Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

እርሃብ ለምን ይከሰታል?እንዴትስ ይወገዳል? ለውይይት የቀረበ – አገሬ አዲስ

$
0
0

the image of Hunger in Ethiopiaየሰው ልጅ እህል በልቶና ንጹህ ውሃ ጠጥቶ ጠግቦ ማደር፣ ለመኖሪያውም እንደ አቅሙ ጎጆ ቀልሶ፣ጤናውም ተጠብቆ በሰላም መኖር ዋናው መሰረታዊ ሰብአዊ መብቱ ነው።የመንግሥትም አስፈላጊነት እነዚህን ለማሟላት ነው። እነዚህን ማሟላት የማይችል መንግሥት በስልጣን ላይ መቀመጥ አይገባውም።

በአገራችን ታሪክ ውስጥ ተደጋግሞ የተከሰተው ችግር ቢኖር አንዱና ዋናው እርሃብ ነው። ከአጼ ምንሊክ ወዲህ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት ብቻ ብንመለከት በተከታታይ ደርሶ የብዙ ሕዝብ ህይወት ቀስፏል።ታላቁ እርሃብ በመባል የታወቀው የተከሰተው በአጼ ምንሊክ ጊዜ ነበር።ይህ የእራብ መቅሰፍት እናት ልጇን የበላችበት ዘግናኝ ክስተት ጥሎ አልፏል።በዚህም አንዲት እናት ልጇን በልታለች ተብላ ተይዛ በንጉሱ ችሎት ላይ በቀረበቸበት ጊዜ ንጉሱ አጼ ምኒልክ ስቅስቅ ብለው አልቅሰው፣ “ምነው አምላኬ በእኔ አገዛዝ ላይ ይህን አይነቱን ቅጣት አወረድክበት” በማለት ለፍርድ የቀረበችውን ሴት “አንድ ጊዜ በራሷ ላይ ፈርዳለች፤ልጇን ከማጣት በላይ ቅጣት አይገባትም ብለው በነጻ እንደለቀቋት ታሪክ ይመሰክራል።

በእኛ ዕድሜ ከሃምሳ ዓመት ወዲህም በተደጋጋሚ እርሃብ ተከስቶ ይባስ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ አንዱና ዋናው፣ከማራቶን እሩጫ ውድድር ጎን የምንታወቅበትና በሃፍረት አንገታችንን የምንሰብርበት ብሄራዊ ገጽ ሆኗል።

ለርሃብ አንዱ ምክንያት የድርቅ መከሰት ቢሆንም ብቸኛ ምክንያት አይደለም።ሌሎች ብዙ ምክንያቶች አሉት።በሀይለኛ ዝናብ፣ ጎርፍና በረዶ ቡቃያ ሲመታና ሲረግፍ፣በተምችና አንበጣ ወረራ ቡቃያ ከወደመ የምግብ እጥረት ይከሰትና ሕዝቡ ሊራብ ይችላል።እርግጥ ነው ዝናብ ጠብቆ ለሚያርስ ገበሬ ከማረሱ በፊት ወይም ካረሰ በዃላ ውሃ በሚያስፈልግበት ወቅት ድርቅ ቢከሰት የገበሬው ጎተራ ባዶ ሆኖ አምራቹና ቤተሰቡ ለእርሃብ ይጋለጣል።ይህን በድርቅ ምክንያት ሊመጣ የሚችለውን እርሃብ ግን ገና ሳይከሰት መቋቋም ይቻላል።በዝናብ ምክንያት እርሃብ እንዳይከሰት ቀደም ሲል የመስኖ መስመር ቢዘረጋ፣በጥሩ የመኸር ወቅት ከሚመረተው ቀንሶ ለክፉ ቀን የሚሆን በጎተራ ቢቀመጥ የመጣውን  እርሃብ ለማሶገድ ይቻላል።ድርቅ ባልሆነበት በሌላ ከባቢ ያለው ሕዝብ የሚያመርተውን ለማካፈል ፍላጎትና ፈቃደኝነት ቢኖረውና ቢያካፍል ወይም መንግስት ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር እየገዛ ለማዳረስ ሁኔታዎች ቢመቻቹ አርሃቡን  ለጊዜው መቋቋም ይቻላል።ለዘለቄታው ግን መፍትሔ ሊሆን ስለማይችል መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊ ነው።ድርቅ በኢትዮጵያ ብቻ የሚከሰት የተፈጥሮ አደጋ አይደለም።በሌሎቹም አገሮች በተደጋጋሚ የታዬና የደረሰ አደጋ ነው። በሃብትና በስልጣኔ ደረጃ ቀዳሚውን ቦታ በያዘችው በአሜሪካ  ሳይቀር በመካከለኛውና በምዕራብ ደቡቡ ክፍል በተደጋጋሚ ጊዜ ድርቅ ተከስቶ ምርት አልባ የተሆነበት ጊዜ ነበር፣አሁንም አለ ወደፊትም ይኖራል፤ግን በከባቢው የሚኖረው ሕዝብ አልተራበም።በሌሎቹም አገራት እንዲሁ በየጊዜው ድርቅ ተከስቶ ሕዝቡ ሳይራብና ለልመና ሳይወጣ  ጊዜያዊ ችግሩን ሊወጣ ችሏል፤ ለእርሻ ያልታደሉት በረሃማ አገሮችም ሳያመርቱ ጠግቦ የሚያድር ሕዝብ የሚኖርባቸው ብዙዎች ናቸው።በሌላው ድርቅ በመታቸው አገሮች ከሌላው ከባቢ የሚመረተው ምርት በስፋትና በፍጥነት እንዲደርስ  በመንግስት ቅድመ ዝግጅትና የተመቻቸ ሁኔታ በመኖሩ፣ከአገር ውስጥ ፍጆታ ተርፎ ለውጭ ሽያጭ ከመለቀቁ በፊት የተወሰነ ምርት ለክፉ ቀን  በጎተራ ተከማችቶ በመቀመጡ፣የእርሻው ተግባር በዘመናዊ መሳሪያና እውቀት የተደገፈና የሚንቀሳቀስ በመሆኑ፣ አምራቹ በተበጣጠሰ መሬት ላይ ከማምረት ይልቅ ሰብሰብ ባለ መልኩ ተደራጅቶ በህብረት (በኮፐሬቲቭና ኮርፖሬሽን)እውቀትና ጉልበቱን አስተባብሮ በመስራቱ፣የመገናኛ ና የመጓጓዣ መስመሮችና መንገዶች በሰፊው በመዘርጋታቸው፣የገጠርና ከተማው ልዩነት በመጥበቡ፣ የሕዝብ የመረዳዳትና ያለው ለሌለው አካፍሎ የመብላት ባህል ፣የብሔራዊ ስሜት መኖሩና መንግስትም አላፊነትና ተጠያቂነቱን በተግባር በመግለጹ እርሃብን ለማሶገድ ሲችሉ ለሌላውም አገር ለመትረፍ በቅተዋል።

አላፊነት በጎደለውና መልካም አስተዳደር ባልሰፈነባቸው አገሮች ቀድሞ መሟላት የነበረባቸው መሰረታዊ ተቋማት ባለመኖራቸው የሚደርሰው ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ጊዜያዊም ሆነ ነባር ችግር ሳይወገድ ሕዝብ ለርሃብና ከዚያም ጋር ለተያያዘ የበሽታ አደጋ ይጋለጣል።ኢትዮጵያንም በተደጋጋሚ የሚገጥማት የርሃብም ሆነ ድህነት ዋና ምንጩ  የመልካም አስተዳደር ድህነት፣በጉልበት ስልጣን ላይ እየወጡ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚጨነቁ “ከራስ በላይ ንፋስ”በሚል መርሆ የሚመሩ አምባገነኖች ለሕዝቡ መሰረታዊ ለውጥ ሳያመጡ ወይም ለማምጣት ለሚችል ሕዝባዊ ስርዓት ዕድሉን ሳይሰጡ በስልጣን ላይ የሙጥኝ ብለው  ለመቆየት እርሃብን እንደመሳሪያና የገቢ ምንጭ አድረገው በመጠቀምና ከውጭ የሚገኘውን እርዳታ ለስልጣን ማቆያ የስለላ መረብና ለመከላከያ ወጭ  በመጠቀማቸው ነው።

ድርቅና ሌላ የተፈጥሮ አደጋ ሳይከሰት ሰላምና መረጋጋት ባልሰፈነበት ቦታም እርሃብ እንደሚከሰት ተደጋግሞ ታይቷል።በጦርነትና በግጭት ምክንያት ሕዝብ በሰላም ሰርቶ የማደር ዕድሉ ሲመነምንና  በተለይም አርሶ አደሩ ለማረስ የሚችልበት ሁኔታ ሲጠፋ፣በፈለገበት የአገሩ መሬት ላይ ሰርቶ የማደር መብቱን ሲገፈፍ ሕዝብ ለርሃብ ይጋለጣል።ይህም በተለያዩ ጊዜያት በእኛም ሆነ በተለያዩ አገሮች ታይቷል፤አሁንም በጊዜያችን እየታየ ነው።

ከዛሬ አምሳ ዓመት ወዲህ ያለውን ብንመለከት በተለይም በ1964-65 ዓ.ም. እ.ኢ.አ. በድርቅና በአስተዳደር ጉድለት በተከሰተ እርሃብ ወቅት ምንም እንኳን የርሃቡን አደጋ ለማሶገድ የሚበቃ ገንዘብ ባይሆንም የንጉሱን የሰማንያ ዓመት ልደታቸውን ለማክበር  ሲባል ምንም እንኳን ችግሩን ለማሶገድ የሚበቃ ባይሆንም በከተማዎች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች የኤሌክትሪክ መብራቶች በልዩ ልዩ ህብረቀለም ባላቸው አምፖሎች በማሸብረቅ ብዙ ገንዘብ እንደወጣ፣ይህም ብቻ አይደለም የንጉሱንና የስርዓቱን ገጽ ያጎድፋል በማለት በርሃብ ምክንያት ከባቢያቸውን ለቀው የተሰደዱ የትግራይና የወሎ ተወላጆች አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ ከርቀት ድንበር ላይ መታገዳቸውን የሚያስታውሱ ብዙዎች ናቸው።እዚህ ላይ የንጉሰ ነገስቱ የልደት በዓል ለምን ይከበራል ለማለት ሳይሆን በዚያ ወቅት ትክክል አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።በምዕራቦቹ አገሮች በተለይም በእንግሊዝና በኔዘርላንድ የንግስቲቱ ወይም የንጉሱ የልደት ቀን  ብሔራዊ በዓል ሆኖ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።የእኛም ነገሥታቶች የደላው ሕዝብ የሚኖርበት ስርዓት ባለቤቶች ቢሆኑ ኖሮ ሕዝቡ በደስታ ቢያከብረው የሚነቀፍ አይሆንም ነበር።ይህንንም ተከትሎ ነው የየካቲቱ 1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የተከሰተው።ይህን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ  ተገን በማድረግ ስልጣን ላይ የተቆናጠጠው የወታደር አምባገነን ቡድን  የሕዝቡን ተቃውሞ ጠምዝዞ፣እራብ ሳያሶግድ በ1976-77 ዓ.ም. የባሰ እርሃብ እንዲከሰት ከማድረጉም በላይ ሕዝብ በድምጽ አልባው እርሃብ ሲረፈረፍ ዓይኔን ግንባር ያድርገው በማለት ከውጭ አገር የተገኘውን እርዳታ ሳይቀር  ለአስረኛ ዓመት የስልጣን ዘመኑ አከባበር  ብዙ ሚሊዮን ብር በማውጣት ከውጭ አገር ውስኪና ኮኛክ በማስመጣት አስረሽ ምችው ድግስና ፌስታ ማካሄዱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።ይህም ብቻ አይደለም ለእርዳታ በተላከው እህል ላይ የወደብ አገልግሎትና ቀረጥ በመጣል የመንግሥት የገቢ ምንጭ አድርጎ ተጠቅሞበታል፤የውጭ ሃይሎችም በእርዳታ ስም ጸረ ሶሻሊስት የፖለቲካ ስራቸውን ለመስራት ተጠቅመውበታል።አሁን በስልጣን ላይ ያለውም የህወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ካለፉት ስርዓቶች በተሻለ መንገድ የርሃብ አደጋውን ሲቋቋም አልታየም፤እንደውም በማባባሱ የአንበሳ ድርሻውን ይዟል።ድርቅ ታይቶ ተሰምቶ በማያውቅባቸው የደቡብ ክልሎች ሳይቀር እርሃብ የብዙ ዜጎችን ህይወት እየቀሰፈ ነው።ገና ጫካ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ከውጭ አገር  ለተራበው ሕዝብ የሚገኘውን እርዳታ እየቸበቸበ ለትጥቅ ትግሉና ለመሪዎቹ በሚጠቅመው መንገድ ተጠቅሞበታል፤በልዩ ልዩ ስም ላቋቋማቸው ኩባንያዎች የካፒታል ተፋሰስ አውሎታል። ስልጣንም ላይ ከወጣ ጀምሮ በሆነው ባልሆነው የድርጅት መታሰቢያ ዝግጅቶችና ድግሶች በሚሊዮን የሚቆጠር ወጭ እያወጣ ዳነኪራ ይረግጣል።በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከፍተኛ እርሃብ ሰፍኖ ብዙ ሕዝብ በማለቅ ላይ ባለበት ጊዜ  ለባለስልጣኖቹ በብዙ ሚሊዮን ብር ወጭ የተንጣለለ ቪላ እየገነባ በአገር ውስጥ  እርሃብ መኖሩን የሚያጋልጡትን ልሳን ከመዝጋት አልፎ  የውጭ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ለመቆጣጠር ሕግ አውጥቷል።በጣም የሚገርመው ነገር ግን ባለስላጣናቱ እርሃብ የለም እያሉ በለፈፉበት አፋቸው ውሎ ሳያድር ለተከሰተው ድርቅ እርዳታ አምጡ እያሉ መወትወታቸው ነው።በሁለት አሃዝ  የሚታይ እድገት አምጥተናል እያሉ   እርሃብና ቸነፈር መኖሩ  በውጭ አገር በመሰማቱ ሳይወዱ በግድ ለማመን ተገደዋል። እርሃቡ ግን ከማንኛውም ጊዜ የበለጠ እንደሆነ ይነገርለታል።

ኢትዮጵያን የሚያህል ፣ በዓመት ሶስት ጊዜ ሊመረትባት የምትችል በውሃ፣በአየርና በለም መሬት የታደለች አገር ሕዝብ ለምን ተራበ ? ብለን ብንጠይቅ ምናልባት መልስና መፍትሔ ለማግኘት ወደ ምንችልበት አቅጣጫ ሊመራን ይችላል።

በአገራችን ያለውን ሁኔታ ስንመረምር ለርሃቡ አስተዋጽኦ ያደረጉት ዋናዋና ምክንያቶች

  1. በተደጋጋሚ የሚከሰተው የተፈጥሮ ድርቅ፤

ይህ ለእርሃብ አስተዋጽኦ ማድረጉ ባይካድም ከላይ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ቅድመ ዝግጅት ቢደረግ አደጋው ሊቀለበስ  ይችላል።ድርቅ ለርሃብ አንዱ ምክንያት ቢሆንም ሳይራቡ ሊቋቋሙት የሚችሉት የተፈጥሮ አደጋ ነው።ወቅታዊና ቋሚ የሆኑ ወንዞችን በመገደብና በመስኖ በማከፋፈል በዝናብ ላይ የተንጠለጠለውን የእርሻ አካባቢ በዘላቂነት ምርታማ ማድረግ ይቻላል። እርግጥ ነው   የዝናብ እጥረት ከተከሰተ ወንዝና ጅረትም መጠኑ ሊቀንስ ይችላል።ለዚያም ቢሆን ብልሃት አይጠፋለትም፤የግድብና የማቆር ስራ ለዚህ አይነቱ ችግር መፍትሔ ይሆናል።በተጨማሪም የውሃ አጠቃቀምን ብልሃትና የቁጠባ ጥበብ (the art of water management)መከተል ሊከሰት የሚችለውን የውሃ እጥረት ሊቀለብሰው ይችላል።

ድርቅ ሲከሰት በሌሎች አገሮች የተከናወነውና በእኛም አገር የተካሄደው ሕዝብ የማስፈር እርምጃ በመሰረቱ ትክክለኛና ተገቢ ነው።የሚወቀስበት ነገር ቢኖር ሕዝብ ከኖረበት አካባቢ ተነስቶ ወደ ሌላው አካባቢ ሄዶ እንዲሰፍር ከመደረጉ በፊት የስነ ልቦና ዝግጅት አለመደረጉ፣የመኖሪያ ቤት፣የሕክምና፣ የትምህርት ቤትና የመሳሰሉት አስፈላጊ ተቋማት አለመሟላታቸው፣ከኗሪው ሕዝብ ጋር ግጭትና ቅራኔ እንዳይፈጠር በቅድሚያ ዝግጅትና ግንዛቤ እንዲኖር አለመደረጉ ነው።ከአንዱ ቦታ ለቆ ሌላ ቦታ መኖር ለሰው ልጅ እንግዳ ነገር አይሆንም።ዜጋ በፈለገበት የአገሩ መሬት ላይ መስፈርና መኖር መብቱ ሲሆን  የሚሰፍርበትን ከባቢ ሰላም፣ባህልና ወግ የማክበርም ግዴታ አለበት።

ለድርቅ  የተፈጥሮ አየር ለውጥ ወይም መዛባት(climate change )መሆኑ ባይካድም ለመባባሱ  አንዱ ምክንያት የከባቢን ተፈጥሮ አለመንከባከብ፣ደንና የጫካ ሃብትን መመንጠሩና ማውደሙ ነው። በማገዶና በቤት ስራ የሚወድመው ዛፍ፣ጫካና ደን ካልተጠበቀ፣አንድ ዛፍ ሲቆርጡ ሁለት የመትከሉ ልማድ ካልተለመደ፣መሬቱ ለጎርፍና ለከፍተኛ ሃሩር ይጋለጥና  የቋያ እሳት እንደሚነሳ፣የከባቢ ድርቀት እንደሚያስከትል የተረጋገጠ ነው።ስለሆነም ለቤት ስራና ለማገዶ የሚሆን አማራጭ መንገድ መለመድ አለበት። ሌላውም አገር ከባቢን ከሚበክሉ የሃይል ምንጮች እየተላቀቀ ለመሄድ ከጸሃይና ከነፋስ አማራጭ የሃይል ምንጮችን  እያጎለበተ ይገኛል። በዚህ ዘርፍ ብዙ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ስላሉ እውቀታቸውን አስተባብረው የአገራቸውን የተፈጥሮ ሃብት (ውሃ፣ንፋስ ጸሃይ ..ወዘተ)ጥቅም ላይ በሚውሉበት መልኩ የሚሰሩበት መንገድ ቢፈጥሩ የዜግነት ግዴታቸውን ከመወጣትም በላይ ጠቅመው ሊጠቀሙ ይችላሉ። “ፍላጎት ካለ መንገድ አለ”!!ድል የማይመቱት ችግርና ፈተና የለም!!

  1. በአገር ውስጥ ገበያ ለሕዝብ ፍጆታ(ኮንዘምሽን)ለሚውሉ ምርቶች ቅድሚያ ከመስጠትና ከማሳደግ ይልቅ ለውጭ አገር ገበያና ለፋብሪካ ፍጆታ ለሚቀርቡ የእርሻ ውጤቶች ቅድሚያና ትኩረት መስጠት፣አንዱ የርሃብ ምክንያት ይሆናል።

በዚህ የተነሳ የአገር ገበያ በመራቆቱና  የዋጋ ግሽበት በመፈጠሩ አብዛኛው ሕዝብ  ሸምቶ ከማይበላበት ደረጃ ላይ ይደርሳል።የበይ ተመልካች  ይሆናል። ለርሃብና ለልመና ይጋለጣል።  ቅድሚያ ለአገር ውስጥ ጥቃሞት ለሚሆን ምርት ቢሰጠው እርሃብ በቀላሉ የሚወገድ ችግር ነው።

3.ለክፉ ቀን ቅድሚያ ዝግጅት ማድረግ፣

በደህና የምርት ወቅት ከሚሰበሰበው የተወሰነውን ለክፉ ቀን መጠባበቂያ በጎተራ በማስቀመጥ ወይም ድርቅ ካልደረሰበት አካባቢ የሚመረተውን ለማካፈል የሚያስችል ሕዝባዊ ትብብርና ፈቃደኝነት(ሶሊዳሪቲ)መኖርና ማሳየት፣ብቃት ያለው የመንግስትና ህዝባዊ ተቋም መኖር፣የመገናኛ መስመርና መንገዶችን መዘርጋትና ማመቻቸት።ችግሩን ለማሶገድ ይረዳል።ከልመናም ያድናል። “ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ” አይሆንም።

  1. በአገራችን ያለውን የመሬት ይዞታ በማስተካከል ባለቤትነትን ማረጋገጥ፣

ይህ ብቻውን ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ሊቀርፈው አይችልም፤በግል በተያዘ መሬት ላይ የውሃ እጥረት አይደርስም፣ድርቅ አይመጣም ማለት ሳይሆን  የገበሬውን ተነሳሽነት ሊያጎለብተው ስለሚችል አንድ እርምጃ ወደፊት ይሆናል፤ለዘለቄታው ግን ለርሃብ አደጋ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው አራሹ በተበጣጠሰ ቁራሽ መሬት ላይ በተናጠል በዶማና አንካሴ ቆፍሮ  ወይም በከሳ በሬ አርሶ የሚያመርተው በቁናና በአቅማዳ የሚለካ የተወሰነ ምርት ሳይሆን በከባቢ ሰፋፊ የእርሻ ልማቶችን በማቋቋም፣በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ ሲደገፍና ብዙ ምርት ማምረት ሲቻል ነው።በተለምዶ የእርሻ ዘዴና መሳሪያ የሚመረተው አነስተኛ ምርት እንኳንስ ለጠቅላላው ሕዝብ ቀርቶ ለባለብዙ ቤተሰብ ለሆነ አርሶ አደር የምግብ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም። የእርሻ መሳሪያዎችንና የምርት አይነቶችን መቀየር በተለይም ብዙ ውሃ የማያስፈልጋቸውን የእህል ዘሮች መልመድና ማራባት አንዱ መፍትሔ ሊሆን ይችላል። በጥቂት ውሃ ብዙ ምርት ማምረት እንደሚቻልም በተግባር ታይቷል።ይህንን በሚመለከት ከዚህ ጽሁፉ ቀጥሎ  ከገጽ ዘጠኝ በዃላ የቀረበውን በስዕል የተደገፈ የጥናት ዘገባ መመልከቱ ይበልጥ ግንዛቤ ይሰጣል።

የገጠሩ ነዋሪ በእርሻ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኤኮኖሚ ዘርፎች እንዲሳተፍ፣ብቃትና እውቀት እንዲኖረው በገጠሩ የትራንስፎርሜሽን ሂደት  ማድረግ በእርሻ ላይ ብቻ የተንጠለጠለውን ሕይወትና ኑሮ ሊቀይረው ይችላል።በደቃቃ መልክ የሚንቀሳቀሰው የእርሻው ስራ በከፍተኛና በተደራጀ መልክ ቢስፋፋ ጎን ለጎንም የምግብ ዝግጅት የሚያከናውኑ ኢንዱስተሪዎች ቢቋቋሙ፣ገበሬው የኢንዱስትሪ ሰራተኛ በመሆን ከአዲስ ቴክኒዎሎጂ ጋር እንዲተዋወቅ ይረዳዋል።በዚህም አስተሳሰቡም ይለወጣል።ከጊዜውም ጋር ይራመዳል። በተጨማሪም በግብርና ሙያ ላይ መተዳደር የማይፈልገው ወጣት አምራች ሃይል ገጠሩን እየለቀቀ ወደ ከተማ በመፍለስ የሥራ አጡን ፣የቤት አልባውንና  የወንጀለኛውን ቁጥር ሊጨምረው ስለሚችል፣የከተማውንም ጽዳት ስለሚፈታተን፣ከግብርናው ጎን ለጎን የልዩ ልዩ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴዎችና የሥራ እድሎች መከፈታቸው እነዚህን ሁሉ ውጥረቶች ሊያሶግድ ይችላል።በአገሩ ላይ የሚተዳደርበት የሥራ ዕድል ከተከፈተለት ወጣቱ ለባርነት ወደ አረብ አገር የመሰደዱን ፍላጎቱን ይቀንሰዋል።በአገሩ ኮርቶና እረክቶ የመኖር ስሜቱን ያሳድገዋል።

5 .እርሻ በኢትዮጵያ ትልቁና ዋናው የኤኮኖሚ ዋልታ እንደመሆኑ መጠን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።የከተማው ሕዝብ ሕይወት የተንጠለጠለው በገጠሩ አርሶ አደር ስለሆነ የገጠሩን ኑሮና እንቅስቃሴ ማሳደግና ማሻሻል ለከተማ እድገትም መሰረት ነው።የእርሻ መስኩ ከሰማንያ እጅ (80%)በላይ የሆነውን ሕዝብ ስለሚያቅፍ በዚያ ዙሪያ የሚደረገው ለውጥና መሻሻል የሕዝቡን ኑሮና የአገራችንን ገጽ የሚለውጥ ሞተር እንደሆነ  መታመን አለበት።

ለእርሻ የማይመቹ ከባቢዎች ባላቸው የከባቢው የተፈጥሮ ገጽና ሃብቶች በሚጠቅሙበት መንገድ እንዲደራጁ ማድረግ ሌላው መፍትሔ ይሆናል፤ተራራማና አሸዋማ የሆኑ ለእርሻ የማይማቹ ከባቢዎች ለግንባታና ለመንገድ ስራ ከፍተኛ አስተዋጽኦና ድርሻ ይኖራቸዋል።የግድ እርሻ ስለማይሰምር ለርሃብ የሚጋለጡ ወይም ሕዝብ የማይኖርባቸው ሌጣ ከባቢዎች ሆነው ሊቀሩ አይገባቸውም።በአንድ ወቅት ላይ በደሴ ከተማ በዳውዶ ተራራማ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ተራራውን እየቦረቦሩ ለደረጃና ለቤት ግንባታ የሚሆን ድንጋይ እየጠረቡ በመሸጥ ይተዳደሩ ነበር።በዚህ ሥራ ከትግራይ የሚመጡ ዜጎችም ይጠቀሙበት ነበር።መንግሥት አደገኛ ነው በማለት በማስቆም ሥራውን በደማሚት እያፈነዱ በብዛት ለሚጠቀሙ አካላት (የአውራ ጎዳና)ጭምር አሳልፎ ሰጥቶታል።ያ ሥራ በተቀናጀ መልኩ ሕዝቡ ቢሰለፍበት ሕዝቡም ተጠቅሞ ተራራውንም ወደ እርሻ መደብ(terras farm) ለመለወጥ ባስቻለ ነበር።ለምሳሌ በሌላው አገር በበረዶ የተዋጡ ከባቢዎች ለእርሻ ስለማይመቹ በሌላ እንቅስቃሴ ለምሳሌም የበረዶ ላይ እስፖርት የሚካሄድበትን ተቋም በማደራጀት ለሕዝቡ ኑሮ የሚሆን ገቢ(ምግብ ለመግዛት የሚያስችል አቅም) ይፈጥራሉ። እህል አይመረትባቸውምና ሕዝብ መራብ አለበት አይባልም።በአገራችንም የአፋር በረሃ ለእርሻ እንቅስቃሴ ባይመችም፣ጨው በማምረት፣በፖታሽና በሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች የታደለ በመሆኑ ከዚህ ጋር የተያያዘ  አማራጭ የገቢ እንቅስቃሴ ቢፈጠርለት ድርቅ በመጣ ቁጥር ከብቶቹ አልቀው ለርሃብ ከመጋለጥና ከመሰደድ ሊድን ይችላል። የሚገፋውንም የዘላን(ተንቀሳቃሽ)ኑሮ በዘላቂ ሰፈራ ሊለውጠው ይችላል፣ልጆቹም የትምህርት ዕድል ያገኛሉ።ከቀረው የዕድሜ አጋራቸው ጋር እኩል ሊራመዱ ይችላሉ።አገራቸውንና እራሳቸውንም ለመርዳት ይበቃሉ።

4.ለተደጋጋሚ የርሃብ መቅሰፍት የዳረገን ሌላው ምክንያት ደግሞ የአስተሳሰብና የባህል ለውጥ አለማድረጋችን ነው።ለማሳደግ አቅም ሳይኖር ብዙ መውለድን እንደዋስትናና በረከት እናያለን፤የሃይማኖት ተቋማትም “ብዙ ተባዙ”እያሉ በመስበክ ደሃ ሕዝብ የማይችለውን አላፊነት እንዲሸከም በአምላክ ስም ያስጨንቁታል። በተለይም በሙስሊሙ ዙሪያ አሁን የሚታየው የቁጥርህን አብዛ መርሆ ልጅነታቸውን ያልጨረሱ ሕጻናት ልጃገረዶች አግብተው እንዲቀፈቅፉ የሚያስገድድ ስብከት በአላህ ስም እየተሰራጨ  ውጤቱ ግን በረሃብና በበሽታ የሞቱትን ቀብሮ የተረፉት ከቻሉ በየጎረቤት አገሩ ተሰደው በባርነት እንዲኖሩ የሚገደዱበት ሁኔታ ፈጥሯል።በኢትዮጵያ አማካኝ የውልደት ቁጥርን ለማስላት የስምንት፣የስድስት፣የአራት፣የሶስት፣የሁለት፣ የአንድ ልጅና መሃን ቤተሰብ የሆነው ሰባት ቤተሰብ ተደምሮ ቢካፈል በአማካይ አራት ልጅ ይሆናል ማለት ነው።ይህም በደሃ አገር ወልዶ ለማሳደግ የሚቻል አይሆንም።በህጻንነት መዳርና መውለድ፣የወሊድ ቁጥጥር አስፈላጊነት አለመታወቁና ልጅን መውለድ ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ የማሳደግ አላፊነት አለመለመዱ ለመራብ አይነተኛ ምክንያት ነው።ከአቅም ጋር ያልተመጣጠነ የቤተሰብ ቁጥር ለችግርና ለእርሃብ መጋለጡ አይካድም።ይህን የሚያሳይ አንድ ታሪክ ለመጥቀስ እወዳለሁ፣-

ታሪኩ የሚያጠነጥነው ወ/ሮ አበበች ጎበና የተባሉት በጎ አድራጊ እናት ኢትዮጵያዊት በስብሰባ ላይ  የተናግሩትን ዋቢ በማድረግ ነው።እንዲህ ይላሉ “ግሸን ተሳልሜ ስመለስ ሃይቅ አካባቢና በደሴ ከተማ ያየሁት የርሃብ መቅሰፍት የሚዘገንን ስሜት አሳደረብኝ፤ከርሃብ ጦርነት ይሻላል፣እየበሉና ሳይበሉ የመሞት ልዩነት ነው።የነበረኝን ዳቦ ለሕጻናት አከፋፍዬ ለአንዷ ሕጻን ለማድረስ ስሄድ ሞታለች፣ሌላዋ ደግሞ ከሞተችው እናት ደረቅ ጡት ላይ አፏን ደቅና ትመጠምጣለች።ሌላው ደግሞ ሶስት ልጆቹን ይዞ ሲያጣጥር ያለችኝን ሰጥቸው ወዲያው አረፈ። የሴትዮዋና የሰውየው ሁኔታ ወደ በጎ አድራጎት ተግባር ቀሰቀሰኝ።ወደ አዲስ አበባ ስመለስ ሕጻናት ሰብስቤ ተመለስኩ፤ከናቴና ከባለቤቴ ጋር ተጣላሁ “ስራዋን ጥላ አስከሬን ትሰበስባለች አሉኝ” 1500 ካሬሜትር ለዶሮ እርቢ አስቤው በነበረው ቦታ ላይ ዳቦ እየጋገርኩ፣ሳንዱች እያዘጋጀሁ፣ቆሎ እየቆላሁ ሕጻናቶቹ እየሸጡ ለመቋቋም ሞከርኩ፤ከጊዜ ብዛት ተሳክቶ እያደገ መጣ።በአንድ ወቅት ላይ በሰሜን ሸዋ ተከስቶ በነበረው እርሃብ ከቦታ ወደ ቦታ ስንቀሳቀስ በአምቦ አካባቢ የሚኖር አንድ ድሃ ገበሬ መምጣቴን ሰምቶ አራት ሚስቶቹንና ከነሱም የወለዳቸውን፣12፣8፣10፣10 በድምሩ አርባ ልጆቹን ከእራሱ ጋር በአጠቃላይ አርባ አምስት ሆነው ካለሁበት ቦታ ድረስ መጡ።የቤተሰብ እቅድ የሌለበት አገር በመሆኑ ባልገረምም አስደነገጠኝ። “እኔ የማሳድግበት አቅም የለኝም እንዳደረግሽ አድርጊያቸው” ብሎ ልጆቹን በትኖ ለመሄድ ሲነሳ በግድ ተይዞ ከአቅሜ በላይ እንደሆነ ተነግሮት ትንሽ ማዝገሚያ ገንዘብ ተሰጥቶት ስምንቱን ልጆቹን ወስጀ ለማሳደግ ተስማምቼ ልጆቹን ይዤ መጣሁ፣እሱም እያጉረመረመ 32 ልጆቹንና አራት ሚስቶቹን ወደ መጣበት ይዟቸው ተመለሰ።”ሲሉ ያለውን ያላቅም መውለድና የሚያመጣውን ችግር  ለማሳየት ሞክረዋል።ይህ በአንድ ከባቢ የሚታይ ችግር ሳይሆን በመላ አገሪቱ ከዳር እስከዳር እንደባህል የተለመደ ችግር ነው።

ሌላው ደግሞ በኢትዮጵያ በተለይም በገጠሩ በበዓላት ምክንያት ከሚሰራበት የማይሰራበት ቀን በመብዛቱ ለችግሩና ለድህነቱ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ከዛም አልፎ ተርፎ በነዚሁ በተወሰኑ የስራ ቀናት ከሚያመርተው ደቃቃ ገቢ ቤተሰብ ሲሞት እስላሙ በሰደቃ ክርስቲያኑ በሰለስት፣በሰባት፣ባስራ- ሁለት፣ በአርባ፣በመንፈቅና በዓመት የተዝካር ድግስ፣ሲወለድ በክርስትና ድግስ ያለችውን አሟጦ ከሌለውም ተበድሮ ችግር ውስጥ እንዲገባ እምነቶቹ ያስገድዱታል።አንድ ጋዜጠኛ  በቪዲዮ በተቀረጸ ዘገባ እንዳቀረበው አንድ ገጠሬ አርሶ አደር ሚስቱ ልጅ ወልዳ በከባቢው ያሉትን ቄስ(የነፍስ አባት)ጠበል እንዲረጩ ቢጠይቃቸው ክርስትና ያልተነሳ ህጻን ካለበት ቤት ጠበል ለመርጨት እንደማይችሉ በመግለጻቸው ከሌላ ገበሬ ጋር እያጣመደ የሚያርስበትን አንድ በሬ ሸጦ በመደገስ ክርስትና ለማስነሳት መገደዱንና፣ከድግሱ በዃላ የሚያርስበት በሬ በማጣት ተቸግሮ ሚስትና ልጆቹን ጥሎ ስራ ፍለጋ ወደ ከተማ መሰደዱን አመልክቷል።እዚህ ላይ ልጅ ክርስትና አይነሳ፣የሞተ ቤተሰብም አይታሰብ ለማለት ሳይሆን ከአቅም ጋር የተያያዘ ቢሆንና በተደጋጋሚ የሚደረገው ዝግጅት በተወሰነ ጊዜ ቢሆን እንደሚሻል ለማሳየት ነው። በሰለጠነው ዓለም በሞት የተለየን ቤተሰብ በፎቶግራፉ ዙሪያ ሻማ በማብራት ዕለቱን ያስታውሱታል።በሞት የተለየን ዘመድ አዝማድ የሚያስታውሱት በድግስ ሳይሆን የተወለደበትን ወይም ያረፈበትን ቀን በማሰብ ነው።

በአገራችን በተለይም በአሁኑ ወቅት አንዳንዱ ከባቢ የሚደረገው የተዝካር፣ዛካትና ሰደቃ ድግስ ሙቶችን ከመዘከር አልፎ የደጋሹ ሃብት የሚታይበት ኤግዚቢሽን እየሆነ መጥቷል።ታዲያ ነብስ ይማር ቢል የሚያምርበት የእኔ ቢጤ ደሃ ከበር እንዳይደርስ እየተከለከለ እለቱ የባለጸጎች የመገናኛና የመዝናኛ  እለት ሆኖ ያልፋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደቀረው የዓለም ሕዝብ በየቀኑ ሃያ አራት ሰዓት  በሚሽከረከረው ኤኮኖሚ  እንቅስቃሴ አካል ሳይሆን በእምነት ሳቢያ በራሱ የጥቂት ቀናትና ሰዓት ስራ የብዙ ቀናቶች እረፍት ልማድ እንዲቀጥል ማድረጉ ከችግርና ከድህነት ላለመውጣት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።

እነዚህን ልማድና ድክመቶች ለማስወገድና በተሻለ መልክ አገሪቱንና ሕዝቡን ለመምራት እስከዛሬው ድረስ የሰፈኑት ስርዓቶች አልቻሉም፤እንደውም ለችግሩ ተጠያቂዎች ናቸው።መሬት በጥቂቶች ተይዞ ሌላው ብዙሃን መሬት አልባ መሆኑ፣የአገሪቱ ንብረትና ሃብት  የስልጣን ዕድሜን ለማርዘም በስለላና በመሳሪያ ግዢ መባከኑ፣ ለብዙ የእርሻ ተቋማት ግንባታ ሊውል የሚገባው መጠነ ብዙ ገንዘብ እየተዘረፈ በባለስልጣኑ መዝናኛና በውጭ አገር ባንኮች መቀመጡና በንብረት ግዥ ላይ በመዋሉ የልማት እቅዶች በሚገባ አለመጠናታቸውና በቅደም ተከተል በተግባር አለመተርጎማቸው፣የገጠሩን ልማት ከማስፋፋት ይልቅ ቅድሚያ በከተማ ውስጥ ለሚገነቡት የሆቴል ሕንጻዎችና የውጭ አገር ሸቀጥ በሚያግበሰብሱ የንግድ ዘርፎች በመፍሰሱ፣የአገር ውስጥ ካፒታል እንዳያድግ ዜጎች በፈለጉበት ቦታና ሙያ እንዳይሰማሩ የሚከላከለው የክልል መንግስታት መዋቅር አንዱና ዋናው እንቅፋት ሆኗል።

ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች የሚያስገኙት ገቢ ጠቃሚ መሆኑ ባይካድም፣ የተገኘው ገቢ ወደአገር ውስጥ ሳይገባ በባለስልጣኑ የውጭ አገር ባንክ የሚከማች ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።ሕዝቡ ሊመገብ የሚችለውን የእህል ምርት ቅድሚያ ሰጥቶ ፤ለውጭ ገበያ የሚቀርቡትን እንደ ጫት፣ቡና፣አበባና፣ቦለቄ…ወዘተ ያሉትን ምርቶች በሁለተኛ ደረጃ ቢቀመጥ በምግብ እጥረት ሊመጣ የሚችለውን ርሃብ ለማሶገድ ይረዳል። የምግብ አቅርቦት እጥረት ከኖረ የዋጋ ግሽበት ይከሰታል።ቁጥጥር ማድረግ የሚቻለው ምርትና አቅርቦትን በማሳደግ ብቻ ነው።እርሃብን የሚወልድ የዋጋ ግሽበት የእድገት ምልክት አይደለም። በነጻ ገበያ ስም ነጻ ዘረፋ መፍቀድ ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ እድገት አያመጣም። እርሃብንም አያሶግድም።

በቡኸ ላይ ቆረቆር እንዲሉ ይባስ ብሎ አገር አቋርጦ ደፋ ቀና ብሎ መሬት ጭሮ የሚያገኛትን ከእጅ ወዳፍ የሆነች ገቢ አምርቶ እንዳይኖር መንግስት ተብየው ጎሰኛ ቡድን በዘረጋው መመሪያ ሕዝብ ከኖረበት አካባቢ እየተፈናቀለ የራሱ አገር ስደተኛ እንዲሆን አድርጎታል፤የከባቢውንም ተወላጅ በክልል አጥር አስሮ እንዳይወጣ፣ሌላውም ወደ እሱ እንዳይመጣ የመጣውም ጥሎ እንዲወጣ፣ከሌላው ጋር እንዳይቀላቀል፣በፈለገበት ያገሪቱ መሬት የፈለገውን ስራ ሰርቶ እንዳያድር፣አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ተናግሮ እንዳይግባባ፣ብሎም እርስ በራሱ እንዲጋጭ፣ቤተሰብና ጎረቤት ሳይቀር አምስቱ መሃል አንድ ሰላይ መድቦ እንዳይተማመን አድርጎታል።በፍርሃትና በሽብር ሃይሉን አዳክሞታል። በሕዝብ መካከል ሊኖር የሚገባውን መደጋገፍና አንድነት እየናደና እያጠፋ በቋንቋና በክልል ታውሮ እርስ በርሱ በጠላትነት እየተያየ አደጋውን በጋራ ለመቋቋም እንዳይችል ከማድረጉም በላይ በጠላትነት እንዲተያይና አብሮ እንዳይኖር አድርጎታል። በዚህ አበይነቱ ስርዓት ስር የሚኖርና በሰላም ሰርቶ ማደር ያልቻለ ሕዝብ ለርሃብ መጋለጡ አይቀሬ ነው።

አሁን በስልጣን ላይ ያለው አካል የአገሪቱን ለም መሬት ለውጭ ባለሃብቶች አሳልፎ በመስጠትና በመቸብቸብ ፣ የተገኘው ምርትና የእርሻ ውጤት ሕዝብ ሳይጠግብና ሳይደርሰው ሙልጭ ብሎ እንዲወጣ በተለይም ኢትዮጵያን  በሃይማኖትና በጎሳ ቀውስ ለማጥፋትና ለመቀራመት የረጅም ዘመን ፍላጎት ላላቸው ጸረ ኢትዮጵያ ለሆኑ ባዕዳን አመቻችቷል።ሌሎቹም የምዕራቡ አገሮች ኢትዮጵያ ለቅኝ ግዛት አገሮች ነጻነት ያደረገችውን አስተዋጽኦ በቂም በቀል መቀጣጫ አድርገው ዳር ድንበሯን፣የበሃር በሮቿን እንድታጣ ተባብረዋል።አሁንም እንደ አገር እንዳትኖር ውስጥ ውስጡን እየሰሩ ተገንጣዮችን   በዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ሰበብ እየደገፉና እያበረታቱ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ በተለያዬ ወቅት ተመሳሳይ የርሃብ አደጋ ተከስቷል።የመሪዎች ለውጥ እንጂ የስርዓት ለውጥ ባለመኖሩ እስከአሁን ድረስ ችግሩ ሳይወገድ ቆይቷል።ለወደፊቱም ቢሆን የስርዓት ለውጥ ሳይኖር መንግስትን በመለወጥና በባለስልጣኖች ቅይይር  ብቻ እርሃብን ድል በማድረግ  የአገራችንን ገጽ ለመለወጥ  አይቻልም።

የስርዓት ለውጥ ብቻም ሳይሆን የአመጋገብ ለውጥም ማድረጉ ሌላው መፍትሔ ይሆናል።በተለምዶ ከምንመገባቸው የእህል አዝርእቶች፣ቅጠላቅጠልና ፍሬዎች ውጭ እያሉ የማንበላቸው ግን በሌላው አገር ሕዝብ የሚመገባቸውን በመመገብ እርሃብን ማሸነፍ ይቻላል።በአመጋገብ ልማዳችን ለውጥ ማድረግ ተገቢና አስፈላጊ ነው። ከጤናም አንጻር ጠቀሜታ አለው።የእርሻና የአመጋገብ ሊቃውንትና ልሂቃን በዚህ በኩል ምርምርና ጥናት እያደረጉ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ ትልቅ አላፊነትም አለባቸው። የምሁራን ሚና ህብረተሰብን ወደተሻለ አቅጣጫ እንዲያመራ ማድረግ ስለሆነ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ብዙ ይጠበቅባቸዋል።የእውነት፣የደፋርነት፣የሰላምና ፍቅር ምሳሌዎች ሊሆኑ ይገባል።እስከአሁን ድረስ በአገራችን ላይ ለተከሰተው ችግር ትልቁን ሚና የተጫወተው ምሁር ነኝ ባዩ ዜጋ ነው።ስልጣን ለመያዝና ለመቆየት የሕዝቡን ደካማ ጎን የሚጠቀመው ፊደል የቆጠረው ምሁሩ ነው።ተራ ሕዝቡ ብሔርና-ብሔረሰብ፣መገንጠል፣ክልልና እራስ ገዝ የሚሉ ጣጣ አያውቅም፤በነዚህ መርዞች የበከለው የተማረው ዜጋ ነው።የእኩልነትና የዜጋ  መብት አይከበር ለማለት ሳይሆን በዚህ ዙሪያ አገር የማፈራረሱ ፍላጎትና ሙከራ ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ነው።ሕዝብ የሚፈልገው በሰላም ሰርቶ ፣ሳይቸገር ማደሩን ነው።የልጆቹን መልካም ኑሮ ማየት ነው።ይንን ደግሞ  ተባብሮ የትልቅ አገር ባለቤት ሆኖ በመኖር እንጂ ባንዲራ በመቀየር፣በተለየሁ ነኝ መዝሙርና ተረት የሚያገኘው አይደለም።የራሱን ቋንቋ በሚናገሩ ጨቋኝ መሪዎችና ስርዓቶች መዳፍ ስር መውደቅም እንደሚኖር ከሚታዩት መማር ይገባል።

ኢትዮጵያ ብዙ የእርሻ ምሁራንና የእርሻ መሃንዲሶችን አፍርታለች፤ግን በተግባር የገበሬውን ኑሮና አሰራር፣መሳሪያውን ጭምር በሚመለከት የታዬ ለውጥ ለማምጣት አልቻሉም።ስርዓቱ ተብትቦ ቢይዛቸውም ከዚያ ለመውጣት ያደረጉት ትግል የለም። አብዛኛዎቹ በተማሩት ትምህርት ገጠር ገብቶ ደሃ ወገናቸውን ከማገልገል ይልቅ በከተማ ቢሮ ውስጥ ከፍተኛ ደመወዝ እያገኙ ተዝናንቶ መኖርን ይመርጣሉ።የመንግስትን ተጽእኖና ችግሩን ተቋቁመው ገጠር ገብተው ሃላፊነታቸውን የሚወጡት በጣም ጥቂቶች ናቸው። የክልሉ ተወላጅ ያልሆነ ባለሙያ ከፈለገበት ቦታ ሄዶ ለመስራት አለመቻሉ ሌላው ማነቆ ነው።ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ የጎሳ ማንነቱ ወሳኝ ነው።ሌላው የተማረው ችግሩን ከሕዝቡ ጋር እየተካፈለ ለውጥ ለማምጣት ከመጣር ይልቅ በውጭ አገር ወይም ለውጭ አገር ድርጅቶች ተቀጥሮ መስራቱን ይመርጣል። የተማረው ግንባር ቀደምና ደፋር ካልሆነ ታዲያ አገርን ማን ያሻሽላል?ሰፊው ሕዝብ ማንን ተከትሎ ለለውጥ ይሰለፍ? እርሃብንና ችግርን እንዴት ያሶግድ?

በኢትዮጵያ ውስጥ እርሃብ ጊዜአዊና የገጠር መቅሰፍት ሳይሆን በቋሚነት የኖረ በከተማዎችም የሚታይ ክሮኒካል ችግር ነው። በቀሩት ከተማዎች በተለይም በአዲስ አበባ ውስጥ ጠግቦ የሚያድረው ከአስር ከመቶ አይበልጥም። ሌላው በቀን ሁለት ጊዜ ወይም አንድ ጊዜ እራብ የሚገታ የተወሰነና አንድ ወጥ ምግብ ቀምሶ የሚያድር ነው።በጉልበት ስራ ላይ የተሰማራው የሚያገኘው አነስተኛ ገቢ አንድ እንጀራ በሽሮ ገዝቶ ለመብላት ስለማያስችለው ጉርሻ ገዝቶ ለማደር ይገደዳል።ከዚህም ባነሰ ደረጃ የሚኖረው ከተሜ ቁጥሩ ትንሽ አይደለም። የኢትዮጵያን ሕዝብ አመጋገብ ከሌላው አገር ሕዝብ ጋር ሲያነጻጽሩት የተሟላ አይደለም ፣ስለሆነም ለበሽታ የተጋለጠና መቋቋም የማይችል ነው።

መሬት ለመሪዎች የገቢና የድጋፍ መሰብሰቢያ ምንጭ ና መሳሪያ መሆኑ አንዱ የችግሩ ምክንያት ነው።በእርሻ ሙያ ለሚሰማራው ዜጋ እንደቤተሰቡ ብዛት መዳረስና ለሚገለገልበት እንደገቢው መጠን ግብርና ኪራይ የሚከፍልበት ቢሆን የመሬት ባለቤትነቱን ጥያቄና ችግር ሊያሶግድ ይችላል።የእርሻ መሬት ሊሰሩበት እንጂ ይዘው ጦም የሚያሳድሩት፣ኪራይ መሰብሰቢያና አትርፎ ለመሸጥ ብቻ የሚይዙት መሆን አይገባውም፤ስለሆነም ተሰጥቶት በጥቅም ላይ ለማዋል ያልቻለው ለሚጠቀምበት እንደሚለቅ የሚያስገድድ ሕግ ቢወጣ የኪራይ ሰብሳቢነትን ባህል ሊሰብር ይችላል።ለመኖሪያ ቤት መስሪያ የሚሆን የከተማም ሆነ የገጠር ቦታ ማግኘት የዜግነት መብት ነው።መንግስት የሚወደውን የሚጠቅምበት የማይወደውን የሚጎዳበት መሳሪያ መሆን አይገባውም።ለሆቴሎችና ለልዩ ልዩ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ለትምህርት ቤት፣ለሆስፒታል የሚሆነው ቦታ አስፈላጊነቱ ተጠንቶ ጥራት ባለው መልኩ  ቢሰራ አሁን የሚታየውን ፉክክር፣በደላላ የሚወሰነው የዋጋ ንረትና ዘረፋ፣ አደገኛ ግንባታ  ሊያሶግድ ይችላል።በተለይም  በከተማዎች የሕንጻ ስራ ላይ የተሰማራውን ዜጋ ፊቱን ወደ ገጠሩ እንዲያዞር ሁኔታዎች መመቻቸት አለባቸው።በአገር ግንባታ ላይ መሰማራት ማለት በከተማ ውስጥ የንግድና ያገልግሎት ዘርፎች፣በሆቴልና ቡና ቤቶች ላይ ብቻ ማተኮር አይደለም።በገጠርና በከተማ ያለው ልዩነት ሊጠብ የሚችለውና የገጠሩ ኑዋሪ ኑሮው ሊሻሻል የሚችለው የኤኮኖሚና የማህበረሰብ አገልግሎት ተቋማት በከባቢው ሲስፋፉ ነው።ለውጭ አገር ቱሪስት ሲባል የአገር ንብረትና ሃብት በመዝናኛ ቦታዎች ላይ ብቻ መባከን አይገባውም።እርግጥ የቱሪስት ገቢ አስፈላጊ መሆኑ ባይካድም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የሕዝቡን ሕይወት በማትረፉና የኑሮ ደረጃውን በማሻሻሉ ላይ ሊሆን ይገባዋል።የዜጎች አፍላቂነትንና የፈጠራ ችሎታ እየተንከባከቡ አገር እራሱን እንዲችል ማድረጉ ከጥገኝነት ያድናል። ለሕዝቡ በጣም የሚያስፈልጉትን በመለየት አላስፈላጊ የቅንጦት እቃዎችን ከውጭ እንዳይገቡ መቆጣጠር የውጭ ምንዛሬን ከማዳኑ በተረፈ በሕዝቡም ኑሮ ላይ ልዩነቱ እንዳይሰፋና እንዳያድግ ያደርጋል። ለወደፊቱም ሊከሰት የሚችለውን የሕብረተሰብ የባህልና የማንነት ቀውስ ይከላከላል።በራስ የመተማመንን ስነልቦና ያጎለብታል።

ሌላው መታየት ያለበት ጉዳይ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄደው የሕዝብ ቁጥር ነው።ምንም እንኳን የሕዝብ ብዛት አንዱ የኤኮኖሚ ምንጭና ሃይል ነው ተብሎ ቢወሰድም ብቃት፣ጥንካሬና እውቀት የሌለው ብዙ ሕዝብ ከሚሰጠው ጥቅም የሚያመጣው ጉዳት ያመዝናል።ልጅ ወልዶ መሳሙን ሁሉም የሚመኘው ጸጋ ቢሆንም ወልዶ የሚያስፈልገውን አሟልቶ ከማሳደግ፣አስተምሮ ለቁም ነገር ከማብቃት ካለው አላፊነት ጋር መታየት ይኖርበታል።  “እውር አሞራ የሚቀልብ አምላክ ያስብለታል ወይም በዕድሉ ያድጋል”የሚለው ዃላ ቀር አስተሳሰብ ከሕዝቡ አእምሮ መወገድ አለበት።ልጅ ጧሪና ቀባሪ ሊሆን የሚችለው ለዚያ የሚበቃበት ሁኔታ ሲዘጋጅለት ብቻ ነው።መውለድ ማለት በበሽታና በርሃብ የሚሞት ልጅ  አልቅሶ ለመቅበር አይደለም።ለዚያ የሃይማኖት ተቋማትና የማህበረሰብ ልሂቃን ስህተቱ ታርሞ የሕዝቡ አመለካከት እንዲቀየር ተግተው መስራት ይኖርባቸዋል።የልጅ ብዛትን መወሰንና የወሊድ ቆጥጥርም ማድረግ ሌላው መፍትሔ ነው።መውለድ የሰብአዊ መብት እንደሆነው ሁሉ ልጆች ካለስቃይና ካለችግር ሳይራቡና ሳይታረዙ በጤነኛ ከባቢ ተንከባክቦ የማሳደግ ግዴታም የዚያው አካል እንደሆነ መታወቅ አለበት። ወልዶ ማሰቃየት ወይም ለስቃይ ማጋለጥ ወንጀል እንጂ  የሰብአዊ መብት ወይም የፈጣሪን ትእዛዝ ማክበር አይደለም።

ከዚህ በላይ በጥቂቱ የተጠቀሱት የመንግስትና የህብረተሰቡ ድክመቶች ካልተወገዱ ለወደፊቱም እንዳለፈውና እንደአሁኑ የርሃብ አደጋው እየተከሰተ ከልመና ሳንወጣ መሳቂያ መሳለቂያ በመሆን እርሃብና ስደት ለኢትዮጵያውያን የዘላለም መታወቂያችን ሆኖ ይቀራል።

መንግስትና ስርዓትን ለመለወጥ እንደምንመኘው ሁሉ እራሳችንን ለመለወጥና ከባህላዊ እግር ብረት ለመላቀቅ ደፍረን መነሳት አለብን።እራሳችንንና ባህላዊ ግድፈቶችን ሳንለውጥ መንግስት ቢለወጥ ስርዓት ተለወጠ ማለት አይደለም፤ በተመሳሳይ ልማድና ስርዓት ቀለበት ዙሪያ ሲሽከረከሩ መኖር ይሆናል።በውጭ እርዳታ መመካትና በየጊዜው እየተመጸወቱ መኖር መፍትሔ ሳይሆን በስነ ልቦና ላይ ትልቅ ስብራት የሚጥል ድክመት ነው።መሪዎች በልመና ስልት ገንዘብና እርዳታ መሰብሰባቸውን የሚያሳፍር እንጂ የሚመኩበት እውቀት አድርገው መውሰድ የለባቸውም።ለሕዝቡም የልመና አስተማሪ መሆን የለባቸውም።የወያኔ /ኢሕአዴግ መንግስት ብዙ እርዳታ በመሰብሰቡ ከሌሎቹ መንግስቶች የተሻልኩ ነኝ በማለት ይመጻደቅበታል። የሚያኮራው ችግር እያናፈሱ ለምኖ ገንዘብ መሰብሰቡ ሳይሆን የሕዝብን መብት አክብሮ፣የሕግ ተገዢ ሆኖ፣ሕዝብ በሰላም ተከባብሮ እንዲኖር የሚያበቃ ስርዓት በማስፈን በታሪክ የሚያስመሰግን ስራ  ሰርቶ መገኘት ነው።

ለወደፊትም የኢትዮጵያን መልክ ለመለወጥ የሚጥሩና የሚፈልጉ ዜጎች፣የፖለቲካ ድርጅቶች ከትግላቸው ውስጥ የገጠሩን ሕዝብ ችግር በሚቀረፍበት ዙሪያ በማተኮር መፍትሔ መፈለግ ማጥናትና መንቀሳቀስ ይገባቸዋል። ለህብረተሰብ የአስተሳሰብና ባህል ለውጥ የግዴታ ስልጣን መያዝ አያስፈልግም።የትግሉ አካል በመሆኑ ሊከውኑት የሚገባ ተግባር ነው።

የውጭ ሃይሎችን ፣ድርጅቶችንና መንግስታትን ለመለመን ከመሯራጥ ይልቅ “እራስን በራስ” የሚለውን በራስ የመተማመንን አርማ ተሸክመው እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚችሉትን ለማበርከት መነሳትና መተባበር ይገባቸዋል።ዘርና ክልል የማይለየውን የእራብ መቅሰፍት በጋራ ሊቋቋሙት ይገባል። ትግሉን በድርጅታዊ ስሜት ሳይሆን በሰብአዊነትና በኢትዮጵያዊነት ዓይን ሊመለከቱት ይገባል።ከድርጅት ጥቅም በላይ፣ከሥልጣን በላይ የሕዝቡን ሰላምና አንድነት፣የተሻሻለ ኑሮ በማስፈኑ ተግባር ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።እርስ በርስ ከመፎካከርና ከመጠላለፍ ባህል በመራቅ ተባብሮ የመስራትን ባህል መከተል ይኖርባቸዋል።ከእንግዲህ ወዲያ የአንድ ድርጅትን የበላይነት የሚያሰፍን አሰራር ሊወገድ ይገባል።የዚህ አይነት አሰራርና አካሄድ የሚከተሉትን ድርጅቶችና ቡድኖች መምከርና መመለስ እምቢ ካሉም ማጋለጥ የአገር ወዳዱ አላፊነት ነው፤በፍርሃትና በይሉኝታ ሲያጠፉ ዝም ማለት ወይም  በጭፍራነት እያጨበጨቡ እንዲቀጥሉበት ማበረታታት የጥፋት ጥፋት ይሆናል።ድርጅቶቹንም የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅማቸው አይሆንም።ኢትዮጵያውያን ካለፉት ተመሳሳይ ጥፋቶች ልንማር ይገባናል።

በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምንገኘው ኢትዮጵያውያን ልንሰራቸው የሚገባን የአጭርና የረጅም ጊዜ ተግባራት

ለወቅቱ የርሃብ አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን እርዳታ የሚያሰባስብ ከሁሉም የተውጣጣ ብሔራዊ ግብረ ሃይል ማቋቋምና የእርዳታ ጥሪና ቅስቀሳ ማድረግ

በረጅም ጊዜ ከሚከናወኑ ተግባራት ስር እርሃብና ሌላም ችግር ቢከሰት ከመሯሯጥ በቅድሚያ የአደጋ መቋቋሚያ እርዳታ (emergency Fund )ማስቀመጥ የሚቻልበትን መንገድና ዘዴ ማመቻቸት፣

በእርሻው ዙሪያ ለውጥ እንዲመጣ በሙያው የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን የሚተባበሩበት አካል መፍጠር፣

የሰብአዊ መብት ሲደፈር ለተጎዱት ጥብቅና የሚቆምና መብት አስከባሪ(እምባ ጠባቂ)የሙያተኞች አካል መፍጠር,

አሁን በአገሪቱ ላይ የሰፈነው ያለመረጋጋት ሁኔታ ፈሩን ለቆ ወደ ከፋ ደረጃ እንዳያመራና የመገነጣጠል አደጋ እንዳይከሰት ሁሉም የሚሳተፍበት የብሔራዊ እርቅና መግባባት ሂደት መጀመር አለበት።ትግል በሁሉም አቅጣጫና መልክ መካሄድ ያለበት ጉዳይ በመሆኑ የሰላማዊ እንቅስቃሴው አካል የሚሆነው ይህ የእርቅ ሂደት ለሁሉም ጠቃሚና አገራችንን ከገጠማት አደጋ ለማውጣት የሚረዳ በመሆኑ እንደ በሳልና ደፋር እርምጃ እንጂ እንደ አጎብዳጅነት መታየት አይኖርበትም።ለውጥ በጠመንጃ ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ትግልም የሚገኝ መሆኑ በአገራችን በየካቲቱ ሕዝባዊ እንቅስቃሴና በ1997 የቅንጅት ውጤት ታይቷል፤ በሌላ አገሮችም  በተደጋጋሚ የታየ ነው።የሰላማዊ ለውጥ ባለቤት መሆን ሁሉንም ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም።በሥልጣን ላይ ያለውም ቡድን የሕዝቡን ጥያቄና ፍላጎት ተከትሎ ሥልጣኑን በአብዛኛው ሕዝብ ለተመረጠ ወገን ለማስረከብ በሚረዳው  ሁሉም ተሳታፊ በሚሆንበት የሽግግር መንግሥት ምስረታ ላይ ትብብር እንዲያደርግ የሚጠይቅ ብሔራዊ የአስታራቂ አካል መመስረቱ የወቅቱ ግዴታ ነው።የእርቅ ኮሚቴው ከሁሉም የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች፣ከሙያና ከሃይማኖት ተቋማት፣ከወጣቶችና ከሴቶች ማህበራት የተውጣጡ ሊሆኑ ይችላሉ።በሂደትም የሽግግር መንግሥቱ አካል ከመሆን የሚያግዳቸው ነገር አይኖርም።የጎሳ ፖለቲካ አንዳይሸፍነው ግን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፤ምክንያቱም አሁን ለሚታየው ችግርና ውዝግብ ዋና ምንጩ በመሆኑ።

እነዚህን በቀላሉና በአጭር ጊዜያት ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል።

ለተሻለችና እርሃብ ለማይኖርባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ተባብረን እንታገል!

አገሬ አዲስ

የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም.(march 4- 2016)

ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን አጭር የጥናት ዝርዝር አባሪ አድርጌ ልኬዋለሁና ጊዜ ወስዳችሁ እንደምትመለከቱትና ለውይይቱም እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ

 

Growing more food with less water

GROWING MORE FOOD WITH LESS WATER.

WATER

Expectations for the population to grow by 40 per cent to more than 9 billion by the year 2050 have raised the global question of how to grow more food with less water. With agriculture responsible for 70 per cent of all freshwater withdrawals, efficient and sustainable water use is needed for our own generation and future generations.

With our global water crisis in mind, we have created this resource to provide factual water news and information.

LATEST NEWS

Wednesday, March 25, 2015

Agriculture Must Adopt Better Water Management to Ensure Sustainable Food Supplies
GLOBAL – As people around the world celebrated World Water Day 2015 last weekend, the United Nations released a new report predicting major water shortages…

Tuesday, January 06, 2015

Substantial Decline Seen in US High Plains Aquifer Groundwater Levels
US – The US Geological Survey has released a new report detailing changes of groundwater levels in the High Plains Aquifer, which saw substantial depletion…

Monday, December 08, 2014

Soil Carbon Advances Could be Key to Improving Food and Water Security
UK – The Global Advances in Soil Carbon Management recommendations, which have been compiled by a team of international scientists, could have a significant…

Blue Fresh surface and ground water, for example, the water in aquifers, streams and rivers
Read More

Green The precipitation on land that does not run off or recharge the groundwater but is stored in the soil or temporarily stays on top of the soil or vegetation.

Eventually, this part of precipitation evaporates or transpires through plants. Green water can be made productive for crop growth.
Read More

Grey Waste water from bathroom sinks, showers, tubs, and washing machines. It is not water that has come into contact with feces, either from the toilet or from washing diapers.

Greywater may contain traces of dirt, food, grease, hair, and certain household cleaning products. While greywater may look “dirty,” it is a safe and even beneficial source of irrigation water in a yard.

If released into rivers, lakes, or estuaries, the nutrients in greywater become pollutants, but to plants, they are valuable fertilizer.
Read More

Black Waste water than has come into contact with fecal matter. It includes sewage and other contaminated water sources, including all forms of flooding from seawater, ground surface water, and rising water from rivers and streamsthey are valuable fertilizer.
Read More

Uses The world population tripled during the 20th century and water use for human purposes multiplied six-fold.

The main uses of water are for domestic use – drinking, cooking, bathing, cleaning, but this area, while important is a per cent of water. Industrial use is about twice that of domestic use, mostly for energy production. The biggest user is agriculture – producing food and fiber to feed and clothe our growing population.
Threats Human activity is increasing the threat to our global fresh water supply.

Climate change, pollution, biodiversity loss and our growing population are immediate threats. Mountain glaciers are shrinking at ever-faster rates, threatening water supplies for millions of people and plant and animal species.
Availability Without question, the world’s freshwater resources are unevenly distributed. One person in five does not have access to safe and affordable drinking water. And by 2025, an estimated 3 billion people will be living below the water threshold. Densely populated and developing regions of the world, such as Asia and Africa, are expected to face the maximum water stress.
Solutions While there is no easy solution to a problem as big as global water use, new technology is helping to reduce use in some areas. Drip irrigation and drought-resistant crops are examples of agricultural technology that is being adopted in parts of the world that can help reduce water use while not limiting yields.
Read More

GLOBAL AND ECONOMIC WATER SCARCITY

 

 

 

በተከታዩ ገጽ ይቀጥላል….

Definitions and Indicators

  • Little or no water scarcity. Abundant water resources relative to use, with less that 25% of water from rivers withdrawn for human purposes
  • Physical water scarcity (water resources development is approaching or has exeeded sustainable limits). More that 75% of river flows are withdrawn for agriculture, industry, and domestic purposes (accounting for recycling of return flows). This definition – relating water availability to water demand – implies that dry areas are not necessarily water scarce.
  • Approaching physical water scarcity. More than 60% of river flows are withdrawn. These basins will experience physical water scarcity in the near future.
  • Economic water scarcity (human, institutional, and financial capital limit access to water even though water in nature is available locally to meet human demands). water resources are abundant relative to water use, with less than 25% of water from rivers withdrawn for human purposes, but malnutrition exists.Source: International Water management Institute analysis done for the Comprehensive Assessment of Water Management in Agriculture using the Watersim model; chapter 2.

PUBLICATIONS

Our growing listing below features in-depth reports on global water supplies.

A Pact for Water Security The Water Footprint Assessment Manual (English) The Water Footprint Assessment Manual (Chinese) The Water Footprint Assessment Manual (Portuguese) Coping With Water Scarcity Water and Food Smallholders and Sustainable Wells The Great Balancing Act

ARTICLES

Keep a close eye on the most recent technical articles about water use, scarcity and solutions.

A Trifecta of Water-Planning Tools
As fall progresses into winter and harvest comes to a close, crop producers might want to consider planning their future crop rotations, crop mixes and…

Reducing Water Scarcity Possible by 2050
Increased water-recycling and improved irrigation techniques among six strategies identified as key to successfully reducing global water scarcity….

Mapping Water Trends for African Maize
Today’s food production relies heavily on irrigation, but across sub-Saharan Africa only four per cent of cultivated land is irrigate


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles