የቢዮንሴ አምላኪዎች ሃይማኖት የሚለውን ርዕስ ስትመለከቱት ቀልድ ሊመስላችሁ ይችላል:: እብደትም ነው:: ይህን ሃይማኖት ላቋቋመው ፓውሊን ጆን አንድሪው ግን ቀልድ አይደለም:: “12 ሆነን የጀመርነው ሃይማኖት በአሁኑ ወቅት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተከታዮችን አፍርቶልናል” ይላል::
beyonce 3
በየሳምንቱ እሁድ እየተገናኙ ክርስቲያኖች እንደሚዘምሩትና መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚያነቡት ሁሉ የቤይዝም ሃይማኖት ተከታዮችም የቢዮንሴን ዘፈን ይዘፍናሉ እንዲሁም ቤይብል (the Beyble) የተሰኘውን መጽሐፋቸውን በማውጣት ጥቅሶችን እየጠቀሱ ይሰብካሉ ያመልካሉ::
beyonce 2
የዚህ ሃይማኖት መስራች እንደሚለው “ከጓደኞቹ ጋር ሞስካቶ እየጠጣና ማሪዋና እያጨሰ የቢዮንሴን አንድ ዘፈን ካደመጡ በኋላ ዘፈኗ መለኮታዊ ሃይል እንዳለው ስለተረዱ ከዚያም በኋላ በሷ ማምለክ መጀመራቸውን” ነው:: “የዘፈኖቿ መል ዕክቶች ሃይል አላቸው” የሚለው አንድሪው ወደፊት ሚሊዮኖች የሚከተሉት ሃይማኖት ይሆናል ይለናል::
አትላንታ ውስጥ በሚገኘው የዚህ የቢዮንሴ ሃይማኖት ተከታዮች የማምለኪያ ስፍራ ክርስቲያኖች የሚጠቀሙበትን የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል በቢዮንሴ ቀይረው ሰርተውታል:: በርሷ ፎቶ ስርም ሻማ በማብራት ይጸልያሉ::
beyonce 4
በአሜሪካ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት ማራመድ ይችላል:: ለምን እንዲህ አመለኩ ብሎ መተቸትም በሕግ ሊያስጠይቅ ይችላል:: ግን ምን አስተያየት አላችሁ?