Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ዴንማርክ ዜጎቿ ከኢትዮጵያ ህጻናትን በማደጎነት እንዳይወስዱ አገደች

$
0
0

denmark

(ሳተናው) ከ2001 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከሚገኘው እናት ዓለም ከተባለ የህጻነት ማሳደጊያ ማዕከል ዴንማርካዊያን ወላጆች እናትና አባታቸውን በተለያዩ መንገዶች ያጡ ህጻናትን ህጋው ፎርማሊቲን በማሟላት ሲወስዱ ቆይተዋል፡፡ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ዴንማርክ በማደጎነት የሚመጡ ህጻናትን በተመለከተ መረጃ የደረሰው የዴንማርክ መንግስት የማህበራዊና የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤቷን ወኪል ካረን ሃከራፕን ወደኢትዮጵያ ሁኔታውን ያጣሩ ዘንድ ይልካል፡፡
ካረን የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቅቀው እንደተመለሱም ለመንግስት ባቀረቡት ሪፖርት ኢትዮጵያዊያኑ ህጻናት የጄኔቫውን የማደጎነት ስምምነት በሚያሟላ መልኩ የሚመጡ ባለመሆናቸው ዴንማርክ የህጻናቱን በማደጎነት መወሰድ ማገድ ይኖርባታል በማለት ምክራቸውን አቀረቡ፡፡
በአዲስ ዓለም የህጻናት ማሳደጊያ የሚሰሩ ሰራተኞችን ጭምር ቃለምልልስ በማድረግ መረጃ የሰበሰቡት ካረን የህጻናት ማዕከሉ ህጻናቱን በማደጎነት ከሚወስዷቸው አዳዲሶሱ ቤተሰቦቻቸው ሲያገናኙ ገንዘብና ርዳታ የሚያገኙ በመሆናቸው ወላጆች ያላቸውን ህጻናትን ጭምር ‹‹ልጆቻችሁ ወደ አውሮፓ፣ስካንዴኒቪያን አገራት በመሄድ የተሻለ ትምህርት ያገኛሉ በማለት እያግባቡ ህጻናቱን ከተፈጥዊ ወላጆቻቸው እንደሚለያዩዋቸው ደርሰንበታል››ይላሉ፡፡
በዴንማርክ የማደጎ ልጆችን ጉዳይ የሚከታተለው የመንግስት መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ ህጻናትን ለመውሰድ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙ ዴንማርካዊያን ብቻ በመስሪያ ቤታችን ድጋፍ የጀመሩትን እንዲጨርሱ ይደረጋሉ፡፡ከእነርሱ ውጪ ግን በኢትዮጵያ የማደጎ አሰራር ዙሪያ እምነት የሌለን በመሆኑ ልጆችን መውሰድ እንዲቆም አድርገናል››ብሏል፡፡
ምንጭ ቼፕ ፖስት


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles