በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር ሲል የኢትዮጵያ (ህወሃት/ኢህአዴግ) ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ዓለም በሙሉ በሚያውቀው በየትኛውም ሚዛን እርምጃው ተመጣጣኝም፣ አስፈላጊም አልነበረም ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም “የኢትዮጵያ መንግሥት እንኳን ያላለውን ኮሚሽኑ ደፍሮ ‘ተመጣጣኝ ነው’ ማለቱ አስቂኝም አስገራሚም ነው”ብለዋል።
ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ግጭት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ሪፖርቱ ሃሣብ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መስተዳድር ቀደም ብሎ ይቅርታ መጠየቁን አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይገኛል ተጭነው ያድምጡ::
(ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ – VOA)