Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የኦሮሞ ሕዝብ ተቋውሞ ትሩፋቶችና የአማራ ሕዝብ ለተቋውሞው ያሳየው ዝምታ … (ግዜነው ደም መላሽ)

$
0
0

 

strategic-goals_satenawእንደመነሻ ሰሞኑን በኦሮሞ ወጣቶች እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ትክክለኛው መንስሄ ምንድን ነው? ብለን እንነሳ።እንደሚታወቀው  በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ የነገሰው ጭቆናና ግፍ ሞልቶ መፍሰስ አንዱና ዋናዉ ነገር ነዉ። ቢሆንም ግን ይችን ቅፅበት  የሞት የሽረት ያደረጋት ነገር ምን ይሆን? ብሎ መጠየቅ ይገባልና የኔ ግምገማ ሁለት ኩነቶች ላይ ይወድቃል። እንቅስቃሴውን ባነሱት ወገኖች ዘንድ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት   “ማስተር ፕላንኑ መሬት ላይ ከዋለ  አርሶ አደር ኦሮሞዎች ካለ በቂ ካሳ ያፈናቅልና ለችግር ያጋልጣቸዋል”   የሚል መፈክር ከፊት  አንግቦ   ከጀርባ  ደግሞ  “ማስተር ፕላኑ የኦሮሞ ሕዝቦችን አፈናቅሎ በሌላ ሕዝብ በመተካት የአካባቢዉን Demography (የሕዝቦች ስብጥር) ይቀይረዋል።ይህ ደግሞ ኦሮሚያን ምህራብና ምስራቅ ኦሮሜያ በማድርግ ለሁለት አስተዳደር ስለሚከፍላት ለነገዋ ነፃ የኦሮሞ ሀገር ምስረታችን እንቅፉት ይፈጥርብናል” በሚል  ኦህዴድን ፣ ኦነግን ፣ እንዲሁም ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶችን በአንድ መስመር ያሰለፈው  የኦሮሚያን ኢንተግሪቲ(አንድነት) የማስቀጠሉ አጀንዳ ። ሁለተኛውና ማስተር ፕላኑን የቀረፀው የህዉሃቱ ቡድን ደግሞ  ላለፉት ዓመታት በአዲስ አበባም ሆና ከትግራይ ውጭ ባሉ ክልሎች ሲያደርግ እንደነበረው  “በልማትና በከተማ ማስፉፉት” ስም ነባር ባለ እርስቶችን እየነቀለ አንድም መሬቱን ቸብችቦ ዶላሩን ወደ ግለሰቦች ኪስና ወደ ወገኖቹ ለማሸሽ ፣ አንድም ዘሮቹንና ደጋፊዎችን ፌደራል ከተማዋ አካባቢ በማስፈር ከላይ የተጠቀሰውን የሕዝቦችን ስብጥር በመቀየር የፖለቲካ የበላይነቱን ለማስጠበቅ የወጠነው ተንኮል ዉጤት ነው። እንግዲህ በርህሱ የተነሱ ሀሳቦችን እነዚህ እውነታዎች ላይ ቁመን ነው የኦሮሞ ወጣቶች መሰዋት የሆኑበትን ትግል ዉጤትና “ አማራዉ ለምን ዝም አለ? እየተባለ የሚሰነዘረውን  ሀሳብ የምንቃኘው።

ከመጀመሪያው ነጥብ ስንነሳ ፦ ላለፉት ወደ አራት ለሚጠጉ ወራቶች በኦሮሞ ሕዝብ እየተካሄደ ያለው ደም አፋሳሽ ተቋውሞ የበርካታ ንፁህ ዜጎችን ሕይዎት የቀጠፈ፣ ብዙዎችን አካለ ጎዶሎ ያደረገ፣የእምነት ቦታዎች ላይ አደጋ ያስከተለ፣እንዲሁም አንዳንድ አካባቢ ደግሞ መጤ ናቸው የሚባሉትን አማራ ወገኖች ንብረት ያወደመ ክስተት ነው። ትግል መሰዋትነትን ይጠይቃልና ይህንን መሰል ነገሮች ይጠበቃሉ። ሆኖም ግን ልጆቻቸውን ባጡ ወላጆችና ወዳጆቻቸው ፣ አካላቸው የጎደለ ወንድም እህቶች ፣ በሕይዎት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት የወደመባቸው ወገኖች ጫማ ዉስጥ ሆኖ ለሚያየው ሰዉ እንዲህ በሩቁ “ትግል መሰዋትነትን ይጠይቃል” ብሎ እንደማለፉ ቀላል አይደለም። በተለይ ልጆቻቸውን ላጡት ወላጆችና ወዳጆቻቸው ክስተቱ አጥንትን ዘልቆ የሚሰማ ሀዘንን፣ከሕሌና የማይፋቅ ፀፀትን፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ የልብ ስብራትን የሚፈጥር ከባድ ነገር ነዉና የሚያመልኩት አምላክ ለወላጅና ለዘመዶቻቸው መፅናናትን፣ ለሟቾችም ምህረትን እንዲሰጥ ከልብ እመኛለሁ ። እፀልያለሁም።

ይህንን ካልኩ ዘንድ እንቅስቃሴውን ማን ነው የሚመራው? አላማ ምንድን ነው? እንዴት ይቆጫል? እና መሰል መላምቶችን በይደር ትተን ፣  በነዚህ ወጣቶች መሰዋትነት በኔ ግምገማ እስካሁን ተገኙ የምላቸውንና ለሁሉም ዜጋ ጠቃሚ በረከቶች ናቸው የምለዉን ብቻ ላንሳ።

ህውሃት ባሳለፍናቸው 25 የመከራ  ዓመታት ውስጥ እንደ ዘንድሮው ተፈትኖ አያውቅም።ይሄ “የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን” የተባለው ዝነኛና መዘዘኛ ፕሮጀክት የህዉሃትን አልጋ ያነቃነቀ፣ በሻብያ ተሰፍቶ የተሰጠውና ለአለፉት 25 ዓመታት በፕሮፖጋንዳ ጋጋታ ሲጎትተው የከረመው ሱሪዉ መዉለቅ መጀመሩን ያሳበቀ ወርቅ አጋጣሚ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚስማማበት ህውሃት እንደ ድርጅት አንድ ፕሮጀክት ቀርፆ ለመተግበር  የሕዝብን ይሁንታ ጠይቆ አያዉቅም። በትግበራ ወቅት ተቋዉሞ ቢገጥመውም በሕዝብ ግፊት ቀልብሶት የሚያቀው  ፕሮጀክት የለም። ስለዚህ የዚህ የኦሮሞ ሕዝብ ተቋውሞ ይህንን የህውሃት  ትቢት የሰበረና ለዚህም ጣፋጭ የትግል ፍሬው ላቅ ያለ አክብሮት ይገባዋል።  ሌላው በ 97 የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት እነ ዶ/ር ብረሀኑ ነጋ  የህውሃት ሰዎች  በሚለብሶቸው ውድና ዘመናዊ ሱፎች የተሸፈነውን ገመናቸውን ገላልጦ ድንቁርናቸውን አጋልጦ ነበር። ይህ የአሁኑ የኦሮሞወች ተቃውሞ ደግሞ የትቢታቸውን ልክ እንድናውቀው እረድቶናል። እንደ ስዩም መስፍን ፣ ስብሐት ነጋ ፣ አባይ ፀሀየ፣ ጌታቸው እረዳ እና መሰል   የህዉሃት ጋንግስተሮች  በርካታ ሕዝብ በተሳተፈባቸው ስብሰባዎች እየተገኙ፣ በትላልቅ ሚዲያዎች  ላይ  እየቀረቡ  በትቢትና  በማን አለብኝነት  ሕዝብ ላይ ፀያፍ ቃላቶችን  ሲሰነዝሩ እንጂ ሕዝብ ይቀየመናል በማለት በይፋ ሲያስተባብሉና ይቅርታ ሲጠይቁ አይቃወቅም ነበር። ዛሬ እንደ ውሻ የተፉትን መልሰው ሲዉጡ ፣ በአደባባይ በሕዝብ እግር ስር ወድቀው ሲንደባለሉ ማየት የሕዝብን ሀያልነትና ሁሌም አሸናፊነት እንዲሁን  የህውሃትን መፍረክረክ የሚያሳይ  አንድ አበይት ክስተት ነዉ።ይበል የሚያሰኝና ልምዱም በሌሎች ወገኖች እንደየ አስፈላጊነቱ መቀሰምና መተግበር ያለበት ነገር ነው።

ሌላውና ወሳኙ ነጥብ ደግሞ  የኙ የማሸማቀቂያ ፕሮፖጋንዳ አዲሱን ትውልድ ላይ ምንም ተፅህኖ እንዳልፈጠረ የታዘብንበት አጋጣሚ ነው። “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” እንዲሉ  ህውሃት  “ደርግን ያህል እስከ አፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት አሸንፌለሁ”ና ምን ይሳነኛል የሚለው ላለፉት 25 ዓመታት ትዉልዱ በፍርሀት ለማሸማቀቅ የተቸረቸረው ቱልቱላ የጀግንነት ታሪክ   “ጨፈቃ” በታጠቁ  ወጣቶች ተፈተነና ልቦለድነቱ ፀሀይ ሞቀዉ።በርግጥ ከታሪኩ ቅርበት አንፃር ህ.ው.ሃ.ት የጀግንነት ተክለ ሰውነቱን የቀረፀበት “በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ሀይል የነበረውን ደርግን አሸነፍኩ” የሚለው ትርክት ብዙም ሚስጥር ያልሆነና ጉልምስናና ከዛ ከፍ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚታወቅ ነገር ነዉ።። ደርግ ይከተለዉ በነበረው የፖለቲካ ፍልስፍና ከምህራቡ ሀያላን ሀገራት ጋር ጠላትነትን ፈጥሮ ነበር። እንደ ዘርን አማክሎ ባይሆንም  የሚገዛውን ሕዝብ በግድያ ፣ በአፈናና በእስር አሳሩን ያሳይ ስለነበር በሕዝቡና በገነባው ሰራዊቱ ሳይቀር አይንህን ላፈር ከተባለ ሰነባብቶ ነበር። በመጨረሻም ይህንን አጋጣሚ በተጠቀመዉ እንደ ሶሪያ፣ ቱርክ ፣ ኢራቅ እና መሰል አረብ ሀገራት  ከፍተኛ እርዳታ ይጎርፍለት በነበረው ሻብያ ተገፍፈታትሮ ፈራረሰ። እንግዲህ ይህ የታሪክ ክፍተት  እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ድረስ  በደርግ ሆነ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ድልድዮችን ከመስበር፣ ቤተ እምነቶችን ከመዝረፍ ፣ አንዳንድ ሰላማዊ ሰዎችን ከመግደል ባጠቃላይ ከሽፍታነት ያለፈ ቦታ ያልነበረዉና  እምብዛም  የማይታወቀው ህውሃት የተበታተነውን የደርጉን ወታደር ከሻብያ ጎን ተሰልፍ እያባረረ አራት ኪሎ ፊጥ አለ።እግዲህ ብዙ የተባለለትና እየተባለለት ያለዉ የ 17 ዓመቱ የህዉሃት የጫካ ቆይታ ከዚህ የዘለለ  አልነበረም። ህዉሃትን በአግባቡ የሚገልፀው ትላንት ያልነበረና በፕሮፖጋንዳ ሊያሳምነን የሚውተረተረው የጀግንነት የጦርሜዳ ዉሎው ሳይሆን በሀገር ላይ የፈፀመው ክህደትና ዛሬ በንፁሀን ዜጎች ላይ እየወሰደ ያለው ዘግናኝ ጨፍጫፊነቱ ነው። ጀግና እንኮን ሰላማዊ ዜጋን  እጅ የሰጠዉን ጠላቱ ላይ ሰይፉን አይመዝምና።የኦሮሞ ወጣቶች የተቋውሞ ፍሬ ይህንን ያስረገጠ ነውና አድናቆት ይገባዋል።በኦሮሞ ሕዝብ የተቋውሞ እንቅስቃሴ የተመዘገቡትን ድሎች በዚህ ልግታና “ አማራዉ ለምን ዝም አለ”የሚለውን ሀሳብ ላንሳ።

አማራው ለምን የተቋዉሞው አካል አልሆነም ?

አማራው ለምን የተቋዉሞው አካል አልሆነም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በሃያ አምስ አመት የህውሃት አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውን ግፍ በስማ በለው መስማት ብቻ ሳይሆን  አማራ ሆኖ መገኘትና ስሜቱን  መረዳትን ይፈልጋል። ጉዳዩን በሦስት ከፍየ ለማየት ልሞክር።

መጀመሪያውና ቀላሉ መልስ የሚሆነው አማራ በህውሃትና በአጋሮቹ  ከአያት ቅድመ አያቶቹ መሬት ሀብት ንብረቱን እየተቀማና ከእርስቱ እየተነቀላ ይሄ የአንተ ሀገርህ አይደለምና ወደ አማራ ክልል ሂድ ሲባል ፣ በጅምላ ሲጨፈጨፍ፣ከፖለቲካ ፣ከማህበራዊ፣ ከኢኮኖሚው መድረክ አድልሆ እየተፈፀመበት  ሲገለልና ሲሰቃይ  ለአማራ ሕዝብ ወገናዊነቱን ያሳየ አካል አለመኖሩ እንደ አንድ ምክንያት ሊወሰድ የሚችል ነው።

ሁለተኛው ምክንያት የሚሆነው ደግሞ ከመነሻው ለመግለፅ እንደተሞከረው የኦሮሞ  ሕዝብ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አላማው ግልፅና አሳታፊ  አለመሆኑ ነው። “ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ እንደ አንድ ቻይናዊና ኬንያዊ መኖር ነው የሚችሉት” ፣ “ኦሮሚያ የኦሮሞ ብቻ” የሚልና ኦሮሚያን እንድንገነጥል ተባበሩን አይነት እንቅስቃሴ ሌሎች ሕዝቦች እንዲደግፋ መፈለግ ስህተት ነው። ይህ አቆም የሁሉም ኦሮሞ ሕዝብ አቆም ነው ለማለት የሚያስችል ሁኔታ ባይኖርም ተቋውሞውን እየመራን ነው የሚሉት ግለሰቦች ግን ደጋግመው ሲያነሱት እየተሰማ ነውና በሌላው ሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬው ቢኖር የሚጠበቅ ነገር ነው። አንድ በወፍራሙ ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ አለ። የአማራ ሕዝብ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ሲባል ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ከፊት መስመር ተሰልፎ  ከትላንት በስቲያ የአባቶቹን ዙፋን አፍርሶል፣   ትላንት ደግሞ “ከደርግ የባሰስ ጨቋኝና አረመኔ አገዛዝ አይኖርም” በሚል ስሜት ለደርጉ ጀርባውን በመስጠት ህዉሃትን አይነት የሀገርና የሕዝብ ነቀርሳ አጅቦ አራት ኪሎ የተከለ ለዛም ውለታው ዛሬ አሳሩን እያየ ያለ ሕዝብ መሆኑን ነው። ስለዚህ የአሁን ነገሮችን በቅርብና በትግስት መታዘብ አንዳንድ ደፋሮች “አማራ ተኝቶል” ፣ “አማራ አከካሪው ተሰብሮል” እንደሚሉት ወይንም በታሪክ ተደጋግሞ በተከሰተው ውድቀት ተሰላችቶ ሳይሆን የማሕበረሰቡን በፖለቲካ መብሰል የሚያሳይ ነው።ዳግመኛ ተመሳሳይ ስህተት ላለመፈፀና  ለችግሮች ቆሚና የማያዳግም መፍትሄ ከመሻት የተወሰደ እርምጃ ነው።

ለአማራ እንደ ሕዝብ ህውሃትን የሚስተካከል ጠላት ገጥሞት አያውቅም ። በአጠቃላይ ሲታይ ህዉሃቶች ላለፉት 25 ዓመታት በሕዝብና በሀገር ላይ በርካታ ግፎችን ፈፅሞል።ነባር ሕዝብን ከርስቱ እየነቀሉ የኛ የሚሉትን ሕዝብ ተክለዋል። ከትግራይ ክልል አጎራባች መሬቶች አይናቸው ያየዉንና ቀልባቸው የወደደውን አካባቢ እየቆረሱ ወደ ታላቋ ትግራይ ቀላቅለዋል።  ከትግራይ ክልል ጋር ኩታ ገጠም ያልሆኑትን  ደግሞ  ቀድሞውንም ለዚሁ አላማ ተመልምለው ስልጣን እንዲይዙ በተደረጉ የየአካባዉ አድር ባይ ባለስልጣናትን በመጠቀም ያሻቸዉንና አቅማቸው የቻለውን መሬት ነጥቀው ሲያርሱ ፣ ከነሱ ከተረፈ ደግሞ በዝቅተኛ ዋጋ ለ”ኢንቨስተር” ቸብችበው ኪሳቸውን አድልበዋል። እንደ ሕዝብ ከታየ ደግሞ በህዉሃት የአማራን  ያህል በደል የደረሰበት ሕዝብ የለም።ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚረዳው፣ ህዉሃቶችና አጋሮቹም ደጋግመው እንደገለፁልን ዋናው ጠላታቸው የአማራ ሕዝብ ነዉ። አነሳሳቸውም “በአማራው መቃብር ላይ ታላቆን ትግራይ መመስረት” ነበረና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራ ወገኖችን አጥፍተዋል፣ ከርስታቸው እየተነቀሉ እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አስርዋል፣ ገርፈዋል ፣ገለዋል። ይህንን እኩይ ድርጊታቸውን ለመተግበርይረዳቸው ዘንድ አማራና የአማራ የሆኑ ባህሎችና ወጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ሰርተው አንዳን ወገኖችን ከጎናቸው ለማሰለፍ ችለዋል። ከነዚህ ወገኖች ግምባር ቀደሙ ደግሞ ዛሬ ባለተራ የሆነዉን የኦሮሞውን ማሕበረሰብ እወክላለው የሚለው ኦነገ  ዋናው ሲሆን ዛሬ ለምንገኝበት አጣብቂኝ ቀላል የማይባል ሚና ተጫውቶል። ደርግ በወደቀ ማግስት  ኦነግ  ኢትዮጵያን የሚያፈርሰዉንና አማራን እርስት አልባ የሚያደርገውን ቻርተር ከመቅረፅ ጀምሮ በትግበራ ላይም ቀጥታ ተሳታፊ በመሆን በርካታ አማራ ወገኖችን አርዶል።በአጠቃላይ ሲታይ  ኦነግ እንደ ቡድን ከተሰባሰበበት ግዜ ጀምሮ በሕዝቦች መካከል ቆሚ ጥላቻ እንዲፈጠር ከፍተኛ ደባ የፈፀመ ፣ ለኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይም ሆነ የአማራ ሕዝብ ዛሬ ለሚገኝበት ነባራዊው ሁኔታ  ከህዋትና ሻብያ ያልተናነሰ ተጠያቂነት ያለበት ቡድን ነው።እንግዲህ ይህ በዚህ ቡድን የተዘራው የፈጠራና  የጥላቻ ታሪክ  ሲደመር በህውሃት ጋባዥነትና አይዞህ ባይነት በአማራ ወገኖች ላይ የወሰዳቸው አሳዛኝና ዘግናኝ ድርጊቶች  በሁለቱ ታላላቅ ሕዝቦች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠርና ተባብረው እንዳይቆሙ እንቅፋት መፍጠሩን ማንም አይስተውም።

በሶስተኝነት መጠቀስ ያለበት ነጥብ ደግሞ የተቋውሞው አላም ግልፅና አሳታፊ ሆኖ ቢሆን ኖሮ እንኮን አማራን አማራ በብሔር አለመሰባሰብና አለመደራጀቱ ለንደዚህ አይነት ወሳኝ ወቅት አፋጣኝና የተቀናጀ መልስ ለመስጠት አመች አይሆንም። ያልተደራጀ ሕዝብ መንግስት አይደለም ድንጋይ መፈንቀል አይችልም።ያልተደራጀ ሕዝብ  ሌሎች ሲጠቁ ፈጥኖ ደርሶ አለኝታ መሆን ይቅርና እራሱን መከላከል አይችልም። መንግስት በጥላቻ፣ በትችትና በስድብ ወድቆ አያውቅም። በግለሰብ ደረጃ እዚህም እዛም  የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መንግስትን መስደብና መተቸቱ ዝናብ ሰዉን ለግዜው እንደሚያበሰብና ፀሀይ ሲመጣ ወዳይው የራሰው እንደሚደርቅ አይነት ነው።የዝናብ ጠብታ ተሰባስቦ ጅረት ፣ ጅረቶች ተሰባስቦ ታላላቅ ወንዞችን፣ወንዝ ተገድቦና በእንዲት ጠባብ ክፍተት እንዲወጣ ተደርጎ ተርባይን ዘውሮ ለሀገር ብርሀን የሚሰጥ ሀይል እንደሚፈጥር ሁሉ ሕዝብ በአንድ አላማ ዙሪያ ተሰባስቦና ተደራጅቶ በአንድ እዝ ስር ከዋለ የሚያቆመው ምድራዊ ሀይል  አይኖርም።እንግዲህ አማራ ተሰባስቦና ተደራጅቶ ሰይፍ የመዘዘበትን ጠላቱ ህውሃት እንዳይመክትና የሰሞኑን አይነት አጋጣሚ ተጠቅሞ አብሮ ህዉሃትን እንዳያሶግድ በህውሃትና በአንዳንድ ምሁራን ከፍተኛ ደባ ተፈፅሞበታል።

የአማራን መሰባሰብ አጥብቀው የሚዋጉት ቡድኖች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያውና ዋናው ህውሃት ነው።እንደሚታዎቀው ህውሃት፣ ሻብያና ኦነግ የትግል ማህቀፍ አድርገው ይንቀሳቀሱ የነበረው አማራን በጠላትነት በመፈረጅ ነበር። ይህንን አቆም ለመያዝ ያስቻላቸው ደግሞ አማራ እንደ ሕዝብ ተደራጅቶ እነሱ እንወክለዋለን በሚሉት ማሕበረሰብ ዘንድ የፈፀመው ግፍ ስለነበረ አይደለም። ይህንን የሚያሳይ አንዳች የታሪክ ምህራፍ የለምና። እንደዉም በታሪክ አማራ በአማራነት ተደራጅቶ ስልጣን የያዘበትና ሌሎችን በዘር ከፋፍሎ ያጠቃበት ግዜ የለም።ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቡድኖች አማራ ጠል አቆም ለመያዛቸው ምክንያት ያደረጉት የኢትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ ከአማራና አማራዊ አስተሳሰብ ጋር ስለሚተነትኑት ነው።የቡድኖቹ አላማ ኢትዮጵያን አፈራርሰው የየራሳቸው ጎጆ ለመቀለስ ስለሆን ይህ አላማቸው ግቡን የሚመታው ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው አማራውንና አማራዊ አስተሳሰብን በማጥፋ ነው ብለው አቆም በመውሰዳቸው ነው ጫካ በነበሩበትም ወቅት ሆነ ዛሬ ቤተመንግስቱን ተቆጣጥረው የአማራ ሕዝብ ላይ ግፍ እየፈፀሙ የሚገኙት።ይህንንም  በቀላሉ ለመረዳት ህዉሃት ስልጣን ከጨበጠ ባኋላ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ማየተ በቂ ነው። ህውሃት ኤርትራን ባርኮ ከሸኘ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሰፈነው ቋንቋን መሰረታ ያደረገው አስተዳደር በብሔር መሰባሰብና መደራጀትን የሚደግፍ ነው።ለዚህም ከአማራ ብሔር ውጭ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉት ሁሉም ብሔሮች በብሔራቸው ተደራጅተው በአንፃራዊነት በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ተደርጎል። ይህ ሕግ ግን አማራ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን አይታሰብም። በተለያየ ግዜ ከህውሃት ደንነት ቢሮ አምልጠው የወጡት መረጃዎች የሚሳዩት የአማራ ሕዝብ በአንድ እዝ ውስ መደራጀት ይቀርና አማራዎች ሁለትና ከዛ በላይ ተሰባስበው ሻይ መጠጣት  ለህውሃት ሰዎች ትልቅ እራስ ምታት መሆኑን ነው። በነ ፕ/ር አስራት ወልደየሱስ ተመስርቶ የነበረው ብቸኛው የአማራ ድርጅትን መአድ ህውሃት መሪውን ገሎ አባላቱን በመብራት እየለቀመ እንዴት እንዳጠፋቸው ሁሉም የሚያውቀው ነገር ነው።

የአማራን በብሔር መሰባሰብ የማይፈልገው ሁለተኛው አካል ደግሞ በግለሰብ ደረጃ በየተሰማሩበት ሙያ አንቱታን ያገኙ ሙሁሮችንና ከአማራው አብራክ የተገኙ ቀላል የማይባሉ ኢሊቶችን ያቀፈው ቡድን ነው። እነዚህ ወገኖች “አማራ ኢትዮጵያን እንደ ድርና ማግ  አሰባስቦ የያዘው ሕዝብ ስለሆነ የአማራ በብሔር መሰባሰብ ኢትዮጵያን ያፈርሳል” የሚል ትንተና ሲሰጡ ይሰማል። ድንቅ ነው መቸም ።ህውሀትና አጋሮቹ አማራና የአማራ አመለካከት ከጠነከር ኢትዮጵያን ማፍርስ አይቻልም ብለው አማራን ሊያጠፋ ሲታትሩ ምሁራኑ ደግሞ በተቃራኒው ይቆሙና አማራ ተደራጅቶና ጠንክሮ ከወጣ ኢትዮጵያ ፈረሰች የሚል አስቂኝና ግልብ ትንታኔ እየሰጡ ለህውሃት መሳሪያ ሆነው እናያለን።ለዚህም አላማቸው የአማራን ህልዉና እስከመካድ ድርስ ሄደው ሲዘባርቁ ታዝበናል። መቸም እነዚህ ቡድኖች በአማራ ሕዝብ ላይ እንደሰሩት ሴራ  የሚገርመኝና እንደግለሰብም የሚያበሳጨኝ ነገር የለም።ህዉሃትና አጋሮቹ የአማራን መጠንከር ከኢትዮጵያ ክብርና ዳር ድንበር መከበር ጋር ማገናኘቱ ታሪካዊ መሰረት ስላለው “አማራ ጠንክሮ የወጣባትን ሀገር ለማፍርስ ከባይ ይሆናል” ብሎ መስጋቱ እውነትና የሚጠበቅ ነገር ነው።የ”አማራን መጠንከር ከኢትዮጵያ መፍርስና መበታተን” ጋር የሚያያይዘው የሙሁራኑ ትንታኔ ግን ከየትኛው የታሪክ አንጎ ላይ እንደተመዘዘ እነሱ ብቻ ናቸው የሚያውቁት።

የኢትዮጵያ የታሪክ  ፀሀፊ የሆኑት አቶ ይልማ ዴሬሳ በፃፉት “የኢትዮጵያ የታሪክ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን”  በሚለው መፀሐፋቸው የሚነግሩን ከላይ የተገለፁት ወገኖች ከሚያቀርቡት ትንታኔ በተቃራኒው ነው።  ከአማራው አካባቢ የተነሱ ነገስታት ሀገሪቶን በመሩባቸው ወቅቶች ሁሉ በተለያየ ምክንያት ቀደምቶቻቸው ያጦቸውን እርስቶች ለመመለስና ግዛታቸውን ለማስፋት ሲተጉ እንጂ ሀገር ሲያፈርሲ ታሪክ መዝግቦ አያውቅም።  ለምሳሌ የአክሱም መንግስት ከወደቀና ንግስናው የዛጉዬ ወገኖች በተያዘበት ወቅት የኢትዮጵያ ድንበር ከሰሜን እስከ ደቡብ እንደ መቀነት በቀጭኑ የተዘረጋ ነበር። በዮዲት ወርራ እንዲህ ተሸማቆ የነበረውን የኢትዮጵያ ድንበር በ1284ዓ.ም ከዛጉዌዉ የመጨረሻ ነጋሲ ከንዋይ ክርስቶስ ከተረከበዉ ከይኩኖ አምላክ  ጀምሮ በዮዲት ወረራ ወቅት የተበታተኑ እርስቶች የተመለሱበት፣የስነፅሁፍና የኪነ ጥበብ ስራዎች እድገት ያሳዩበት፣  ገዳማትና አድባራት የተስፋፉበት ወቅት እንደነበረ ነው።እነ አምደ ጽዮን ፣እነ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ፣እነ አጼ ናዖድ አይነት ታላላቅ ነገስታት የኢትዮጵያን  የጥንት እርስት እያስመለሱ ከአክሱም ነገስታት በደረሱበት ስልጣኔ ደረጃ የደረሱበት፣ አክሱሞች እንኮን ያልደረሱበት ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በህንድ ዉቅያኖስ ማዉለብለብ የቻሉበት ዘመን ነበር።ይህ የኢትዮጵያ ታላቅነት እስከ  አጼ ልብነ ድንግል  ድርስ የተራዘመ ነበር። በዛን ዘመን የቱርኮች አቶማኑ ኢምባየር ጉልበቱ የፈረጠመበት ወቅት በመሆኑና በክርስቲያን ሀገራት “እስልምናን በጎራዴ” የሚለው  ጅሐድ የታወጀበት ወቅ ነበር። በዚህ ወቅት  የሐረሩ አህመድ ቢን ኢብራሂም ኤልጋዚ (ግራኝ) ከቱርኮች በዘነበለት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ፣ መድፍና የሰው ሀይል በመታገዝ አጼ ልብነ ድንግልን አሸንፎ ኢትዮጵያን እንዳልነበረች አድርጎ ሀብትና ቅርጾቾን ዘርፎ በእሳት አጋየ።በመጨረሻው ግራኝ በአጼ ገላውዲዮስ ተሸንፎ ቢገደልም የክርስቲያን መንግስት በመዳከሙና በነ ሚካሄል ስውል ሸር ኢትዮጵያ የዛሬው አይነት መበታተን ደርሶባት የነበር ቢሆንም ከዛ በኋላ የተነሱት  በነ አፄ ቴዎድሮስ፣ በነ አፄ ምኒሊክ፣ በነ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ መልሳ ማንሰራራትና መጠናከር ጀምራ እንደነበር የቅርብ ግዜ ታሪክ ነው። ይህን የሚያሳየን ከአማራው አካባቢ የሚነሱ ነገስታት በየዘመናቸው የሚተቹበት ነገር ባይጠፋም የሀገርን ልዋላዊነት በተመለከት ግን አንዳች የሚነሳ እፀፅ አለመኖሩን ነው።

ሌላው እነዚህ ግለሰብና ቡድኖች  “አማራ በብሔር ከተደራጀ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች”  ከሚለውን አስተምሮት ጎን ለጎን አማራ አሁን ባለበት ነባራዊዉ ሁናቴ እንዴት አድርጎ የኢትዮጵያን መፍርስ እኅደሚታደግ ሲያስረዱ አይታይም። መችም ህውሃት በሚዘዉራት ኢትዮጵያ ውስጥ ባሳለፍናቸው 25 ዓመታት በአማራው ላይ ያልደረሰ የግፍ አይነት አለመኖሩን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚረዳው ጉዳይ ነዉ። ሲጀመር አማራው ባልተወከለበትና ሀሳቡን ባላዋጣበት “ዋና ጠላታች አማራ ነው” ብለው ሰነድ አዘጋጅተውና ጦር መዘው ደርግን በተኩ ጠላቶቹ በሆኑ በነ ህዉሃት፣ ሻብያና ኦነግ በተረቀቀ ሕገ መንግስት ስር የሚተዳደር ፣ ከፖለቲካዉ ፣ከማህበራዊዉ፣ ከኢኮኖሚው እና ከመሳሰሉት ዘርፎች ዉስጥ የተገለለ ሕዝብ መሆን ይታወቃል። ሌላው ቀርቶ በአንድነት ስም የሚሰባሰቡ ድርጅቶች በህዉሃት እንዲበታተኑ የሚደረገው የአማራ ጅርጅቶች ናቸው የሚል ታፔላ እየተለጠፈባቸው ነው።ይባስ ብሎ ዛሬ ዛሬ ደግሞ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንኮን እየተደራጁ ባሉት እንደ ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር አይነት ድርጅቶት “በአማራነት እንዳንታማ” በሚል አመራራቸውን ከአማራው ሲያፀዱ እየታዘብን ነው። እና አማራ እንዲህ በተገለለባት ሀገረ ኢትዮጵያ አማራ እንደ ዛሬው ተበታትኖ እራሱን በማያድንበት ደረጃ መገኘት እንዴትና በምን አስማት ለኢትዮጵያ አለኝታ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል??ብሎ ለሚሞግት አካል ምላሽ የሚሰጥ አይኖርም።

ለማጠቃለል ይህን ሀሳብ እያራመዱ ያሉ ወገኖች የህዉትን አማራንና የአማራን አመለካከት የማዳከም አጀንዳ እያራገቡ ነዉ። አማራዉን ተበታትኖ እንዲጠቃና ጨርሶም እንዲጠፋ ድንጋይ እያቀበሉ ነዉ። እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች ሌላ የተደበቀ አጀንዳ ከሌላቸው የያዙት አቋም ስህተት ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል ።  ልብ ገዝተውና አቆማቸውን አስተካክለው አማራን እያሰባሰቡ ለሚገኙት እንደ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት (ሞረሽ)  አይነት ሲቪክ ማህበራትንና እንደ የቤተ አማራ ንቅናቄ(ቤአን) ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ቢደግፋ የመከራ ቀኖችን ማሳጠር ይቻላል ብየ አምናለሁ።

ቸር እንሰንብት!!

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles