በጅዳ ቆንስላ ጸ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” የተሰኘው ቡድን ጽ/ቤቱ ለሕዝብ መሥራት ከሚገባው ጉዳይ በመውጣት በግለሰቦች ማንነት እና ሃይማኖት ላይ ጽንፈኛ አቋም እየያዘ መምጣቱ ታወቀ፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት “በመልካም አስተዳደር ሽፋን” ዙሪያ ይካሄዳል ተብሎ የተጠራው አሁን ካለው የከረረ ሁኔታ አኳያ ግጭት ያስነሳል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡
በተለያዩ ሁኔታዎች ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት “በመልካም አስተዳደር” ዙሪያ ሰሞኑን በተደረገው ግምገማ ጥቂት የደቡብ ተወካይ ነን የሚሉ ግለሰቦች አማራውን በብሄር እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በሃይማኖት በመከፋፈል የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ ጅዳ እና አካባቢዋን ስጋት ውስጥ ከቷል። በተለይ እራሱን “ወገን ለወገን” እያለ የሚጠራው በአቶ ሰመሩ እና ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ የሚመራው የቆንስላ ቡድን የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ በቆንስላው ተገልጋይ ላይ ሲፈፀም ለነበረው በደል እና መጉላላት በቀጥታ የአማራውን ብሄር ተወላጆች ተጠያቂ በማድረግ የጀመሩትን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማጠናከር በአካባቢያችን የሚገኙ ታዋቂ የብሄሩ አባላትና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመግለጽ ግምገማውን ለሌላ አጀንዳ ማስፈፀሚያ መጠቀማቸውን የቆንስላው ምንጮች ይገልጻሉ።
ይህ ቆንስላ የመሸገው ቡድን በተገልጋዩ ችግሮች ዙሪያ ከመስራት ይልቅ ማህበረሰቡን መቋጫ ወደሌለው የእርስ በእስር ቅራኔና ግጭት ለመዝፈቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይናገራሉ። ቆንስላ ውስጥ የአንድ ብሄር አባል እና እምነት ተከታዮች ነጥሎ ለመምታት እየተደረገ ያለው ጥረት በአሁኑ ሰዓት ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ ላልተወሰን ጊዜ መራዘም እንደሚገባው የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂዎች በመልካም አስተዳደር ሽፋን በተጠራው ስብሰባ ላይ ሊደርስ ለሚችለው ግጭት የቆንስላው ሹማምንቶች ሃላፊነቱን መውሰድ እንደሚገባቸው ያሳስባሉ። ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ግለሰቦች የሚመራው ቡድን በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያቀነባበረውን ሴራ ከጀመረ አመታትን ቢያስቆጥርም፤ ሰሞኑንን ቆንስላ ውስጥ ቁልፍ ሃላፊነት ቦታ ላይ በተቀመጡ አንዳንድ ሹማምንቶች አይዟችሁ ባይነት በአዲስ መልክ ቡድኑ የጀመረው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እየደረሰ መምጣቱ ለማወቅ ተችሏል።
ቡድኑ እስከ ሪያድ በዘለቀው ፀረ ብሄርና ሃይማኖት ቅስቀሳው የ2008 አዲስ አመት ተከትሎ የአማራ ብሄር ተወላጆች ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ሊያከብር የነበረውን አውደ ዓመት አሳግዷል። የአማራን ብሄር ተወላጆችን ከመጠጥ እና ከሴስኝነት ጋር በማያያዝ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ያጠናከረው ይህ ቆንስላ የመሸገው ቡድን እየፈፀመ ባለው አስነዋሪ ተግባር በአካባቢው ማህበረሰብ የሁለቱም እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።
በቪዛ ነጋዴዎችና ደላሎች የሚደገፈው በአቶ ሰመሩ እና ወ/ሮ ሙሉካ የሱፍ የሚመራው ይህ ቡድን ቆንስላ ውስጥ በህዝባችን ላይ ለተፈፀመው በደል የቆንስላው ሹማንቶችን በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባው “በመልካም አስተዳደር” ሽፋን በጅዳ የአማራ ብሄር ተወላጅ እና የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነው የኢሚግሬሽን ኃላፊ ሹም በመወንጀል ቡድኑ ድብቅ አጀንዳውን ለማስፈፀም በመራወጥ ላይ ይገኛል።
ይህ በዚህ እንዳለ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለውን በጅዳ የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ እና በኮንትራት ሰራተኞች ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እና በደል በመዘገብ የሚታወቀውን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ጨምሮ በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጅ የሃገር ሽማግሌዎችና ተዋቂ ሰዎች በዘር ሃረጋቸውና በሃይማኖታቸው ብቻ የዘመቻው ስለባ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ለጥቅምት 5፣ 2015 ህዝባዊ ስብሰባ መጥራቱ አግባብ አይደለም የሚሉ ነዋሪዎች ጥሪው በጅዳ እና አካባቢ የተፈጠረውን ውጥረት የሚያባብስ ከመሆኑም በላይ ጥቂቶች የብዙሃኑን ፍቅር ለማግኘት “የቀይ ሽብር ወንጀለኞች የማጋለጥ ድራማ” የሚለይ ባለመሆኑ ከስብሰባው በፊት በኃይማኖት እና በብሄር ጥላቻ የተዘፈቀው ቡድን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እና ከቆንስላው መታገድ እንዳለበት ይስማሙበታል። (ዘገባውን ከምስል ጋር ለጎልጉል የላኩት Ethiopian Hagere Jed Bewadi ናቸው፡፡)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
<!–
–>
The post ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የመሸገው “ወገን ለወገን” ቡድን አፍራሽ ተግባሩ ቀጥሎበታል appeared first on Medrek.