አቶ ስብሃት ነጋ፦ “ አንተ የምታቀርበው ሪፖርት ሁሌም ሞት ጠሪ ነው! ችግርህ ምንድነው!? አንተ ከአመራርነት ለመውጣት የቀረህ ጊዜ አጭር ስለሆነ ነው?! … በአንተ ሪፖርት ኢህአዴግን ደርግ ሆኖብኝ ነው ያገኘሁት! እኛ ነጻ አውጭዎች እንጅ ጨቋኞች አይደለንም!!”
አቶ በረከት ስምዖን ፦ “ አንተን ደስ እንዲልህ ፣ መብራቱ ሲቆም የሚቆም የባቡር ሃዲድ ተሠራ ብዬ ሪፖርት አላቀርብም! ኢህአዴግ ደርግ ሆነ ላልከው አንተ ብለኸዋል! የእኔን ሰነዶች እያነበብክ ተቃውሞ ከምታደራጅ፣ ከእኔ የተሻለ ሰነድ መጻፍ ብትችልና ብታቀርብ ጥሩ ነበር! እኔም ከዚህ የስልጣን ዘመን በሁዋላ ብትለምነኝም አታገኘኝም! ያውም አንተ ከቆየህ!”
ሰብሳቢው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦ “የበረከት የመልካም አስተዳደር ውይይት እቅድና ውጤት ራሳችንን እንድናይ መስታዎት ሆኖናል።