Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የመጨረሻው ዘመን ትውልድ – የቢዮንሴ አላማ |ከቀሲስ ዘበነ ለማ

$
0
0

ይቺ በፎቶ ላይ የምናያት ዘፋኟ ቢዮንሴ ናት ፡ የመጨረሻው እራት ተብሎ በሚታወቀው የጌታችን ስእል ፊት ለፊት ቀምጣለች፡ ፊት ለፊት በመቀመጧ ማንን እንደከለለች ታያላችሁ? ጌታችንንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው:: በርግጥ እሱን መከለል ይቻላታልን? እርሱ በሁሉ ስፍራ ሙሉ ነውና ፤ ነገር ግን የሰይጣንን ተልእኮ ታስፈፅም ዘንድ በክርስቶስ ፈንታ እሷ መታየትን ወዳ እርሱን ከለለችው ፡ አለም ከክርስቶስ ይልቅ ለእርሷ እንደተማረከ አይታለችና ፡ አለም ከክርስቶስ ይልቅ ለዲያቢሎስ እንደተገዛ አይታለችና በዲያቢሎስ ሃይል ከፍ ብላ የክርስቶስን ቦታ ልትይዝ ደፈረች፡፡

ይህን ለማድረግ ይቻላታልን? እርሱ ተወዳጅ መድሃኒት ክርስቶስ የማይደፈር ሃያል ፡ የማይነቀንቁት ልዑል ፡ የማይነኩት ግሩም ነውና ከእርሱ ይልቅ ማን ይበረታል? ከአፉ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያወጣል ፡ ፊቱም ከፀሃይ ይልቅ ያበራል ፡ አይኖቹ የእሳት ነበልባል ናቸው ፡እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ የሚመስሉ ፡ በእጁ መዳፍ ምድሪቷን የያዘ ፡ የሰማይና የምድር ንጉስ ፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን ማን ሊገዳደረው ይችላል?

ነገር ግን የመጨረሻው ዘመን እንደደረሰ ያሳዩ ዘንድ እኒህ የበረቱ መሰሉ ፤ የነፃነት አምላክ እርሱን ተፈታተኑት ፡ የፍቅር አምላክ እርሱን ዘበቱበት ፡ በዝና፣ በገንዘብ፣ በውበት ህይወት ክርስቶስን ካዱ ፡መድሃኒት ክርስቶስን ሰደቡ ፡፡ አንደበትን የፈጠረ ጌታችንን በፈጠረው አንደበት ተሰደበ።

ምን እንላለን? አለም በክርስቶስ ላይ ጦርነት አውጃለች ፡ አለም ለዲያቢሎስ ተንበርክካለች ፡ነፍሷንም ለእሱ አስማርካለች ፡: ክርስቶሳውያን ጠውልገው ዲያቢሎሳውያን ደምቀው እያየን ነው ፡እንግዲህስ አሰላለፋችንን እናስተካክል ፡ የማን አድናቂ ነን? ለማን እናጨበጭባለን? ለማን ነፍሳችን ትማረካለች?
የማንንስ ተልእኮ እናስፈፅማለን? መድሃኒት ክርስቶስ ግን በጴጥሮስ በኩል አሁንም እኛን ትወዱኛላችሁን? ይለናል ፤ ምን እንመልሳለን? ይህን ተወዳጅ ጌታ እንወደዋለንን? እንኪያስ ይችን አለም ክደን ለክርስቶስ እንበርከክ፡ የዚችን አለም ጣእም ንቀን መድሃኒት ክርስቶስን እንከተል ፤ አለም የክርስቶስ የሆኑትን ልትሰቅል፡ የዲያቢሎስ የሆኑትን ልትሾም በርትታለችና ጌታችንን የምንወድ የክርስቶስን መስቀል እንሽከም፡፡

ዲያብሎስ ይፈር ከድንግል ማርያም ተወልዶ በመስቀል ተሰቅሎ በደሙ የዋጀን ጌታችን በህይወታችን ላይ ይንገስበ አሜን። —
beyonce


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles