Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በወሎ በጎጃምና በሸዋ የሚደረጉ ሰልፎችን በተመለከተ – ‪[ግርማ ካሳ]

$
0
0

5646

በቀድሞ የጎጃም ክፍለ ሃገር በሆነችው በታሪካዊቷ ከተማ ደብረ ማርቆስና በሌሎች የጎጃም ከተሞች፣ በታላቂቴ ደሴና በመላው ወሎ፣ እንዲሁም በአጼ ዘረያእቆብ ከተማ በደብረ ብርሃንና ሌሎች የሸዋ ከተሞች ሰለማዊ ሰልፎች ለማድረግና ድምጹን ለማሰማት ህዝቡ እየተንቀሳቀስ እንደሆነ ይታወቃል።

በባህር ዳር እና በጎንደር እንዲሁም በኦሮሚያ በተነሱ ተቃዉሞዎች ራስ ምታታቸውን መቋቋም ያልቻሉት ህወሃቶች፣ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ወደ ሌሎች የአማራው ክልል ከተሸጋገረ ስትሮክ ሊይዛቸው እንደሚችል ስለተረዱ ተቃዉሞዎችን እንዳይነሱ ለማድረግ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆኑ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ ነው።

ከፍተኛ የብአዴን ባለስልጣናት በማሰማራት ህዝቡን የመደለልና የማግባባት ሥራ መስራት አንዱ ስትራቴጂያቸው ነው። ለምሳሌ ወ/ሮ ገነት ዘዉዴ ከየት እንደመጣች ሳይታወቅ አባተ መሐመድ ከተሰኘ ከፍተኛ አመራር ጋር በአሁኑ ሰዓት ኮምቦልቻ ነው የምትገኘው።
ለነገ ሐሙስ ወያኔ በደሴ ከተማ የሃይማኖት አባቶችን የጠራ ሲሆን፣ አባቶችም በስብሰባው እንደማይገኙ ተናግረዋል። የሃይማኖት አባቶቹ የተጠሩት ከደሴ ከኮምቦልቻና አካባቢው ከሚገኙ አዲባራት አብያተ ክርስቲያናትና መስጊዶች ሲሆን እስከመቼ ከህዝብ ተነጥለን እንኖራለን በሚል በስብሰባው ላለመገኘት መወሠናቸውን ተስፋዬ መንበሩ የተሰኘ ጦማሪ ምንጮች ዋቢ አድርጎ አስረድቷል።

ሕዝብን ለመደለል የሚደረገው ሙከራ በአንድ በኩል እየቀጠለ፣ ተቃዉሞ እንዲነሳ ሊያደራጁ የሚችሉ የተባሉ ወጣቶችን አፍኖ መዉሰድ ሁለተኛ ስትራቴጂያቸው ነው።
አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሀይቅ ከተማ ነዋሪ ” አሁን ከመሸ በኃላ ሀይቅ ከተማ ሁለት አይፋ መኪና አንድኛው ሽፍን ነዉ። ከተማዋ ላይ ቆመው ይታያሉ፡፡ በከተማዋ ህዝባዊ እንቢተኝነቱን ያቀጣጥላሉ በሚል የሚጠረጠሩ ወጣቶችን አፍኖ ለማጓጓዝ ታስቦ እንደሆነም የውስጥ አዋቂዎች ሹክ ብለውናል፡፡ እናም ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ መልዕክቴን አድርሱልኝ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለተመሳሳይ ተልኮ በደብረ ማርቆስ ከተማ ሁለት የወታደር ኦራል መኪኖች አጋዚዎችን ጭኖ እንደገባም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በደብረ ማርቆስ የሚገኙ መዉጫና መግቢያ በሮች ላይ ሕወሃቶች ህዝቡን ካሁኑ በጀሌዎቻቸው በማስፈተሽ ላይም እንደሚገኙ እየተሰማ ነው። ይህ ከተማዋን በቁጥጥር ስር ማድረግ የታሰበ ሲሆን፣ ተሰሚነት ያላቸዉ የከተማይቱ ግለሰቦችና በወያኔ የሚጠረጠሩ ሰዎችን ያለ ፍ/ቤት ትእዛዝ ቤታቸዉን እየፈተሸ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የቀበሌዉ ጽ.ቤት ያሉ የሕወሃት ተላላኪ ካድሬዎችን ከተማይቱን ተከፋፍለዉ፣ ቤት ለቤት እዬዞሩ ለእሁዱ ነሀሴ 8 ሰልፍ ህዝቡ እንዳትወጡ በሚል ምልጃ ላይ ናቸዉ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles