Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ከሕይወት ሞትን ለምን? – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

$
0
0
Mesfin 674
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

ዓይን ያለው ያያል፤ ጆሮ ያለው ይሰማል፤ አእምሮ ያለው ያስባል፤ ልብ ያለው ስሜቱ ይነካል፤ ዓይን ካላየ፣ ጆሮ ካልሰማ፣ አእምሮ ካላሰበ፣ ልብ ካልተሰማው ሰውን ሰው የሚያደርገው ምንድን ነው? የትናንቱ ችግር መልኩን ለውጦ ሲመጣ፣ ትናንት ተሞክሮ ያልተሳካው የሕገ አራዊት መፍትሔ ዛሬ ዘመን ከተለወጠ በኋላ ይሠራል ብሎ መወራጨት ጥፋት ነው፤ ዓይን እያለ አለማየት ነው፤ ጆሮ እያለ አለመስማት ነው፤ አእምሮ እያለ አለማሰብ ነው፤ ልብ እያለ ስሜት ሲጠፋ ሰዎች ነን ወይ? ብሎ መጠየቅ ግድ ቢሆንም ያሳፍራል፤ካላፈርን ይበልጥ ያሳፍራል፡፡
ከአርባ ዓመት በፊት ለመላው አፍሪካ የሽማግሌና የአስታራቂ አገር የነበረችው ኢትዮጵያ በተከታታይ የአረም ጎረምሶች ትውልድ ተወርሳ እንኳን ለአፍሪካ በአጠቃላይና ለራስዋም የምትበቃ አልሆነችም፤ በአረም የተወረረች አገር!
ይኸ ሁሉ ትርምስ፣ ይኸ ሁሉ ጭካኔ፣ የማንን ጥቅም ለማስከበር ነው? ማንን ገድሎ ማንን ለማዳን ነው? ማንን አደህይቶ ማንን ለማበልጸግ ነው?
ትርፉ በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ የሚከተል ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ችኮ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ነው፤ የተገኘውም ሀበት ቢለብሱት እከክ፣ ቢበሉት ቃር እየሆነ በጸጸት አለንጋ እየተገረፉ መኖር ነው


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles