አደገኛ አገዛዝ – ለሰው ልጅ ሕይወት ደንታ ቢስ የሆነ አገዛዝ – አደገኛ የሆኑ የሃሰት የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ የሚፈጥር ውሸታም አገዛዝ – ዛሬም የተንሰራፋውን እውነት ለመዋጥ የማይፈልግ አገዛዝ – በሃገሪቱ የተስፋፋውን ድርቅ እና ረሃብ በመካድ በሕዝብ ሕልውና ላይ የሚዘባበት አገዛዝ – አለም አቀፍ ሚዲያዎች እና ተቋማት የመሰከሩትን እውነት ለመሸፈን የሚድህ አገዛዝ – 7.6 በመቶ ያሽቆለቆለ ኢኮኖሚ ይዞ አስረአንድ በመቶ አድገናል የሚል ራሱን የሚሸውድ ትእቢተኛ አገዛዝ:: ብልህ አገዛዝ ራሱን አይሸውድም::
አስረ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ በረሃብ በተጋለጠበት በ350 ሚሊዮን ስተርሊንግ ፓውንድ በላይ የምግብ እህል እርዳታ በሚያስፈልግበት በዚህ ወቅት በቀን ሕጻናት አዋቂዎች እና እንሰሳት በረሃብ እና ድርቅ ምክንያት ለሞት በሚዳረጉበት አገር በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል ለዚህ ያበቁንን ገበሬዎች ደሞ እየመረቅን ነው ብሎ በየሚዲያው መናገር ምን ያህል ሃቅን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ለመሸፈት የሚጥር ጅል አገዛዝ እንዳለ ያመለክታል::ከሶሪያ ጦርነት በበለጠ በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ ሰብኣዊ ቀውስ ባሳደረበት በዚህ ወቅት በምግብ እህል ራሳችንን ችለናል ማለት እብደት እነ ቴቢት ነው::በሰው ልጅ ሕይወት ላይ እንደመቀለድም ሲሆን በሕይወት ላሉ ዜጎችም ንቀትን ከማሳየት አይበላለጥም::ይህ በረሃብተኛ እና በድርቅ የተጎዳው ላይ የሚደረቅ ስላቅ ነገን ከተጠያቂነት አያድንም:sourse,,ሚኒሊክ ሳልሳዊ
The post ድርቅ እና ረሃብ = አደገኛ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ appeared first on Medrek.