የአስራ ሁለተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሰረቀ!
ነገ በኢትዮጵያ የሚጠበቀው ወደ ዩንቨርስቲ የሚያስገባው የአስራ ሁለተኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ሃገር አቀፍ ፈተና መሰረቁን ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም በስልክ እና በመሳሰሉት መቀባበያ መንገዶች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።
የትምህርት ሚኒስቴሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ግን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው ነገሩ ሃሰት ነው ሲሉ ለማስተባበል ሞክረዋል። ቢሆንም ግን የትምህርት ሚኒስቴሩ ማሰተባበያ የገዛ የራሱ የመንግስት ደጋፊዎች ሳይቀሩ እየተቹት ይገኛሉ። የትችቱ መነሻ፤ የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ማስተባበያ የተቀረጸው ፈተናው ተሰረቀ ከመባሉ በፊት ነው እና ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ በሚል ነው።
ስለ ብሄራዊ ፈተናው አስራረቅ እየመጡ ያሉት መረጃዎች ሁለት ሲሆኑ አንደኛው የመንግስት ባለስልጣናት ልጆች በጥሩ ውጤት እንዲያልፉ ፈተናው ቀድሞ እንዲወጣላቸው በታዘዘው መሰረት ሲወጣ በቂ ጥንቃቄ ባለመደረጉ ለበርካቶች ተሰራጨ የሚለው ሲሆን፤ ሌላኛው መረጃ ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች በተቃውሞ ላይ ሆነው በቂ ዝግጅት ባላደረጉበት ሁኔታ እንዴት እኩል ፈተና ይቀመጣሉ በሚል የተቃውሞ እንቅስቃሴው ደጋፊዎች እና ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ናቸው ያሰራጩት የሚል ነው።
(ሰአቱ ስለመሸ) ለሁለቱም መረጃዎች ማስረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት የለም! ነገር ግን የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከጀት የፈጠነ ማስተባበያ የመጀመሪያውን ግምት *ጮክ ብለን እንድንመለከተው ያስግድደናል።