Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በሕወሃቶች የተዋረደ ሰራዊት (ግርማ ካሳ)

$
0
0

1341በሶማሊያ የሶማሊያውያን ብቻ ሳይሆን የሰዉ ልጆች ሁሉ ጠላት የሆነውን አልሻባባ ለማጥፋት በሚደረገው ትግል በጣም አመርቂና ጥሩ ዉጤቶች እየታዩ ነው። ሆኖም በዚህ ሂደት፣ ሕይወታቸውን የሚያጡ የአሚሶን (የአፍሪካ ሕብረ ጦር) ወታደሮች አሉ። ከአልሻባባ ጋር የሚደረገው ጦርነት ውጤት እያመጣ ያለው ትልቅ ዋጋ እየተከፈለ ነው።

ብዙ የኬንያ ወታደሮች ሞተዋል። ኬንያ ወታደሮቿ ሲሞቱ በአክብሮት ነው የሚቀበሩት። ህዝብ ማንነታቸውን ያውቃል። ህዝብ ለከፈሉት መስዋእትነት ክብር እንዲሰጣቸው ይደረጋል። ከዚህ በታች የምታዩት በዉጉያ ላይ የሞቶ ኬንያናዉያን ወታደሮች አስክሬን ወደ ኬንዳይ ሲወሰድ ነው። በክብር እና በማእረግ።

የኛ ጉዶች ህወሃቶች ግን፣ የነርሱ መሪ ሲሞት 15 ቀናት ለቅሶ አውጀው እንዳልነበረ፣ ከሽብርተኞች ጋር ሲዋጉ የወደቁ ወገኖቻችንን ስም እንኳን ሕዝቡ እንዳያውቅ እያደረጉ ነው። ለህወሃቶች፣ ወታደሮች ሰዎች ሳይሆኑ፣ እንደ ተበላሸ እቃ የትም የሚወረወሩ ናቸው።

እንግዲህ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስብ፣ ለዜጎቹ የሚቆረቆር እንደ ኬንያ ያለን መንግስትና ለአገርና ለሕዝብ የማያስብ፣ ለዜጎች (ወታደሮችንም ጨምሮ) ደንታ የሌለው የሕወሃት አገዛዝ ያላቸውን ትልቅ ልዩነት ተመልከቱ።

በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይህን እላለሁ፡

” ህወሃቶች እናንተን የሚፈልጉት ሊጠቀሙባችሁ ብቻ ነው። ህዝባቹህ ላይ እየተኮሳችሁ፣ ሕዝባችሁን እየደበደባችሁ፣ እድሜያቸውን እንድታረዝሙላቸው ብቻ። እናንተ በተለያዩ መልኩ ሕይወታችሁ ሲያልፍ ግን፣ እመኑኝ፣ አምስት ሳንቲም አይቆረቁራቸውም። ቅንጣት ያህል ደንታ የላቸውም። አስክሬናችሁን የትም ነው የሚጥሉት። በሰለጠነ አለም ያሉ ወታደሮች ያላቸውን ከበሬታና እንክብካቤማ ተዉት። ጎናችን ያለችዋን የኬንያ ወታደሮች እንኳን ብትመለከቱ ከናንተ መቶ እጥፍ በመንግስታቸው የሚከበሩ ናቸው። እናንተ ግን ለሕዉሃቶች ምናምንቴዎች ናችሁ። እንግዲህ ንቁ።ክብራችሁን አስጠብቁ። ስማችሁ እንደሚለው የጥቂቶች ሳይሆን የሕዝብ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሁኑ”


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles