Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

“ሳልሰማ ከሰደበኝ የነገረኝ አሳመመኝ” ሁለት (ግዜነው ደም መላሽ)

$
0
0

Tesfaye Gebreab - 1“ከሰጠሁት ጥቆማ በላይ ግን በሁለቱ መጽሃፍት- እነዚያን ጥቆማዎች ለማድረግ በተደረገ እንቅስቃሴም።…… እነዚህ ሁለት መጽሃፍት (የጋዜጠኛው ማስታወሻ እና የደራሲው ማስታወሻ ) ለመጻፍ ችያለሁ።እነዚህ ሁለት መጽሃፍት ያስገኙት የፖለቲካ ፋይዳ በአንድ ባለሙያ ማስጠናት ብቻ በቂ ነው። ያለፈውን ገድል በማንሳት ጉራ መንዛትም ብቻ ግን ዋጋ የለውም።ወደ ሚቀጥለው ተግባር መሸጋገር ያስፈልጋል።”  ይህ ጥቅስ “ጌዜ መስታወቱ”  በሚል እርህስ አለማየሁ መሰለ የተስፋዬ ገአብን ሰላይነት ካጋለጠበትና ከተስፋዬ  ማስታወሻ ላይ በእጅ ፅሁፍ ተከትቦ እባሪ ሆነ ከቀረበ ሰነድ ላይ የወሰድኩት ነው። መልክቱ ተስፋዬ ኤርትራ ውስጥ ላለ አለቃው የላከው ነው። ሙሉውን ከታች ያለውን ሊንክ በመክፈት ማንበብ ይቻላል።

ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?   http://www.satenaw.com/amharic/archives/12214

ወደኔው ሀሳብ ስመለስ ቁጥር “ሁለት”ን የተጠቀምኩት እርህሱን ከዚህ ቀደም ዘአበሻ ላይ ተመሳሳይ አስተያየት ለመስጠት ተጠቅሜበት ስለነበረ ነው። እ.አ.አ በየካቲቲ  17 /2016 ዓ. ም ገጣሚ በእዉቀቱ ስዩም ከአሜን ባሻገር በሚለውን መፀሐፍ ውስጥ በአባቱ  ከኦሮሞ የዘር ግንድ  እንደሚጋራ መግለፁን ተከትሎ ተስፋዬ ገ/አብ የገጣሚውን ቀደምት ስራዎች ከብሔርተኝኘት አንፃር ያየበትንና የአማራን ሕዝብ የዘለፈበትን ሀሳብ ለመሞገት ነበር። በውቀቱ በመፀሐፋ የግለሰቡን የፈጠራ ድርሰቶቻ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እያጣቀሰ አፈር አልብሶአቸው ስለነበር ተስፋዬ ሀሳቦችን ይሞግታል ተብሎ ሲጠበቅ ለገጣሚው ስራዎች ምናባዊ ትርጉም በመስጠት ወደሚቀለውና ወደ ዋናው አጀንዳው ወደ ሆነው አማራን መዝለፍና ማንኮሰስ ቀይሮ ሲውተረተር በማየቴ ነበር ከላይ በተጠቀሰው እርህስ ሀሳቤን የገለፅኩት።

“መጥፎ ቁራኛ ካለመቃብር አይለቅም”  ነውና  ይህ ግለሰብ በምንም አይነት አጀንዳ ላይ ቢሆን የሚያገኘውን  መድረክ  የሚጠቀመው በዋናነት በእሱ አመለካከት የአማራን ስነ ልቦና ይጎዳል ብሎ የሚያምንበትንና በምናቡ የፈጠረውን ሀሳብ ለማስተላለፍ  ነው።ከዚህም ከፍ ሲል ደግሞ  በተግባር እንደምናውቀው በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ውስጥ ጠላትነት ይፈጥሩ ይሆናል የሚላቸውን በማር የተቀቡ መርዝ ሀሳቦችን ለመርጨት ነው።

ኤርትራዊው ሰላይ ተስፋዬ  ገ/አብ እ. አ.አ ሰኔ 7/ 2016 ዓ.ም በዘሐበሻ ድህረገፅ ላይ “የግንቦት ፖለቲካ”  በሚል አንድ መጣጥፍ ለቋል። የመጣጥፉን መግቢያ ላነበበ ፀሀፊው በእርህሱ እንደገለፀው የግንቦት ወርን ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር ያለውን ትስስር ለመተንተን ከፍ ካለም በገዢው መንግስት ውስጥ ያሉ አንዳንድ መረጃዎችን ለማካፈል የፈለገ ነው  የሚመስለው።  ነገር ግን ይህ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ግለሰብ ከተነሳበት አጀንዳ ጋር አንዳች ግኑኝነት የሌላቸው የተለመዱ ምናባዊ የፈጠራ ወሬዎቹን በመደርደር አጋጣሚውን የአማራን ሕዝብ ለመዝለፍ ተጠቅሞበታል።

የመጀመሪያው ሀሳብ እንዲህ ተብሎ ተቀምሯል።

“ አንድ ጊዜ ሰንገዴ ተብላ የምትታወቅ የኢህዴን ክፍለ ሰራዊት ከOLF ጋር ውጊያ ገጥማ ተሸነፈች። መሪዋ ተፈራ ካሳ የኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ነበር። በዚያን ጊዜ ገና የተዋሃደ ሰራዊት አልተቋቋመም። ሰንገዴ በOLF ተሸንፋ ከተበታተነች በሁዋላ ጄኔራል ሳሞራ በህይወት የተረፉትን ወታደሮችና መሪያቸውን ለግምገማ ሰበሰበ። እንዴት ሽንፈቱ ሊከሰት እንደቻለ ሰፊ ግምገማ ከተደረገ በሁዋላ ሳሞራ በጣም ስለተበሳጨ፣ “ሽንፈት የተከሰተው ተፈራ ካሳ ፈሪ ስለሆነ ነው። ችግሩ ይሄ ነው።” አላ ይለንና  ትንሽ መቀባቢያ ካከለ በኋላ ይወርድና መጨረሻ ላይ  “እውነት ነው የተናገርኩት። ልጨምርላችሁም እችላለሁ። አማራ ራሱ በተፈጥሮው ፈሪ ነው!!” አለ ብሎ ይደመድማል።

እኔ ላነሳው የፈለኩት ቁም ነገር ሳሞራ “አማራ በተፈጥሮ ፈሪ ነው”  ብሏል ወይም አላለም የሚል አይደለም። ሳሞራም ሆነ ድርጅቱ ህውሃት በአማራ ሕዝብ ላይ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር ለቁጥር የሚታክቱ ግፎችን ፈፅመዋል። የኔ መከራከሪያ ተስፋዬ  በተደጋጋሚ  ይህንን ግለሰብ እየተጠቀመና ያለአንዳች ማጣቃሻ  “ሳሞራ አማራን አርቀን ቀብረነዋል” አለ  ሳሞራ ፣ “አማራ በተፈጥሮው ፈሪ ነው”  አለ   እና መሰል ሌላም ሌላም ድርሰቶችን እየደረሰ አማራ ላይ ቅርሻቱን እንዲተፋ መፍቀዱ ላይ ነው። ማንኛውም ሰው  (የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑን ለሕዝብ ይፋ በሆነ በተጨባጭ ማስረጃ የተረጋገጠለትና በእኩይ ስራውም በሁለት ሕዝቦች መካከል ቋሚ የሚባል ሀውልት እንዲተከል ያደረገውን ኤርትራዊ ተስፉየን ጨምሮ)  ሀሳቡን በነፃት የመግለፅ ተፈጥሮአዊ መብት አለው የሚል መከራከሪያ ማቅረብ ይቻላል።በአንድ ነገር ላይ የራሱን አስተያየት መሰንዘር፣ በእድሜው በአካል ያለፈባቸውን  ልምዶቹን ለሌሎች ማካፈል፣ በወቅቱ ያለው ስርሀት እየተገበረ ባለው ፖሊሲዎችም ሆና ባጠቃላይ ስርሀቱን ደግፎም ሆነ ተቃርኖ ሀሳብ መስጠት፣ ዛሬ ከሚስተዋሉት ነባራዊ እውነታዎች ተነስቶ በመሰለውና በተረዳበት መልኩ ነገን መተንበይ፣ እና መሰለ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀሳብን መወርወር ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ውስጥ  የሚከተቱ ናቸው።  ነገር ግና እንደኔ ግንዛቤ አንድ ግለሰብ እሱ ባልነበረበትና በሌላ አካል የተፈፀመን ድርጊት  ደጋግሞ አያነሳ የልብ ወለድ ድርሰት ሲፅም ፣ እሱ ባልነበረበት ትውልድ ተፈፀሙ የሚላቸውን ምናባዊ ፈጠራዎቹን ያለ አንዳች ማጣቀሻ ይዞ ሲቀርብ አሜን ብለን የምናስተናግድበት ጉዳይ ሁሌም የሚገርመኝ ነገር ነው።

ከላይ ወደ ተተረከው ድርሰት ልመለስ።  በመጀመሪያ በህውሃትና በኦነግ መካከል የተደረገ ጦርነት መኖሩን እኔ የምሰማው ለመጀመሪያ ግዜ መሆኑ ነው። እነዚህን ሁለት ፀረ ኢትዮጵያ ቡድኖች ያዋጋቸውን አጀንዳ አብሮ ቢያስረዳን ለግንዛቤ በጠቀመን ነበር። ህውሃትና ኦነግ ኢትጵጵያን ማፍረሱን በተመለከተ የነበራቸው አቋም አንድ አይነት ነበር። እነዚህ ቡድኖች በህውሃትና በኢህአፓ እንዲሁም በህውሃትና በኢዲዩ መካከል እንደነበረው የአላምም ሆነ በመታገያ ቦታ ሽሚያ ትግል ውስጥ የገቡበት ታሪክ ሰምቸም አንብቤም አላውቅም። ከተሳሳትኩ እታረማለው። እነዚህ ቡድኖች ተመጋጋቢ እንደነበሩና ኦነግ ሆነ ህውሃት የስልጠናና የስንቅ ድጋፍ ይደረግላቸው የነበረው በአባታቸው በሻብያ እንደነበረ እነሱም ደጋግመው የሚተርኩት ጉዳይ ነው። እንደውም ሌንጮ ለታ በቅርቡ እንደተናገረው ኦነግ ከሶማሌዎች በኩል ይደርስበት የነበረውን ጥቃት ለማስቀረት ሻብያዎቹ በአማላጅነት ዚያድባሬን መለመናቸውን ነው።

“ሰንገዴ”  ባብዛኛው ከከዱት ኢህአፓ አባላት የተቋቋመና በኋላም የቀድሞ ድርጅቱን ኢህአፓ እንዲሁም የትግል ወንድሞችን በህውሃት አጋዥነት የደመሰሰ  የኢህድን ሀይል   እንደነበር እውነት ነው። ነገር ግን ይህ የህውሃት ክንፍ ከኦነግ ጋር ስላደረገው ጦርነት የመኖሩ ጉዳይ እንግዳ ታሪክ ይመስላል።ሌላው ተስፋዬ  እንደሚለው ድርጊቲ የተከሰተው “የተዋሃደ ሰራዊት”  ከመቋቋሙ በፊትና ህውሃቶች ገና  ከነ ኢህአፓ ጋር የነበራቸውን ጉዳይ ከመጨረሳቸው በፊት ነው።  በዚህ ወቅት ደግሞ ተስፋዬ  ደብረ ዘይት ጭቃ እያቦካ ነበርና ታሪኩን እሱ በቦታው ተገኝቶ እንደሰማው በማስመሰል መዘገቡ የግለሰቡን የፈጠራ የተለመድ ተንኮል የሚያሳይ ነው።ቦታው ላይ የነበሩና በሕይዎት ያሉ ግለሰቦች ስለሚኖሩ ሊያርሙን ይችላሉ ብዬ እጠብቃለሁ።  ለማንኛውም  የዚህ ሀሳብ አላማ ሁለት ነው። አንደኛው እንደ ሁል ግዜው ሳሞራንም ሆነ ሌላ ምናባዊ የአማራ ሰዳቢ በመሳል አማራን የመስደብ ሱሱን ለመወጣት ነው።  ሁለተኛው ደግሞ በአማራ የተዋቀረውን የህውሃት ክንፍ ኦነግ በትግል መድርክ አሸንፎታል በማለት በሞጋሳ ዜግነት ላገኘበትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደ መሳሪያ ለሚጠቀምበት የኦሮሞ ማሕበረሰብን የስነ ልቦና ድጋፍ እያደረገ ለማስመሰል ነው።

ይህ የአማራና የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ግለሰብ በዚሁ መጣጥፉ ላይ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦና ይጎዳልኛል በማለት የተጠቀመበት ሌላው ስልት ደግሞ በአካል የሌለ  የ “አውሮፓውያኑ ሪፖርት” የሚልና በአውሮፖዊያን የተጠና ጥናት እንዳለ ለማስመሰል በመጣር ነው። ኤኔ ባለኝ መጠነኛ መረጃ የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ ካካሄደ በኋላ የአውሮፖ ሕብረት ሪፖርት ያወጣው አንድ ግዜ ብቻ ነው። በዚህ ሪፖርት ውስጥ ገዢውን መንግስ በመክሰስ ከተዘረዘሩት በርካታ ነጥቦች ዉስጥ በ E ውስጥ ከተቀመጠውና አማራን ከትግሬዎቹ ጋር የተቀሩትን ሕዝቦች ላይ ተፅእኖ እያደረሰ ነው ከሚለው የተሳሳተ ሀርግ ውጭ አማራን የተመለከተ ሌላ  እፀፅ የለም።  ሙሉውን ማንበብ ለሚፈልግ ሊንኩ እዚህ ይኛል።http://www.europarl.europa.eu/sides/getDoc.do?pubRef=-//EP//NONSGML+MOTION+P8-RC-2016-0082+0+DOC+PDF+V0//EN

ጠላታችን እንዲህ ብሎ ይጀምራል  “በአዲሳባ በምእራባውያን አገራት ኤምባሲዎች የሚሰሩ ወይም ዲፕሎማቶችን የሚያማክሩ በአብዛኛው የአማራ ልሂቃን መሆናቸው ይታወቃል። በቅርቡ ያየሁዋቸው ሰነዶች እንደጠቆሙኝ የአማካሪዎቹ ምክሮች በአብዛኛው ከኦሮሚያ አመፅ በሁዋላ “ጊዜ ያለፈባቸው” ተብለው ወደ መጋዘን ተልከዋል። አማካሪዎቹ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ፌደራል ስርአቱ ደካማ ጎን ሲያቀርቡ የነበረው መረጃ ከኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ጋር ያልተስማማ ሆኗል። አማካሪዎቹ ወይም ጥቆማ ሰጪዎቹ የሚያመጡት መረጃ ወደ መጋዘን ከመላኩ በፊት፣ “የውስጥ ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያንፀባርቅ፤ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን እውነታ ያላካተተ” ተብሏል።”

በመጀመሪ በህውሃት የአገዛዝ  ዘመን በመንግስ ተቋማትም ሆነ በምእራባውያን አገራት ኤምባሲዎች የሚሰሩና ዲፕሎማቶችን የሚያማክሩ  አማራዎች ናቸው ብሎ ማለት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁናቴ ከማያውቅ ደንቆሮ ሰው የሚጠቅ ድምዳሜ ነው። ይህንን ማረጋገጥ የሚያስችል አንድም ጥናታዊ ነገር የለም።መንግስታዊ ተቋማትን ትተን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አለም አቀፍ ድርጅቶች ቅጥርን በተመለከተ እንዴት እየሰሩ እንዳለ በቅርቡ የጀርመን ኢምባሲ በግልፅ ለጥፎት የታየ ጉዳይ ነው።ትግረኛ ቋንቋን እንደ ዋና መስፈርት በግላጭ አስቀምጠው አይተናል። በታሪክም አፍሪካ ዉስጥ መቀመጫቸውን የሚያደርጉ የውጪ ድርጅቶች ከአምባገነን መሪዎች ጋር ሲሞዳሞዱ እንጂ በስርሀቱ ተጠቂ ከሆኑት ማሕበረሰብ ጋር ሲያብሩ አይስተዋልም።

ሌላው ተስፋዬ  በምናብ የበላዩነቱን የሰጣቸው ዲፕሎማቾቹን የሚያማክሩ የአማራ ሊእቃን “ስለ ፌደራል ስርአቱ ደካማ ጎን ሲያቀርቡ የነበረው መረጃ ከኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ጋር ያልተስማማ ሆኗል” ይላል። ስለየትኛዎቹ ደካማ ጎኖች እንደሚያወራ ባለውቅም  ከግለሰቡ ቀደምት ስራዎችና  አማራ አንድነት አቀንቃኝ ነው ከሚለው ብነሳ “የአማራ ሊቅአን ላላቸው የውስጥ ፍላጎታቸውን ብቻ የሚያንፀባርቅ”  ብሉ ለመግለፅ የሞከረው የኢትዮጵያ ሕዝብ  ህሃትና ኦነግ የተከሉትን አድሎአዊና ወጥነት የሌለው፣ መገንጠልንና የአገር መፍረስን የሚደግፍ ፌደራል ስርአት  እንደማይደግፈውና አንድነቱን እንደሚፈልግ ብለው የሰጡትን ሀሳብ ይመስላል።ስለዚህ ሊለን የፈለገውና እሱም ሆነ ለስለላ ያሰማራው መንግስት እንደሚመኙት ከዚህ በተቃራኒ ያለው የኦነግ ሀሳብ በ”አውሮፓውያኑ”  ተቀባይነት አግኝቶል ነው።

በመቀጠልም ወደ ዋናው አላማው ሲወርድ  “በተጨማሪ ሪፖርቱ “የህወሃት አመራር በአማራ ልሂቃን ላይ ያለውን ንቀት” ይጠቁማል። አማሮች በአማራነትም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ጠንክረው መደራጀት አለመቻላቸውን፣ ወደፊትም ሊደራጁ ስለመቻላቸው እንደሚያጠራጥር፣ በመንግስት ስራ ላይ ያሉ አማሮች የህወሃት አለቆቻቸውን ንቀት መለማመዳቸውን ፅሁፉ በጥቅሉ ያነሳል። ንቀቱን በተመለከተ ከዚህ በላይ ዝርዝር ነገር አላቀረበም።”

እንግዲህ ይታያችሁ ይህ ግለሰብ “አውሮፓውያኑ”  ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ጥናት መሰረት  “አማሮች በአማራነትም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ጠንክረው መደራጀት አለመቻላቸውን፣ ወደፊትም ሊደራጁ አይችሉም”  የሚል ሪፖርት አውጥተዋል ነው የሚለን።ከሪፖርቱ ቀጥታ እንደቀዳው ለማሳየት ደግሞ በትምህርተ ጥቅስ ነው ያስቀመጠው።  ሪፖርቱ ተዘጋጅቶል የሚለን  በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ ከተፈጠረው ተቃውሞ በኋላ መሆኑ ነው። ይህ ሀሳብ  በአንድ ግለሰብ የወቅቱን የኢትዮጵያን ሁናቴ በማጤንና በአማራው ማሕበረሰብ ዘንድ ተከስቷል የሚለውን  ዝምታ በመታዘብ እንደ ግል አስተያየት ቢሰነዘር ምንም ግምት ባልተሰጠው ነበር። ጉዳዩን  ሀሳብን በነፃነት የመናገር መብት በሚለው ውስጥ አካተን ሀሳቡን በሀሳብና በማስረጃ  በማስደገፍ ወደመሞገት ነበር የሚገባው።። ግለሰቡ ግን የግሉ ሀሳብ ሳይሆን የአውሮፖ ሕብረትን  በሚያህል ግዙፍ አካል ተጠንቶ የቀረበ ሪፖርት አድርጎ በማቅረብ ነው የስነ ልቦና ጦርነቱን የሚያካሄደው። ከዚህ ቀደም የምናውቀው “አንድ አባት እንዲህ አሉኝ” ፣ “ከሌንጮጋ ጅን እየጠጣን ስናወራ እንዲያ ብሎ ነገረኝ”፣ “የኦሮሞ ሕዝብ የልቡን ትርታ ብታዳምጡት እንዲህና እዲያ ነው የሚያስበው”  እና መሰል  የማጭበርበሪያ ስልቶችን ነበር የሚያቀርበው። አሁን እረቀቅ ያለ ስልት መሆኑ ነው የ“አውሮፓውያኑ ሪፖርት” የሚል ደመና ማስቀመጡ።

እኔ በዚህ ሀሳብ ላይ ማንሳት የምፈልገው ስለ አማራ መደራጀት መቻልና አለመቻል ጉዳይ አይደለም።ሲጀመር ይህ ጉዳይ የአማራ ጉዳይ እንዲ የአንድ ኤርትራዊ ሰላይ ሆድ የሚቆሥጥ ጉዳይ አይደለምና ። ሌላው የሞኝ ክርክር ነው የሚሆነው። ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ገናና ስም ከሚያሰጦትን አድዋን ከመሳሰሉ የታሪክ ድርሳናት ጀርባ ማን እንዳለ አሁንም የሕውሃትም ሆነ የኦነግ እራስ ምታት የሚሆናቸው ሕዝብ ማን እንደሆነ ሁሉም በሚገባ የሚያውው ጉዳይ ነው።  ተስፋዬንስ እንዲህ አቅሉን አስቶ የሚያስወተውተው ጉዳይ ምን ሆነና?? እርግጥ ነው የዛሬው ወንድም ወንድሙኑ የገደለበትንና ሀገርን ወደብና ድንበር አልባ እንዲሆን ያስቻለው የታሪክ ክፍል የአማራ የታሪክ ክፍል አይደለም። የሻብያ የህውሃትና የኦነግ ገድል ነው።እርግጥ ነው አማራ እራሱን በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር አድርጎ ሲንገታገት 25 አመታት ማለፋቸውና በዚህም ዋጋ እንደከፈለበት መሬት ላይ ያለ ሀቅ ነው። ይህ ማለት ግን እንደ ተስፋዮ ባሉ ባለጌዎች ኦሮሞን ለማጀገንና የአማራን ስነ ልቦና ለመጫን በአግባቡ ማጣቀሻ ባልቀረበበትን በምናባዊ ሪፖርት እንዲያላግጡበት መድረክ መስጠት አሳዛኝ ነው።

በኔ ትውልድ ከፊት መስመር ከምናውቃቸው ከሻብያ ፣ህውሃትና የኦነግ መሪዎች በተጨማሪ እንደ ግለሰብ በሕዝብ መካከል ከፍተኛ ጥላቻ እንዲፈጠርና ሀገር በማፍረሱ ሂደት ወሳኝ ድንጋይ ያቀበለ ሰው ካለ ይህ ኤርትራዊ ነው። አኖሌን ደርሶ በአካል ሀውልት እንዲተከል ያስቻለ መርዝ። ሌላው ግለሰቡ ኢትዮጵያን በበጎ ጎን የማያየው የሻብያ የስለላ አባል መሆኑ በነ አለማየሁ ምንም ጥርጥር በሌለውና በማያሻማ መልኩ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው።የአማራን ሕዝብ ለመዝለፍ ፣ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን አደጋ ውስጥ ለመክተት እንደትል ሳያንቀላፋ የሚተጋ እኩይ ፍጥረት። እና ይህ ግለሰብ በሰው ዘር ላይ በተፈፀመ ወንጀል በአለም ማሕበረሰብ የተከሰሰች አባት ሀገር ኤርትራ ዜጋ ሆኖ ፤ሕዝቤና ሀገሬ ለሚለው አካል የመፍትሄ ሀሳብ እንደማዋጣት የኛን ሕዝብና ሀገር እንዲያደማ መፍቀድ ይኖርብናል ትላላችሁ ወገን??  ምናለ በአንድ እባብ ደጋግማችሁ ባታስነክሱን??

ግዜነው ደም መላሽ

gizdemelash@gmail.com

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles