የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን ገልጾ እንደዘገበው ኤርትራ በ2 ቀን ጦርነት 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድላ 300 ማቁሰሏን አስታወቀች::
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ጥቃት ፈጸመብኝ ማለቱ ይታወሳል::
እንደሚኒስትሩ መግለጫ እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተደረገው ጦርነት 200 ሰዎችን መግደሉን ይገልጽ እንጂ ከራሱ በኩል የተጎዱ ወይ የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ የገለጸው ነገር የለም::
የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለኤርትራ መንግስት እስካሁን ለፈጸመው ትንኮሳ ተመጣጣኙን እርምጃ ሰጥተነዋል:: ወደፊትም እንደ ኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ ጦራችንን እናንቀሳቅሳለን ማለቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም ከኤርትራ ጋር ወደለየለት ጦርነት መግባት የኢትዮጵያ ምርጫ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል::
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ1998 – 2000 ዓ.ም ድረስ ባደርጉት የድንበር ግጭት ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ::