ወንድም ተስፋሁን አለምነህ በተመለከተ ብዙ አስተያየቶች ደርዉኛል። አንድ አንድ ወገኖች ለምን እንደሚንጨረጨሩ ግን አይገባኝም። ዜጎችን እኮ አስተያየት መስጠት፣ ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ። መብቱ አላቸው። አትናገሩ፣ አትጻፉ፣ አትተንፍሱ የማለት አባዜ ካለብን አንደኛውኑ የጌታቸው አሰፋን የወያኔ ደህንነት ሄደን እንቀላቀል።
እኛ ጥያቄ ነው ያቀረብነው። ተስፋሁን በሕይወት ካለ እሰየው ነው። ያድርገው። “የት ነው ያለው?” ብለን ስንጠይቅ “ተገድሉዋል ተብሎ የተወራው ውሽት ነው። ይኸው መረጃ” ብሉ የሚነግረን ካገኘን ፈረንጆች እንደሚለት case closed ነው። ይሄ አንዱ ነጥብ ነው። (በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ የደረሰኝ መልእክት ወደ ኋላ አካፍላቹሃለሁ)
ሌላው ኢሳት ቅራቅንቦ አያቀርብም ያሉም አሉ። ስለ ኢሳት ያነሳነው ኢሳት ተስፋሁን ኤርትራ ሲገባ ቃለ መጠይቅ ስላደረጉለት ነው። ያኔ ቅራቅንቦ ነው ብለው ዝም አላሉም። ታደያ። “በሻቢያ ተገደለ” የሚል ወሬ ሲወራ፣ ምን አልባት በሌላ ሃይል ተፅኖ ውስጥ ካልሆኑ በስተቀር፣ እንደ ጋዜጠኞች ማጣራት የለባቸውምን ? እኔ አለባቸው ባይ ነኝ። ያደርጉታልም ብዬ አምናለሁ። ለምን በግለሰብ ደረጃ ብዙዋች የኢሳት ጋዜጠኞች አንቴግሪቲ ያላቸው ፕሮፌሽናል ጋዜጠኞች ናቸው ብዬ ስለማምን። በተለለይም ደግማ ተስፋሁን በሕይወት ካለ በቅርቡ ያቀርቡታል ብዬ እጠብቃለሁ። ይሄ ሁለተኛ ነጥብ ነው።
ሶስተኛ “ተስፋሁን ቢሞትስ ? ሊሞት አይደለም ወይ ኤርትራ የሄደው። ስንቱስ በወያኔ እጅ እየረገፈ አይደለም ወይ ?” የሚሉ heartless እና ለስብእና ክብር የሌለው አስተያየት የሰጡ አሉ። እነዚህ ግለሰቦች ለስሙ ከተቃዋሚ ጎራ ነን ይላሉ እንጂ በሁሉ ነገራቸው እዚያ ማ እከላዊ ካኡ ቶርቸር አድራጊዎች በምንም የማይለዩ ናቸው።
ተስፋሁን በጦርነት ላይ ቢሞት ለምን ሞተ አንልም። አንድ ሰው ጦርነትን ከመረጠ ሞት እንደሚጠብቀው ያውቃል። ነገር ግን አንድ ሰው ዝም ብሎ ቢሰወርና የሄደበትን አላማ ሳይጨርስ፣ ውጊያ ሳያደርግ ተገደለ ቢባል ያ በጣም የተለየ ነገር ነው። በተለይም ለመታገል ብለው ኤርትራ ሄደው የተገደሉ ፣ እንደ ኮሌኔል ታደሰ ያሉትን ስናስብ ፣ ጥያቄው ከአንድ ግለሰብ ያለፈ፣ መሰረታዊ የስትራቴጂና የደህንነትን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው የሚሆነው።
ተስፋሁንን ብዙ ሰው ስለሚያውቀው ነው። በዚህ ሁኔታ ለትግል ብለው የሄዱ እጅግ በጣም ብዙዎች እርምጃ ተወስዶባቸው የተሰወሩ ይኖራሉ ማለት ነው። እና እየተያያዙ የሚነሱ ብዙ ጥያቄዎች ይኖራሉ።
እና።ወገኖች ይህ ጉዳይ በተስፋሁን ምክንያት አነሳነው እንጅ፣ በኤርትራ ያሉትን ሁሉ ወንድሞችና እህቶች ደህንነት የሚመለከት ነው። በዚያ ያለ የአንድ ውጣት ሕይወት እዚያ መሪ ነን ከሚሉ ያነሰም ወይም የከበረም አይደለም።የሁሉም ሕይወት ክብር ነው።
ይሄን ብዬ በዉስጥ መስመር የደረሰኝ አንድ “አስደሳች”፡ ዜና ላካፍላችሁ። በቅንፍ ያደረኩት ለማረጋገጥ ስላልቻልኩ ነው። ከታመነ ምንጭ የደረሰን ነው በሚል ፣ ተስፋሁን በወታደራዊ ስልጠና እየወሰደ እንደሆነ፣ በዚያም ኔትዎርክ እንደሌለና ስልጠናዉን እንደጨረሰ ቃለ መጠይቆች እንደሚያደረግ የሚገልጽ መልእክት በዉስጥ መስመር ደረሰኝ። እንግዲህ “እዉነት ያድርገው” ብዬ እዘጋለሁ።
The post ተስፋሁን አለምነህን በተመለከተ – ግርማ ካሳ appeared first on ሳተናው .