Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ልጅ የአባቱን ልደት ሲያከብር

$
0
0

በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራ ተወላጆች ሻዕቢያ “ትጥቅ ትግል” የጀመረበትን 54ኛ ዓመት ማክበራቸውን የህወሃት ዜና አገልግሎት ፋና ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ የምትባለው አገር ጠ/ሚ/ር እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ የሻዕቢያን ጉዳይ አስመልክተው ሲናገሩ የትኛውን ሻዕቢያ እንደሆነ በግልጽ ሳይጠቅሱ ሻዕቢያ እየወጋን ነው፤ ሕዝብን አስፈቅደን እርምጃ እንወስዳለን ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ለኤርትራ ተቆርቋሪነታቸው ወደር የሌለውና ይህም “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወደየት” የሚል መጽሐፍ እስኪጽፉ ያደረሳቸው ሞት የቀደማቸው መለስ በኢትዮጵያ የሻዕቢያ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ ነበሩ፡፡ በዚሁ መጽሃፋቸው ላይ የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው በማለት እምዬ ምኒልክን እንደ ቅኝ ገዢ የአውሮጳ ነገሥታት ኢትዮጵያንም እንደ ቅኝ ገዢ አውሮጳዊ አገር በማድረግ በማንም ቅኝ ተገዝታ የማታውቀውን ኢትዮጵያ የቅኝ ገዢነትን “ክብር አጎናጽፈዋታል”፡፡

ባለራዕዩ በዚሁ የሻዕቢያ ተላላኪነታቸው ኢሣያስን እንደ ግለሰብ “አጉራ ዘለል”፣ “ዕብድ” ፣ … እያሉ ከመዝለፍ በስተቀር ሻዕቢያን እንደ ድርጅት በከረረ ቃል ለመናገር ይከብዳቸው እንደነበር አብሮ የሚጠቀስ ቢሆንም በመለስ ፋውንዴሽን ግን የተዘነጋ “ሌጋሲያቸው” ይመስላል፡፡

የዛሬ 54ዓመት ትግል የሚባለውን የጀመረው ጀብሃ ነው፤ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ሻዕቢያ ተከሰተ፤ እርሱም ህወሃትን ወለደ፤ ህወሃትም ኢህዴንን (የአሁኑን ብአዴን) የአማርኛ ክፍል አድርጎ ከአባትና አያቶቹ በተማረው መሠረት ፈጠረ፡፡ ህወሃት ወላድ በመሆኑ የኦሮሚኛና ሌሎች “ጠቃሚ” የሆኑ የቋንቋ ክፍሎች ወለደ፣ እንደ ጭቃ እያቦካ ጠፈጠፈ፡፡

አሁን የኤርትራ የነጻነት ትግል የሚባለውን በባለቤትነት የሚወስደው ኤርትራን ነጻ አውጥቶ የሚገዛትና አንዳንዴም ለኢትዮጵያ ነጻነት ጥሩ አሳቢ እንደሆነ የሚደሰኮርለት ሻዕቢያ ነው፡፡

ሻዕቢያ የኢትዮጵያ የቅርብ ጠላት ነው በማለት አጥብቃችሁ በመቃወማችሁ የተገመገማችሁ፣ የታሰራችሁ፣ መከራ የተቀበላችሁ፣ … ያላችሁም የለቀቃችሁም የህወሃት አባላት፤ የአይደር ህጻናት ደም ከኅሊናችሁ ሊጠፋ ያልቻለ የትግራይ ተወላጆች፤ እንዲህ ያለውን ቤት ድረስ የመጣ የሻዕቢያ ድፍረት “የኤርትራ ሕዝብ የነጻነት ትግል የጀመረበት” በማለት አለባብሳችሁ ነው የምታልፉት ወይስ …?

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

<!–

–>

The post ልጅ የአባቱን ልደት ሲያከብር appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles