Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

አባ ማቲያስ:- ከመሳሳም ይቅርታ ይቅደም! – ደጀ ሰላም

$
0
0
·        “ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው” (አባማቲያስ ሕዳር 2008)
·        ” ከቫቲካን ጋር የነበረንን የቀድሞ ፍቅር(?)እንመልሰዋለን” (አባ ማቲያስ የካቲት 2008)
·         ” ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስትያንን የገዛ ቅኝገዥ ነው” (አባ ማቲያስ ጥቅምት 2008)
·        ወራሪዋን ቫቲካንን ፍቅር : ልጆቻቸውን ቅኝ ገዥ— አባት ብሎ ዝም!!
matias

(ዘአዲስ እንደፃፉት):- አባ ማቲያስ በዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ትግራይ ሄደው ጉብኝትማድርጋቸው ይታወሳል:: አዲግራት ላይ የአዲግራቱ የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቦታ ላይ ” ከካቶሊክጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው” በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል::

ሀገራዊ ማህበራዊና ብሔራዊ በሆነ ጉዳይ ላይ ” አንተ ኦርቶዶክስ : አንተ ካቶሊክ” መባባሉሳይኖር የሁሉም እምነት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በአንድነት መቆም እንዳለበት ግልጽ ነው:: “ኦርቶዶክስና ካቶሊክ መካከል ያለው ልዩነት ጠባብ ነው” ብሎ የማይመስል ነገር መናገሩ ( ያውምከፓትርያርኩ አንደበት) ግን እጅግ የሚያስተዛዝብና ግምት ውስጥ የሚጥል ስህተት ነው:: የሆነው ሆኖይህን ባሉ በሶስተኛው ወር የካቶሊኳ ራስ ቫቲካን ደርሰው የበርካታ ኢትዮጵያውያንን አንጀት አቁስለውተመልሰዋል::
 ፓትርያርኩ ቫቲካን መሄድ ነበረባቸውን?
በመሰረቱ: ቫቲካን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እጅግየመረረ ግፍ ፈጽማለች:: ፋሺስት ጣልያን ኢትዮጵያን ስትወር : የቫቲካን ጳጳሳት የመርዝ ጋዝ እየባረኩኢትዮጵያን ለመውረር የሚደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት እንደሆነ አውጀዋል:: የወርቅ መስቀላቸውንሳይቀር ለጦርነቱ አዋጥተዋል:: የሙሶሎኒምና የግራዚያኒ ቀኝ እጅ የነበረው የቫቲካኑ ጳጳስ ባደባባይወረራውን ደግፎ መግለጫ ሰጥቷል::
ፋሺስት ጣልያን አንድ በዛ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ገድላለች:: በሺዎችየሚቆጠሩ ካህናትን አቃጥላለች:: በውል የታወቁትን እንኳን ብንቆጥር ወደ 2 ቪህ አብያተ ክርስቲናትንአውድማለች:: ጣልያን ከመውረሯ በፊትም የጣልያን ሰላይ እየሆኑ ይሰሩ የነበሩት የቫቲካን መነኮሳትነበሩ::
ቫቲካን ስለሰራችው ጥፋት ኢትዮጵያንን እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ ለመጠየቅፈቃደኛ ስላልሆነች : ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት የቫቲካንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት ግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ቫቲካን ይቅርታ እስካልጠየቀች ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስቤተ ክርስትያን አባቶች ከቫቲካን ጋር አንድነት እንዳይኖር በመወሰናቸው የሁለቱ አብያተ ክርስትያናትግንኙነት በጣም ቀዝቃዛ ነበር:: ( የአለቃ አያሌው ” መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና” መጽሓፍንይመልከቱ)
በተለይ አሁን በቅርቡ ለጨፍጫፊው ግራዚያኒ ጣልያን ውስጥ ሀውልት እንዲቆም ከተወሰነበኋላና የቫቲካን ጳጳሳትም ይህን ጉዳይ የመደገፋቸው ዜና በመሰማቱ : በመላው ዓለም የሚገኙኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በማሰማታቸው የሃውልቱ ስራ ቆሟል:: እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ቫቲካንኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ቢወተውቱም : ቫቲካን ካላት ንቀትየተነሳ ፈቃደኛ አልሆነችም:: የሙገርመው ግን ” የ ጀርመን ናዚዎች አይሁዶችን ሲጨፈጭፉ ዝምበማለቴ ( ባልሳተፍበትም) ይቅርታ ጠይቃለሁ” ብላ አይሁዶችን ይቅርታ ጠይቃለች::
ራሷ የጨፈጨፈችውንና ያስጨፈጨፈችውን ኢትዮጵያውያንን ግን ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛባለመሆኗ : ቫቲካን ኢትዮጵያን ይቅርታ እስክትጠይቅ ድረስ ይፋዊ ግንኙነት እንዳይኖር በኢትዮጵያበኩል ተወስኖ ነበር:: የአለቃ አያለውውን መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና ያነቧል::
አባ ማቲያስ ግን ያንን እግድ ጥሰው ቫቲካን ድረስ በመሄድ ” እኛና ቫቲካን ድሮም ፍቅር ነን:የድሮውን ፍቅር እንመልሰዋለን ” በማለት የብዙ ኢትዮጵያውያንን ድካም መና አብልተውታል::
የአባ ማቲያስ ቫቲካን መሄድ እንግዳ ቢሆንም ብዙዎ ” እዛው ሀገራቸው ላይ ሄደው ቫቲካንለሰራችው በደል ይቅርታ ትጠይቅ” ብለው ይናገራሉ ተብሎ ተጠብቆም ነበር:: በተገላቢጦሹ ግን አባማቲያስ ” ድሮም እኛና ቫቲካን ፍቅር ነበርን ወደፊትም ያንን ፍቅር እንመልሰዋለን” ብለው አረፉት::
የቀደመው የቫቲካንና የኦርቶዶክስ ፍቅር የቱ እንደሆነ አልገባኝም:: የዲዮስቆሮስ ይሆንን?ከጥንት ጀምሮ ቫቲካን የምትልካቸው ሚሺነሪዎች ሕዝብ ሲያጨፋጭፉ ነገር ሲተክሉ እንጂ ፍቅርመስርተው ሲሄዱ አይታወቅም:: እነ አልፎንሱ ሜንዴዝን መጥቀስ ይቻላል:: ቃል በቃል ” ኢትዮጵያቤተ ክርስትያን ላይ ሁለት እሾክ ተክዬባት ሄድኩ” እስከማለት የደረሱ ናቸው:: ጸጋና ቅባትንያስትውሷል:: ነ ጂሴፔ ሳፔቶና አባ ማስያስም ኢትዮጵያን ለጋ ቅቤ ሲቀቡ አናቃቸውም:: በሁለቱምየጣልያን ጦርነት ወቅትም ቫቲካን የሰራችው ወንጀል እንጂ የፍቅር ስራ አይደለም:: (አቡነ ጎርጎርዮስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ታሪክ)
የኦርቶዶክስና የቫቲካን የቀደመ ፍቅር የቱ እንደሆን አይገባኝም:: ፓትርያርኩ እንደዛ ከሚሉ “ቫቲካን አትፍታለችና ይቅርታ ትጠይቅ” የ,ኢለውን ያባቶቻቸውን ቃል አጽንተው እሳቸውም ይሄንቢያደርጉ ለነፍሳቸውም ለስጋቸውም ታሪክ ነበር:; ማኅበረ ቅዱሳንን ” ቅኝ ገዥ” ያለ አንደበትእውነተኛዋ ቅኝ ገዥን ምን ይላት ይሆን ብዬ ጠብቄም ነበር::
ምን ያደጋል ! አባታችን አገላበጡት

Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles