Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ዐማራው ከወልቃይት፣ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል!

$
0
0

የማንኛውም አመፅ መነሻ መሠረቱ፣ ገዥዎች በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የመብት ረገጣ፣ የማንነት ነጠቃ እና የሥነ-ልቦና ሰለባ ልኩን አልፎ ገደብ ሲጥስ የሚፈጥረው ምሬት እንደሆነ ይታወቃል። የትግሬ ወያኔ ዘረኛ እና ከፋፋይ የፋሽስት ሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ ቡድን፣ በወልቃት ፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ እንዲሁም  በዐማራው ነገድ ላይ በወል፣ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት በተከታታይ ፈጽሟል፤ እየፈጸመም ነው። በዚህ ረገድ የወረዳ ግዛቶቹም ሆኑ ነዋሪው ሕዝብ በየትኛውም ጊዜ፣ የትግራይ የግዛት አካል ሆነው አያውቁም። የትግሬ ግዛት ደንበርም ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም። ሕዝቡም ጥንትም ሆነ ዛሬ፣ በጉርብትና ከሚናገረው ትግርኛ፣ ዐረብኛ እና መሰል ቋንቋዎች በቀር፣ የትግሬነት ባህል፣ ታሪክ፣ ወግ፤ ሥነልቦና እና መሰል የማንነት ማረጋገጫ ዕሴቶች ኖሮት አያውቅም፤ እንዲኖረውም አይሻም።

የትግራይ ሕዝብ በተከታታይ በድርቅ እና በርሃብ ሲጠቃ እየፈለሰ የተጠጋው በእነዚህ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ነው። ስለዚህ በድርቅ እና በርሃብ ምክንያት ከትግራይ የሚሰደዱት ሰዎች ኑሯቸውን ሲደጉሙ የኖሩት በቀን ሠራተኝነት እየተቀጠሩ የወልቃይቶችን የሠሊጥ እና የማሽላ አዝመራ በማረስ፣ በማረም እና በመሰብሰብ እንደነበረ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። ሆኖም፣ «እንግዳ ሲሰነብት፣ ባለቤት የሆነ ይመስለዋል» የሚሉት አባባል ዕውነት ሆኖ፣ የዐማራው ነገድ ባለው የእንግዳ ተቀባይነት የዳበረ ባህሉ ተቀብሎ ባስተናገዳቸው ሰዎች የውስጥ አርበኝነት፣ ወያኔ ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት ላደረገው ዝግጅት፣ የጥቃቱ የቅድሚያ ሰላባ የሆነው በነዚህ ወረዳዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ እንደነበር በተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።  በዚህም መሠረት በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣ በጠለምት ፣ በሠቲት እና በአርማጭ ሕዝብ ላይ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ከፈጸማቸው እጅግ የበዙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መካከል የሚከተሉት ለናሙና ያህል የቀረቡ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።

ሀ) በ1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ የትግራይ እና የጎንደር ክፍለ ሀገሮች የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን የተከዜን ወንዝ ተሻግረው የሚከተሉትን ያገር ዘቦች በግፍ ገደሉ። እነዚህም፦

  1. አቶ ማሞ ዘውዴ፣
  2. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
  3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
  4. አቶ በርሄ ጎይቶም፣
  5. አቶ ሐጎስ ኃይሉ፣
  6. አቶ  ልጃለም ታዬ፣
  7. ግራዝማች ወልዴ የኔሁን፣
  8. ቄስ በለጠው ተስፋይ፣
  9. ቄስ ትዕዛዙ ቀለመወርቅ፣
  10. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣
  11. ወጣት ግዛቸው ዳኜው፣
  12. ወጣት አዲስይ ልጃለም፣
  13. ወጣት ደረጀ አንጋው፣
  14. ወጣት ዋኘው መንበሩ፣
  15. ወጣት ሕይዎት አብርሃ፣
  16. ወጣት ታደለ አዛናው፣
  17. ወጣት ማሞ አጀበ ናቸው።

ለ) በ1986 ዓ.ም. «ርዋሳ» የተባለውን ከ500 በላይ ቤቶች የነበሩበትን የገበሬ መንደር አቃጥለው ትግሬ አሰፈሩበት። በዚህ ቀበሌ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል አቶ ጫቅሉ አብርሃ፣ አቶ አብርሃ ሣህሉ፣ ወይዘሮ ስንዱ ተስፋይ፣ አቶ ዋኜው ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሐ) ከ1988 እስከ 1989 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ከ3,000 (ሦስት ሺህ) በላይ ጥማድ በሬዎች ባለቤቶች የነበሩ ገበሬዎችን ገድለውና አሰድደው ትግሬ አስፍረውበታል። ሠፈራ የተካሄደባቸው ቦታዎችም ማይደሌ፣ አንድ አይቀዳሽ፣ እምባ ጋላይ እና ትርካን ናቸው።

መ) ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ማይ ኽርገጽ፣ ቤት ሞሎ፣ ማይ ጋባ፣ ቃሌማ፣ እጣኖ፣ መጉዕ ወዘተ ይኖሩ የነበሩ ነባር የዐማራ ነገድ ተወላጆችን አባረው ትግሬን አስፍረዋል። በአጠቃላይ በጎንደር ለም መሬቶች ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ሠ) የትግሬ-ወያኔዎች ዐማራዎችን የጎንደር ክፍለሀገር ተወላጆችን አደህይተው እና አዋርደው፣ ከሰው በታች አድርገው ይገዛሉ። በአካባቢው የትግሬን የበላይነት አስፍነው ቀጥቅጠው እና አዋርደው ለመግዛት እንዲያመቻቸው የአካባቢውን ታዋቂ እና ባለሀብት ሰዎች አስረዋል፣ ገድለዋል፣ ሀብት ንብረታቸውን ዘርፈዋል። በዚህ ረገድ ለአብነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት አዛውንቶችን የቁም ከብቶቻቸውን መዘረፋቸውን የወልቃይት ጠደገዴ ተወላጆች ያስረዳሉ።

  1. ከአቶ ዘነበ ሐጎስ ከ450 ባላይ የቀንድ ከብቶች ዘርፈዋል፤
  2. ከአቶ ባየው ቢያድግልኝ ከ600 በላይ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈው በመጨረሻም ባለሀብቱን ገድለዋቸዋል፤
  3. ከአቶ ገብረሕዎት ኃይሌ ከ80 በላይ የቀንድ ከብቶች እና ፍየሎች ዘርፈዋል፤
  4. በ1981 ዓ.ም. ከአቶ አለባው ሕደጎ ከ500 በላይ የቀንድ ከብቶች እና በርካታ ኩንታል እህል ተዘርፏል።
  5. የቀኛዝማች ገብሩ ገብረመስቀል 24 በሬዎቹ ታርደው ከ900 መቶ ባላይ ማድጋ እህል ተወርሷል።

ረ) የካቲት 21 ቀን 1972 ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ የቃብትያ አዲህርድ ከተማን ለመቆጣጠር በነዋሪው ላይ በከፈተው ጦርነት 9(ዘጠኝ) ሰዎችን ገድሎ 18(አሥራ ስምንት) ማቁሰሉን የዓይን እማኝ የሆኑት ተሰደው በብሪዝበን ከተማ፣ አውስትራሊያ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፈረደ ያስረዳሉ። በዚያ በትግሬ-ወያኔ እና በነዋሪው መካከል በተደረገው ጦርነት ከሞቱት እና ከቆሰሉት መካከል ስማቸውን ማስታወስ የተቻለው የሚከተሉት ይገኙበታል።

  1. አቶ የልፋዓለም ተኮላ፣ ዕድሜ 65፣
  2. አቶ ጎኦይ መብራቱ፣ ዕድሜ 30፣
  3. አቶ አለነ ክንድሽ፣ ዕድሜ 60፣
  4. አቶ አታላይ አበራ፣ ዕድሜ 64፣
  5. አቶ ባሕታይ ወንድምአገኘሁ፤
  6. አቶ በለጠ ወንድምአገኘሁ፤
  7. አቶ በየነ ያዕብዮ፣ ዕድሜ 70፣
  8. አባ ኃይሌ፣
  9. አቶ ገብሩ ጋሼ፣ ሲሆኑ

ከቆሰሉት መካከል ደግሞ፦

  1. አቶ አሰፋ ገብረመድኅን፣
  2. ሙላው ኃይሌ (አለቃቸው ኃይሌ)፣
  3. አቶ መብራቱ ዋሴ፣
  4. አባ ጎላ ዘለለው፣
  5. አቶ አነጋው ገብረእግዚአብሔር፣
  6. አቶ አበራ አጀቢ፣
  7. አቶ ጥሩነህ ከሰተ፣ እና
  8. አቶ ፈቃዱ ይገኙበታል።

ሰ) ነሐሴ 10 ቀን 1972 ዓ.ም. ወያኔ ከወልቃይት እና ከጠገዴ ወረዳዎች አስሮ የወሰዳቸው እና እስካሁን የደረሱበት ያልታወቁ የአገር አዛውንቶች የሚከተሉት ናቸው።

  1. አቶ ሞላ ዘውዴ፣
  2. አቶ ተበጄ በቀለ፣
  3. አቶ አያሌው ሰሙ፣
  4. አቶ እንደሻው ታፈረ፣
  5. አቶ እሸቴ አያልነህ፣
  6. አቶ ጎኢቶም ሐጎስ፣
  7. አቶ በርሄ ሐጎስ ታፈረ፣
  8. አቶ በየነ አየልኝ፣
  9. አቶ ኃይሉ ልዩነህ፣
  10. አቶ አብርሃ ነጋ፣
  11. አቶ አለባቸው መብራት፣
  12. አቶ ድራር ገሠሠው፣
  13. አቶ ገብረሥላሴ ረዳ፣
  14. አቶ ገብረሕይዎት ባሕታ፣
  15. አቶ ኃየሎም ይርጋ፣
  16. አቶ አለባቸው ደፈርሻ፣
  17. አቶ ሊላይ ሐድጎ፣
  18. አቶ ጎኢቶም ምህረት፣
  19. አቶ ታገለ ወርቄ፣
  20. አቶ መሓሪ አዱኛ፣
  21. አቶ ባየው ቢያድግልኝ፣
  22. አቶ ሢሣይ ዘነበ፣
  23. አቶ አታላይ ዘነበ፣
  24. አቶ ተፈራ ሊላይ፣
  25. አቶ ገብረመድኅን የኋላ፣
  26. አቶ ነጋሺ ተበጄ (አራት አንበሣ ገዳይ የነበረ ጀግና፣ ሆኖም በመኮንን ዘለለው የታፈነ)
  27. ወጣት ግፋባቸው ዳኛቸው፣
  28. አቶ ጌትየው ታምሬ፣
  29. አቶ ርስቀይ ኃይሌ፣
  30. አቶ ተድላ ርስቀይ፣
  31. ቄስ ትዛዙ ቀለመወርቅ፣
  32. ቄስ አለነ ቀለመወርቅ፣

በአጠቃላይ ከ1970 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሬ-ወያኔ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት እና በሠቲት ወረዳዎች ዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግድያ፣ አፈና እና ደብዛ ማጥፋት እጅግ ብዙ ትላልቅ ጥራዞች እንደሚሆን ይታመናል። ሆኖም ሞረሽ-ወገኔ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መካከል ለአብነት የሚከተለው ሠንጠረዥ በዝርዝር ቀርቧል።

 ሠንጠረዥ፦ በወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ላይ ወያኔ ግፍ የፈጸመባቸው ሰዎች በከፊል፣

ተራ ቁጥር ሙሉ ስም ተራ ቁጥር ሙሉ ስም ተራ ቁጥር ሙሉ ስም
1 አባቴ እሸቴ 2 አባው  ጠጅነህ 3 አበበ ይርጋ
4 አበራ ኃይሌ 5 አበጄ ክፍሌ 6 አበራ ዓለማዬሁ
7 አበራ ገብረመስቀል 8 አበራ አስረስ 9 አበራ ሐጎስ
10 አብርሃ አዳነ 11 አብርሃ አርጉ 12 አብርሃ ነጋ
13 አብራሃ በላይ 14 አቻምየለህ ሽታዬ 15 አቸናፊ ጽጌ
16 አዳነ ደረሰ 17 አዳነው ርስቴ 18 አዲስ አብተው
19 አዲሱ አበበ 20 አደበ ዓለም 21 አደራጀው ገብሬ
22 አዲስ ልጃለም 23 አላቸው ልጃለም 24 አላቸው ገብረመድኅን
25 አለባቸው ደፈርሻ 26 አለበል ይርጋ 27 አለኸኝ መሥፍን
28 አለማው ታረቀ 29 አለማይ ካሣ 30 ዓለሙ ጌታቸው
31 ዓለሙ ፈንታይ 32 ዓለሙ ለገሠ 33 አለነ ክንዲሽ
34 አማረ ፈንቴ 35 ዓለማየሁ አበጠለው 36 አንዶም ካሣ
37 አንገረብ ተሰማ 38 አረፈዓይኔ መኮንን 39 አረፈ በለጠ
40 አረፈ ግደይ 41 አረጋ ወልዴ 42 አረጋው አየነው
43 አስማረው ግደይ 44 አስማረው መለሰ 45 አጥናፈይ ዓለማየሁ
46 ዐወቀ ዘውዱ 47 አያሁነኝ ወንዶሻል 48 አያሌው ሰሙ
49 አያና ገብሬ 50 አየነው ሙሉ 51 አየነው ርስቴ
52 አየነው በየነ 53 ኣዛናው ቸሬ 54 ኣዛናው ይደግ
55 አዛናው ጽጌ 56 አዘነህ ልጃለም 57 ባሕታ ፈንታይ
58 ባሕታ መኩሪያ 59 ባሕታ ወንድምአገኝ 60 ባሕታ ረዳ
61 ባሕታ እርትብ 62 ባሕታ መንግሥቱ 63 ባየው ባሕታ
64 ባየው ቢያረግልኝ 65 ባየው ልጃለም 66 በዕዱ ወንድም አገኝ
67 በላይ ሙሉ 68 በላይ ታደሰ 69 በላይ መኮንን
70 በለጠ ዓለምመብራት 71 በለጠ ተስፋዬ 72 በልጤ ወንድም አገኝ
73 በራ የማነ 74 በራ ወልደሥላሴ 75 በርሄ ሐጎስ
76 በሪሁን ይርጋ 77 በሪሁን ይግዛው 78 ቻላቸው ታደለ
79 ጫሉ ይዘዘው 80 ጫኔ ይርጋ 81 ዳኜው ሢሣይ
82 ደቢል ዘነበ 83 ደቢል ተክለሃይማኖት 84 ደገፋ ጎኢቶም
85 ደሣለኝ ዋርካው 86 ደስታ ሠርጸ 87 ድራር ገሠሠው
88 እንዳልካቸው ጠጆ 89 እንደሻው ታፈረ 90 እንግተይ አየልኝ
91 እሪበይ ገብሩ 92 እሸቴ አያልነህ 93 እሸቱ መሥፍን
94 ፋንታዬ አየልኝ 95 ፋንቱ ሢሣይ 96 ፈለቀ ግርማይ
97 ፈረደ ዘራይ 98 ፈረደ ፍሉይ 99 ፈንቴ ዘነበ
100 ፈንቴ ገብራይ 101 ፍሬይ ተወልድ 102 ፍታለው ታፈረ
103 ገብረሕይዎት ባሕታ 104 ገብረሕይዎት ገዛኸኝ 105 ገብረማርያም አረፈዓይኔ
106 ገብረመድኅን ዘርፉ 107 ገብረመድኅን የኋላ 108 ገብረመስቀል ጥርፊነህ
109 ገብረስላሴ ረዳ 110 ገብሬ ሐጎስ 111 አስማረው አስረስ
112 አስማረው ወልዴ 113 አስፋው መንግስቴ 114 አስረስ ታከለ
115 አስፋው ወርቁ 116 አስገዶም ጥሩነህ 117 አሸናፊ ወንዱ
118 አስመላሽ ይገዙ 119 አታላይ አበራ 120 አታላይ አማረ
121 አታላይ ዘነበ 122 በሪሁን ደስታ 123 በየነ ፍሬይ
124 በየነ አየልኝ 125 ቢያድግልኝ ዘውዴ 126 ብላታ አብርሃ
127 ብርሃኔ ማሞ 128 ብርሃ ኑ ዳኛቸው 129 ብርሃኑ ሽታዬ
130 ጫቅሌ ገበየሁ 131 ቻላቸው ታደሰ 132 ቻላቸው አበራ
133 ገብረሕዎት ኃይሌ 134 ገረመው ዳኜ 135 ገሪማ ተኽሌ
136 ጌታቸው ተገኜ 137 ጌታቸው ብዙነህ 138 ጌታቸው ብዙነህ
139 ጌቴው ታምሬ 140 ጌቱ ጠለለው 141 ግደይ ማሙ
142 ግደይ ካሣ 143 ጊፍታቸው ዳኜው 144 ግንባይ ጌታሁን
145 ወልዴ የኔሁን 146 ግርማ ይደግ 147 ግርማ ትኩዕ
148 ግርማ ጥቄ 149 ጎኢቶም ምኅረት 150 ጎኢቶም ሐድጎ
151 ጎርፉ ገብሩ 152 ጎሹ አሰፋ 153 ጎሹ ትርፍነህ
154 ጉበን ፈያሃጸን 155 ጊዎይ መብርሃቱ 156 ጉዎይ አዳነ
157 ሀብቱ ይርጋ 158 ሀፍቴ ዘነበ 159 ሐጎስ ገብራይ
160 ሐጎስ መንግሥቱ 161 ሀጎስ ይስፋ 162 ኃይሉ ልዩነህ
163 ኃየሎም ይርጋ 164 ካሂሱ ንጉሡ 165 ካህሱ ጌታሁን
166 ካሳሁን ሲሣይ 167 ካሣ መብራት 168 ከሰተ ይርጋ
169 ካሡ ንጉሤ 170 ሢሣይ አበራ 171 ለማ ታደሰ
172 ክንፈ ከበደ 173 ክንፈ ናሁ 174 ልጃለም በላይ
175 ልዑል ገብረ መስቀል 176 ልጃለም ታዬ 177 ማለፊያ ጉዎይ
178 ሊላይ ሐድጎ 179 ሉሌ መሥፍን 180 ማማይ አብርሃ
181 ማሌ ዘነበ 182 ማማይ ረዳቴ 183 ማማይ ሙሉ
184 ማማይ በላይ 185 ማማይ አየልኝ 186 ማማይ በላይነህ
187 ማማይ ፈረደ 188 ማማይ አለዩ 189 ማሙ ዋርካው
190 ማሞ ደስታ 191 ማሞ ዘውዴ 192 ማሙነህ ይደግ
193 ማሙ ቸሬ 194 ማሙ ታደሰ 195 መሓሪ አዱኛ
196 መብርሃቱ ይግዛው 197 መብርሃቱ ገብረእግዚአብሔር 198 መኳንንት ዋርካው
199 መኮንን ለውጤ 200 መኮንን አበራ 201 መርዕድ ገብረሚካኤል
202 መኩሪያ ገብረማርያም 203 መንገሻ ሙሉጌታ 204 ሞላ ጠለለ
205 መሣፍንት ዳኜው 206 ምራጭ  ተሰማ 207 ሙሉዓለም ዋርካው
208 ልዕልቲ ወንድምአገኝ 209 ሙኮጠይ ታደሰ 210 ሙሉ አማረ
211 ሙላው ዞፌ 212 ሙሉ አታላይ 213 ሙሉነህ ደመወዜ
214 ሙሉ በርሄ 215 ሙሉ ገብረኪዳን 216 ነጋ ጌታሁን
217 ነጋ ተበጄ 218 ነጋ አስረስ 219 ነጋ በበል
220 ነጋ ምትኩ 221 ነጋ ሐጎስ 223 ንጉሡ አብርሃ
224 ንግሸት ሐድጎ 225 ንጉሤ ቀለመወርቅ 226 ረዳኢ ለማ
227 ፓስረት በለጠ ተስፋይ 228 ቁዊይ ተዘራ 229 ርስከይ ይልማ
230 ርስከይ ኃይሌ 231 ርስከይ ምንተስኖት 232 ሰረበ ረዳ
233 ርስከይ መለሰ 234 ሮስኬ ማንጆስ 235 ሸንቆ በለጠ
236 ሰጠኝ እንዳለው 237 ሰጠኝ ሽታዬ 238 ሽፈራው ንጉሤ
239 ሽፈራው ውብነህ 240 ሽፈራው ተስፋይ 241 ሺሙዬ አለሜይ
142 ሽሁን ኪዳኔ 243 ሺሙዬ ማሙ 244 ስማቸው ዓለሙ
245 ሺሙዬ ደምሰው 246 ስማቸው ማሙ 247 ታደሰ ከሽ
248 ሢሣይ ተስፋሁነኝ 249 ታደለ አባተ 250 ጣሌ ገብሬ
251 ታፈረ ሊላይ 252 ታገል ተድላ 253 ተበጄ በቀን
254 ጣሰው አሰፈ 255 ተበጄ መለሰ 256 ተካልኝ አበበ
257 ተገኜ ነጋ 258 ተገኜ ደምሴ 259 ተስፋ ፀጋዬ
260 ተካልኝ መንግሥቱ 261 ጤላ ኃይሌ 262 ተስፋይ መኮንን
163 ተስፋይ ኃይሉ 264 ተስፋ አብርሃ 265 ተሾመ ፈረደ
266 ተስፋይ አጽብሃ 267 ተሻገር ገብረመድኅን 268 ተሰማ ፍሬይ
269 ተሾመ ጠለለ 270 ተሰማ አብቅሃለሁ 271 ጥላሁን ታደሰ
272 ጥጋቡ መክንንት 273 ጥላሁን ተወልደ 274 ፀጋዬ አበበ
275 ጥሩነህ መብራቱ 276 ቶጋ ተገኜ 277 ጽይተይ አብርሃ
278 ፀጋዬ የኔሁን 279 ፀጉ ዘነበ 280 ወረታ ገብሩ
281 ዋኜው መንበሩ 282 ወግሃታይ መንበሩ 283 ወንድም ፍስሃ
284 ወልዴ የኢብዮ 285 ወልዴ የኔሁን 286 ወንድምአገኘሁ ታረቀኝ
287 ወንድም ጠለለ 288 ወንድም ጠጋ 289 የኋላሸት ዘለቀ
290 ወርቅየ ገብረመድኅን 291 ወርቅነህ አታላይ 292 ይዘዘው ገብረመስቀል
293 የሻለም በሪሁን 294 የሻለም ጽጌ 295 ይደግ አያሌው
296 ይበይን ገብረእግዚአብሄር 297 ይደግ አየነው 298 ይስፋ ፋንታይ
299 ይላቅ ተዘራ 300 ይርጋ ደምሰው 301 ዘሩ በላይ
302 ዘለቀ ግርማይ 303 ዘራይ መርሻ 304 ዘውዱ መርሻ
305 ዘውዴ ሢሣይ 306 ዘውዱ ሺበሽ 307 ዘሩ መርሻ

ይህ እንግዲህ በግልጽ መረጃ የተገኘላቸው ናቸው። ዛሬ በእነዚህ ወረዳዎች የእህት ልጅ እንጂ፣ የወንድም ልጅ የሚባል አለመኖሩ የትግሬ-ወያኔ ወንዱን አንድም አስሮ መግደሉን፣ ሁለትም በገፍ ማሰደዱን የሚያመለክት ነው። የትግሬ-ወያኔ በድብቅ አስሮ የገደላቸው ቤታቸው ይቁጠራቸው። የእነዚህ ወገኖቻችን ደም ይጣራል።

ሰሞኑን የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሠቲት እና የአርማጭሆ የዐማራ ነገድ ተወላጆች፣ የትግሬ-ወያኔ ራሱ «ሠራሁት፣ የኢትዮጵያን ብሔር፣ ብሔረሰቦች ዕኩል አደርኩ» እያለ በሚደሰኩርበት እና በያመቱ «የብሔረሰቦች ዕኩልነት ቀን» እያለ ገንዘብ የሚያጋብስበትን ሕገመንግሥት ተብየ የሚለውን የማንነት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ከጀመሩ ጊዜ ወዲህ 116(አንድ መቶ አሥራ ስድስት) የወልቃይት-ጠገዴ ሰዎች በወያኔ ታፍነው የደረሱበት አለመታወቁ ታውቋል። በተለያዩ ጊዜዎች የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍራረስ፣ ዐማራን ፈጽሞ ለማጥፋት እና ለማጽዳት ላቀድነው ዕቅድ አስቸጋሪ ይሆናሉ ብለው የገመቷቸውን የወልቃይት-ጠገዴ ተወላጆች እያፈኑ ወደ ሱዳን እንደሚወስዷቸው እና የደረሱበት የማይታወቁት ቁጥር እጅግ በርካታ እንደሆነ ከአካባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ወያኔ በጠበንጃ አፈሙዝ ወደ ትግራይ በከለላቸው ወረዳዎች በአማርኛ መማር ከመከልከሉም በላይ፣ ቋንቋውን መናገር እንደወንጀል ተቆጥሮ አማርኛ የሚናገሩ ሰዎች ግፍ እንደሚፈጸምባቸው ለማወቅ ተችሏል። በትግርኛ ትምህርት ሲሰጥ፣ «ኀ፣ ሠ፤ እና ፀ» የተሰኙት ፊደሎች የአማርኛ ድምፅ ወኪሎች በመሆናቸው፣ ፊደሎቹ ራሳቸው እንደዐማራ የተጠሉ መሆኑን በአካባቢው ስለጉዳዩ ጥናት ያደረጉ ቡድኖች እና ግለሰቦች ያስረዳሉ። በወልቃይት-ጠገዴ አማርኛ መናገር የሚያዘውትሩትን ሰዎች «የኢሕአፓ ቅሬቶች» የሚል መጠሪያም እንደሰጡዋቸው እና ምናምን እንደያዘው ሰው በመቁጠር በመጠየፍ እና በመናቅ እንደሚያንቋሽሿቸው ታውቋል።

ከላይ ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ወደ ትግራይ ባጠቃለሉዋቸው ወረዳዎች ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን ገድለው፣ አስረው እና አሰድደው በቦታው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺ) በላይ ትግሬዎች አስፍረውበታል። ከሁሉም በላይ ዳንሻ ላይ እንዲሰፍሩ የተደረጉት የትግሬ-ወያኔ ተዋጊዎች የነበሩ 30,000(ሰላሳ ሺ) ወታሮች መሆናቸውን ስናስብ፣ ወያኔ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ለሚነሳ የማንነት ጥያቄ በቶሎ አፍነው ለመጨፍለቅ ያለውን ቅድመ ዝግጅት አመልካች ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ላይ ያለው «የጥቁር አፓርታይድ» ጥላቻ ከሚገለጽባቸው መልኮቹ አንዱ አዘውትረው ለወልቃይት-ጠገዴ ነዋሪዎች የሚሉት ቃል ነው። ይኸውም፦ «እኛ ወልቃይት-ጠገዴን መሬቱን እንጂ፣ ሰውን አንፈልገውም» የሚሉት ነው። በዚህ አቋማቸውም በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጅምላ የዘር ፍጅት ፈጽመውበታል።

ከሁሉም በላይ በወልቃይት-ጠገዴ ዐማሮች ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ ቡድን ከሚፈጽማቸው ዘግናኝ ግፎች፣ ለአቅመ-ሔዋን ያልደረሱ ሴት የዐማራ ሕፃናት ተማሪዎችን ዘወትር የትግሬ መምህራኖችን ቤት በተራ እንዲያጸዱ የሚል ትዕዛዝ በመስጠት፣ ይህን ትዕዛዝ አክብረው የሚሄዱትን ሴት ሕፃናት መምህራኖቹ በመድፈር አሳዳጊ የሌላቸው ልጆች እንዲወለዱ፤ ሴቶቹም ከትምህርት ገበታ እንዲያቋርጡ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። ይህ ድርጊት የትግሬውን ቁጥር ለማበራከት እና የነዋሪውን ሥብጥር ትግሬ-ጠቀም ለማድረግ ከሚሠራው ሤራ አንዱ ክፍል እንደሆነ ግልፅ ነው።

በአጠቃላይ፣ በወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ ላይ ላለፉት 36(ሰላሣ) ዓመታት የትግሬ-ወያኔ የፈጸመው ግፍ እና መከራ በዐማራው ላይ የተፈጸመ የዘር ጥቃት በመሆኑ፣ የዐማራው ነገድ ብቻ ሳይሆን፣ ለሰብአዊነት የሚቆረቆር ማናቸውም ሰው ከወልቃይት-ጠገዴ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ጎን ሊቆም ይገባዋል። ዛሬ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት እና በአርማጭሆ ያሉ ወገኖቻችን የጀመሩት «ማንነታችን ይከበር» ጥያቄ ወያኔ ባቀደው መልኩ በድፍጠጣ የሚዳፈን ከሆነ፣ ነገ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የቀሪው ጎንደር ነዋሪ፣ በአጠቃላይ የዐማራው ነገድ በተናጠል እንዲመታ መንገድ መክፈት እና ድርጊቱ እንዲፈጸም በለሆስታ ፈቃድ መስጠት እንደሆነ ስለሚቆጠር፣ የዐማራው ነገድ በያለበት ከወገኖቻችን ጎን ልንቆም ይገባል።

ይህን በተመለከተ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ከአገር ውጭ የሚኖረው የዐማራው ነገድ ለወልቃይት-ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ተገቢ የሆነ መልስ እንዲያገኝ፣ ጥያቄ ያነሱት ወገኖች ለሚያስፈልጋቸው የገንዘብ፣ የቁሳቁስ እና የመረጃ ድጋፍ በተቀናጀ መንገድ መስጠት እንዲቻል አጠቃላይ የስልክ ስብሰባ ለማድረግ አቅዷል። የስብሰባው ቀን እና ጊዜ ወደፊት በማስታወቂያ ስለሚገለጽ፣ ሁሉም የዐማራ ልጅ በስብሰባው በመገኘት ለወገኖቻችን የምንችለውን በማድረግ አጋርነታችንን እንድናሳያቸው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በአክብሮት ይጋብዛል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ-ማንነት ጥያቄ በተባበረ ትግላችን ይመለሳል!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

<!–

–>


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles