መኃኑን ታሪክ ለማዋለድ በሚደረገዉ “ጥረት” አብዝቼ ባዝንም፣ የቀደመዉን የሃገሬን ጠመዝማዛ የታሪክ መንገድ ግን ከነእንከኑ እቀበለዋለሁ፡፡ የታሪክ ክህደትም ሆነ የታሪክ ብዜትን ሊጭኑብኝ ለሚሞክሩ ሰንባችም ሆኑ አርፋጂ ብሄረተኞች ጆሮዬንም ሆነ አዕምሮዬን የምሰጥ ሰዉ አይደለሁም፡፡
ትላንትን በዛሬ መነጽር ባላየዉ እንኳን የቀደመዉን ዘመን በሰብዓዊነትና በማህበረሰባዊ ዉል ሚዛን ላይ አስቀምጬ እንድመለከተዉ ሰው-ነቴ ያስገድደኛል። ሰው ነኝና። ሰው።. . . .
በገባኝ መጠን የዛሬዋን ቁርጭምጭሚት ኢትዮጵያ ወደ ቀደመ ከፍታዋ ለማውጣትና ገጽታዋን ለማደስ ሲሚንቶው ሰብዓዊነት ሊሆን ይገባል። ከብሔር አጥር ባሻገር ዜግነት የሚባል ሰፊ ሜዳ እንዳለ ልብ እንበል። ኢትዮጵያችንን ከሁለንተናዊ ውድቀት ለመታደግም ሆነ ዳግም ለመገንባት የቀጥታ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ብቻ መፍትሄ አይደለም። ይልቁንስ በሁለንተናዊ . . . መስክ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መዋቅሮችን (ድርጅቶችን) መደገፍ ሃገሪቱን ከገባችበት ማጥ ለመታደግ አማራጭ መንገድ ይመስለኛል። ጋኑ በጠጠር ሊደገፍ እንደሚችለው ሁሉ የዚህኛው መንገድ አብርክቶም ጋኑን ከደገፈው ጠጠር አያንስም፤ እንዳውም ባይበልጥ።
. . . ለቀይ-መስቀል ደማችን ስንለግስ “ብሔር”ን ታሳቢ ያደረገ ነው ወይስ ሰው-ነትን፣ ሰብዓዊ እርዳታን ግምት ውስጥ ያስገባ? መንገድ ላይ ምጽዋት ለሚጠይቀን ሰው እጃችን የምንዘረጋለት በምን መለኪያ ነው? ከ”ብሔር”ወይስ ከሰብዓዊነት አኳያ? ድንቡሼ ህጻናትን መንገድ ላይ ስናገኝ ጎንበስ ብለን የምንስማቸው በ”ብሔር” ስበት ተገፍተን ነው ወይስ ሰዋዊ የፍቅር ስሜት መርቶን?
. . . እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው . . . ኢትዮጵያን ከውድቀት ለመታደግም ሆነ ከፍታዋን በጋራ ተሳትፎ ለመገንባት ሲሚንቶው ሰብዓዊነት ነው። ከሁሉም ነገር በፊት ሰው መሆን ይቀድማል። ሰው።
ሙሉአለም ገ.መድህን
(“ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ” የሚለው ንዑስ ርዕስ እና ፎቶው የተወሰደው አቶ ኦባንግ ሜቶ ከሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድረገጽ ነው፡፡ ይህ ጦማር ጸሃፊው ለዝግጅት ክፍላችን ልከውት የታተመ ነው)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
<!–
–>
The post ብሔር ወይስ ሰው-ነት? appeared first on Medrek.