‹‹ በሻቢያ ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ካስፈለገ፣ ህዝባችንን አስፈቅደን ነው፤….›› የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡
የዓለም መገናኛ ብዙሃን፡-
ማን እንደጀመረ ግልጽ ባያደርጉም/ባያረጋግጡም ‹‹ በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ግጭት/ጦርነት ተጀመረ….›› ብለውናል፡፡ የፈረንሳይ ዜና ደግሞ አለፍ ብሎ ‹‹ የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ ጦርነት ከፈተብኝ…›› ሲል ከሰሰ ፣ ይለናል፡፡
አቶ ጌታቸው ረዳ፡-
‹‹ በኤርትራ/ሻዕቢያ በተደጋጋሚ/ተከታታይ ለተፈጸመው ትንኮሳ አስፈላጊ የተባለውን ጠንካራ እርምጃ / ተመጣጣኝ አጸፋዊ ምላሽ/ ወስደን ወደ ቦታችን ተመልሰናል…፡፡ ›› (ይቅርታ ‹ሽብርተኞች› እኚህን ሚ/ር በጀርመን እንዲያ ማሳደድና ማዋረድ ምን ይሉታል፣ አያሳዝኑም ? (ነጻነትና ዲሞክራሲ አገር ናፈቀኝ፤ እርሳቸውንስ አይናፍቃቸው ይሆን ? –እንነጋገር ሲሉ ነበርና ማን ያውቃል …?)
እኛ የምናውቀው እውነት፡-
‹‹በጠ/ሚ/ሩ ቃል መሰረት እንኳን ፍቃድ ልንጠየቅ፣ ስለተደረገብን ተደጋጋሚ ትንኮሳና ጦርነት ስለመጀመሩ እንኳ ግልጽና ወቅታዊ መግለጫም እንዳልተሰጠን ነው ፣ሁሌም የሚነገረን ጠንካራ እርምጃ ከተወሰደ በኋላና ጉዳት እንደምናደርስ ብቻ ነው፡፡ ››
እግረ መንገድ ‹‹ በሰላም አስከባሪነት ሱማሊያ ሄደው ለበርካታ ዓመታት የሞቱ ልጆቻችንና ወንድሞቻችን እንደሌሎች አገራት ዜጎች በክብር መቅበር ቀርቶ ቁጥራቸውና ስማቸው እንኳ አልተነገረንም፣ በዚህ አጸፋዊ ምላሽስ ስንት አጣን ወይስ የእኛ ሠራዊት ይገድላል እንጂ አይሞትም፤ አጸፋዊ ምላሽ ይሰጣል እንጂ አይወሰድበትም … ? ›› ብለን ጠይቀን እንለፍ፡፡
መፍትሄው– ተዋሸን፣ ተናቅን… ብለን ማሳቀልና ማልቀስ ሳይሆን ለአዎንታዊ ዘላቂ ለውጥ መታገል ነው፡፡ የህወኃትን ጠባብ ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በአንድ አገራዊ ዓላማ ዙሪያ በተናጠልና በጋራ በየተሰማራንበት የትግል መስክ ኢህአዴግን ለብሄራዊ ውይይትና ዕርቅ ማስገደድ፣ በሽግግር መንግስት አልፈን አዲስቱን በሁላችን የሁላችን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመመስረት ቆርጦ መታገል፡፡
ለአገራችን የሚበጀውን ደግ ደጉን ያሰማን፡፡
በቸር ያገናኘን፡፡