Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ብሔራዊ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል ተባለ፤ የደመ ነፍስ ዕቅድ ወይስ ዳግም ‘’ምን ታመጣላችሁ?’’

$
0
0

ብሔራዊ ፈተናው ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል ተባለ፤ የደመ ነፍስ ዕቅድ ወይስ ዳግም ‘’ምን ታመጣላችሁ?’’

ትላንት ለተ0001111ቋረጠው ፈተና፤ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ተቃውሞ ትምህርታቸው ተዘግቶ ለከረሙ ልጆች በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱ በሽማግሌ ሳይቀር አስለምነን እምቢ ሲሉን ይሄንን እርምጃ ወስደናል ሲሉ ለፈተናው ሾልኮ መውጣት የኦሮሚያ ተቃውሞ አስተባባሪዎች ሃላፊነቱን መውሰዳቸውን ሰምተናል።

መንግስትም ‘’ፕላን ቢ’’ አለኝ በጥቂት ቀናት ውስጥ ድጋሚ ፈትናለሁ… ብሎ ሲቀውጠው ተመልክተናል። ዛሬ ራዲዮ ፋና ሰበር ዜና ብሎ ባወጣው ዜና ታድያ ፈተናው ከአንድ ወር በኋላ ከሰኔ ሃያ ሰባት እስከ ሰኔ ሰላሳ እንደሚሰጥ ዘግቧል።
እንግዲህ አንድ እቅድ ሲነደፍ ካላንደር ተዘርግቶ በዕለቱ ምን ምን አለ… የሚለውን ከግንዛቤ ማስገባት የመጀመሪያው ስራ ነው። አሁን እንደምናየው ግን እነ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ይቺን እቅድ ሲነድፉ እግራቸውን ዘርግተው እንደሆነ እንጂ ካላንደር መዘርጋታቸውን ጥርጣሬ የገባው ጦማሪ አጥናፍ ፈተናው ይሰጣል፤ የተባለበት እለት የረመዳን ቀን ሊሆን እንደሚችል ጠቅሶ ስጋቱን በሶሻል ሚዲያ አጋርቶናል።

እኛም ካላንደራችንን በመዘዝን ግዜ በሰዕሉ ላይ እንደምንመለከተው ረመዳን ሰኔ ሃያ ዘጠኝ ይወላል… ያ ካልሆነ በሰላሳ ሊሆን ይችላል። (በጥቅሉ ፈተናው ይሰጣል በተባለበት ኢድ አልፈጥር የመሆን እድሉ ሰፊ ነው!)
ታድያ አሁንም ሙስሊም ተማሪዎችን እንዲሁም ብሄራዊ ባህልን ያላገናዘበ ወይ በደመ ነፍስ ፤አልያም በ ምን ታመጣላችሁ? የታቀደ እቅድ መታቀዱ ሰዎቹ እውነትም ሳይማሩ የሚያስተምሩን መሆናቸውን ያሳብቃል።

እና ወዳጄ፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ድጋሚ እንዲያስቡበት እንዳልነግራቸው ስልክ ቁጥራቸው የለኝም… እስቲ የምትቀርቧቸው ደውሉላቸው!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles