የጭንቀት ስሜት ደረጃው ይለያይ እንጂ በእያንዳንዱ ሰው ላይ ያጋጥማል፡፡
በአብዛኛው ከድብርትና አብዝቶ ከማሰብ ይመነጫል የሚባለው ጭንቀት፤ ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ ዘመድ፣ ከጓደኛ እና ከስራ ባልደረባ ጋርም ያቃቅራል።
ብዙ ሰዎች ላይ ትምህርት ወይም የስራ ፈተና ላይ መቀመጥ፣ በህክምና ወቅት፣ ለፈተና ቃለመጠይቅ መቅረብ፣ አልያም አዲስ ስራ ሲጀመር የመረበሽና የጭንቀት ስሜት ይስተዋላል።
ይህ ቀለል ያለ የጭንቀት ስሜት ሲሆን፥ ከ6 ወራት በላይ ከዘለቀ ግን ለተባባሰ የጭንቀት ህመም ያጋልጣል።
እንቅልፍ ማጣት ወይም ማብዛት፣ ድካም፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ አካባቢ ህመም፣ የምግብ እንደ ልብ አለመዋጥ፣ የፍርሃት ስሜት፣ ግልፍተኝነት፣ አለመረጋጋት ወይም መቅበጥበጥ፣ ቶሎ መበሳጨት፣ በከፍተኛ ላብ መጠመቅ፣ ማቅለሽለሽ እና ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ምልክቶቹ ናቸው።
ከዚህ ባለፈም የልብ ምት መጨመር እና ሽንት ቤት ማብዛት ወይም ቶሎ ቶሎ መጠቀምም የዚሁ ችግር ተጠቂ በሆኑት ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶች ናቸው።
እናም ይህ ችግር ሲከሰት ምን ማድረግ አለብኝ ካሉ ደግሞ፤
ሰውነትን መታሸት፦
አካልንና አዕምሮን ዘና ለማድረግ እንዲሁም ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት ስለሚረዳ መታሸት መልካም አማራጭ ነው።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፦
መረበሽን ለማስወገድ፣ በአካል ብቃት እንስቅስቃሴ ወቅት ጡንቻን ለማዝናናት፣ ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘትና ለመንፈስ መረጋጋት የሚረዱ ኬሚካሎች ይመነጫሉ።
እናም በየእለቱ ለተወሰነ ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለዚህ ችግር መፍትሄነት ይረዳል።
ጤናማ አኗኗር መከተል፦
የጭንቀት በሽታን ከሚያባብሱት ቡና፣ የአልኮል መጠጥ ፣ ሲጋራ እና መሰል ልማዶች መቆጠብ፡፡
አመጋገብን ማስተካከል፦ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና አመጋጋብን አለማስተጓጎል።
በቂ እንቅልፍ ማግኘት፦ በሰአቱ እንቅልፍ ማግኘት እና የእንቅልፍ ሰአትን አለማዛባት።
ሃሳብዎን ለሌላ ማጋራት፦ አንድ ነገር ላይ ብቻዎን ያለ መፍትሄ አለመብሰልሰል፤ ከዛ ይልቅ ለቅርብ ወዳጀዎ ጉዳዩን ማማከር ቀለል ያለ ስሜትን ይፈጥርልዎታል።
ጊዜ ወስዶ ጉዳዩን በአግባቡ ማጤንና ትንሽ የመፍትሄ ጊዜ ማበጀት መልካም እንደሆነም ይነገራል።
ለራስ የሚደረግ ጥንቃቄ እና ደህንነትን ከሚያደርጉት ወይም ከሚከውኑት ስራ አንጻር እንዴት እያስኬዱት እንደሆነ መመልከትም ተገቢ ይሆናል።
ከምንም በላይ ግን የሚያስጨንቅዎት ጉዳይ መፍትሄ እንዳለው ማመንና ያለ መፍትሄ በዛ ጉዳይ ላይ ብቻ ማተኮሩ አግባብ አለመሆኑን አምኖ መቀበል።
ከ
ዚያ ይልቅ ሞክረው ያልተሳካ ከሆነ ሌላ መፍትሄ ማበጀት እንጅ ነገሩን እየደጋገሙ ራስን ማስጨነቅ አግባብ አይደለም።
source፦ helpguide