የህወሃት አመራር ከበረሃ ይዞት የመጣ ሙሁሩን በማግለልና ከሌሎች የኮሚንሥት ጠላቶች ናቸው ከሚባሉ ጠላቶች ማለት ከፊውዳሊዝም ፣ ቢሮክራቲክ ካፒታሊዝም ፣ ፋሽዝም ፣ ኢንፐራሊዝም ፣ ጎን በማሠለፍ እንደጠላት ይመለከታቸው የነበረ አሁን ከብዙ አመት በኃላ አገርሽቶበት እኖሆ በከፍተኛ መሁራን የነበረውና ያለው አቃም ይፋ አድርጓል ።
ይህም 523 የተከላካይ ጠበቆች በህወሃት ተመልምለው የተሸሙ ዳኞች በዜጎች ላይ ሊያሣርፉት ለሚፈልጉት ብይን በሙያቸው በመከራከር ቡዙ ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ በማድረጋቸው ባለፈው ሣምንት የህወሃት የጠበቆች ግምገማ በመጥራት ፣ በአሁኑ ጊዜ ጠቦቆች በዚህ ክልል የሚገኙ 523 ጠበቆችና በመላው ሀገራችን የሚገኙ ተከላካይ ጠበቆች በሃገራችን ፍትህ ፣መልካም አሥተዳደር እንዳይሠፍን ፣ ከአቃቢያን ህግ በመመሣጠር ፍርድ በማዛባት ህዝብ እንዲጎዳ ጠንቅ ሆነዋል ተብለዋል ።
ከወቀሣው በመያያዝ በትግራይ ያሉ 523 ተከላካይ ጠበቆችና በሃገር አቀፍ ደረጃ ባካየዱት የጥብቅና ሥራቸውን የክርክር ሠነዳቸው እንዲፈተሽ በግምገማው መድረክ ተነግሯል ። ይህ ድርጊት ደግሞ በሃገራችን የሚኖሩ ሙሁራን በሙሉ ሽብር መፍጠር ነው ። በሌላ በኩል ግን ለሙሁራንና ለሙያቶኞች ቆም ብለው እንዲያሥቡ ፣ ሥለወደፊት እጣቸው አርቀው እንዲገነዘቡ አሠችሏል ።
↧
በትግራይ ክልል 523 ተከላካይ ጠበቆች በጥብቅና ሥራ የተሠማሩ በክልሉ ፍትህ እንዲጠፋ ጠንቅ ናቸው ተባለ !
↧