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል የሚጠቀሰው ምክንያት ደግሞ፦ “ትግሬ ነን! ካላቹህ ተቀመጡ፡፡ አይደለንም! የምትሉ ከሆነ ግን መሬቱ የእኛ ነውና ለቃቹህ ውጡ!” የሚል ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ጽሑፎቸ ላይ በሚገባ የተነተንኩት ጉዳይ በመሆኑ ጽሑፌ በጣም ስለረዘመ በጣም ይቅርታ አድርጉልኝና ይሄን በዚህ ልለፈው፡፡ በአፋርና በሌሎች የወያኔ ክልሎች በአማራ ማኅበረሰብ ላይ ለሚፈጸመው የዘር መጥፋትና ማፅዳት ወንጀል የሚሰጠው ምክንያትም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ እነሱንም አልፋቸዋለሁ፡፡

ጽሑፌን ላጠቃልለውና እንዳያቹህት ጅቡ ወያኔ ሳያመኻኝ ላለመብላት ዘጠና ዘጠኙን ይቀባጥራል፡፡ አንዴ ታስታውሳላቹህ አቶ ዓለምነው የተባሉ የብአዴን ባለሥልጣን የአማራን ሕዝብ እንዲህ ፈጅቶ ለመጨረስ ላበቃቸው ጉዳይ ምክንያት ለማበጀት ሲከጅሉ ምን ነበር ያሉት? “አማራ የትምክሕት ለኻጩን ካልጣለ ካላራገፈ በስተቀር ከሌሎች ሕዝቦች ጋር መኖር አይችልም!” ሲሉ ነበር በአራት ነጥብ የደመደሙት፡፡ “እንዲህ እያደረግን በስውርና በግልፅ በምንፈጽምብህ ጥቃት አጥፍተን ፈጅተን እንጨርስኻለን እንጅ!” ማለታቸው ነው፡፡

አቶ ዓለምነው ማየት የተሳናቸው ልበ ዕውር ደንቆሮ ሆነው ነው እንጅ ሥነሥርዓት አክብሮት ጨዋነት የሚባል ነገርን ከቶውንም የማያውቁትን በባሕርያቸው እንደ ፋብሪካ ዕቃ አንድ ዓይነት የሆኑትን ስድ፣ ዋልጌ፣ ባለጌ፣ ጭንጋፍ፣ ውርጋጥ፣ ቆሻሻ፣ ምናምንቴ፣ ጥጋበኛ የዕድሜ መግፋት እንኳ ከእነኝህ የሥነምግባር ጉድለቶቻቸው የማያርማቸውን የወያኔን መንጋ ከጎናቸው አስቀምጠው አክብሮቱና ሰላምታው ከሰው አልፎ ለእንስሳት የሚተርፈው ሥነሥርዓት ባሕሉ የሆነውን ታጋሽ አስተዋይ በሳል የአማራን ሕዝብ እንዲያ ብለው ለመዝለፍ ድፍረት ባላገኙም ነበር፡፡ ሲጀመር አእምሮውና ሥነልቡናው ከላይ አስቀድሜ  በጽኩላቹህ ሁኔት እንዲያ ሆኖ የተዛባና የታወከ በሽተኛ ይሄንን እንዴት ሊረዳ ይችላል?

የዚህ ሁሉ ሐተታ ቁልፍ መልእክት ፈጥነን እንንቃ! ይህ አሁን ሕዝባችን እያደረገ ያለው ዐመፅና ተቃውሞ ወያኔ አጋሮቹ ለ25 ዓመታት በመላ ሀገሪቱ በአማራ ሕዝብ ላይ በሥውርና በግልፅ ሲፈጽምብንና ሲያስፈጽምብን የኖረውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት አደገኛና ከባድ ወንጀል በዋናነት ታሳቢ ባደረገና አደጋውንም ለመቀልበስ በቆረጠ ዝግጅት መነቃቃት ወኔ ቁርጠኝነትና እልህ መሆን ይኖርበታል!! የሚለው ነው፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኩዳን

amsalugkidan@gmail.com

አፍርጠው’ አዲስ ሃገራዊ ሙዚቃ በ ሻምበል በላይነህ

$
0
0

 

አፍርጠው’ አዲስ ሃገራዊ ሙዚቃ በ ሻምበል በላይነህ
አፍርጠው’ አዲስ ሃገራዊ ሙዚቃ በ ሻምበል በላይነህ

አቡነ አብርሃም: ሕዝቡና ሠራዊቱ እንዲተዛዘኑ መከሩ፤ መንግሥትንና ሚዲያውን አሳሰቡ፤“በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፤ እያየነውም ነው፤ ሊኾንም አይችልም!”

$
0
0

ሐራ ዘተዋሕዶ

  • የመሣርያ ምላጭ ከመሳብ ይልቅ፣ የፍቅር መሳቢያን ተጠቀሙ፤ የፍቅር ማሰርያን ተጠቀሙ
  •  ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው
  •  ሰላም፣ የሰዎችን ድምፅ ሰምቶ፣ መልስ በመስጠትና ችግርን በማስወገድ ነው የሚመሠረተው
  •  በኃይል ሰላምን አምጥተው በሰላም የኖሩ፣ በየትም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በቀር!

*                *             *

  • ምንጊዜም ችግር የመሪው መንግሥት እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፤ በቤተ ክህነትም!
  •  መንግሥት፣ እንደ ወላጅም እንደ መሪም፣ ችግሮችን በመፍታት መፍትሔ መስጠት አለበት
  •  በግድያ እና ሕዝቡን በማላቀስ፣ ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳያኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል!
  •  የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ ለጩኸቱ ካልመለሰ፣ ሕዝቡ ጩኸቴን አላቆምም ቢል የተለመደ ነው

*                *             *

  • ሚዲያዎች፣ ያሻችኹን እየቀጠላችኹ ከሕዝቡ አጋጫችኹን፤ ምን አባት አለን? አሰኛችኹ
  •  የቤተ ክርስቲያን፣ ድምፅዋ ይሰማ! ለማንም አትወግንም፣ የምንናገረውን በትክክል አድርሱ!
  •  ቤተ ክርስቲያንን የሚናፍቃት የውሸት ዕርቅና የምፀት ሰላም ሳይኾን የመስቀሉ ሰላም ነው
  •  እርስበሳችን በፈጠርነው መከራና ችግር መሣቂያና መሣለቂያ ከመኾን እግዚአብሔር አድነን!!

*                *             *

meskel-demera-celebration-in-bahirdar09

“ኹለችኁም ወደዚኽ መስቀል ተመልከቱ፤ በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፤ እያየነውም ነው፤ ሊኾንም አይችልም!”ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የምዕ/ጎጃም፣ አዊ፣ መተከልና ባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ

በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ በትሩፋቱና በትምህርቱ ልቆ በአንብሮተ እድ የሚሾም ኤጲስ ቆጶስ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ በተመደበበት ሀገረ ስብከት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል፣ በበላይነት ለሚመራቸው ካህናትና ምእመናን ያለበትየኖላዊነትና የመግቦት ሓላፊነቱ ቀዳሚው ነው፡፡ ምእመናኑ፣ በተደራጀና በተሟላ ኹኔታ የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት እንዲያገኙና ስለ ሃይማኖታቸው በሚገባ እንዲያውቁ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲጸኑና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሩ በትኩረት መሥራትና መከታተል ይኖርበታል፡፡ ከዚኽም ጋር ኤጲስ ቆጶሱ፡- የሀገር ፍቅር እና አንድነት በሰላም ተጠብቆ እንዲኖር በማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያንን ጥንታዊና ታሪካዊ አገራዊ ሚና አጠናክሮ የማስቀጠል የመንፈሳዊ አባትነት ድርሻም አለበት፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የየጊዜውን ሥልጣኔ ተከትሎ እንዲሔድና ስለ ሀገር ፍቅር፣ ስለ ነፃነት ጥቅም፣ ስለ ዳር ድንበር መከበር፣ ስለ ብሔራዊ ምንነት ከምትሰጠው የተቀደሰ ትምህርት ሌላ፣ ለወገንና ለሀገር ትምክህት የሚኾኑ ጀግኖች ከታሪክ እንዲወለዱ ወቅቱ የሚፈቅደውን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት በማዘጋጀት ስታስተምር የኖረች የኢትዮጵያ ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ የአኹኑ ትውልድም የአባቶቹን ታሪክ ተከትሎ ሀገሩን፣ ነፃነቱን፣ ክብሩንና ሃይማኖቱን ጠብቆ እንዲኖር ቤተ ክርስቲያን ከማስተማር የተገታችበት ጊዜ የለም፡፡

ከትላንት በስቲያ፣ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.፣ በባሕር ዳር መስቀል ዐደባባይ በተከበረው፣ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የምዕራብ ጎጃም፣ አዊ፣ መተከል እና ባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ያስተላለፉት መልእክትም በዚኹ ዐይን የሚታይ ነው፡፡ ባሳለፍነው ፳፻፰ ዓ.ም. መገባደጃ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ በርካታ ግድያዎች፣ የአካል መጉደልና የንብረት ውድመት በተፈጸመበት የሠቆቃ ድባብ ውስጥ፣ በተከናወነው በዚኹ ክብረ በዓል፣ ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ በርካታ ኦርቶዶክሳውያንና ዜጎች ደስታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ብፁዕነታቸውን፣ ከሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ እና ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር እያመሳሰሉ ያወደሱ ወገኖች፤ ኢሰብአዊነትንና ኢፍትሐዊነትን ያለአድልዎ በመቃወም፤ ያዘኑትን በማጽናናትና የተጨነቁትን በማረጋጋት፣ በተቃራኒዎች መካከል በአስታራቂነት የመቆም የቤተ ክርስቲያን ሞራላዊ ልዕልና እና የገለልተኛነት ሚና አኳያ፣ ሌሎችም አባቶች ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ አርኣያነት ያለው ወቅታዊ መልእክት እንደኾነ በአጽንዖት ጠቅሰዋል፡፡

“ቤተ ክርስቲያን ከሕዝብዋ ጋር በመወገን፣ መንግሥት የሕዝብ እምባ ጠባቂ ግዴታ እንዳለበት የሚመክርና የሚያስጠነቅቅ ፈር ቀዳጅ አስተምህሮ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል፤” ብለዋል፣ አንድ ታዋቂ ፖሊቲከኛ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት አስተያየት፡፡ “ነዋ ብእሴ መስቀል – እነኾ የመስቀሉ ሰው” ሲሉ ብፁዕነታቸውን ያመሰገኑት ዲያቆን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ በበኩላቸው፣ “ፍርሃት በራቀለት የጥብዓት አንደበት የተጌጠ ግሩም ቃል ከሊቀ ጳጳሱ ሰማን፡፡ ወሰኑን ሳያፋልስ፣ በዓለማዊ ፖለቲካ ውስጥ ዠቅ ሳይል፣ መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያየ ነው የሚለውን ብሂል ሳይጋፋ ሓላፊነትን መወጣት፣ የመንፈሳዊ መሪ ድርሻ እንደኾነ የብፁዕነታቸው ቃል ያረጋግጣል፤ ዝም በማይባልበት ዝምታ ተገቢ አለመኾኑንም ያመለክታል፤” ብለዋል፡፡

“በሃይማኖት መሪነት ለብዙ ዓይነት አካላት ብዙ ዓይነት መልእክት ማስተላለፍ ይገባል፤” የሚሉት ዲያቆን ዓባይነህ፣ የብፁዕነታቸው ትምህርት በአድራሻው፣ ከሚዲያውና ከሕዝቡ ጋር በተለይም “ለባለጡንቻው” መንግሥት የተላለፈ መልእክት እንደኾነ በጭብጥ በመለየት አብራርተዋል፡፡ ለክብረ በዓሉ ምክንያት የኾነውን የመስቀሉን መገኘት ታሪክ፣ ከወቅቱ ኹኔታ ጋር በማገናዘብ ያስተማሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ መንግሥት የሕዝቡን ብሶትና ጩኸት በቶሎ ሰምቶ ችግሮቹን በመፍታትና ጥያቄዎቹን በመመለስ የማስተዳደር፣ የመሪነትም የአባትነትም ድርሻ እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡ ሰላምን የማስፈን ግዴታ ቢኖርበትም፣ በቀጠለው የሕዝቡ ጩኸት ሳቢያ በሚወስደው የጭካኔ ርምጃ፣ “ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳያኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል፤” ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም፡- በመግባባት፣ የሕዝብን ድምፅ በወቅቱ ሰምቶ ተገቢ ምላሽ በመስጠትና ችግርን በማስወገድ እንጂ፣ በመሣርያ ኃይል የሚመሠረት እንዳልኾነ፣ ይልቁንም የሀገርን አንድነትና ህልውና ለአደጋ በመዳረግ፣ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን መሣቂያና መሣለቂያ እንደሚያደርገን አመልክተዋል – “ሰላምን በኃይል አምጥተው በሰላም የኖሩ በየትኛውም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በስተቀር፤” ሲሉ አስጠንቅቀዋል – ብፁዕነታቸው፡፡ ከዚኽም አኳያ ፣ ዳር ድንበርንና የሀገርን ሰላምን ለሚጠብቅበት የመከላከል ትድግናው ቤተ ክርስቲያን ሌት ተቀን የምትጸልይለት ወታደሩና ሠራዊቱ፣ መሣርያውን ይያዝ እንጂ ምላጩን ከመሳብ ይልቅ የፍቅር መሳቢያን፣ የፍቅር ማሰርያን እንዲጠቀም፤ ሕዝቡም በአላስፈላጊ ጉልበትና ስሜታዊነት ከመተላለቅ፣ መስቀሉን መሣርያው አድርጎ ወደ እግዚአብሔር እንዲጮኽ በመንፈሳዊ መሪነታቸውና አባትነታቸው መክረዋል፡፡

ስለዚኽ ኹላችንም በያለንበት እንደ ወገንነት እንተዛዘን፡፡ እንደ ወገንነት እንተባበር፡፡ ስንቱ ወገን ነው በበረሓ ያለቀው፤ ስንቱ ወገን ነው እንጀራ ፍለጋ በየሀገሩ የተሰደደው፤ ስንቱ ወገን ነው ባሕር የሰጠመው፤ ስንቱ ወገን ነው ዘንዶ የዋጠው፤ እዚኽኮ ሰላማችን ቢበዛ፣ መደማመጥ ቢኖር፣ መቀባበል ቢኖር፣ መፍትሔ በየሰዓቱ ቢሰጥ ኖሮ ኹሉም ሰላም ይኾን ነበር፡፡ ሰላም ካለ ደግሞ ኹሉም ነገር አለ፡፡

እንደ ቅዱስ መጽሐፍ ቃል፣ ቤተ ክርስቲያን፣ የእምነት ነፃነትዋና ተቋማዊ ሉዓላዊነትዋ እስካልተጣሰ ድረስ፣ “ነፍስ ኹሉ፣ ለበላይ ባለሥልጣኖች እንድትገዛ” ብታስተምርም፣ ለማንም እንደማትወግን፣ ብፁዕነታቸው፣ በተለይ ለሚዲያ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ የመንግሥት እና የሃይማኖት መለያየት፣ በኤፌዲሪ ሕገ መንግሥት ብቻ ሳይኾን፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ስምንት የተደነገገ የገለልተኛነት መርሖዋ ነው፡፡ በመኾኑም፣ ሚዲያዎች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና አባቶችን ቃል እንዳሻቸው እየቀጣጠሉ፣ ከሕዝቡ ጋር ከማጋጨትና ሕዝቡን ተስፋ ከማስቆረጥ እንዲታቀቡ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምክርና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

በዚኹ ክብረ በዓል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ከወትሮው በተለየ፣ ተባርኮ የተለኮሰው ደመራ ተቃጥሎ እስኪያልቅ በዚያው በዐደባባዩ ከሚዘምሩት የሰንበት ት/ቤቶችና ማኅበረ ምእመናን ጋር በመቆየትና ሕዝቡን ወደየመጣበት አስቀድመው በመሸኘት ነበር፣ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ያመሩት፡፡ የበዓል አዘጋጅ ኮሚቴው፡- ከሀገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ ከአካባቢ የጽዋ ማኅበራት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማዕከል አባላት የተውጣጣ ሲኾን፣ ከብፁዕነታቸው ትምህርት አስቀድሞ ጸሎተ ምሕላ ደርሷል፤ በሊቃውንቱ፣ በሰንበት ት/ቤቶቹ ወጣቶችና በማኅበረ ቅዱሳን የተሰማው ያሬዳዊ ወረብም፣ ያለከበሮ በጽፋት ብቻ የቀረበ ነበር፡፡ ከበሮ የተመታውም ደመራው ከተለኮሰ በኋላ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ብቻ ነበር፡፡

ምእመናኑና ካህናቱ፣ “ዘንድሮም መስቀል አለ እንዴ” እስኪሉ ድረስ ስጋት የነበረባቸው ቢኾንም፣ የኖላዊነትና የአባታዊነት ሓላፊነታቸውን በአግባቡ በተወጡት ብፁዕ አቡነ አብርሃም አጽናኝነት መንፈሳዊ ደስታውን ገልጧል፤ በእልልታና በጭብጨባም እግዚአብሔርን አመስግኗል፤ የቤተ ክርስቲያናችንን ቀጣይ አገራዊ ሚናን በተመለከተም ተስፋው ለምልሟል፡፡ በደመራው ምሽት፣ የብፁዕነታቸውን ከፊል ትምህርት የያዘ ቪድዮ፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ በስፋት ተሰራጭቷል፡፡ “በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ” በሚል ርእስ፣ ለ25 ደቂቃ የዘለቀውና በጽሑፍ የተገለበጠው፣ የብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር መስቀል ዐደባባይ ትምህርት ሙሉ ይዘት ደግሞ እንደሚከተለው ተጠናቅሮ ቀርቧል፡፡


በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ
በዚኽ የመስቀል ምልክት ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ!

/በብፁዕ አቡነ አብርሃም/

ኹላችኁም ወደዚኽ ወደ መስቀል ተመልከቱ(መስቀላቸውን ከፍ አድርገው እያሳዩ) ፡፡ መስቀል፣ ነፍስንና ሥጋን፣ ሕዝብንና አሕዛብን፣ ሰውንና መላእክትን ያገናኛል፡፡ መስቀል በአጠቃላይ፣ ሰውንና እግዚአብሔርን ያገናኛል፡፡ የክብር ባለቤት፣ የኹላችን ንጉሥ፣ የኹላችን ገዥ፣ በመስቀሉ ደሙን አፍስሶ፣ በደሙ ዋጅቶና ቀድሶ፣ አክብሮ፣ ልጆቹ አድርጎ፣ ነፃነትን ከማጎናጸፉ በፊት፣ እንደሚታወቀው ኹሉ፣ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ፣ የኃጢአተኞች መግደያ ኹኖ ኖሯል፡፡ በዚኽም የመጀመሪያዎቹ ፋርሳውያን እንደኾኑ ቤተ ክርስቲያናችን ትተርካለች፡፡ የምድር አምላክ የሚሉት ነበርና የምድር አምላካቸው እንዳይረክስ ወንጀለኞችን በመስቀል ላይ ይቀጡ ነበር፡፡ በታሪክም ብንሔድ ወንጀለኞች ሲገኙ የሚቀጡት በመስቀል ነበር፡፡ የክብር ባለቤት ግን የተዋረደውንና የተናቀውን ከፍ ማድረግ፣ ማንም ማን የለውም የተባለውን ያለው ማድረግ፣ የባከነውን የተቅበዘበዘውን፣ የጠፋውን፣ የተቸገረውን መርዳት፤ እርሱ የባሕርይው ነውና፣ የተዋረደውን መስቀል ለክብር ይኾን ዘንድ እነኾ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ስላዳነን፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፡- መስቀል ነፃነታችን፣ መስቀል የነፃነታችን ዓርማ ብላ ታከብራለች፡፡

ዛሬ፣ ይህን በዓል ስታከብር፣ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ የተባለው ቆስጠንጢኖስ ነው፡፡ ምንጊዜም በዓሉን ስናከብር ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እና እናቱ እሌኒ ይጠቀሳሉ፡፡ የእሌኒን ታሪክ እንዳልተርክ ረዥም ሰዓት ይወስዳል፡፡ ባለፈው ዓመትም በሰፊው ተነጋግረንበታል፡፡ እሌኒ፣ የተቀበረውን መስቀል ፈልጋ በማግኘት፣ በደመራው፣ ቅድም መንፈሳውያን ወጣቶችም ሲዘምሩልን እንደነበረው፤ ‹‹ሰገደ ጢስ››(ጢሱ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ወርዶ መስቀሉን ስላመለከተ) መስቀሉ የተቀበረበትን ያወጣችበትን ዕለት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብረዋለች፡፡

demera-celebration-at-bahirdar2009

፳፻፱ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር – በባሕር ዳር ሀ/ስብከት፣ ባሕር ዳር መስቀል ዐደባባይ

የመስቀሉ ነገር ሲነሣ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስም አብሮ ይነሣል፤ በሥርዓት ያሳደገችው በመኾኑ፡፡ ቆስጠንጢኖስ በእናቱ አይሁዳዊ፣ በአባቱ አሕዛባዊ፣ እናቱ አምልኮተ እግዚአብሔር ያላት፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ፣ በኋላም ክርስቲያን የነበረች ናት፡፡ አባቱ ደግሞ በጣዖት አምልኮ የሰከረ፣ ለማንም ለምንም ስሜት የሌለው፣ ደም አፍሳሽ ነፍሰ ገዳይ እንደነበረ የታወቀ፣ የተረጋገጠ ነው፡፡

እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ፣ እሌኒ ወደዚያ ሔዳ፣ የቆስጠንጢኖስን አባት ቁንስጣን አግብታ፣ ቆስጠንጢኖስን ወልዳ፣ በሥርዓት ስላሳደገችው፣ እነኾ በዚያ ዘመን አብያተ ክርስቲያናት ኹሉ ተዘግተው፣ አብያተ ጣዖታት ተከፍተው፣ ክርስቲያኖች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ ጩኸታቸውን ወደ እግዚአብሔር የሚያስተጋቡበት ዘመን ነበረና፣ ቆስጠንጢኖስን አሥነስቶ፣ ጠላቶቹን ኹሉ በመስቀሉ ኃይል ድል አድርጎ፣ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ከፍቶ፣ የተከፈቱ አብያተ ጣዖታትን ከፍቶ፣ ለክርስቲያኖች ነፃነት የሰጠበት በዓል ስለኾነ፣ ይህን በዓል በዐደባባይ እንድናከብረው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከወሰነችበት ጊዜ ጀምሮ፣ በመከራም ይኹን በደስታ፣ ወደ ዐደባባይ ወጥታ፣ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ፣ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ፣ በመስቀሉ ሰላምን ስጠን፤ በመስቀሉ ክብርን አጎናጽፈን፤ በመስቀሉ ጠላትን ድል አድርግልን፤ የሰው ልጅ ጠላት ሰው ሳይኾን ሰይጣን ነውና፣ እርስ በርስ እንድንጣላ፣ አንዱ የአንዱን ደም እንዲያፈስ፣ አንዱ አንዱን እንዲያሳድደው፣ አንዱ አንዱን እንዲያስጨንቀው፣ አንዱ አንዱን እንዲያስቸግረው የሚያደርግ ሰይጣን እንጂ ሰው ሲፈጠር በርኅራኄ፣ በቅድስና፣ በክብር ነውና፣ እነኾ ሰይጣንን ቅጣልን፤ አሳፍርልን፤ አንድነታችንን ሰላምን ስጠን፤ እያለች በዓሉን ታከብረዋለች፡፡

ዛሬም ይህን በዓል ለማክበር ዐደባባይ የተገኛችኹ በሙሉ፣ እንኳን ደስ አላችኹ፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችኹ፡፡ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ የክርስቲያኖች ድል ማደረጊያችን፣ የክርስቲያኖች አለኝታችን፣ የክርስቲያኖች ጋሻችን፤ ለዚኽም ነው፣መስቀል ኃይልነ – መስቀል ኃይላችን ነው፤ መስቀል ጽንዕነ – መስቀል መጽኛችን ነው፤ መስቀል ቤዛነ – መስቀል ቤዛችን ነው፤ መስቀል መድኃኒትነ፤ መስቀል መድኃኒታችን ነው፤ ብለን የምንሰመሰክረው፡፡

abune-abreham
በመስቀሉ እናማትባለን፤ በመስቀሉ ርኵሳን መናፍስትን እንገሥጻለን፤ በመስቀሉ ሰላምን እንዋጃለን፤ በመስቀሉ የራቁትን እናቀርባለን፤ በመስቀሉ የታመሙትን እንፈውሳለን፤ በመስቀሉ የተቸገሩትን እንረዳለን፤ በመስቀሉ የተጨነቁትን እንባርካለን፤ እናረጋጋለን፤ እያለች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ መስቀል በእጆችዋ፤ መስቀል በልጆችዋ አንገት ላይ ጎልቶ ደምቆ የሚታይ እንደ መኾኑ፣ በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ ዛሬም ያጣነውን ሰላም እንዲሰጠን፤ የጥያቄዎቻችንን መልስ እንዲሰጠን፣ መግባባት የሚፈጠርበት፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ስሜትና እንደ ኢትዮጵያዊ ባሕርይ፡- አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ ተባብለን የምንኖርበትን፣ አንዱ አንዱን የማያሳድድበትን፣ የማያስጨንቅበትን፣ ንጹሕ ደም የማይፈስበትን፣ ሰዎች ያለአግባብ የማይታሰሩበትን፣ በነፃነት በሀገራቸው በፍቅርና በሰላም ሠርተው፣ ጥረው ግረው እግዚአብሔርን እያመለኩ፣ የሚኖሩበትን በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ ይህን እንዲያደርግልን ነው፣ ጸሎቱም ልመናውም፡፡ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይስማ፡፡(ሕዝቡ፣ አሜን እለ ይከተላል)

ምንጊዜም መስቀልን መሣርያ እናድርግ፡፡ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መሣርያ ስለያዙ፣ በመሣርያ ድል የሚያደርጉ ይመስላቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ በመሣርያ ድል አድርጎ ማንም ማን አልኖረም፡፡ የዕለቱን በዓል ስናስታውስ፣ ቆስጠንጢኖስ እና መክስምያኖስ፣ ትልቅ ምስክሮች ናቸው፡፡ መክስምያኖስ እጅግ ጦረኛ የኾነ፣ ክርስቲያኖችን ያስጨነቀ፣ አብያተ ጣዖታትን የከፈተ፣ ብዙና ብዙ መከራ ያደረሰ ነበር፡፡ ለዚኽ ነበር ክርስቲያኖች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እግዚአብሔር እየጮኹ፣ በክርስትና ሕይወቱ የታወቀውን፣ በምግባር ያደገውን፣ በትሩፋት የበለጸገውን፣ በርኅራኄ የተሞላውን ቆስጠንጢኖስን፣ እባክኽ ርዳን፤ ክርስቲያኖች በዋልንበት ማደር አልቻልንም፤ ባደርንበት መዋል አልቻልንም፤ ብለው ለመኑት፡፡ እርሱም ነገሩን መረመረ፤ ችግሩን ተረዳ፣ ግፉንም አየ፡፡ ‹‹የተቃጠሉትን አልባሳት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት፣ የተሠባበሩትን መስቀሎች፣ ጽዋዎች በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አሳዩት፤›› ይላል የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፡፡

ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ያን ከተመለከተ በኋላ፣ መሣርያ አለኝ፤ ኃይል አለኝ፤ ወታደር አለኝ፤ ጉልበት አለኝ ብሎ በጉልበቱ ተመክቶ፣ በመሣርያው ራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ ወደ ጦር ሜዳ አልሔደም፡፡ የመጀመሪያ መሣርያው ያደረገው መስቀሉን ነው፡፡ በጸሎት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ ከዚያም በጸፍጸፈ ሰማይ፣ በዝንቱ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀረከ፤ በዚኽ የመስቀል ምልክት ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ፤ ተብሎ ተጽፎ አነበበ፡፡ ቋንቋውንም የሚተረጉሙ ተረጎሙለት፤ ከዚኽ በኋላ ውጊያውን ገጠመ፤ እርሱም ቻለ፤ ትእምርተ መስቀሉን ትምክሕት፣ መሪ አድርጓልና፡፡ ጠላትን ድል አድርጎ ለክርስቲያኖች የእምነት ነፃነትን አጎናጸፈ፡፡ አኹንም ለሀገራችን ነፃነትን ያጎናጽፍልን፡፡ መተሳሰብን ይስጥልን፡፡ መተዛዘንን ይስጥልን፡፡ አንተ ትብስ፣ አንቺ ትብሽ መባባልን ይስጥልን፡፡ ጠላታችንን ያርቅልን፡፡(ሕዝቡ፣ አሜን እያለ ይከተላል)

በመስቀሉ ጥላቻንም አስወግዷል፡፡ በኤፌ. ምዕ. 2 ቁ. 16 ላይ ስናነብ፣ ‹‹ጥላቻን ያስወገደ፤ ኹለቱን አንድ ያደረገ በመስቀሉ ነው፤ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ››፤ ሰላምን ያጡ ኹሉ በመስቀሉ ነው ሰላምን ያገኙት፡፡ በመሣርያ ሰላም አይገኝም፤ አይተነዋል፡፡ እያየነውም ነው፡፡ ሊኾንም አይችልም፡፡ ሰላም በፍቅር የሚመሠረት ነው፤ ሰላም በመስቀሉ ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም በሃይማኖት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም በመግባባት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም የሰዎችን ድምፅ በመስማትና መልስ በመስጠት ነው የሚመሠረተው፡፡ ሰላም ችግርን በማስወገድ ነው የሚመሠረተው፡፡ በኃይል ሰላምን አምጥተው በሰላም የኖሩ በየትኛውም ዓለም የሉም፤ የቀን ቆጠራ ካልኾነ በስተቀር፡፡

ስለዚኽ ማንኛውም ባንኖ፣ ከችግሩ ነቅቶ፣ ሰላምን አስፍኖ፣ ኹሉም የሰላምን አየር እንዲተነፍስ፣ በመግባባት እና ሰላም፣ ችግርን ፈትቶ፣ እነኾ አገራችንን የነፃነት አገር፣ ለማንም ያልተገዛች፣ ለማንም ያልተንበረከከች፣ ለማንም እጅዋን ያልሰጠች፣ በሃይማኖትም በጀግንነትም የጀግኖች አገር፡፡ ያች የጀግና አገር፣ ዛሬ እርስ በእርሳችን በመጠላላት፣ ባለመደማመጥ፣ ለችግር መፍትሔ ባለመስጠት፣ እንዲኹ ዝም ብሎ በስጋት ላይ የተመሠረተ አኗኗር፤ ነጋዴው ነግዶ የማይበላበት፣ ገበሬው ሠርቶ አምርቶ የማያፍስበት፣ የማይቆፍርበት፣ ራሱን የማይረዳበት፣ ተማሪው ተምሮ ተምሮ በትምህርቱ ነገ ለሀገር ደራሽ የማይኾንበት አኗኗር፣ አኗኗር ሊኾን ስለማይችል፣ እነኾ ማንም የሚመለከተው ኹሉ ችግሩን ለመፍታት እንደየሃይማኖቱ(ከአቅራቢያው መስጊድ አዛን ይሰማ ነበር)፣ ክርስቲያኑም ወደ መስቀሉ በመመልከት፣ በመስቀሉ ጥላ ሥር ሰላም መኖሩንና ንጹሕ አየር ያለ መኾኑን በማመን፣ የተጣሉ በመስቀሉ የሚገናኙ መኾኑን በማመን፤ ቅድም እንዳልነው አሕዛብና ሕዝብኮ ተገናኝተው አያውቁም፤ ሕዝብ የሚባለው በእግዚአብሔር የሚያምን ነው፤ አሕዛብ ደግሞ እግዚአብሔርን የማያምን፣ በዘፈቀደ የሚመላለስ ነው፡፡ ሕዝብ እና አሕዛብ የተገናኙ በመስቀሉ ነው፡፡ ነፍስና ሥጋ እንኳ የተዋሐዱት፣ የተገናኙትና የእግዚአብሔርን ክብር ለመውረስ የበቁት በመስቀሉ ነው፡፡

ዛሬም በዓለ መስቀሉን ስናከብር፣ መስቀሉን እንመልከት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተናግሮታል – ‹‹ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ››፤ ጉልበታችን ሊያስመካን አይገባም፡፡ ሊያስመካን የሚችል ቢኖር መስቀሉ ብቻ ሊኾን ግድ ነው፡፡ መስቀሉን የመረጠ ሰው ደግሞ ሰላም አለው፡፡ መስቀሉ ስንል፣ መስቀል የሰላም ዓርማ ስለኾነ ነው፡፡ ከመስቀል ጋር ጥላቻ አይስማማም፡፡ ከመስቀል ጋር እሰጥ አገባ አይስማማም፡፡ ከመስቀል ጋር አንዱ አሳዳጅ ሌላው ተሳዳጅ፤ አንዱ ገዳይ ሌላው ተገዳይ እንዲኾን አይስማማም፡፡ መስቀሉ ኹሉንም እኩል ይዋጃል፤ በመስቀሉ ድነናልና፡፡ በዚኽ መስቀል ላይ ነው፣ መድኃኒታችን ተሰቅሎ የነፃነትን ዐዋጅ ሲያውጅ፣ ይህ መስቀል የክርስቶስ ዙፋን ነው፤ ይህ መስቀል የነፃነት ዐዋጅ ማወጃ ነው፡፡ ለዚኽ ነው፤ አማናዊትዋ፣ ጥንታዊትዋ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ መስቀሉን የምታከብረው፡፡ እግዚአብሔር ያከበረው ስለኾነ ነው፡፡

ቅድም የዕለቱ ወንጌል(ዮሐ. ምዕ.19 ቁ.25) ሲነበብ ሰምታችኋል፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ አላዋቂዎች ሲዘባበቱበት፣ ሲቀልዱበት፣ ሲተፉበት፣ ራስኽን አድን እያሉ የምፀት ቃል ሲናገሩበት፣ ከመስቀሉ ላይ እንዳለ ለቅዱስ ዮሐንስ፣ ‹‹እነኋት እናትኽ››፤ ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ደግሞ፣ ‹‹እነኾ ልጅሽ›› በሚል ቃል ኪዳኑ የጸናበትእኛ ልጆቹ፣ የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ልጆች፣ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእኛ እናት ትኾን ዘንድ በመስቀሉ ቃል ኪዳን የገባበትም ስለኾነ፣ የተዋሕዶ እናት ቤተ ክርስቲያናችን መስቀሉን በዚኽ ዓይነት ታከብረዋለች፡፡

ስለዚኽ ባለንበት ሰዓት ብዙ አይተናል፡፡ የዘመኑን የማኅበራዊ መገናኛ መሥመሮችን ብዙ ተመልክተናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝንም፣ የሚዘገንንም ድርጊት ሲፈጸም፣ ሲደረግ፤ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ፣ ወገን በወገኑ ላይ ያደርጋል ተብሎ በማይታሰብ መልኩ እያየን ነው፡፡ ይህ ይበቃል ልንል ይገባል፡፡ በቃ! ወደ ሰላማችን እንመለስ፤ ችግሮች ይፈቱ፤ መግባባት ይስፈን፤ ኹሉም ሥራውን እየሠራ ለጥያቄው በሰላም መልስ እያገኘ መኖር አለበት፤ ወደሚለው ኹሉም ማዝመም አለበት፡፡ እንደ ፖሊቲካ አይደለም የምናገረው፤ እንደ ሃይማኖት ግን መናገር ያለብኝ ነገር አለ ብዬ አምናለኹ፣ መንግሥትንም በተመለከተ፡፡ በፖሊቲካ ከመነዘረው የእርሱ ጉዳይ ነው የሚኾነው፤ የእኔ አይደለም፤ እንደ ሃይማኖት ግን በነፃነት፣ በድፍረት ነው የምናገረው፡፡

ትላንትና መንግሥት፣ የሞቱትን ዐፅም በማውጣት፣ በመሰብሰብ፡- ‹‹አረመኔው እና ጨካኙ፣ ይኸው ልጆቻችኹን ገደለላችኹ›› ብሎ፣ ማላቀሱ የትላንትና ትዝታ ነው፡፡ ይህ ታሪክ ደግሞ ዛሬም በውስጣችን ተፈጽሞ፣ ነገ ሌላ የታሪክ ጠባሳ በስሙ እንዳይኖር ሊጠነቀቅ ይገባዋል፡፡ ነገሮችን ኹሉ በመወያየትና ችግሮችን በመፍታት፣ ሰላምን ለማስፈን መንግሥትም ግዴታ አለበት – ከላይ እስከ ታች፡፡ ያ እስከ ኾነ ድረስ ሰላምን የተጠማ ሕዝብ ነው፡፡

ማንኛውም እንደሚናገረው፣ በርግጠኝነት፣ ምንጊዜም ችግር የመሪው እንጂ የተመሪው ሕዝብ አይደለም፡፡ በቤተ ክህነትም፣ ኹልጊዜም ችግር የመሪው እንጂ የሕዝብ አይደለም፡፡ የምለውን ካላደረግኽልኝ፣ ጩኸቴን ካልሰማኸኝ…(የምእመናን እልልታና ጭብጨባ ይሰማል፤ ብፁነታቸውም …ግዴለም፣ ግዴለም አጨብጭቡልኝ እያልኩ አይደለም፤ ዝም ብላችኹ ስሙ፤ በማለት ይቀጥላሉ) የጩኸቱን ድምፅ ሰምቶ ለጩኸቱ ካልመለሰ፣ ማስተባበያ ካልሰጠ፣ አዎንታዊነቱን፣ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ብሎ ካላረጋገጠ፣ መልስ እስካልሰጠኸኝ ድረስ ጩኸቴን አላቆምም ማለት የተለመደ ነው፡፡

አንድ ሕፃን ልጅ ወደ ወላጆቹ ያለቅሳል፤ እናት ይኑረውም አይኑረውም ጡትዋን ስትሰጠው ጸጥ ይላል፡፡ ማግኘት አለማግኘት፣ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እንደ እርሷ አመጋገብ ነው፡፡ ለምግብም የደረሰ እንደ ኾነ እርጥብም ይኹን ብስል እንደ አኗኗሯ፣ የተወሰነ ነገር ስትሰጠው ያን ይዞ ዝም ነው፡፡ አለበለዚያ ሕፃኑ ማልቀሱን አይተውም፡፡ መንግሥት፣ እንደ ወላጅም እንደ መሪም እንደ ሀገር ጠባቂም ኹለንተናዊ ሓላፊነት እጁ ላይ የተጣለበት እንደ መኾኑ፣ ችግሮችን በመፍታት መፍትሔ መስጠት አለበት፡፡

በአንፃሩ፣ የሚዲያ ሰዎችም እዚኽ አያችኋለኹ፡፡ ወደፊት በዚኽ ዓይነት እንድትቀርጹ የምንፈቅድ አይመስለኝም፤ ከይቅርታ ጋር፡፡ ዛሬ፣ እዚኽ ነፃ ስለኾነ መልካም ነው፡፡ ለምን ቢባል፣ አንዳንድ ጊዜ እኛን ትጠይቃላችኹ፤ ታናግሩናላችኹ፤ እኛ ከሕዝቡ ጋር የምንጋጭበትን የፈለጋችኹትን ቃል ቀጥላችኹ ታስተላልፋችኹ፤ ሕዝቡ ያን ይሰማና፣ ምን አባት አለን? ይላል (ጭብጨባ ይሰማል)፡፡ የምንናገረውን በትክክል አድርሱ፡፡

ቤተ ክርስቲያን፣ ለማንም ለማን አትወግንም፡፡ ጥላቻን አትሰብክም፤ መገዛትን ታምናለች፤ ተገዙም ትላለች፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነውና አትገዙ አትልም፡፡ ቤተ ክርስቲያን፣ አልገዛም የምትልበት ጊዜ ቢኖር፣ በሃይማኖትዋ ሲመጣ፤ ሃይማኖትን ካድ፤ ማዕተብን በጥስ፤ ቤተ ክርስቲያን የሚዘጋ ካለ፣ አዎ፣ አልገዛም ብላ አንገትዋን ትሰጣለች፡፡ ግደል ግን አትልም፡፡ ሞትን ተማርን እንጂ መግደልን አልተማርንም፡፡ መሰደድን ተማርን እንጂ ማሳደድን አልተማርንም፡፡ ክርስቲያን ይህ ነው – ይሰደዳል እንጂ አያሳድድም፡፡ ይሞታል እንጂ አይገድልም፡፡ ይወቀሳል፤ ይሰደባል እንጂ አይወቅስም፣ አይሰድብም፡፡ እውነትን ግን በዐደባባይ ይናገራል፡፡

ለዚኽ ነው ዛሬ፣ ከትንሽ እስከ አዛውንቱ በአማናዊት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስቦ፣ ለሀገር ሰላም የቆመው፤ ለሀገር አንድነት የሚጸልየው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሀገርን ሰላም ትፈልጋለች፤ ባለታሪክ ስለኾነች፡፡ ከጥንትምኮ ለዚኽች ሀገር ነፃነት ማን ነው አንድዋና ተጠቃሹዋ ባለታሪክ? ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ታቦትዋን መስቀልዋን አዝማች፣ መሪ አድርጋ፡፡ እስከዛሬ ድረስኮ ቋንቋችን፣ ባህላችን፣ ሥርዓታችን ተደበላልቆ የባዕዳን አገር ትኾን ነበርኮ፣ እንደሌላው፡፡

ይህች አማናዊት ቤተ ክርስቲያን ግን ኹልጊዜ በመስቀል እየባረከች፣ በመስቀል እያቀረበች፣ በመስቀል እየሳበች፣ በመስቀል እያስታረቀች፣ የተለያየውን በመስቀል እያገናኘች፣ በመስቀል ነፃነት ያላትን አገር ለትውልድ አውርሳለች፡፡ ዛሬም ምኞትዋም ዓላማዋም ይኸው ነው፤ ሌላ ዓላማ የላትም፡፡ ሌላ የሚናፍቃት ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሚናፍቃት ሰላም ነው – የመስቀሉ ሰላም፡፡ የምፀት ሰላም አይደለም፡፡ የመስቀሉ ሰላም፣ ‹ለማግባቢያ› የሚነገር ሰላም አይደለም፡፡ ለማጥመጃ የሚነገር ሰላም አይደለም፡፡ የውሸት ዕርቅም አይደለም፡፡ በመስቀሉ የተፈጸመው አማናዊ ሰላም፣ ዛሬም፣ ነገም ከነገ ወዲያም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይናፍቃታል፡፡ ሥራዋም፣ ልመናዋም፣ ጸሎትዋም ይኸው ነው፡፡ (ጭብጨባ)

ለዚኽም ነው፣ ሌትም ቀንም፣ አይደለም ስለ ሰው ልጆች ስለ ሀገር ጠባቂዎች፣ ስለ ወታደሩ፣ በሀገሩ በድንበሩ፣ ‹‹ዕቀብ ሕዝባሃ ወሠራዊታሃ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ፤ ዳር ድንበሯን፣ ሕዝብን የሚጠብቀውን ሠራዊት በአጠቃላይ ከላይ እስከ ታች ከጠላት ከወራሪ ጠብቅ፤ ታደግ›› እያለች በመስቀሉ የምትጸልይ ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ስለዚኽ የቤተ ክርስቲያን ድምፅዋ ሊሰማ ይገባል፡፡

ዐዋጅዋ፣ ማንኛውም ነገር፣ የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ያዘኑት እንዲጽናኑ ነው፡፡ በማወቅም ባለማወቅም፣ የሚገርመው ነገር፣ እያንዳንዱ የየግሉን ጥላቻ ምክንያት አድርጎ፣ የመስቀሉን ቃል ኪዳን ረስቶና ዘንግቶ፣ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ጠላትን ለመበቀል፣ ባልሠራው፣ ባልዋለበት፣ ሰውዬው ያለ፣ ሌላ አገር ነው፣ እንዳለ እየተደረገ ታስሯል፡፡ ይኼ በደል ነው፡፡ አንድ ሰው ባልሠራው ከታሰረ፣ ባላደረገው ከተወነጀለ እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም ይላል? ሰላምን ያሳጣል፡፡

eth-demera09
ስለዚኽ ማንኛችንም ለሰላም፣ ለሀገር ፍቅር፣ ለሀገር ነፃነት፣ ለሀገር ዕድገት፣ ለኹለንተና፣ ከልመና ለምንላቀቅበት ነገር ኹሉ፣ በአንድ ድምፅ ቤትን ዘግቶ ጠላት ሳይሰማ፣ በእልክ፣ በአላስፈላጊ ነገር፣ እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ፣ እስኪ የታባትኽንስ ምን ታመጣለኽ ብሎ፣ ዘመን የፈጠረውን መሣርያ አንግቦ ከመሮጥና፤ ሌላውም የመጣው ይምጣ ልሙት ብሎ ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ወደ መስቀሉ ተመልክተን፣ ወደ እግዚአብሔር ነግረን፣ እውነተኛ ፍርድ ሰጪው እግዚአብሔር፣ ፍርዱን ሰጥቶ፣ ሰላሙን አብዝቶ፣ በቃችኹ ብሎ ኹላችንም በሰላም እንድንኖር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልእክት ነውና፣ ኹላችን ይህን ገንዘብ ልናደርግ ይገባል፡፡(ጭብጨባ እና እልልታ)

ለክርስቲያኑ፣ ለሠራዊቱ – ወታደራዊው ትእዛዝ፣ ከዚያው ካላችኹበት ኹኖ፣ ለክርስቲያኖች፣ እንደ መንፈሳዊ መሪነቴ የማዝዘው፣ ለሠራዊቱ፣ ለወታደሩ፣ ለኹሉም፤ መሣርያው ይያዝ እንጂ ምላጩን ከመሳብ ይልቅ የፍቅር መሳቢያን ተጠቀሙ፡፡ የፍቅር ማሰርያን ተጠቀሙ፡፡(እልልታ እና ጭብጨባ) አዎ፣ ሌላውም ደግሞ እስኪ ምን ታደርገኛለኽ ብለን፣ እሳት ይዞ እሳት በሚተፋ ፊት፣ በአላስፈላጊ ጉልበትና ስሜታዊነት አትተላለቁ፡፡ ወደ እግዚእብሔር ቀርበን እንጩኽ፤ እግዚአብሔር መልስ ይሰጣል፣ ከዚያ በላይ ከኾነ፡፡(እልልታ እና ጭብጨባ)

ስለዚኽ ኹላችንም በያለንበት እንደ ወገንነት እንተዛዘን፡፡ እንደ ወገንነት እንተባበር፡፡ ስንቱ ወገን ነው በበረሓ ያለቀው፤ ስንቱ ወገን ነው እንጀራ ፍለጋ በየሀገሩ የተሰደደው፤ ስንቱ ወገን ነው ባሕር የሰጠመው፤ ስንቱ ወገን ነው ዘንዶ የዋጠው፤ እዚኽኮ ሰላማችን ቢበዛ፣ መደማመጥ ቢኖር፣ መቀባበል ቢኖር፣ መፍትሔ በየሰዓቱ ቢሰጥ ኖሮ ኹሉም ሰላም ይኾን ነበር፡፡ ሰላም ካለ ደግሞ ኹሉም ነገር አለ፡፡

ስለዚኽ ዛሬ ስጋት ነው፤ መስቀል እናክብር አናክብር፤ እንዲኽ ቢኾንስ እንዲኽ ቢደረግስ፣ ብዙ ተብሏል፡፡ ይህ የምታዩት ሕዝብ፣‹ሃይማኖቴ ነው፤ የመጣው ይምጣ› ብሎ ለሃይማኖቱ ቆርጦ የመጣ እንጂ፣ አኹን እገሌ ይጠብቀኛል እገሌ ያስጠብቀኛል ብሎ አይደለም፡፡

ሃይማኖት ከኹሉም በላይ ስለኾነ፣ ተደብቆ መዋልን ትታችኹ፣ በዚኽ ሃይማኖት፣ በዚኽ መስቀል ዐደባባይ፣ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችኹና ተቀብላችኹ፣ መስቀሉን መሪና ሠሪ፣ በመስቀሉ ሰይጣንን ድል አድርጋችኹ፣ በአንድነት በፍቅር መስቀሉን እንድናከብር፣ ጥሪውን ሰምታችኹ በዚኽ የተገኛችኹ ኹሉ፣ እግዚአብሔር በኃይለ መስቀሉ ይባርካችኹ፤ እግዚአብሔር ይጠብቃችኹ፤ ኹሉንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡

ዛሬ ለጠላት መሣቂያና መሣለቂያ የኾነችውን አገራችንን፤ በሩቅ ኹነው እየተመለከቱ፡- አለቀላቸው፣ አበቃላቸው ለሚሉት ባዕዳን፤ ትላንት፡- በሰማይ በራሪ፣ በምድር ተሽከርካሪና ተወንጫፊ ኾነው መጥተው በኀፍረት ለተመለሱ፣ የሀገራችንን ጀግንነትና ወኔ ለቀመሱ፣ ካህናቱ በመስቀላቸው በታቦታቸው፣ ጀግናው በጀግንነቱ ተከላክሎ ማንነታቸውን አሳፍሮ ለሰደዳቸው፤ ዛሬ እርስ በርሳችን በፈጠርነው መከራና ችግር መሣቂያና መሣለቂያ ከመኾን እግዚአብሔር አድነን፤ ምኞታቸውን ኹሉ አርቅልን፤ ተማምነን ተደማምጠን፣ መንግሥትም የሕዝቡን ጩኸትና ብሶት ሰምቶ፣ ችግሩን ፈትቶ፣ በሰላማዊ መንገድ እንኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን፡፡

እንደ ዛሬው ኹሉ ለሚመጣው ዓመትም ያድርሰን፡፡ አሜን፡፡ ጸሎት፡፡


“የመለስ ልቃቂት” ሆድ እቃ ሲገለጥ” [ሚካኤል ደርቤ (ቦስተን ማሳቹሴት)]

$
0
0

መንደርደሪያ    

%e1%8b%a8%e1%88%98%e1%88%88%e1%88%b5-%e1%88%8d%e1%89%83%e1%89%82%e1%89%b5-satenaw-newsደረቅ ፖለቲካዊ መረጃዎች የተዘጋጀበት መጽሀፍ እንዲነበብ ከተፈለገ በአቀራረቡና በአፃፃፍ ስልቱ የሚያጓጓ ሊሆን ይገባል። በተለይም ስለ ዘረኛ ኋላቀርና ቆሞ ቀር የሆነውን የወያኔ ፖለቲካ መጽሐፍ ጽፎ አንባቢ መሳብ በጣም አስቸጋሪ ነው። ሩቅ ሳንሄድ  የእንግሊዝ የወያኔ መፈንጫ የሆነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተከማችቶ የአይጥ መናኸሪያ የሆነውና በአስወጋጅ ኮሚቴ የተቃጠለው የውሸት አለቃ የሆነው በረከት ስምኦን የበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ መጽሃፍ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። የውሸት አለቃው መጽሃፉን በውድ ዋጋ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ቢያሳትምም፣ በሸራተን ሆቴል ውስኪና ሻምፓኝ አስከፍቶ ቢያስመርቅም፣ በታዋቂ ሆድ- አደር አርቲስቶችን ምዕራፍ እያስነቀሰ ቢያስነብብም፤ በማዕዛ ብሩ ሸገር ሬዲዮ በግድ እንዲተረክ ሙከራ ቢያደርግም መነበብ አልቻለም ከዚህ በተጨማሪ አንባቢዎች መጽሃፉን የፃፈው ሰው የደበቀው ነገር ሊኖር ይችላል፤ አሊያም ሃሰትን በእውነት ተለውሶ የተከተበ መሆን ጥርጣሬ ካሳደረ የመነበብ እድሉ ዝቅተኛ ነው። እርግጥ “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” የሚባል የተለመደ ሀገራዊ ብሂል ቢኖርም የወያኔን የሴራ ፖለቲካ ለማንበብ ከዚያም በላይ ትዕግስት ይጠይቃል። ወያኔ በጠላትነት መጥቶ እንደ ንብ መንጋ ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል አሰራር ተቆጣጥሮ ያደረሰው የግፍ ግፍ የሂሳብ ስሌት ሳይሰሩ የሚያቀርቡ ሰዎች ለማውራትም ሆነ ለማርዳት የመታመን እድላቸው ጠባብ አይደለም። የሚቀርቡት መጽሀፎች በመረጃ የተጠናከሩ፤ ግራ ቀኝ  አመለካከቶችን ማገናዘብ ከቻሉ፤ በሀቅ ላይ የተመሰረቱ ትናንትናዎች ይዘው የሚነሱ ከሆነ መነበብ የሚችሉበት እድል ሰፊ ይሆናል።

ስለሆነም በአንድ በኩል ተጨባጭ መረጃዎችንና እውነታዎችን ሳይዛቡ የሚቀርቡበት፤ በሌላ በኩል ከሙያም ከፖለቲካ ልምድም በመንሳት የግል ምልከታን ሳያቅማሙና ሳይተሻሹ ለማቅረብ ከፍተኛ ድፍረት ይጠይቃል። ለምሳሌ ወያኔ ከልቡ ማውጣት ያልቻለው ገብሩ አስራት ጠቃሚ መረጃዎችን የያዘ ዳጎስ ያለ መጽሃፍ ቢያበረክትም በርካታ ሚስጥሮችን ሊሸሽግ በመሞከሩ “ከነገረን የደበቀን ይበልጣል” መባሉ መነሻው ይሄ ነው። በተለይም ኤፈርትን የመሳሰሉ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አጥንት የጋጡ የዝርፊያ ማዕከላት “በኢትዮጵያ ያሳደሩት ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ እዚህ ግባ አይባልም” ማለት እንኳን የገፈቱ ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለገብሩ የመንፈስ ልጆችም አያሳምንም። ከገብሩ አስራት ጋር “መድረክ” የሚል ድርጅት የመሰረቱን ፕሮፌሰር መረራንም ሆነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በገብሩ አገላለጥ ከማዘን አልፈው መናደዳቸው አይቀርም።

 

“የመለስ ልቃቂት” የተባለው የኤርሚያስ ለገሰ መጽሀፍ በቅድሚያ ለመመርመር የሞከርኩት ከዚህ አንጻር ነበር። ይህንን ጽሁፍ ለመሞነጫጨር ያነሳሳኝ የመጀመሪያ ምክንያት ይሄ ነው። ያለማጋነን ከገመትኩት በላይ በበርካታ መረጃና ማስረጃዎች የታጨቀው ይህ መጽሀፍ የህዉሃት በዝርፊያ የተመሰረቱና የፋፉ ኢኮኖሚያዊ ሃይሎች ላይ መብረቃዊ ምት ያሳረፈ ነው። ፀሃፊው ኤፈርት-መር ካፒታሊዝም እያለ በተደጋጋሚ ቢገልጠውም ለእኔ ግን በዝርፊያ የገነባው ካፒታሊዝም (Crony Capitalisim) ሆኖ አግንቼዋለሁ። በሌላ በኩል ፀሃፊው የዝርፊያ ማዕከሉን በግማሽ መንገድ እንዳለ አስልቶ “ልቃቂት” ደረጃ ደርሷል ቢልም በዚህ መልኩ ለጥቂት ጊዜያቶች ከቀጠለ የአገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት በአያሌው የሚናጋ ይሆናል። ጊዜ ከተሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ስርአቱን ለመገርሰስ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል ይሆናል። ከልቃቂት ያለፈው የዝርፊያው ካፒታሊዝም (ክሮኒክ ካፒታሊዝም) በጠምንጃና በሰደፍ የፖለቲካ ስልጣንን ማቆየትንና በህዝብ ላይ ሸክሙ የሚከብድበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከመጽሀፉ መገንዘብ የቻልኩት ነገር ቢኖር የወያኔ አገዛዝ በዝርፊያ ቁምጣን የያዘው ቢሆንም በቃን የሚል አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ባደረሰባቸው አደገኛ ምት እንደተጎዱ መውሰድ ቢቻልም የቆሰለ አውሬ ሆነው የሚቀትሉበት ሁኔታ እድሉ ዝግ አይደለም። አደብ እንዲገዙ ካልተደረገ አልጠግብ ባይነታቸው በበለጠ ቁጭትና በቀል ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል።

የአገሪቱን ሀብት የተቆጣጠሩት የህዉሃት የብርቅ ልጆች በአንድ በኩል በሃብት ጋራ ላይ ሰማየ ሰማያት እየረገጡ የሚሄዱበት፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሃዘን ቤትነቷ የሚቀጥል ይሆናል። ይህ እንደ አሳ ከጭንቅላቱ የገማ ስርአት ያለምንም ከልካይ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ይፈጠራል። ፀሃፊው በመጽሐፉ እንደገለጸው ሁኔታዎች በፍጥነት ካልተቀየሩ ነገ ከነገወዲያ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ”፣ “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ”፣ “የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን” የሚባሉ ተቋማት በባለቤትነትና በስም ተቀይረው የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ዛሬ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር 40% ያህሉን ወያኔ ኤፈርትን ለመሰሉ ዘራፊ ኩባንያዎች እንዲሰጥ ካስገደደ፤ ከአመታት በኋላ እንደ አንፀባራቂው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ ውጤት የብድር መጠኑም ተመሳሳይ ይሆናል።

ለምሳሌ ያህል “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 139 ላይ “ልማት ባንክ የማነው? የትግራይ አይደለምን?” በሚል ርዕስ ስር እንዳመለከተው “በዘመነ መለስ ዜናዊ” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው 8.5 ቢሊዮን ብር ብድር ውስጥ 5ቢሊዮን ያህል (59%) የወሰዱት የትግራይ ክልላዊ መንግስትና የዘረፋ ካፒታሊዝም እየገነባ ያለው ኤፈርት ነው። ልማት ባንኩ ዳይመንድ ጁባይል ኢዩቤልዩውን ባከበረ አመት ብቻ  ለማበደር በእቅድ ከያዘው 2.78 ቢሊዮን ብር ውስጥ 1.7 ቢሊዮን ብር (63%) የዘራፊው ቡድን ንብረት ለሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስቀድሞ የተያዘና የተፈቀደ ነው። ከሁሉም የሚያሳዝነው አበዳሪም ተበዳሪም የሆነው ኤፈርት በራሱ የሰጣቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ጆፌ አሞራ ከየቦታው የለቃቀማቸውን የኤፈርት ብድሮች የተበላሹና የማይሰበሰቡ በማለት ከአካውንቱ እንዲወጣ አድርጓል። “የመለስ ልቃቂት” የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምዕራፎች አየር መንገዱ፣ ጉምሩክ ባለስልጣን፣ ቴሌ ኮሙዩኒኬሽን፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣ ንግድ ባንክ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ ደህንነት ቢሮ፣ መከላከያ፣ ኢምግሬሽን ቢሮ፣ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ኤምባሲዎች፣ የሚዲያ ትርቋማት (ኢቲቪ፣ ፋና፣ ዋልታ)…. ወዘተ በምግባር የማናቸው የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ነው።

 

“የመለስ ልቃቂት ጭብጦች”                                                                                                                                                                       

ye-meles-lekakit-standing-bookእስከገባኝ ድረስ “የመለስ ልቃቂት” መፅሃፍ ውስጣዊ ይዘት ስመረምር ለጊዜው ሦስት ያህል ቁልፍ ጉዳዮችን ተመልክቻለሁ። እነዚህ ቁምነገሮች በተጠናጥል የቆሙ ሳይሆን አንደኛው ለቀጣዩ መሰረት ሆኖ የሚያገለግል ነው። ለዚህም ሃፍረተቢስነታቸውም ያስመሰከሩ በቂ ምክንያቶች ቀርበዋል። ወያኔዎች ከራስ በላይ ንፋስ እንደሚባለው ብሂል “ወደ ውስጥ ተመልካች” (Inward Looking) በመሆናቸው ስለደህንነት መዋቅራቸው፣ ስለ ኢኮኖሚ ሞኖፖሊያቸውና የፖለቲካ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚሰሩት የተቀናጀ ስራ ጠቅላላውን የፖለቲካ ሃይል አሰላለፍና ጉዞ እንድንመለከት ያስችለናል። ለማንኛውም “የመለስ ልቃቂት” ዋና ዋና ጭብጦች የሚከተሉት ይመስሉኛል።

ጭብጥ አንድ፦ የመጽሃፉ መንደርደሪያና ፍሬ ሃሳብ በምዕራፍ አምስት “የማስታወሻ አስኳል” በሚል ርዕስ እናገኘዋለን። የማስታወሻው አስኳል ባለቤት ሟቹ መለስ ዜናዊ ሲሆን ኤርሚያስ “ስድስቱ የመለስ አስተምህሮዎች” በማለት ከፋፍሎ ለብቻ አቅርቦታል። እነዚህ አስተምህሮዎች መለስ ዜናዊ ድንክዬ ልጆቹንና የቤት ውስጥ ባለሟሎቹን ለማደቆን ያዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደሚገኝ ያስገነዝባል። “የመለስ ልቃቂት” ገጽ 165- 166 ስድስቱ አስተምህሮቶችን ጭማቂ እንደሚከተለው ይገልጻል፦

 

አስተምህሮ አንድ፦“ትእምት የህዉሀት ንብረት ያልሆነ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በተሠባሠበ ገንዘብና ንብረት በህግ የተቋቋመ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ነው”

አስተምህሮ ሁለት፦“ትእምት የተቋቋመበት ተልዕኮ በመንግስትም ሆነ በባለሀብቶች ሊሸፈን የማይችል ቀዳዳ ለመድፈን  ነው።”

አስተምህሮ ሶስት፦  “ትእምት አመራር ስርአት በግልፅነት መርህ ላይ የተመሠረተ ነው።”

አስተምህሮ አራት፦ “ትእምት ከመንግስት ያገኘው ወይም የወሰደው ቅንጣት ሳንቲም የለም። ወደፊትም አይኖርም።”

አስተምህሮ አምስት፦ “ትእምት ኢኮኖሚውን ሊቆጣጠር፣ ባለሀብቶችን ሊያፍን ነው የተቋቋመው በማለት የሚናፈሠው  አሉባልታ መሠረ-ቢስ ነው”

አስተምህሮ ስድስት፦ “ትእምት በክልሎች መካከል የተመጣጠነ እድገት መኖር አለበት ብለን ያስቀመጥነውን መርህ  አይጻረረም”

ኤርሚያስ በመጽሀፉ አስኳል ላይ የመለስን አስተምህሮ ለምን በስድስት ገድቦ ለማቅረብ እንደፈለገ ግልፅ አይደለም። የማስታወሻውን አስኳል ነጥብ በነጥብ ለተመለከተ ሰው ተጨማሪ የመለስ የቅጥፈት አስተምህሮቶችን መመልከት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል “በመለስ ልቃቂት” ገጽ 182 ላይ እንደተገለጸው መለስ ዜናዊ “ኩባንያዎቹ የወያኔን ፖለቲካዊ ስራዎች ለማከናወን ገንዘብ አይሰጡም” የሚል የጠራራ ፀሃይ ውሸት ጽፏል። ድንክዬዎቹና ባለሟሎቹ “የደንቆሮዎች ውይይት” በመሰለ የሃሳብ ውዥንብር ውስጥ ካልዳከሩ በስተቀር ህዉሃትና በተለያየ ጊዜ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው ድርጅቶች በዘረፋ የተደራጁት ኩባንያዎች ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች ናቸው። ከዚህ አንፃር የዝርፊያ ኩባንያዎቹ ያደረጉትና እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ በለሆሳስ የሚታለፍ አይደለም። ፓርቲዎቹ ለሚሰሩት ስራ፣ ለአባሎቻቸው የሚከፍሉት መደለያ ገንዘብ ህዝቡን ለማፈን ለሚዘረጉት መዋቅር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገንዘብ ምንጫቸው እነዚህ ኩባንያዎች ናቸው።

ያም ሆነ ይህ “የመለስ ልቃቂት” ከመጀመሪያው ምዕራፍ እስከ መጨረሻው  ገጽ ድረስ የሟቹ መለስ ዜናዊ ኑዛዜ ቃላት (“አስተምህሮ”) በቅጥፈት የተሞሉና ውሸት መሆናቸውን በመረጃ አስደግፎ ያቀርባል። በዝርዝር እንዳየሁት ከሆነ ይህ “አሳ ጎርጓሪ” የሆነ መጽሃፍ ከኢኮኖሚ ሂሳብ ባሻገር የወቅቱን የህዉሃት የፖለቲካ የበላይነት የተረጋገጠበት ነው።

ጭብጥ ሁለት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዘረፋ የኢኮኖሚ ሃይሎች የሆኑትን ኤፈርት፣ ትልማ(ትግራይ ልማት ማህበር) እና ማረት (ማህበረ ረድኤት ትግራይ) አስቀድሞ በታቀደና የአፓርታይድ መርሆ በሆነ መንገድ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት የማግበስበስ ስራ በቅንጅትና በመደጋገፍ እንደሚፈጽሙት ያስረዳናል። በጠምንጃ የተደገፈው የወያኔ ስልጣነ መንግስት ለሦስቱ የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች የተለያየ ተልዕኮ በመስጠት የኢትዮጵያንም ሆነ ከውጭ የሚመጡ እርዳታዎችን በመቀራመት ወደ ትግራይ እንዴት እያሻገረ መሆኑን መረዳት ይቻላል። የኤፈርት፣ ትልማና ማረት ጓዳ ጎድጓዳ ሲመረመር በአገሪቷ ላይ ያደረሱትና እያደረሱ ያሉት የጥፋት መጠን ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ርግጥም በኢትዮጵያ የሰፈነውን ኢ-ፍትሃዊነትና የተዛባ ተጠቃሚነት ለመዳሰስ የሦስቱን የፖለቲካል- ኢኮኖሚ ሃይሎች አመሰራረት፣ አደረጃጀት፣ ራዕይ፣ ተልዕኮና ተጨባጭ ተግባራት አብጠርጥሮ ማወቅ የወያኔ መሪዎች የኢኮኖሚ ራዕይ “የትግራዋይ” መሆኑን ይደርስበታል። ያለምንም ማጋነን “የመለስ ልቃቂት” ኢትዮጵያን አፓርታይድ በሚመስል መልኩ የያዙት የወያኔ መሪዎች ለሩብ ክፍለዘመን ቆዳቸውን እየቀያየሩ የሚያሳዩትን ድራማ በመረጃ አስደግፎ ያቀረበ በሳል መጽሃፍ ነው።

በተለያዩ መጽሃፍትና መጣጥፎች እንደተገለጠው የወያኔ የኢኮኖሚ አውታር ስለሆነው “ኤፈርት” ብዙ ተብሏል። ኤርሚያስ በዚህ መጽሃፍ ላይ በርካታ መረጃዎችን በመጨመር ያጠናከረው ሲሆን በአገሪቷ ህግ መሰረት የተቋቋመ መሆኑና አለመሆኑን ጥያቄ አስነስቶበታል። የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ላይ መነጋገር መጀመር እንዳለባቸው አስገንዝቧል። እኔም የጸሃፊውን ሃሳብ እጋራለው። ከወያኔ በኋላ የሚገነባው አዲስ ስርአት በእነዚህ የዝርፊያ ተቋማት ላይ አስቀድሞ አቋም መውሰድ እንደሚገባው አምናለሁ። የተዘረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት ለባለቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል። በስሙ የሚነግድበት የትግራይ ህዝብም ኤፈርት፣ ትልማም ሆነ ማረት ህገ-ወጥና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ የተቋቋሙና የኢትዮጵያን ህዝብ አጥንት በመጋጥ የፋፉ መሆኑን ተገንዝቦ ድርጅቶቹ ላይ ለሚወሰዱት እርምጃዎች ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል።

ጭብጥ ሦስት፦ “የመለስ ልቃቂት” የወያኔ ሦስቱ የዝርፊያ ድርጅቶች የትግራይ የህዝብን በልዩ ሁኔታ ተጠቃሚ አድርገዋል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን በተለያዩ ቦታዎች አሳይቷል፡፤ ይህንን ድምዳሜ በመጽሃፉ ሆድ እቃ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጀርባ ሽፋኑም ላይ አጽንኦት ሰጥቶ አስፍሯል። ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ይላል፣

“ትግራይ አልተጠቀመችም የሚለው የፖለቲካ መንገድ በየትኛውም መከራከሪያ እያረጀና እያፈጀ ሄዷል። ተጠቃሚነት መለካት ያለበት በየደረጃው ነው። …. ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ሚሊኒየር ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የመንግስት ተቀጣሪ ሊሆን አይችልም። ሁሉም የትግራይ ተወላጅ ዩንቨርስቲና ኮሌጅ ሊገባ አይችልም።…. ትግራይ ተጠቅማለች ሲባል ሁሉም የትግራይ ወጣትና ሴት የፋብሪካ ሰራተኛ ኩባንያዎች በሆኑት አዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ፣ አልመዳ ጨርቃጨቅ፣ በትራንስ፣ በህይወት ሜካናይዜሽን፣ መሶቦ ሲምንቶ፣ ኢዛና…. ወዘተ የመሳሰሉት ዘመናዊ ፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሰሩት የትግራይ ተወላጆች ናቸው” ይላል።

“የመለስ ልቃቂት” የወያኔ መሰረት የትግራይ ስለሆነች የትግራይ ህዝብ በየደረጃው እንዲጠቀም አድርጓል ትለናለች። ወያኔ ከምንም በላይ የሚፈራውና የመኖር ህልውናውን የሚያናጋው የትግራይ ህዝብ ስለሆነ ህዝቡ ቢፈልግም/ባይፈልግም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጡ የማይቀር እንደሆነ ያስገነዝበናል። ትግሬዎች ለወያኔ አገዛዝ ባላቸው ቅርበትና ርቀት ልክ ተጠቃሚነታቸው እንደሚረጋገጥላቸው ኤርሚያስ እማኞችን እያቀረበ ያሳየናል።  በዚህ ማስረጃ ውስጥ ገዥዎቻችን ምን አይነት ሰዎችና ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው እንመለከታለን። ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ስለመፈጠራቸው ሳንወድ በግድ ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል።

በአጠቃላይ መልኩ ብዙ እንደተላለፉት የሚያስታውቀው “የመለስ ልቃቂት” መጽሃፍ ወያኔ የፖለቲካ ሞኖፖሊውን እያስፋፋ የሄደውን ያህል የኢኮኖሚ ሞኖፖሊውን በአስተማማኝ መሰረት ላይ እየገነቡ ነው። ለፖለቲካው ፍፁም የበላይነትና መደላድል ወሳኝ የሚሆነው ኢኮኖሚውን መቆጣጠር እንደሆነ የሚገለጥበት አባባል ትክክል መሆኑን ያረጋገጠበት ነው። አዋጁን በጆሮ ካልተባለ በስተቀር ወያኔ የገነባው የዝርፊያ ካፒታሊዝም በራሱ መናገር ጀምሯል። የንቅዘቱ ደረጃ ከወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን ከሚነዛበት ቅጥፈት በላይ ተሻግሯል። ሦስቱ የወያኔ የዝርፊያ ማዕከላት ሁሉንም እየጠቀለሉ ነባር ሀገራዊ ከበርቴዎችን ከጨዋታ ውጭ እየወጡና ከትግራይ ውጭ አዳዲሶች እንዳይወለዱ እየተደረገ ነው። ከዚህ ሁኔታ ተነስተን አገራችን ኢትዮጵያ ያለችበት የወቅቱ ሁኔታና የወደፊት እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል። በአድሎና መገለል ምክንያት ጨጓራው የተላጠውና ቆሽቱ ድብን ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ባልታወቀ ጊዜ ፈንድቶ የወጣ እለት ውጤቱ ምን እንደሚሆን ለመገመት ነብይ መሆን አይጠይቅም።  “የመለስ ልቃቂት” የታመቀውን የህዝብ ብሶት በንዴት ገንፍሎ ሊያወጣው እንደሚችል ሙሉ እምነት አለኝ። ከዚህ አንጻር ኤርሚያስ መጽሓፉን መታሰቢያ ያደረገለት አንጋፋው ሙሉጌታ ሉሌ በጦቢያ መጽሔት ላይ “ስም ያልወጣለት ወንጀል” በሚል ርዕስ ያቀረበው መጣጥፍ ይታወሰኛል። አንጋፋው ብዕረኛ እንደገለጠው ከሆነ አንድ በአገዛዝ ውስጥ ያለ ህዝብ ደም የሚያስተፋ ንዴትና ቁጣ ካልተሰማው መሰረታዊ ለውጥ አይመጣም ይለናል።

“መናደድ ትልቅ ነገር ነው። መናደድ ብንችል ደግሞ አንዱ የዚች አገር ማዳኛ የትግል መቅድም ይሆናል። ግን ለመናደድ ለመብሸቅና ከተቻለም እህህህ ብሎ ደም መትፋት መቻል አለብን!! በማለት ብዕረኛው ይገልፃል።

“የመለስ ልቃቂት” መናደድ የማይፈልገውን ከውስጡ ፈንቅሎ በተዋረደ ስሜት የሚናደድበት ሁኔታ ይፈጥራል። ወጣቱ አዲስ የቁጭት ስሜት ፈጥሮ ወደ ተግባር የሚገባበት “የማታገያ ሰነድ” እንዳገኘ እቆጥራለሁ።

መልካም ንባብ!!

ዜና ኢየሩሳሌም HMD የኔቲኒያሁን ቁጣ አስተናገዱ [ልያ ፋንታ]

$
0
0

14470396_1801475800094729_4946485483949888038_nእስራኤል ለብዙ አመታት ሲመሩዋት የነበሩት መንግስት ሽሞን ፕሪየስ ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው ምክንያት የ70 አገሮች መሪ ተገኝተዋል ከእነሱም መካከል የኢትዮጵያው መንግሰት ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ነበር የቀብር ስነስርአታቸው በተለየ መልኮ ተፈፅሞአል ከቀብር ምላሽ የእስራኤሉ መንግስት ቢንያም ናታንያው ከእነ ሜስታቸው ሰሀራ ናታንያው ከመኖርያ ቤታቸው በመውሰድ ከፍተኛ ወቀሳ ወቅሰዋቸዋል አሁን የምታደርገው አስተዳደር ወደ መጥፎ ደረጃ እየወሰደህ ነው የህዝብን ጥያቄ መቀበል አለብህ መቀበል ካልቻልክ ግን እንደ መሀመድ ገዳፊና ኦሱም ሙባረክ አይነት ይገጥምሀል ብለውታል የህዝብ ቆጣን በመሳሪያ አይደለም መመለስ ምትችለው በመወያየትና የጠየቁትን ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ነው ብለው አስጠንቅቀው ንግረዋቸዋል በመቀጠል የአፍሪካን አንድነት ጥሪ በመቀበል የተባልከውን በሙሉ እንድትፈፅም በሰላማዊ ዜጉችህ ላይ ወታደራዊ እርምጃ አትውሰድ ብለው በመውቀስ ሸኝተዋቸዋል።
የሜገርመው ግን አሉ ብንያሜን ናታንያው ሽሞን ፕሪስን አየሀቸው አይደል ወደ ማይቀረው አለም ሲሄዶ እኛም ነገ ያው ነን ይሄን እያየህ ለህዝብህ ጥሩ አስተዳዳሪ ትሆናለህ ብየ አምናለሁ ብለውታል ሀይለማርያምም በመፀፀት አተኮሮ ያያቸው ነበር
አመሰግናለሁ የጄሩሳሌሙ ወንድሜ
ልያ ፋንታ

ዜና ጎንደር – ከኮረኔል ሰፈር ጎንደር የተገኜ ዜና [ልያ ፋንታ]

$
0
0

Gonder 789የአንበሶች አንበሳ የተባለው ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ለመጄመሪያ ጊዜ በድብቅ ቀረበ ።
ኮረኔል ዛሬ ወደ ፍርድቤት መምጣቱን ህዝቡ ባለመስማቱ እንደ አለፉት ጊዚያት ፍርድ ቤቱ በህዝብ አልተጥለቀለቀም። ይል ቁንም የአማራ ክልል መከላከያ በብዛት ፍርድ ቤቱን በክፍተኛ ጥበቃ ዙሪያውን ከብበውት ነበር።
ኮረኔል ደመቀ ቀደም ሲል በክልሉ የአቃቤ ህግ የተመሰረተበት ሰው የመግደል ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ የተደረገም ቢሆን ከፌደራል መንግስት የመጣው አቃቤ ህግ አንድ ዘርን በማጥቃት እና በአሸባሪነት ተጠርጣሪ ነው በማለት ክስ መስርቶበታል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለመጭው ጥቅምት ወር ቀጠሮ ሰጥቷል።
የጎንደር ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው ኮረኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረቡነረ ዘግይቶ የሰማው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በተለይ እናቶች አሁን ነው የገደሉን እያሉ ሰብሰብ ብለው ሲያነቡ ታይተዋል።
በተያያዘ ዜና በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ ወጣቶች ታስረው የነበረ ሲሆን በሌሊት የት እንደወሰዷቸው ማዎቅ አልተቻለም። የታሳሪ ቤተሰቦች ስንቅ ለማቀበል ሲሄዱ እዚህ የሉም የት እንደተወሰዱ አናውቅም የሚል መልስ ከጣቢያው ፖሊሶች መሰጠታቸውን ከስፍራው የአይን እማኝ አረጋግጦልኛል።
፣ጎንደር የሰማዕታት መንደር፣

 

ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል ለውጥ!   [አስራት አብርሃም]

$
0
0
አስራት አብርሃም
አስራት አብርሃም

በአሁኑ ሰዓት የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም፤ ሁላችንም ለውጥ እንዲመጣ እንፈልጋለን። መሰረታዊው ጥያቄ ግን ዘላቂ ጉዳት የማያስከትል፤ ሁሉንም አሸናፊ፤ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የስርዓት ለውጥ እንዴት ማምጣት ይቻላል? የሚለው ነው። ከደርግ ወደ አሁኑ ስርዓት ለመሻገር እንደ ሀገር ብዙ አላስፋለጊ ዋጋ ከፍለናል፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን ቤት ፈርሷል፤ በመቶ ሺዎች ህይወታቸውን አጥቷል፤ አካለ ጎደሎ ሆኗል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ የባህር በራችን አሳልፈን እንድንሰጥ ተደርገናል፤ ይሄኛው ከደረሱብን ጉዳቶች ሁሉ የከፋ፣ ለቀጣይ ትውልዶች ሳይቀር ዋጋ የሚያስከፈል ነው። አሁን ማሰብ ያለብን እንደነዚህ ዓይነቶቹ ተጨማሪ ጉዳቶች ሳናስተናግድ እንዴት ነው ከዚህ መንግስት መላቀቅና የተሻለ ስርዓት ማምጣት የምንችለው የሚለው ጉዳይ ነው። ለዚህ የተሻለ መፍትሄ ለማግኘት በጉዳዩ ላይ በስፋትና በጥልቀት መወያየት፣ መግባባት መቻል አለብን፤ ፍላጎቶቻችን ማቀራረብና ማስማማት መቻል አለብን።

ስርዓቱን የሚቃወም ሁሉ ለውጥ ለውጥ ፈላጊ መሆኑ እውነት ቢሆንም ሁሉም ግን ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ እየታገለ ነው ማለት አይቻልም። አንዳንድ የምናያቸው ምልክቶችም የሚያሳዩት ይህኑኑ ነው። ስለመጭው ጊዜ፣ ስለሀገር አንድነት፣ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ስለሚኖርባት ኢትዮጵያ እያሰበ የሚታገለው ኢትዮጵያዊ ድምፁ እየሰለለ ነው፣ እዚህም እዚያም በጎጥ በተደራጁ ቡድኖች እየተዋጠ ነው ያለው። አንዳንዶች ደግሞ አንድም በተስፋ መቁረጥ አንድም ደግሞ በራራቸው መንደር በሚኖረው ጊዚያዊ ሞቅታ ልባቸው እየተሰለበ ከነበሩበት የዜግነት ከፍታ ወርደው ወደ ጎጣቸው ገብቷል፤ እርግጥ ነው በዚህ መንገድ መታገል ቀላልና ጥረት የማይጠይቅ ነው። በጎጥ ተደራጅቶ እንደፈለጉ ማውራት፣ በቀላሉ ህዝብን ማነሳሳትና ማሰለፍ ይቻላል። ዘላቂ ውጤት፣ ሰላምና አብሮነት ማምጣት ባይቻልም፤ ለራስህ ጠባብ ቡድን ጊዜያዊ ድልና ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል በህወሀትም እያዩት ስለሆነ ሊያጓጓቸው ይችላል።

በመሆኑም እኔ በዚህ ፅሁፍ በወደፊቷ ኢትዮጵያ የሁሉም የዜግነት መብት በእኩልነት የሚረጋገጥበት፤ ተከባብሮ በፍቅርና በአንድነት መኖር ስለሚቻልበት ነው ሀሳብ መስጠት የምፈልገው። ከአሁን በፊት እንደገለፅኩት ሁላችንም በኢትዮጵያ የተገኘነው መርጠነው አይደለም፤ ተፈጥሮ ነች አንድ ላይ እንድንሆን ያደረገችኝ። መለያየት ብንችል እንኳ ሀሳባዊ ልዩነት እንጂ ከቦታው ነቅለን መሄድ የምችል አይደለንም። ስለዚህ አንድ ላይ መኖር እጣ ክፍላችን ከሆነ እንዴት ነው አብረን ሳንጎዳዳ፤ ተጠቃቅመን፤ ተደጋግፈን መኖር የምንችለው የሚለው ጉዳይ ላይ መነጋገር አለብን።

በአሁኑ ወቅት በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሰዎች የተለያዩ ሀሳቦች እየሰጡ ነው ያሉት፤ እኔም የበኩሌን ሳቀርብ ሀሳቡን ለማዳበር ይረዳ ይሆናል በሚል እምነት ነው። ከሌሎች፤ ከሚመስሉኝ ሰዎች ጋር ሆኜ በጋራ ለመስጠት ብችል ደስ ይለኝ ነበር፤ ነገር ግን በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ እንዳይሆን የነበርኩበት ፓርቲ (አንድነት) ተወስዷል። ከዓረና ከወጣሁም ቆይቻለሁ (ይሄ የምለው አንዳንድ ሰዎች አሁንም ዓረና የምመስላቸው ስላለሁ ነው) በእርግጥ ዓረና ሲታሰብ ጀምሮ የነበርኩበት፤ የፖለቲካ ጥርሴ የነቀልኩበት፤ በሁኔታዎች የማይለዋወጡ ጓደኞች ያፈራሁበት ቢሆንም በአንዳንድ አካሄዶች ላይ በነበረኝ ልዩነት ምክንያት ከፓርቲው እንደተለየሁ የሚታወቅ ነው። ከተለመደው የሀገራችን የመለያየት ባህል በተለየ ሁኔታ በሰላምና በክብር ነው የተለየሁት። ስለዚህ ከቀድሞ የአንደነት አመራሮች ጋር በግል ከማደርጋቸው ውይይቶች ውጪ በአሁኑ ሰዓት የየትኛውም ፓርቲ አባል አይደለሁም።

ወደ ዋናው ዳጉይ ስገባ፣ በመጀመሪያ ምን እናድርግ በሚለው ጉዳይ ላይ እየቀረቡ ባሉት አማራጮች ላይ የራሴን ምልከታ ላስቀምጥና ወደ መፍትሄ ሀሳብ እሻገራለሁ። በአንዳንድ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ቡድኖች በቀዳሚነት እየቀረበ ያለው አማራጭ የሽግግር መንግስት ይመስረት የሚል ነው። የሽግግር መንግስት ጥያቄ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን የሚገኝበት መንገድ እንጂ በአሁኑ ሰዓት አዋጭ የመፍትሄ ሀሳብ አይደለም፤ ኢህአዴግም በዚህ መንገድ ወደ ድርድር ማምጣት የሚቻል አይመስለኝም፤ ይህን የሚያደርግበት አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል ብዬም አላስብም። ስለዚህ የሽግግር መንግስት የሚለው አማራጭ አሁን ባለው ሁኔታ እውን የሚሆን ነገር አይደለም፤ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ሁሉንም ነገሮች ከዜሮ እንዲጀመር የሚያደርግ በመሆኑ ጠቃሚነቱም ያን ያህል ነው።

ሁለተኛው አማራጭ የባለአደራ መንግስት ነው። ይህ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እስኪቋቋም ድረስ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሲቪል ተቋማት፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ የባለአደራ መንግስት ተቋቁሞ ሀገሪቱን በጊዚያዊነት እንዲመራ ማድረግ ነው። እንዲህ ዓይነቱ መንግስት ሰላምና ስርዓት ለማስፈን ሰራዊቱንና የፀጥታ አካላትን እንዴት አድርጎ ሊያዛቸው እንደሚችል ግልፅ አይደለም፤ ምን ዓይነት የህግ መሰረት እንደሚኖረውም ለመገመት የሚያስቸግር ነው። ከሽግግር መንግስትም ብዙ የሚለይ አይመስልም፤ የሚለየው ነገር ቢኖር የሽግግር መንግስት በፖለቲካ ኃይሎች የሚቋቋም መሆኑ ላይ ነው።

በሶስተኛው ረድፍ የሚቀመጡት ደግሞ ከኢህአዴግ ጋራ ጥምር መንግስት መመስረት የሚፈልጉ ናቸው። ከሁሉም በላይ ይሄ አማራጭ የከፋ ይመስለኛል። አንዳንድ የስልጣን ጥማት ያላቸው የፖለቲካ መሪዎች በአቋራጭ ስልጣን እንዲያገኙ ይረዳ እንደሆነ እንጂ ወደ ለውጥ ጎደና የሚወስድ አይደለም። በአንፃሩ ገዢው ፓርቲ ራሱን ዳግም ለማጠናከር እድል የሚሰጥ ነው የሚሆነው። ከኢህአዴግ ባህርይና አሁን በሀገራችን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ካየነው የጥምር መንግስት ጥያቄ የፖለቲካ ሽርሙጥና ነው። በእርግጥ ጥምር መንግስት መመስረት ተገቢ የሚሆንበት ሁኔታ አለ፤ ህዝባዊ ምርጫ ተካሄዶ አንዱ ፓርቲ አሸናፊ ሳይሆን ሲቀር ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ፓርቲዎች ባገኙት የህዝብ ድምፅ መሰረት ድርድር አድርገው በስምምነት የጥምር መንግስት ሊያቋቁሙ ይችላሉ። ከዚህ ውጪ የሆነ ጥምር መንግስትም እንበለው ሽግግር መንግስት ዘላቂ መፍትሄ የማያመጣ ያለህዝብ ውክልና በአቋራጭ ስልጣን ፍለጋ ነው የሚሆነው።

ስለዚህ ለእኔ የተሻለ አማራጭ የሚመስለኝ ፓርላማውን በትኖ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ማድረግ ነው። ኢህአዴግ ከልብ ለበጎ ነገር የሚነሳ ከሆነ፣ በዚች ሀገር ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ከቆረጠ ማድረግ ያለበት በሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ያገባናል የሚሉ፣ በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ፤ በሰላማዊ መንገድም በጥትቅም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትን ቡድኖች ሁሉ ጠርቶ ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡና በሰላም እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ቀጥሎ ምርጫ ቦርድን ሙሉ ለሙሉ አፍርሶ ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ተነጋግሮ በስምምነትና በመተማመን አዲስ ምርጫ ቦርድ በማቋቋም፤ ነፃና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ አድርጎ በህዝብ ለተመረጠው አካል ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ማስረከብ ነው።

እዚህ ላይ መታየት ያለበት ዋናው ነገር ሁሉንም ነገር እንደአዲስ ከመጀመር ይልቅ አሁን ያሉትን የመንግስት ተቋማት ገለልተኛ ሆነው የሚሰሩበትና የሚጠናከሩበት መንገድ ነው። ለምሳሌ ጦር ሰራዊቱ ከላይ ያሉትን የጦር አዛዦች ጡረታ እንዲወጡ በማድረግ የብሄር ተዋፅኦ የጠበቀ አመራር እንዲኖረው በማድረግ ማስተካከል የሚቻል ነው። የደህንነት መስራቤቱንም እንደዚሁ፤ ሌላውም በተመሳሳይ መንገድ ማስተካካል ይቻላል። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ሙሉ ለሙሉ መፍረስና መቀየር ያለበት ምርጫ ቦርድ ነው፤ ከሁሉም ገለልተኛ የሆነ በሁሉም ዘንድ ተአማኒነትና ከበሬታ ያለው፤ በሰው ኃይል፤ በአደረጃጀት ጠንካራ የሆነ ምርጫ ቦርድ ማቋቋም ያስፈልጋል።

ሌላው መስማማት የሚያስፈልገው ነገር ቢኖር የህገ መንግስት ማሻሽያ ጉዳይ ነው፤ ህገ መንግስቱ ለሚደረገው የስርዓት ለውጥና እንዲኖር ለሚፈለገው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚያመች መልኩ መሻሻል መቻል አለበት። በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖረው አስተዳደርም ለልማትና አስተዳደር በሚያመች መልኩ፤ የብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳችው የማስተዳደር መብት ሳይገፋ፤ ቋንቋቸውን ለመጠቀም፣ ባህላቸውን ለመጠበቅና ለማሳደግ እንቅፋት በማይሆን መልኩ መስተካከል አለበት። ይህ ማለት ግን አንድ ቋንቋ የሚናገር ሁሉ በአንድ ክልል መጠቃለል አለበት ማለት ላይሆን ይችላል። ይህም የሚሆነው በህዝብ ፍላጎትና ፍቃደኝነት ተመስርቶ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉት የአከላለል ጥያቄዎች በኗሪው ህዝበ ውሳኔ እንዲፈቱ በማድረግ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚደረግባቸው መስማማት ያስፈልጋል። እዚህ ስምምነት ላይ ለመድረስ ግን መደረግ ያለባቸው ቅድመ ሁነቶች ይኖራሉ፤ ከላይ ለመግለፅ እንደፈለኩት ኢህአዴግ ስልጣኑን በህዝብ ለተመረጠ አካል ለማስረከብ ቁርጠኛ መሆኑን ማረጋገጥ መቻል አለበት። በምትኩ ለኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጥ ልዩ ልዩ ዋስትና ሊኖር ይችላል።

በነገራችን ላይ “የኢህአዴግ ባለስልጣናት ስልጣን ይልቀቁልን እንጂ በወንጀል ያለመጠየቅ ዋስትና መስጠት ይቻላል” የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እኔ የተለየ አቋም ነው ያለኝ። “አተርፍ ባይ አጉዳይ” እንደሚባለው ወንጀልና ወንጀለኞችን ማበረታታት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በግልፅ የሚታወቅ በተለይ ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር የተገናኘ ወንጀል ያለባቸው ባለስልጣናት ያለመክስስ መብት ሊሰጣቸው አይገባም። በአንፃሩ ምንም ወንጀል የሌለባቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት በሰላም የመኖር መብት ሊከበርላቸው፤ ከዚያም ባሻገር በቀሪ ህይወታቸው ሊያኖራቸው የሚችል ነገር ሊሰጣቸው ይችላል።

ዋስትና ስለመስጠት ጉዳይ መነጋገር ካለብን በእርግጥም ዋስትና የሚያስፈልገው የትግራይ ህዝብ ነው። በተለይ ከክልሉ ውጩ የሚኖረው ትግርኛ ተናጋሪ ዜጋ ከለውጥ በኋላ አሁን ካለው ስርዓት ጋር በተያያዘ ምንም ነገር እንደማይደርስበት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እንደማነኛውም ዜጋ በፈልገው ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት፤ የመኖርና ሀብት የማፍራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ይህ ስጋት ተገቢ ይሁንም አይሁንም ሊታይና ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው። በእርግጥም ይሄ ሀሳባዊ ስጋት አይደለም፤ በአሁኑ ሰዓት በኢህአደግ በኩልም በአንዳንድ ፅንፈኛ ኃይሎችም ተደቅኖበት ያለ ስጋት ነው። ስጋት ካለ ደግሞ አንድም የለውጡ ሂደት የሚያዘገየው ነው የሚሆነው፤ ሌላው ደግሞ የሆነ ህዝብ መስዋዕት በማድረግ የሚመጣ ለውጥ ከሞራልም ከህግም አንፃር ተቀባይነት የለውም፤ ይሄ የህወሀት መንገድ ነው። ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ሲደርስ የነበረው መፈናቀል፤ ጭቆናና ስቃይ ዳግም በየትኛውም ህዝብ ላይ እንዲደርስ መመኘት የለብንም። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት የሚታገል ማነኛውም ኃይል አንድን ህዝብ በሌላ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ተደጋጋሚ ስህተት አይሰራም፤ የጥላቻ፣ የፍረጃና የፍርሀት ፖለቲካም አያራምድም።

በተወሰነ መልኩ በጎንደርና በመተማ አከባቢዎች እንደተየው ዓይነት በስርዓቱ ምክንያት የትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጠር ያልነበረበት ነው። እንዲህ ማድረጉ ለትግሉም የሚጨምረው ነገር የለም፤ በእርግጥ “ከስርዓቱ ጋር ግንኙበት ያላቸው ብቻ ናቸው ጥቃት የደረሰባቸው” የሚል ነገር ተደጋግሞ ሲነግር ሰምቻለሁ፤ በእነዚህ አከባቢዎች ከሚኖረው የትግራይ ተወላጆች ብዛት አንፃር ጉዳት የደረሰባቸው ጥቂት መሆናቸው ሲታይ የተባለው እውነትነት ሊኖረው እንደሚችል መገመት ይቻላል። ነገር ግን አንድ ግልፅ መሆን ያለበት ነገር አለ፤ አንድ ሰው ከስርዓቱ ጋር ያለው ትስስር በማስረጃ ማረጋገጥ የሚችል የተደራጀ አሰራር በሌለበት ህዝባዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንፁሃን ሰዎች አይጎዱም ማለት አይደለም። በራሴ አቅም በተለያየ መንገድ ለማጣራት ሞክሬ የተረዳሁትም ይሄኑኑ ነው። በአጋጣሚው ንፁሃን ዜጎች ላይም ጉዳት ደርሷል። በመሰረቱ ህዝቡ በየአከባቢው እንደመሰለው እርምጃ ይውሰድ ብሎ መቀስቀስ በደርግ ጊዜ እንደነበረው ዓይነት ሁኔታ መፍጠር ነው የሚሆነው፤ በየቀበሌው ለሚገኘው አብዮት ጥበቃ ሳይቀር እንደመሰለው እርምጃ እንዲወስድ በመፈቀዱ ጉዳዩ ሀገር ከመከላከል ወደ ግል ቂም በቀል ወርዶ የብዙ ንፁሃን ህይወት ጠፍቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ ስርዓትና ቁጥጥር የሌለው እርምጃ እንዲኖር መፍቀድ በህዝብ ላይ ጉዳት ማድረስና ስርዓት አልበኝነት እንዲነግስ ማድረግ ነው የሚሆነው። የዘር ፍጅትም የሚከተለው እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ነው።

ስርዓቱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ማውገዝ አለብን፤ መታገልም ያስፈልጋል። በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈፀመው የህይወት መጥፋት እጅግ የሚያንገበግብ ነው፤ የወገን ህይወት ነው የጠፋው፤ የወገን ደም ነው የፈሰሰው፤ ይሄ መታገል ያስፈልጋል። ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው አካላትም ተለይተው በህግ መጠየቅ አለባቸው። ህወሀትን ይደግፋሉ በሚል መነሻ ጥረው ግረው በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ማድረስ ግን ፈፅሞ ተቀባይነት ያለው ጉዳይ አይደለም። ህወሀት ባጠፋ ቁጥር የራስ ወገን በሆነ የትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት ማድረስ መቼም ቢሆን ተገቢነት ሊኖረው አይችልም። እንኳን ዛሬ ዓለም በሰለጠነበት፤ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ በሆነበት ዘመን ቀርቶ በድሮ ጊዜም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ ነገር ተቀባይነት አልነበረም። ለዚህ አንድ የሚገርም በአፄ ምኒልክ ዘመን የሆነ ጉዳይ ብጠቅስ ደስ ይለኛል፤ የእንደርታ ገዥ የነበሩት ደጃች አብርሃ በማመፃቸው ምክንያት በሸዋና በሌሎች አከባቢዎች በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ደርሶ ነበር ይባላል፤ በዚህ ምክንያት አፄ ምኒልክ አዋጅ አውጥተው ነበር፤ እንዲህ የሚል፦

…አንድ ሰው ደጃች አብርሃ ቢከዳ እዚህ የተቀመጡትውን እኔን የሚወደኝን የትግሬ ሰወ ሁሉ ታስቀይማለህ አሉ። አባያ ወንድሙ ይታሰርበታል እንጂ ይታረዳልን። አሁንም ዳግመኛ በአደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም ነገር የተናረ ትቀጣለህ። አደባባይ ያለውን የትግሬ ሰው የሚያስቀይም የተናገረውን ተያይዘህ አምጣልኝ ዳኝነት ይታይልሃል።

                    (የአጤ ምኒልክ የሀገር ውስጥ ደብዳቤዎች፣ ገፅ 589)

የድሮ መሪዎቻችን ቢያንስ ፈሪሃ እግዚአብሄር የነበራቸው በመሆኑ ከአሁኖቹ በእጅጉ ይሻላሉ። የራሳቸው የሆነ ጥሩ ነገርም እንደነበራቸው የምንረዳው እንዲዚህ ዓይነቱ ነገር ስናገኝ ነው። በሌላ በእኩል ደግሞ አሁን ያለንበት ሁኔታ፣ የሞራል ድቀት ከመቼም ጊዜ የከፋ መሆኑ እንረዳለን። ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መጠቀል አለባቸው፤ ግን ደግሞ በስርዓቱ ላይ ያነጣጠሩ እንጂ ፍፁም ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ መሆን የለባቸውም፤ እንደዚህ ዓይነት አሰራር በግልፅ ነው መወገዝ ያለበት። በራስ ወገን ላይ በፖለቲካ ምክንያት ጥቃት ማድረስ ዘላቂ ሰላምና አብሮነትም የሚፈጥር አይሆንም። በአንድ ወገን የሚኖርን ተቃውሞና ውግዘት በመፍራት ዝም መባል የለበትም፤ እንደህ ዓይነቱ አካሄድ አደርባይነትና እወደድ ባይነት ነው (opportunism and populism) ነው።

እስካሁን እንደታዘብኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የሰማቸው ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም እና ፕፎሰፌር ብርሃኑ ነጋ ይመስሉኛል። ፕሮፈሴር መስፍን ለአዲስ አድማስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “ወያኔን ትግሬ እያደረጉ፣ ትግሬን ሁሉ ወያኔ እያደረጉ የሚኬድበት ሁኔታ መታረም አለበት፤ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡” ማለት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በትግራይ ህዝብ እየተደገሰ ያለው አደጋ እንደሚያሳስባቸው ተናገሯል። ፕሮፈሴር ብርሃኑ ነጋም በዴምህት ሁለተኛ ጉባኤ ላይ “ከትግራይ አብራክ የወጡና ይህን ስርዓት የሚቃወሙትን በቆራጥ ወኔ ነው የምናደንቀው” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር የጥላቻ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ ወገኖች እንዲህ ብሏል፦

…ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጉልበትነት እንጠቀምበታለን ብለው የሚያስቡ አክራሪና አጥፊ ኃይሎች ትግሉን ወደ ጥላቻ ትግል ለማስቀየስ የሚሞክሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለን። እንደነዚህ አይነት ጥቂት ኃይሎች በህዝቡ ትግል ውስጥ ተመሽገው የሚወስዷቸው እርምጃዎችንና የሚያካሂዷቸውን የጥላቻ መርዛማ ፕሮፓጋንዳ ህወኃት/ኢህአዴግን ስለተቃወሙ ብቻ ዝም ብለን “የህዝቡ ትግል አካላት ናቸው” ብለን የምናልፋቸው ሊሆኑ በፍጹም አይገባም። እንዲህ አይነት እኩይ ኃይሎችን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን አስቀያሚ ገጽታቸውን በሚያሳዩበት ጊዜ ሁሉ እነሱን ማጋለጥና ከህዝቡ ፍትሀዊ ትግል ማግለል ለእውነትና ለፍትህ፤ ኢትዮጵያችንን ከተጋረጠባት አደጋ ለመታደግ፤ ብሎም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንታገላለን የምንል ኃይሎች ሁሉ ያለማሰለስ ልንሰራው የሚገባን ስራችን ነው።

ይህ የሁሉም ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ አቋም ነው ሊሆን የሚገባው፤ እንደ ዜጋ ከፍ ሲል ደግሞ እንደሰው ለሰብአዊነት፣ ለእውነትና ለትክክለኛነት መቆም ያስፈልጋል። በመሰረቱም አንድን ህዝብ በጠቅላላ ማስፈራራት ውጤት የሚያመጣ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ህዝቡ የስርዓት ለውጥ ቢመጣ ስለሚኖረው የተሻለ ነገር በማስረዳት ነው ማሰለፍ የሚቻለው። ከለውጥ በኋላ ከህወሀት ጋር በተያያዘ ምንም የሚደርስበት ጉዳት ሊኖር እንደማይችል፤ እንደማነኛውም ዜጋ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ በነፃነት ሰርቶ የመኖር መብቱ እንደሚከበርለት ማሳየት ያስፈልጋል። በተለይ ደግሞ በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ቅስቀሳ የሚያካሄዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በማሻማ ሁኔታ ማውገዝና ራስን ከእነዚህ አካላት መለየት ያስፈልጋል። ከእስትራቴጂ አንፃርም የተደባለቀ ትግል ለውጤት የሚበቃ አይደለም፤ ለውጤት ቢበቃም እንኳ ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ አይችልም፤ ሀገር ከመበታተን፤ ህዝብ ለህዝብ ከመተላለቅ የሚያድን አይደለም። አዋጪው መንገድ ኢትዮጵያ የሁላችን እንድትሆን፤ የጋራ ራዕይና ህልም መፍጠር እንጂ የተወሰነ ህዝብ በመነጠል እንዲመጣ የምንፈልገው የተሻለ ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ጠቡ ህዝብ ለህዝብ ስለሚሆን አሸናፊ ወገን አይኖርም፤ ተያይዞ መውደቅ ነው የሚሆነው፤ የፖለቲካ ኃይላት ናቸው ሊሸናነፉ የሚችሉት፤ ህዝብ እንደህዝብ ሊሸነፍ አይችልም።

የመጣህበትን ህዝብ ከቻልክም ደግሞ በማነኛውም ህዝብ ላይ በደልና ጭቆና ሲደርስ መጮህና መታገል ተገቢ ነው። ከዚህ ባለፈ ሁኔታ የራስህን ህዝብ የተጎዳ፣ ከሌላው በተለየ ሁኔታ አደጋ ያንዣበበት በማስመሰል ፖለቲካ መስራትና የኑሮ መሰረት እንዲሆን ማድረግ ከሞራልም ከሰብአዊነትም አንፃር ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው። በተለይ ለለውጥ ከሚታል ሰው የሚጠበቅ አይደለም። አብሮ ለዘላለም የሚኖር፤ ተለያየቶ ላይለያይ ህዝብ መሀል ዘላቂ ጠብና ቂም መፍጠር ተገቢ አይደለም። ስልጣን መፈለግ ኃጢአት ባይሆንም በዚህ መንገድ የሚገኝ ስልጣን ግን ቢቀር ነው የሚሻለው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከቋንቋ በስተቀር በዘርም፣ በኃይማኖትም፣ በባህልም፣ በመልክም አንድ ዓይነት በሆነው የትግራይና የጎንደር ህዝብ ማሀል የጥላቻ ግንብ እንዲገነባ ማድረግ ይቅር የማይባል ስህተት ነው። ለወደፊት በሚኖሩት ትውልዶች ፊትም የሚያሳፍር ኋላቀር ተግባር ነው የሚሆነው። በአጠቃላይ የትግራይና የአማራ ህዝብ ተመሳሳይ ዕጣ ክፍል ያለው፤ ተደጋግፎና ተገባብቶ ከመኖር ውጪ ሌላ አማራጭ ተፈጥሮም ታሪክም ያልሰጠው ህዝብ ነው። በመሰረቱ በሁለቱም ወገን ባሉት የስልጣን ኃይሎች እንጂ በሁለቱም ህዝብ መሀል ጥላቻ አለ ብዬ አላምንም።

የምናደርገው ትግሉ ሁሉም የሚያሳትፍ፤ ለሁሉም ተስፋ የሚሰጥ፤ በማንም ህዝብ ላይ ስጋት የማይፈጥር እንዲሆን መጣር ያስፈልጋል። እንኳን በአንድ ሀገር የሚኖር፤ በደም፣ በአጥንት፣ በታሪክ፣ በዜግነት የተሳሰረ ህዝብ ይቅርና ከአውሮፓ ድረስ መጥተው ለብዙ መቶ ዓመታት ህዝቡን በቀኝ ግዛት ይዘው ሲገዙትና ሲጨቀኑት የነበሩትን የደቡብ አፍሪካ ነጮችም የሚያቃፍ ትግል እነማንዴላ አድርጓል። ታሪክ ሰርተው፤ ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚያገለግል ስርዓት መስርተው አልፏል፤ እኛ ኢትዮጵያውያንም እንዲህ ያለ የተገባ ትግል እንዳናከሄድ የሚያግደን ነገር ምንድነው?!

 

በኮንሶ አፈና፣ እስራቱና ዝርፊያው ተጠናክሮ ቀጥሏል

$
0
0

ዛሬ መስከረም 20/ 2009 ዓ.ም.
konso-people-4-satenaw-news1. በኮንሶ ካራት ሆስፒታል ሁለት ሰራተኞች — የሆስፒታሉ የሰው ኃይል ሃላፊና የፋናንስ ሃለፊ በመከላከያ ኃይል ከቢሮኣቸው ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሆስፒታሉ ለህዝቡ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ መስተጓጎል ፈጥሯል፣ በቀጣይም በአገልግሎቱ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ህዝቡ ሥጋቱን እየገለጸ ነው፡፡

2. ከ600/ስድስት መቶ/ በላይ ታጣቂ ኃይል አባላት ከካራት ወደተለያዩ የኮንሶ ገጠር ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ በህዝቡ ላይ ችግር እየፈጠሩ ውጥረት ነግሷል፡፡ ሠራዊቱ የተንቀሳቀሱት ወደ- ናላያ ሰገን፣ ጃርሶ፣ ቡቶ፣ ዴራ፣ ዴበና፣ እና ቶካች ቀበሌዎች ነው፡፡

በሁሉም ቀበሌዎች ታጣቂዎች ቤት ለቤት እየገቡ አሰሳ ያካሄዱ ሲሆን በሁለት ቀበሌዎች በግለሰቦች ላይ እስራትና ዝርፊያ ተፈጽሟል፡፡ ታጣቂዎች በዴበና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትን ጡረተኛ መምህር ጋሬ ቦያ ቤት በመበርበር ያገኙትን 31 ሺህ/ 31 000 ብር/ በጥሬ ገንዘብ፣ 2 /ሁለት/ ጄሪካን የተነጎረ- በከፊል የተነጠረ ሁለት/2/ ቅቤና አራት/4/ ጄሪካን የተጣራ ማር ዘርፈዋል፡፡ ከላይኛው ቶካች መንደር አቶ ሮቢቾ ረጋሳ ታፍነው ተወስደዋል፤ የት እንደተወሰዱ አልታወቀም፡፡

3. ከቀኑ 10 ሰዓት – ት/ቤታቸው ውጤት እንዲቀበሉ ተጠርተው የሄዱ የአስረኛና አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በታጣቂ ሃይል ተከበው በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ታግተዋል፡፡ እስካሁን 11፡45 ሰዓት ድረስ አልተለቀቁም፡፡ ከነዚህ ውስጥ አምስት ተማሪዎች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን የአስራ-ሁለተኛ ክፍል ፈተናን 612 ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ያለፈው ተማሪ ተስፋዬ በደረሰበት አሰቃቂና ዘግናኝ ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበትና በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ይህን መረጃ ያቀበለኝ ወዳጄ የተማሪ ተስፋዬ ድብደባ በወረታ ሁሉንም ትምህርት ‹ኤ› አምጥቶ- ውጤቱ ሲመጣ በህይወት ያልተገኘው (የተገደለውን) የ10ኛ ክፍል ተማሪ በለጠ ንብረቱን ያስታውሰናል ፣ በማለት በከፍተኛ ቁጭት ገልጾኣል፡፡ በማያያዝም ስለኮንሶ ህዝባዊ ትግል ‹‹ሁላችን ኢትዮጵያዊን በተባበረና በተቀናጀ ትግል በአንድነት ቆመን ይህን አምባገነን ሥርዓት እስካላስወገድን በተናጠል ያጠቁናል፣ የምንቀዳጀው የተናጠል ነጻነት ግን የለም፡፡ ስለዚህ በተናጠል ነጻ ላንወጣ በተናጠል ማለቅ የለብንምና ትግሉን ማስተባበርና ማቀናጀት አለብን›› በማለት የመተባበር ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በተባበረና በተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ኢትዮጵያዊ ክብርና ነጻነታችን እናስመልሳለን፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት 8 የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

$
0
0

ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2009)
tplf-and-tigray
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሰርቀሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በነዋሪዎችና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 8 የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉት በስፍራው ወርቅ ለማውጣት በሚል በቅርቡ ከ1ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች መስፈራቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ አለመግባባት መሆኑ ተነግሯል። በዚሁ ግጭት ከተገደሉት የጸጥታ ሃይሎች በተጨማሪ ከ20-30 የሚደርሱ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል።

የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ዮሴፍ ሃሚድ ናስር በቅርቡ በአካባቢው ያለን የወርቅ ሃብት ለማልማት በሚል ከትግራይ ክልል የመጡ ወታደራዊ አመራሮችና ሌሎች አካላት በጊዛን ሸርቆሌ መስፈራቸውን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።

በአካባቢው ተካሄዷል ያሉትን ህገወጥ ወራራ ተከትሎ በነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱንና ሰፋሪዎችም ቦታውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ረቡዕ ግጭት መቀስቀሱን ገልጸዋል።
በነዋሪዎችና የወርቅ ሃብት ያለበትን ይዘው በሚገኙ አካላት ዘንድ በተፈጠረው ግጭት በትንሹ ስምንት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውንና አካባቢው በውጥረት ውስጥ መሆኑን የንቅናቄው ሃላፊ አስታውቀዋል።

በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው። [ታደሰ ብሩ]

$
0
0

teachers-training-satenaw-newsበብዙዎች የመምህራን “ስልጠናዎች” ላይ ዝምታ ከቃላት በላይ ተቃውሞን ለማስተላለፍ ጠቅሟል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ግን አላስችል ያላቸው መምህራን ካድሬዎቹን አሳፍረዋል። ”ለምን እንዲህ አደረጋችሁ”፤ “ምን አቅብጧችሁ ተናገራችሁ?” ማለት አይቻልም፤ የካድሬዎቹ ድፍረት ትዕግስት ያስጨርሳል። ክፋቱ በእነዚህ አዳራሾች ውስጥ የነበሩ ጆሮጠቢዎች ሪፓርት የሚያደርጉትን አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ መምህራን ከቤታቸውና ከመንገድ እየተወሰዱ እየታሰሩ ነው።

ተናገሩ ተብለው ተወትውተው ስለተናገሩ ታሰሩ !!! ያሳዝናል !!! ለዚህ ኢፍትሀዊነት ውሳኔ የምሰጠው ምላሽ ምንድነው?

ዘንድሮ ት/ቤቶች እንደተከፈቱ ወዲያውኑ የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች መጀመር አለባቸው። በሥራ መለገም፤ የታዘዙትን ሳይሆን ያልታዘዙትን መፈፀም … ወዘተ ከቀን አንድ ጀምሮ ተግባራዊ ልናደርጋቸው ይገባሉ ብዬ አምናለሁ።

“የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች” እና “የሕዝባዊ አሻጥር ተግባራት ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን” የሚሉ ሁለት አጫጭር መጣጥፎችን በፌስቡኬ ለጥፌዓለሁ። እነዚህ ለመነሻ ያህል የቀረቡ ናቸው። ዜጎች እኔ ከዘረዘርኳቸው የተሻሉ ተግባራት ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህም ሆኑ ሌሎች ትምህርት እንደተጀመረ በሥራ ላይ ቢውሉ መልካም ነው እላለሁ።

ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ መምህራን የሚሆኑ ሌሎች ዝርዝሮችን ማዘጋጅት የሚያስፈልግ ከሆነም እናስብበት።

2009 የትምህት ዘመን የሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ የሕዝባዊ አሻጥር እና የአዝባዊ አመጽ – ማለትም የሁለገብ ትግል – ዘመን ይሆናል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

Tadesse Biru Kersmo


ሰበር_መረጃ !… የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩ ስዩም ተሾመ በወያኔ ደህንነት ታፍኖ ተወሰደ

$
0
0

danielየአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህሩ ስዩም ተሾመ በወያኔ ደህንነት ታፍኖ ተወሰደ! በቅርቡ የመምህራንን ስብሰባ ተከትሎ ስዩም ተሾመ ሰፊ ትንታኔ አቅርቦ ነበር! ለረጅም ጊዜ በዚሁ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ትንታኔ በመፃፍ እንዲሁም በሆርን አፌርስ ድህረ ገፅና በሌሎችም የማህበራዊ ሚድያ ገፆች ላይም ፅሁፎቹ በተከታታይ ይወጡ ነበር።

Daniel Feyssa Atew Qorcha

ሽግሽግ እናደርጋለን እድሜ ለማራዘምና ለማጭበርበር?? [ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ]

$
0
0

21 / 1 / 2009 መቀለ

woyane-satenaw-news-5የህዝብ ፍላጎትና የህወሐት የሽግሽግ እስትራተጂ ህዝብን አታልሎ ለመግዛትና የስልጣናቸው እድሜ ለማራዘም ነው እንጅ ከ15 አመት በፊት ከነበረው የመተካካት ፡የመሸጋሸግ የተሀድሶ እናደርጋለን ብለው የሀገራችን ሚዲያዎች በሞኖፖል ይዘው በመሬት የለለ ለወጥ አመጣን እያሉ ለ90 ሚልዮን ህዝባችን የማይታይ ፡የማይዳሰስ ፡ የማይጨበጥ ፡የህልም እንጀራ አብልተውናል ።

በዛን ጊዜ መሸጋሸግ ያሉን የተባላሹ ፡በሙሱና የበሰበሱ ጋንግሪናቸው ቆርጠው ማስወገድ ሳይሆን የበሰበሱ ተብሎው ወደ የህዝብ አይን ብሌን የገቡ ከማእከላይ ኮሚቴ ወደ አምምባሳደርነት ፡ ወደ ያረጁና ያፈጁ መሰብሰበያ የሆነው በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በአማካሪነት ሰብስቦ ማስቀመጥ ደበቁዋቸው ፡ አጃቢ፡ ዘበኛ፡ የነበሩ ተላላኪዎች በስቢል ሰርቢስ ሞቅሞቅ ሰሚናር የውሼት 1ኛ ዲግሪ ፡ 2ኛ ዲግሪ (ማስትሬት ) በማስያዝ ማእከላይ ኮሚቴ ፡ስራ አስፈጻሚ በማድረግ አሮጌዎች ፡ሽሪኮቻቸው ፡ዘር ዘራቸው ለፈጸሙት ሙሱናና ኪራይ ሰብሳቢነት ፡ ስልጣናቸው ተጠቅመው ለሚፈጹሙት ምዝበራ ።በህዝብ ሲጠየቁ ዘበኛ ሆነው ሊጠብቋቸው ታሳቢ በማድረግ ነበር የተመለመሉና 15 አመት ሙሉ አየሰሩት የመጡ ነው ።

መላው ህዝባችን በሚገባ መገንዘብ ያለበት እነዚህ ፍጡራን ለዝህቺ አገር በሳይንሳዊ መንገድ ልትመራ የሚፈልጉ ቢሆኑ ንሮ በጠቅላይ ምኒስቴር ቢሮ አማካሪ መሆን የነበራቸው ፡ የኢኮኖሚ፡ብቁ የፓለቲካ ሳይንስ ፡ የጤናና የተፈጥሮ ሀብት ፡ የህግ ፡ የታሪክ ፡የትምህርቲ ወዘተ ተማራማሪዎች መመደብ ነበረባቸው ። እስከአሁን ግን 90 ሚሊዮን የኢትዮጱያ ህዝብ እንደ መንጋ እንስሳ እኩል በመቁጠር አሁንም ማጭበርበሩ ተያይዘውታል ።

ሌላ የፈጸሙት የመሸጋሸግ ስልት ፡በክልል አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ደረጃ የተባላሹ ፡በህዝብ የተጠሉ ፡አቅማቸው የጨለጡ ፡ ወደ ፓርላማ ተመራጭ አድርገው ምርጫው 100% ወንበር ተቆጣጥረው እንዲያመቁና እንቅልፋቸው እንዲጨርሱ ተደርገዋል እየተደረጉም ናቸው ።ጥቂቶቹ ደግሞ አንባሳደር ተሽመው የሀገራችን ዶላር በቪአይቪ ለመስተላለፍ ተጠቅመውባቸዋል ።
ዝቅያሉ ባለስልጣናት በዞን በወረዳ ሆነው ዋናዎቹ የምዝበራ አቀባዮች ደግሞ ወረዳ ወደ ዞን እርከን ፡ዞን ወደ ክልል ቢሮና ኤፈርት ኩባኒያዎች ተመድበዋል ። በአጠቃላይ ባለፈው 15አመት በተደረገው ተሀድሶ ቡዙ ተነግሮለት ግን ለኢህአደግ ህወሀት በሀሳብ የሚቃወም ካልሆነ በስተቀር በእከከኝ ልከክህ የትግል ስልት ነው የተጓዙትና ሀገራችን የመዘበሩት።

ታድሰናል የኪራይ ሰብሳቢነት ፡ሙሱና ጠነቅ ፡የምልካም አስተዳደር ፍትህ ዲሞክራሲ እንቅፋት ናቸው ብለው ለይምሰል ያሰሩዋቸው ፡የቀጡዋቸው ተራ የቀበሌ የጎጥ አስተዳዳሪዎች ያለክፍያ ሲያሰርዋቸው የነበሩ ናቸው ። በዛ ተሀድሶ የዋና ገዥዎች ታማኞችና አቀባዮች በለፉት 15 አመታት የነበሩ በአሁኑ ጊዜ የሀገራችን ሀብት ተቆጣጥረው ዘመናዊ ዘንዶ ሆነዋል ። እንዳውም እነዚህ ዞንዶዎች በአሁኑ ጊዜ ፍጹም የማይገፉ በቤተሰብ በገጥ ተሳስረው የታጠቁ ሀይል ሆነዋል ።

ከዘንድሮ የ2009ዓ ም ተሀድሶና ሽግሽግስ ምንእንጠብቃለን ???????,,
የተከበራችሁ ወገኖቼ በእኔ እምነትና በሁሉም የኢትየጱያ ህዝቦች በተለይ ቀለም የቆጠሩ ፡የገጠርና የከተማ ነዋሪ ምራቃቸው ዋጥ ያደረጉ ሽማግሌ ወይ የሚገነዘቡ ፡ ሙሁራንና ተመራማሪዎች በዚሁ የዘንድሮ የማጭበርበር የታድሶ ሽግሽግ እቅዳቸው እምነት የላቸውም ። ይህም ከወዲሁ ባደረጉት ስብሰባ በዩንቨርሲቲዎች በአስተማሪዎች በመንግስት ሰራተኞች ተቀባይነት አጥተዋል ።

እነዚህ መሪዎች ራሳቸው ባመኑበት ያለፈው የ15 አመት ተሀድሶ አልሰራም በባሰው በስብሰናል ብለዋል ። በተለይ ደግሞ ሀይለማርያም ደሳለኝ ብቻቸው ሆኑ እንጅ ሀቁን በማውጣት የሀገራቸን የስርአታች ጠንቅ ሆነው ያሉ ኢህአደግና አጋሮቹ ፡እሱ የሚመራው መንግስት አመራር ስልጣናቸው ተጠቅመው የሀገራችን ሀብት ከመመዝበራቸው አልፈው ኪራይ ሰብሳቢነት ጸረ ዲሞክራሲ ጠባብነት እና ትምክህት ተስፋፍቶ አደጋላይ ወድቀናል ። የጠባብነትና የትምክህት የዘረኝነት በግንባር ቀደምትነት ተጠያቂዎች የህወሐትና የበአዴን መሪዎች ናቸው ቡለዋል ። ባዶ ንግግር ጥርስ የለለው አንበሳ ሆኖ ቀረ ።

ባለፈው ሳምንታት አራቱ ዓንኳር ፓርቲዎች ስራ አሰፈጻሚና ማእከላይ ኮሚቴ በስብሰባና በገምጋም ተጠምደው ሰንብተው ውጤቱ ደግሞ ፡ ሽግሽግ እናደርጋለን ብው ህወሐት፡ በአዴን ፡ዴሄደን ፡ኦሆዴድ ወስነው ወጥተዋል የስብሰባቸው ውጤት በሁሉም ሚዲያዎች ታውጀዋል ።በተለይ የህወሀት የገምጋም ውጤት እጅጉን አጭበርባሪና ተቀባይነት አለገኜም ። ምክንያቱም አዋጁ ካለፉት የ15አመት የተሀድሶ ዘመን የቃላት ለውጢም የለውም ።

የህወሐት አህአደግ ስርአት ሊታደስ ከሆነ ፣ አቅማቸው ሟጥጦው አጨረሱ ፡አገልግለታቸው ጨርሰው ሀሳብ የማመንጨት ይሁን የአማራር ድጋፍ አቅማቸው ፍጹም የጨረሱ በአመካሪነትበታሀድሶ ስብሰባቸው ከሚያሳትፉ አቅም ያላቸው ሁሉም አቀፍ ተመራማሪዎች ዜጎች ለምን አያሳትፉም ።
ለምን ከሁሉ ገለልተኛ የሆኑ ዜጎችና ይመለከተናል ወይ ያገባናል ለሚሉ ተሳታፊነት ለምን አይፈቅድም ? እነዚህ ፍጡራን ወደ ጎናቸው ሙሁራን ለማስጠጋት አይፈቅዱም ምክንያቱም ከጥንት ይዘውት የመጡ ባህሪ ነው ።

ይቀጥላል
ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ
21 /1 2009 ዓ ም

ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ የሳበው ካርድ አልቆበታል [ናትናኤል አስመላሽ]

$
0
0

የህውሓት የመጨረሻ ካርድ !!!

TPLF (1)የቀሩት ሁለት ካርዶች ብቻ ናቸው። አንደኛው በትግሉ ጊዜ ሲጠቀምበት የነበረው አማራ እና ኦሮሞ ነው ጠላትህ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ዓረና የአማራ የኦሮሞ ተላላኪ ነው ከአማራ እና ከኦሮሞ ጋር ሆኖ ሊያጠፋቹ ነው የሚል ነው። ህውሓት አሁን መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ አመኔታ ተነግፈዋል(አጥታለች)፣ ይህ ብቻም አይደለም የህውሓት አባላት በህውሓት ላይ ተስፋ ቆርጠው አማራጭ ፓርቲ ፍለጋ ላይ ናቸው።
.
ህውሓት በየገጠሩ እና ከተማው አማራ እና ኦሮሞ ተባብረው ሊያጠፍዋቹ ነው ተነሱ ዓረናም ተባባሪ ነው በማለት ቀን ከለሊት እየቀሰቀሰች ነው። የዚህ ሁሉ ምንጭ የህውሓት የስልጣን ጥም እና የህውሓት መጨረሻችን ምን ይሆን ከሚል ፍራቻ ነው። ህውሓት ከትግራይ ውጭ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ ለውስጥ በማስፈራራት እና ተጠንቀቁ በማለት የስልጣን ማራዘምያ ዘዴም ከፍታለች። ለምሳሌ በሃረህ ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በተለይ የትግራይ መታወቅያ ያለባቸው በማስፈራራት ላይ ትገኛለች።
.
የህውሓት መጨረሻ ልክ የሳዳም እና የጋዳፊ መጨረሻ እንደሚሆን አጠያያቂ አይደለም !ይህንን የምታውቅ የትግራይ ወጣት ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተባባር በአንድነት እንደሚኖር አውቀህ በየከተማው እና በየገጠሩ ላለው የትግራይ ህዝብ በማስረዳት አዲስትዋን ኢትዮጲያ ለመገምባት ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ። የትግራይ ህዝብ እንደ ማንኛው የኢትዮጲያ ህዝብ ከህውሓት በፊት የተፈጠረ ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ከህውሓት አልተጠቀመም አዎ የህውሃት ባለስልጣናት እና ቤተሰቦቻቸው ግን ከትግሉ ተጠቅመዋል፣ ስለሆነም ከህውሓት ቦሃላ የትግራይ ህዝብ እንደማንኛው ጭቁን ህዝብ ከህውሃት የጭቆና ቀንበር ወጥቶ አብሮ እንደሚኖር ምንም ጥርጥር የለውም ፣ ስለሆነም የትግራይ ወጣት ሆይ የትግራይ ህዝብ ከህውሓት ቦሃላ ከሁሉም ህዝቦች ጋር አብሮ እንደሚኖር በማወቅ በማስረዳት እና መከታ በመሆን ታሪካዊ ግዳጅህን ተወጣ።
.
ዓረና ትግራይ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ተላላኪዎች ሳይሆን የትግራይ ህዝብ አማራጭ ፓርቲ መሆኑን ታውቃለህ፣ የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ጠላት ህውሓት ነው። አዎ ትናንትም ዛሬም ነገም የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!! የትግራይ ህዝብ ሆይ በከፈልከው ደም እና አጥንት ለዓረና የመታገል እና የማታገል መብት የምትሰጠው አንተ የትግራይ ህዝብ እንጂ ህውሓት አይደለም ! ህውሓት ሃያ አምስት አመት ሙሉ በስምህ ነግደዋል፣ዘርፈዋል፣ገድለዋል አሁን የትግራይ ህዝብ ልክ እንደ ሌላው ህዝብ ለውጥ ትፈልጋለህ፣ የለውጡ መሪ ደግሞ አንተ ነህ።
.
ህዝቦች በታሪክ ተጣልተው አያቁም አምባገነኖች ግን አዎ ህውሓቶች ግን አዎ።የትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ከሌሎች ህዝቦች እንጂ ከህውሓት ጋር አለመሆኑን የተገነዘብከው የህውሓት ካድሬም በርታ፣ ጊዜው አሁን ነው ዓረና ማለት ሰላም ፍቅር አንድነት መከባበር ማለት ነው። የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ከሚያፋቅር ዓረና ጎን ተሰልፈህ የትግራይን ህዝብ መከራ ስደት ወዘተን ለማስቆም ታገል።የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ከትግራይ ህዝብ የወጡ የህውሓት አምባገነኖች እንጂ ከትግራይ ህዝቦች ጋር ለአመታት የኖሩ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች አይደሉም።አዎ “ትናንትም ዛሬም ነገም ” የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ጠላት ህውሓት ነው!!!

በአዲስ አበባ “አቧሬ” አካባቢ ሁለት ሺህ ሕጋዊ ቤቶች ይፈርሳሉ [ዋዜማ ራዲዮ]

$
0
0

abware-area-satenaw-newsዋዜማ ራዲዮ- በየካ ክፍለ ከተማ ሚስስ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚገኙ ሁለት ሺሕ የሚጠጉ ቤቶች በቅርብ ወራት ዉስጥ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባቸዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሰፋፊ የግለሰብ ይዞታዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የቀበሌ ቤቶች ናቸው፡፡ እንዲፈርሱ የዉሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው የአቧሬ ሰፈሮች ሕገወጥ በመሆናቸው ሳይሆን ቦታው ለመልሶ ማልማት ፕሮጀክቶች በእጅጉ በመፈለጉ ነው፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት በጽሑፍ የተላለፈላቸው መመሪያ እንደሚያስረዳው አቧሬና አካባቢውን በአስቸኳይ ለማልማት አቅጣጫ በመያዙ በወረዳ 6 (በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 09) ዙርያ የሚገኙ የግል ይዞታዎችና የቀበሌ ቤቶች ቁጥርና ስፋት በዝርዝር አጥንተው በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲያቀርቡ በማዕከል ኃላፊዎች ታዘዋል፡፡

በአንጻሩ የቤቶቹን መፍረስ ዉሳኔ በጥርጣሬ የሚመለከቱ በክፍለከተማ በተለያየ ኃላፊነት ደረጃ እየሰሩ የሚገኙ የዋዜማ ምንጮች በቅርብ ወራት ዉስጥ ምንም አይነት የቤት ማፍረስ ሥራ እንደማይከናወን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ቤቶችን ለልማት ሲባል የማፍረስ ተግባር ለተቃውሞ እንቅስቃሴ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት በካቢኔው ዘንድ በመኖሩ ነው፡፡

አገሪቱ ወደለየለት ብጥብጥ እንድታመራ የሚሹ አክራሪ ኃይሎች በዋና ከተማዋ አመጽ ለመቀስቀስ አጀንዳ አጥተዋል፤ እኛ ቤቶችን ለልማት ስናፈርስ እነርሱ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት ይችላሉ የሚል ስጋት በከንቲባው ዋና የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ተወልደ ገብረጻዲቅ ሲንጸባረቅ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ ይላል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የይዞታ ጽሕፈት ቤት ዉስጥ በኦፊሰርነት የሚያገለግል ወጣት የድርጅት አባል፡፡

ቤት የማፍረስ ተግባር ዘንድሮ የማይታሰብ ነው የሚሉት ወገኖች እንደ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያቀርቡት በ2008 መጨረሻ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀርሳ፣ ኮንቶማና ማንጎ ሰፈሮች ዉስጥ ሕገወጥ ሰፋሪዎችን ለማንሳት በተደረገው ሙከራ የወረዳ አንድ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ የነዋሪዎች ሕይወት መጥፋቱን ተከትሎ ዉጥረት መንገሱን በማስታወስ ነው፡፡ በወቅቱ በነዋሪውና በፀጥታ ኃይሎች መሐል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ከንቲባው አቶ ድሪባ ኩማ ሕገወጦችን የማፍረስ ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም የሚል መግለጫ ቢሰጡም በዚያው ሰሞን እንዲፈርሱ ቀነ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበሩ ሰፈሮች ለጊዜው እንዲታለፉ ለክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ማደስ ኃላፊዎች የቃል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

እንደ ምሳሌም የቀርሳና ኮንቱማ ሰፈሮችን የሚያዋስነውና በርካታ ሕገወጥ ሰፋሪዎች ይገኙበታል የሚባለውን የአቃቂ ቃሊቲ መንደር ለማፍረስ ግብረኃይል ተደራጅቶ፣ ቀን ተቆርጦ፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል ተመድቦ፣ ዶዘሮች ወደ አካባቢው እንዲቀርቡ ከተደረገ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት የማፍረስ ሂደቱ ድንገት እንዲታጠፍ ሆኗል ይላሉ የወረዳው ባልደረቦች፡፡

የዋዜማ ዘጋቢ ያናገራቸውና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰራተኛ ዉሳኔው የታጠፈው ዜጎችን በክረምት ማፈናቀል አግባብ እንዳልሆነ በካቢኔው አቅጣጫ በመያዙ ነው ሲሉ ሌሎች በመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤት የሚሰሩ ኦፊሰሮች ደግሞ በተቃራኒው እንዲያውም ሕገወጥ ቤቶች እንዲፈርሱ የሚመረጠው በክረምት ወቅት ነው፡፡ ይህም በበጋ ቤቶችን ማፍረስ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ሊያርቃቸው ስለሚችል ነው ሲሉ ተጻራሪ ሐሳቦችን ያቀርባሉ፡፡

በኦሮሚያ መንግሥትን ለሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ የዳረገው የተቀናጀ ማስተር ፕላን ለጊዜው እንዲታጠፈ ከተደረገ በኋላ አዲስ አበባ የተናጥል የከተማ መሪ ፕላን ለማዘጋጀት ተገዳለች፡፡ ኾኖም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እስከዛሬም በይፋ አላጸደቀችውም፡፡ የሕዝብ ዉይይት ተደርጎ በአስቸኳይ ይፀድቃል የተባለው መሪ ፕላን ከዛሬ ነገ እየተባለ ለወራት ሲንከባለል ቆይቷል፡፡ ያም ኾኖም አስሩም ክፍለ ከተሞች በአሁኑ ሰዓት የመሬት ጉዳዮችን እየፈጸሙ ያሉት ያልጸደቀውን የከተማዋን መሪ ፕላን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ባይፀድቅም እየሰራንበት ነው፤ በሱ መስራት ከጀመርን ዓመት አልፎናል ይላል ለዋዜማ ሐሳቡን የገለጸ አንድ የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ባለሞያ፡፡

በአዲሱ መሪ ፕላን የከተማዋ 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት የሚፈለግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለአረንጓዴ ቦታ የተከለሉ ሥፋራዎች ዉስጥ እየኖሩ ያሉ ዜጎች በሂደት እንዲነሱ እንደሚደረግ የከተማዋ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ ኾኖም ቁጥራቸው በርካታ ከመሆኑ ጋር ምትክ ቦታ ለመስጠት አስተዳደሩ ፈተና እንደሚገጥመው ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት የከተማዋን አብዛኛዎቹን የቆረቆዙ መንደሮች በመልሶ ማልማት ለማልማት በተደረጉ እንቅስቃሴዎች በሰንጋ ተራና አካባቢው 14 ሄክታር መሬት ለፋይናንስ ተቋማትና ለ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት የተላለፈ ሲሆን በልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ 16 ሄክታር መሬት ደግሞ ለ20/80 ቤቶች ልማት ማከናወኛ የተሰጠ ነው፡፡ በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ የልደታና አካባቢው መልሶ ማልማት ፕሮጀክት በመስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል ደረጃ በስኬታማነቱ በተደጋጋሚ የሚወደስ ፕሮጀክት ነው፡፡ የግልና የመንግሥት ባንኮች ሕንጻዎችን፣ ፀሜክስ ኢንተርናሽናል እያስገነባው እንዳለው አይነት ባለ ኮከብ ሆቴል ፕሮጀክቶችን፣ ፍሊንስቶን ያስገነባውን ዘመናዊ የገበያ ማዕከል (ሞል) ተግባራዊ ማድረግ የተቻለው በዚህ እንደ ሞዴል በሚወሰድ የመልሶ ማልመት ሥራ እንደሆነ በኃላፊዎች በተደጋጋሚ ይገለጻል፡፡

ይህ የልደታ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት የኮንዶሚንየም ነዋሪዎች ከመሀል ከተማ ርቀው እንዳይሰፍሩ፣ በመካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች መሐል መራራቅ እንዳይኖር ያደረገ ልማት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ በተደጋጋሚ ሲያሞካሹት ይሰማል፡፡ ኾኖም ተመሳሳይ የመልሶ ማልማት ስኬት ሊደገም አልቻለም፡፡ ብዙዎቹ በመልሶ ማልማት ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ዜጎች ከነባር ይዞታቸው ተፈናቅለው በከተማዋ ጫፍ በሚገኙና መሠረተ ልማት ባልዳሰሳቸው ሥፍራዎች እንዲሰፍሩ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በቅርቡ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠበት አቧሬ ሰፈር ከአንድ ሺ ካሬም የሚልቁ ሰፋፊ ይዞታዎች የሚገኙበት ሲሆን የመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ዋና መቀመጫም የሚገኘው በዚህ ወረዳ ነው፡፡ በመልሶ ማልማት ምክንያት የሚነሱ ዜጎች ይዞታቸው ምንም ያህል ሰፋፊ ቢሆን እንኳ በመኖርያ ቤት እስከተመዘገበ ድረስ በምትክነት የሚሰጣቸው የካሬ ስፋት ከ500 ሜትር ስኩዌር ካሬ በላይ እንዳይሆን መመሪያው ያዛል፡፡ ኾኖም ተነሺዎቹ ይዞታቸውን በግላቸው የማልማት ፍላጎት ካላቸውና የፋይናንስ አቅም በራሳቸው መፍጠር ከቻሉ መሪ ፕላኑ በሚያዘው መሠረት በአካባቢው ዘጠኝ ፎቅና ከዚያ በላይ የመገንባት መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ግን ለብዙ የከተማዋ ጎስቋላ ነዋሪዎች የሚታሰብ ጉዳይ አይሆንም፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት ዉስጥ በልማት ስም ከፈረሱ የአዲስ አበባ ከተሞች መሐል አሜሪካን ግቢ ተጠቃሽ ነው፡፡ በአካባቢው ለ30 አመታት ነዋሪ የነበሩ ዜጎች የይዞታ ባለቤትነትን ከማረጋገጥና ከካሳ ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ዉዝግብ ዛሬም ሙሉ በሙሉ ምላሽ አላገኘም፡፡ ኾኖም ከአካባቢው የተነሱ ሱቆች ራሳቸውን በቡድን እያደራጁ ቁራሽ መሬቶች እየተሰጣቸው ቆይቷል፡፡

ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ አዲስ ከተማ፣ ጎጃም በረንዳ፣ ቁጭራ ሰፈር፣ ጣሊያን ሰፈርና ገዳም ሰፈር በመልሶ ማልማት የሚፈርሱና እየፈረሱ ያሉ አካባቢዎች ናቸው፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የመስቀል አደባባይ ኢሲኤ ጀርባ 4 ሄክታር መሬት፣ አራዳ ክፍለ ከተማ ዉስጥ የሚካተተው የ አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ 24 ሄክታር መሬት በመልሶ ማልማት ተነስቷል፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ በሊዝና በምሪት ለባለሀብቶችና ለድርጅቶች የተላለፈ ሲሆን ቦታ ከወሰዱ ድርጅቶች መሐል የብአዴን ጽሕፈት ቤት ግንባታ፣ ሁለት የግል ሆስፒታሎች ግንባታ፣ የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ፣ የሂልኮ ኮምፒውተር ኮሌጅ ግንባታ በአመዛኙ ተጠናቋል፡፡

የባሻ ወልዴ ችሎት አካባቢ እየተከናወኑ ካሉ ፕሮጀክቶች ትልቁ በአምባሳደር ልብስ ስፌት ባለቤት በአቶ ሰኢድ መሐመድ ብርሃን እየለማ ያለው ቦታ ሲሆን ከአርበኞች ግንብ ሕንጻ ጎን ከፓርላመው ባሻገር የሚገኝ 3ሺ ካሬ ቦታ ነው፡፡ አገልግሎቱም ባለ 4 ፎቅ ሰፊ የገበያ ማዕከል ግንባታ ነው፡፡ ይህ ግንባታ ረዥም ዓመታትን የወሰደ ቢሆንም እስካሁንም አልተገባደደም፡፡ የባሻ ወልዴ ችሎት መልሶ ማልማት ቦታዎች በተፈለገው ፍጥነት አለመሄዳቸው ብቻም ሳይሆን ብዙዎቹ ቦታዎች ከፈረሱ አመታት ቢያስቆጥሩም አሁንም አለመልማታቸው የነዋሪዎች መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ በመሪ ፕላኑ መሰረት አካባቢው ለቤተመንግሥትና ፓርላማ ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከ4 ፎቅ በላይ መገንባትን አይፈቅድም፡፡

ተመሳሳይ ሰፊ የመልሶ ማልማት ሥራ ካከናወኑ ክፍለ ከተሞች መሐል የቂርቂስ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ሲሆን ለአፍሪካ ሕብረት አዲሱ ሕንጻ ግንባታና ለኢሲኤ (የቀድሞው አፍሪካ አንድነት ድርጅት የመጀመርያ መሰብሰቢያ አዳራሽ) ማስፋፊያና ፓርክ ሲባል ኢስጢፋኖስ ጀርባ የነበሩ በርካታ ነዋሪዎችን ከቀያቸው ለማፈናቀል ተገዷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ካዛንቺስና አካባቢዋ በርካታ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ መከናወን የቻለውም ቦታው ለመልሶ ማልማት በመዋሉ ነው፡፡

አሁን ተመሳሳይ ሰፋፊ የሆቴል ፕሮጀክቶች ይካሄዱበታል ተብሎ የሚገመተውና የካዛንቺስ 2 መልሶ ማልማት ዘመቻ በሚል የሚታወቀውን የልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ራዲሰን ብሎ ማዶ፣ ኢንተርኮንቲነንሰታል ሆቴል ፊትለፊት፣ ኦራኤል ቤተክርስቲያን ተሻግሮ የሚገኙ ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ቦታዎቹ ከጸዱ ዘለግ ያለ ጊዜ ቢያስቆጥሩም የፈረሱት ቦታዎች እስከአሁንም ለአልሚዎች አልተላለፉም፡፡

በከተማዋ ነዋሪዎች እንደ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚነሳውም ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ድሀን በልማት ስም አፈናቅሎ መተው፣ ወቅቱን ያገናዘበ ተገቢ ካሳን አለመስጠት፣ የማኅበራዊ ምስቅልቅል የሚፈጥሩ አሰፋፈሮችን መከተል የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለረዥም አመታት ያማረረ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የፈረሱ ቦታዎች ለአመታት ያለምንም አገልግሎት ተጥረው እንዲቀመጡ መሆናቸው ግርትን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አንድም በመስተዳደሩ ድክመት ቦታዎቹን ለአልሚዎች በጊዜ ያለማስተላለፍ ችግር ጋር የሚያያዝ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አልሚዎች ቦታዎቹን አጥረው ይዞታቸውን ካስከበሩ በኋላ ለዓመታት ግንባታ ለማከናወን ሳይፈቅዱ መቆየታቸው ነው፡፡

ይዞታዎች ለአልሚዎች ሲተላለፉ የግንባታ መጀመርያ ጊዜና ማጠናቀቂያ ጊዜ በዉል ተለይተው፣ የሊዝ ዉል ፈርመው የሚገቡበት አሰራር ቢኖርም ይህ ሁኔታ ለሁሉም ዜጎች በእኩል የሚሰራ አልሆነም፡፡

በዚህ ረገድ በከተማዋ የአስተዳደር እርከን በሁሉም ደረጃ ከኤህአዴግ አባላት ሳይቀር ሰፊ ትችትና ትዝብትን የሚያስተናግዱት በሳኡዲያዊው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲ የተያዙ ሰፋፊ የከተማዋ ይዞታዎች ናቸው፡፡ በተለይም ከካዛንቺስ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ጎን ተቆፍሮ የሚገኘው ቦታ መለስተኛ ኩሬ ፈጥሮ ለአካባቢው የጤና ጠንቅ እስከመሆን የደረሰ ሲሆን በኢንተርኮንቴኔንታል ሆቴል የሚያርፉ እንግዶች መስኮቶቻቸውን ለመክፈት እስከመቸገር መድረሳቸው ይነገራል፡፡ የሸራተን ማስፋፊያ በሚል ለጎልፍ ክለብና ልዩ ልዩ መዝናኛዎች የታጠረውና በተለምዶ ፖሊስ ጋራዥ የሚባለው ሰፊ ቦታ ማጅራት መቺዎችና ኪስ አውላቂቆች መሸሸጊያ እየሆነ እንደመጣ ነዋሪዎች ብቻም ሳይሆን የከተማዋ ፖሊስ ጽሕፈት ቤትም የሚያነሳው ጉዳይ ሆኗል፡፡ የፒያሳው ግዙፍ የመንታ ሕንጻዎች ፕሮጀክት በዲዛይን ለውጥና በሌሎች ጥቃቅን ሰበቦች የተነሳ ይህ ነው የሚባል ግንባታ ሳይካሄድበት ለ18 ዓመታት ታጥሮ መቀመጡም የከተማዋ ነዋሪ በአስተዳደሩ ላይ እምነት እንዲያጣ ካደረጉት አበይት ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

$
0
0

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

slide15-e1466825122855ሰዎችን እንደ እህል በዘር ጆንያ እየሠፈረ በፈለገበት ሣጥን ውስጥ ማስገባት ዓላማው የሆነው የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጪ ግምባር (ህወሃት)፤ በኦሮሞ ተቃውሞ #oromoprotest እና በአማራ ተጋድሎ #amhararesistance የተነሳው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዕንቅልፍ ስለነሳው በተለይም ደግሞ የሁለቱ በኅብረት መቆም ኅልውናው ላይ አደጋ ስለጣለበት ሶማሊና አፋር ክልል መንጎዳጎድ ጀምሯል፡፡

ለኢትዮጵያ ቅንጣት ታህል ደንታ የሌለው ህወሃት የኦጋዴንን ሕዝብ እንዴት እንደፈጀ፣ ሴቶችን (ህጻናትንና ወንዶች ልጆችን ጨምሮ) እንደደፈረ፣ ለመከራና ለስቃይ እንደዳረገ የተረሳ መስሎት ሰሞኑን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቅኝቱንም ሆነ ዜማውን የሶማሊ አድርጎታል፡፡ የህወሃትን ግፍ እንኳንስ የክልሉ ነዋሪዎች ሊረሱት ስዊድናውያኑ ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን እስከ ሞት የሚረሱት አይደለም፡፡

“ዝም የተባለው ዳርፉር” በመባል ከዳርፉር እልቂት ጋር በእኩልነት የሚጠቀሰው የኦጋዴን ሰቆቃ ፈጻሚዎች ጨካኞቹ ህወሃቶችና ተባባሪዎቻቸውን ድርጊት ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ዳጎስ ያለ መረጃና ማስረጃ የያዙበት ነው፡፡

የኦጋዴን ጉዳይ የመለስ ራስምታት መሆኑን ጠቅሶ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በቦታው ስለተፈጸመው ግፍ መግለጫአውጥቶ ነበር፤

“… ለወራት ያህል በመለስ ታማኞች ትዕዛዝ ሰጪነት የተከበቡት ኦጋዴኖች በረሃብ ተጠበሱ። ችግሩ ሲጠናባቸው ሽማግሌ በመላክ “በረሃብ ማለቃችን ነው። እኛ ንፁሃን ዜጎች ነን። ህፃናት እየተጎዱ፣ ከብቶቻችን እያለቁ ነው’’ በማለት ከከበባው ለመውጣት ጥያቄ ቢያቀርቡም ትእዛዝ ከተላለፈላቸው የጦር አዛዦች ያገኙት መልስ ጥይት ነበር። በተፈጥሯቸው አንድ ቦታ ተወስነው መኖር የማይችሉ አርብቶ አደሮች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ተከልክለው ለአራትና አምስት ዓመታት እንዴት ኖሩ? ምን ያህልስ ሰብዓዊ ቀውስ ደረሰ? ከአመታት የስቃይ ኑሮ በኋላ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ደርሶ በኦጋዴን የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሄደ። ንፁሃን ጉድጓድ ተምሶ በጅምላ እንዲቀበሩ ተደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መለስ ስለ ኦጋዴን ሲነሳ ያማቸው ጀመር። ከዋናው የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የሰላም ስምምነት አድርጌያለሁ ቢሉም አካባቢውን ገለልተኛ ወገኖች ገብተው እንዲመለከቱት ፈቅደው አያውቁም። ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች (ማርቲን ሺብዬና ዩሃን ፐርሸን) ላይ የተወሰደው ርምጃም የዚሁ ‹ምስጢር ይወጣብኛል› ፍርሃቻ አካል ስለመሆኑ ጥርጥር የለንም … ” (የመግለጫው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ከሶስት ወር በፊት “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም አውጥቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ June 25, 2016 አትመነው ነበር፡፡ የሰሞኑ የህወሃት የማስመሰያ “የፍቅር እሽሩሩ” ፈጽሞ የማይረሳ እንደሆነና የኦጋዴን ወገናችን መከራ የእኛም በመሆኑ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከህወሃት ቀንበር ነጻ መውታት ያለበትና ፍትህ ማግኘት የሚገባው መሆኑን ለማሳየት እንዳል ደግመን አትመነዋል! “በጭራሽ አንረሳውም!!”


 “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

“አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

ogaden 4የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል)

“በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላogaden 1 የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ ከተናገረችው፡፡

የሚዲና የዕርዳታ ሥራዎችን የሚያካሂዱ ሁሉ ወደ ኦጋዴን እንዳይገቡ በህወሃት ትዕዛዝ ተደርጎባቸው ባለበት ባሁኑ ወቅት በኦጋዴን የሚካሄደው ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፤ እስር፣ እንግልት፣ ወከባ፣ … በድብቅ ቀጥሏል ይላል ጋዜጠኛ ግራሃም፡፡

ዘጋቢ ፊልሙን ለመሥራት መረጃው የተሰበሰበው ከሚሊታሪው የኮበለሉና ሌሎች ለህይወታቸው ያልሳሱ ደፋሮች በሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ ኮብለለው በቅርቡ ኬኒያ ልትዘጋው ወደ ወሰነችው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ሦስት ሴቶች የህወሃት ሠራዊት ስላደረሰባቸው መከራ፣ ሥቃይና አስገድዶ መድፈር ተግባራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሚሪያም

ወደ ዳዳብ በግንቦት 2006ዓም የመጣችው ሚሪያም ለሁለት ዓመት ተኩል እንዴት እንደተሰቃየች፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዴት እንደተፈጸመባት ትናግራለች፤

“እንደ ማሰቃያ ይሆን ዘንድ እስኪደክመኝ ድረስ ሬሣ አቅፌ እንድቆም ተደርጌአለሁ፤ ከዚያም ሚጥሚጣ የሞላበት ላስቲክ በራሴ ላይ አስረውብኛል፤ ገመዱን ሲያስሩት አጥብቀው ከአንገቴ ጋር በማሰራቸው ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡ ከዚያ ለብዙ ሆነ እየተፈራረቁ አስገድደው ደፈሩኝ …”ogaden 10

“ኦጋዴን በሚገኘው እስርቤት 1097 የምንሆን ነበርን፤ ቁጥሩን በትክክል አውቀዋለሁ ምክንያቱም በየቀኑ ማለዳ ላይ እያሰለፉ ከቆጠሩን በኋላ በቡድን በቡድን እያደረጉ ይከፋፍሉን ነበር፤ …

“(የተያዝን ጊዜ) እህቴን ጉሮሮዋን አንቀው መረጃ አምጪ አሏት፤ ምንም እንደማታውቅ ብትነግራቸውም አልሰሟትም፤ ከሌሎቻችን ጋር ተቀላቅላ እንድትቀመጥ አደረጓት ከዚያም ሁላችን እያየን አራት ቤቶቻችን አቃጠሏቸው፤ ቤቱን እያቃጠሉ እህቴን ከመካከል ነጥለው ግምባሯ ላይ በጥይት መቷት፤ እህቴን እስከሞት ስትደማ አየኋት፤ ከእርሷ አጠገብ ሌላ ሴት ልጅ በድብደባ ብዛት ሞታ ነበር፤ ከዚያም እኔን ሬሣ ባለበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉኝ፤ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ አራት ቀንና አራት ምሽት አሳለፍኩ፤ ጥፋተኛ መሆኔን እንድናዘዝ ምርመራ ይካሄድብኝ ነበር፤ አለበለዚያ መጨረሻዬ እንደ ሬሣው እንደሚሆን ይነግሩኝ ነበር፤ እኔም ምንም የምናዘዘው የለኝም የምታርዱኝ ከሆነ እረዱኝ አልኳቸው፤ (ጉድጓድ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ) ከሬሣው መካከል አንዱ ጉሮሮው ታርዶ፤ አንገቱም በዱልዱም ነገር ተቆርጦ ጭንቅላቱ እዚያው የቀረው አካሉ ጎን ነበር፤…”

አናብ

በመስከረም 2007ዓም ወደ ዳዳብ ካምፕ የመጣቸው አናብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅምላ ከገደሉ በኋላ በጅምላ የሚቀብሩበትን ቦታ በመደበቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ አንዳንዶቹ መቼም አይገኙም፤ አንዳንዶቹ ግን በቁሻሻ ጉድጓዶች ውስጥ ተገኝተዋል” ትላለች፡፡

በእርሷ ላይ የደረሰውን በተመለከተ ስትናገር አናብ እንዲህ ትላለች፤ “ወደ እስር ቤት ተወስጄ በሽቦ ታነቅሁኝ፤ ይህ ዓይነቱን ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ቆይተው በኋላ እስርቤት ተዉኝ፤ በተያዝኩ ጊዜ ከፊት፥ ከኋላና ጭኔ ላይ በጎማ ጠፍር ገርፈውናል፤ ከእኔ ጋር የተያዙ አምስት ልጃገረዶች ነበሩ፤ ከተያዙት ውስጥ ትልቋ 19ዓመቷ አካባቢ ነበር፤ ትንሽዋ ደግሞ ወደ 15ዓመት አካባቢ ነበረች፤ በተያዝንበት ወቅት ልጆቹን ክፉኛ ሲደበድቧቸውና በሰደፍ ሲመቷቸው አይቻለሁ፤ ልብሳቸውንም ቀዳድደውባቸው ብጣቂ እራፊ አድርገው ተመልሰዋል፤ ይህንን በየጊዜው የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ …Ogaden 11

“መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”

ፋጡማ

እንደ ሚሪያም በግንቦት 2006 ዓም ወደ ዳዳብ የመጣችው ፋጡማ “ወታደሮቹ እናንተ የኦጋዴንን ሰዎች እናጠፋችኋለን፤ ምንም ዓይነት ነዋሪ እዚህ አካባቢ አንፈልግም፤ እንጨርሳችኋለን” ይሉናል፡፡ “እስርቤት ሳለሁ አንቀውኝ ነበር፤ በሳንጃም ወግተውኛል፤ በየጊዜው መላ አካላቴን ደብድበውኛል፤ ጭንቅላቴን በኤሌትሪክ ጠብሰውታል፤ የማያደርጉት ዓይነት ስቃይ የለም …” በማለት ምሬት እና ሰቆቃ በተሞላበት ድምጽ ምስክርነቷን ስትሰጥ ትደመጣለች፡፡ ኦብነግ በአካባቢው እንዳለ እና ሠራዊቱ አንድ መቀመጫ ቦታ እንደሌለው፤ በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሰፈር እንደሚመጡ እና የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ፋጡማ ትናገራለች፡፡Ogaden 12

ህወሃት በበረሃ በነበረበት ጊዜ ተጋዳላዮቹ በየምሽቱና በየሌሊቱ ወደ መንደራቸውና ሰፈራቸው በሚመጡበት ጊዜ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብና መጠጥ እያሲያዙ፤ ስንቅ እንየቋጠሩ ይልኩ ነበር በሙስና ወንጀለኛ ሆነው ታስረው የተፈቱት አቶ ስዬ አብርሃ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እንዲያውም የራሳቸውን እናት ጠቅሰው ብዙዎችን ይመግቡ እንደነበርና ለበርካታ ተጋዳላዮች “እናት” እንደነበሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

በህወሃት አዛዥነት ወደ ሥፍራው የተላከው ሠራዊት አስገድዶ መድፈር አንዱ የጥቃት መሣሪያው ነው፡፡ በወታደራዊ ሠፈሮች ውስጥ ሴቶች ለወሲብ መገልገያ ሆነዋል፤ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በበርካታዎች ይደፈራሉ በሚለው የግራሃም የቪዲዮ ዘገባ ላይ የስቃይ እንባ የምታፈሰውን ሚሪያም “በተደጋጋሚ ተደፍሬአለሁ፤ ድርጊቱ መደበኛ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ተቀበልነው” ስትል ያሳያል፡፡ “ብዙዎች በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ አንዳንዶችም የሚጥል በሽታ ይዟቸዋል ሌሎችም እውር ሆነዋል፤ እኔም ራሴ ከደረሰብኝ ስቃይና ድብደባ የተነሳ አሁን እየተሻለኝ ቢሆንም የጡንቻ መኮማተርና የሚጥል በሽታ ይዞኛል፡፡”

የኦጋዴን ጭፍጨፋ መሃንዲሱና ጀማሪው ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ነው፡፡ የሙት ውርስ እንጠብቃለን የሚሉት አወዳሾቹም በሙት መንፈስ እየተመሩ ግፉን ቀጥለውበታል፡፡Ogaden 13

የኢትዮጵያን ስም ይዞ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የዘመተው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሠራዊት ኦጋዴን በደረሰበት ጊዜ የፈጸመውን እማኞቹ በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ይሁኑ ወይም ልዩ ፖሊስ እኔ አላውቅም” የምትለው ፋጡማ ሰፈሮቻቸው በወራሪው ሠራዊት ከተከበበ በኋላ ከብቶቻቸው፤ ግመሎቻቸው፤ … በአጠቃላይ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ትናገራለች፡፡ ከሁለቱ ሴቶች ጋር በመስማማትም ወንዶች እየተነጠሉ እንደተገደሉ ታስረዳለች፡፡ በተለይ የተማሩ የሚባሉ የኦጋዴን ወጣቶችን እየለዩ እንደገደሉ የሟች ቤተሰብ የሆኑት እነዚህ እህቶች በቃለምልልሱ ላይ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ሁልጊዜ የሚባሉትም “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” መሆኑን ግፍ፤ እልህና ሲቃ በሞላው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ግዢው ህወሃት በልዩ ሁኔታ ያሰለጠናቸው በትምህርት ያልታነጹ፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሌላቸውና ከወሮበላ የማይተናነስ ባህርይ ያላቸው ጨካኝ ፓራሚሊታሪዎች እንደሆኑ ያስረዳል፡፡

ህወሃትንና ሹሞቹን በዚህ የኦጋዴን ዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ በሚፈጸም ወንጀል ማስከሰስ፤ ለፍርድ ማቅረብ የኦጋዴን ወገኖችንና የመላ ኢትዮጵያ ልጆችን ትብብር ይጠይቃል፡፡ ስቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ፣ … ካላስተባበረን ሌላ ምን ሊያስተባብረን ይችላል? ሰዎች ደስታን እንደመሰላቸው ሊተረጉሙት ይችላሉ፤ ግፍ ግን ቋንቋውና ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው – እስከ አጥንት ይዘልቃል፤ መቅኔን ይቆጠቁጣል፡፡

Ogaden 15ከአዘጋጆቹ፤ ምንም እንኳን በጋዜጠኛነት ተግባር ላይ የምንገኝ ቢሆንም የእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ያመናል፤ ያስለቅሰናል፡፡ ከአንዲት እናት የተወለድን ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናችን የሴቶች ስቃይ ከምንም በላይ ልባችንን ያሳምማል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ስቃይ ማቅረብ ሌላውን ዜና የመዘገብ ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድርጊቱ አሁን የተፈጸመ ያህል እየተሰማቸው አሁንም ትኩስ እንባ እያፈሰሱ ስቃያቸውን የገለጹት እህቶቻችን ህመም የማያመውና የማያስለቅሰው ህወሃትና በድንቁርና ጭለማ ውስጥ የገቡት ጀሌዎቹ ናቸው፡፡ ህወሃት ይህንን ዓይነቱን ግፍ ሲደርግ ኖሯል፤ አሁንም እያደረገ ነው፤ ኢትዮጵያ ግን አሁንም ከእናንተ የኦጋዴን ግፉአን ጋር ታለቅሳለች፡፡

 

Viewing all 2265 articles
Browse latest View live