Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

መጪው ኢትዮጵያዊነት  – ግርማ ቢረጋ

$
0
0

Europe -Woayeመከተል በቻ ሳይሆን አላማውና እርምጃውን በትክክል አውቀው ተረድተው ስለሃገራችን ያገባናል የሚሉ ወገኖች መበርከት ለብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን አድናቆትና ፍቅር ያተረፈ ስለመሆኑ እርግጠኛ ማስረጃ ነው ።

አልፎ ተርፎም ለራሳቸው ለባንዳ ወያኔዎች ሳይቀር አግራሞት እንደፈጠረባቸው አንዳንዴ ሳት  እየዳረጋቸው መናገራቸው አልቀረም ምክንያቱም ወደው ሳይሆን  ውስጣቸውን በተሞላው የዘረኝነትና  ፣ የበታችነት መንፈስ በመለከፋቸው ብቻ የሚበሉት ምግብ የሰው ስጋ ሆኖባቸው ሆዳቸውን ሳይሆን ህሊናቸውን ሲቆፍረው ራሳቸውን ሳይሆን በስግብግብ የባንዳ ውላጆች የተሞላ ባዶ ጭንቅላታቸውን ጭንቀት ሲወጥረው ሃገር ማለት ትርጉሙ እሰኪጠፋቸው ድረስ የሰውነት ደሃ ሆነው ፣ ያልፈጠረባቸው በራስ መተማመን ስሙ እንኳን ከበከተው ህውሃት ጋር አብሮ ያሸለበ  የምንትስ ውላጆች ጭንቀታቸው ከግዜ ወደ ግዜ እያሻቀበ  አሁን ያሉበት የባዶነት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ። ለዚህም እኮ ነው ከፊታቸው የቆመውን ሁሉ ገርስሰው ለመሄድ የሚችሉ መስሎ የሚሰማቸው ፣ እነዚህ ባዶነት የሞላቸውን ቡችሎች ከሃገራችንና ከደሃው ገበሬ ጨርሶ ለማላቀቅና ነፃ እና ዲሞክራሲያዊት አትዮጵያ ለመመስረት ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ባሻቀበና ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ የሚያያይዛቸውን መንገድ ግልፅና እውን በሆነውና ከዘረኝነት በጸዳው አመለካከት ውስጥ ማሰባሰብና ቁርጠኝነት ማሳየት እየበዛ መምጣቱ የኒህን የሙት መንፈስ አምላኪ ባዶዎች ጓዳ ከምንጊዜውም በላይ እያተረማመሰው ነው። ታዲያ ከሃገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ በየቦታው  መደራጀት ፣ ስለወደፊትዋ የጋራ ሀገራችን የመወያያ መድረኮችን በመፍጠር እጅ ለእጅ ሊያያይዘን የሚችለውን ኢትዮጵያዊነት ላይ መግባባት በመፍጠር ፣ይህን የሃገርና የሕዝብ  ጠላት የባንዳ ቡችላ ከአንዴም ለመጨረሻ ጊዜ ጠራርጎ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል ላይ የራስን ድርሻ ለመወጣትና ህሊናችን እንደ ባንዳ ወያኔዎች ላለማቆሸሽ ተግተን ልንሰራ ግድ ይለናል ። ለዚህም ቢሆን ቀስቃሽ የሚያስፈልገን ልንሆን አይገባም በተለያየ ሁኔታ የወገኖቻችን ስቃይ ፣ረሃብ  ግድያ እንዲሁም ስደት  ሊቆጠቁጠንና ሃላፊነት ሊሰማን ይገባል። ኢትዮጵያዊነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች ክብር ነው።

ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች!!!

ጁን 2016

Ethiofri@gmail’com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles