Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የቅድሙ ‹‹ ጉድሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ ›› እንዲሉ ሆነብኝ – ግርማ በቀለ

$
0
0

1483335_774412919325832_8269392789268101621_nዛሬ ቀን ላይ የደቡብ/ደኢህዲን ምሁራን ‹‹..በሆዳቸው የሚገዙ…›› መባላቸው ያሳደረብኝን ቁጭትና ዛሬስ በዚያው ቦታ ይገኙ ይሆን ብዬ አደባባይ መውጣቴን ታስታውሳላችሁ፡፡ እኔ ምሁራኑ በስብሰባ ላይ ሆዳም መባላቸውን እንዴት ተሸከሙት ብዬ ስጠይቅ ‹‹ ከምሁራኑ›› አልፎ የኦሮሚያና የደቡብ ድርጅቶችና አባላቱ በተጻፈና በተሰራጨላቸው ሰነድ ‹‹ዝንቦች›› መባላቸውን ማምሻዬን አነበብኩ፡፡ ያነበብኩት ‹‹ጉድሽን…›› አስባለኝ፣ግጥምጥሞሹ አስገረመኝ፡፡ ጽሁፉ እንዲህ ይነበባል፡፡

‹‹…ሥልጣን የያዝን እንደመሆናችን ወደእኛ የተጠጋ የተለያዩ ጥቅሞች ማግኘቱ የማይቀር ነው፡፡ማር ባለበት አስቀድሞ የሚያርፈው ዝንብ ነው፡፡ስልጣን ባለበት አስቀድሞ የሚያንዣብበው ከስልጣኑ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልገው ነው፡፡ በደቡብና ኦሮሚያ አባላት በብዛት እንመለምላለን፡፡ዝንቦች ሆነው ይገኛሉ፡፡እናራግፋቸዋለን፡፡ ስ ሆኑ ናቸውእንደገና እንሞላለን፤ዝንብ ሆነው እናራግፋለን፡፡…›› የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የአመራር ጥበብ- የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፡፡
ጽሁፉ ከላይ ያልኩትን ተረት ቢያስታውሰኝም ሁለት የምንጠቀምባቸውን አገላለጾች ትክክለኛነት አጠናከረልኝ፡፡
የመጀመሪያው — ‹‹ህወኃት/ኢህአዴግ›› እያልን የምንገልጸው ነው፡፡ አቶ መለስ ‹‹ስልጣን የያዝን እንደመሆናችን….. ወደእኛ የተጠጋ… ›› ያሉት ግልጽ ስለሆነ ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡

ሁለተኛው — ከህወኃት ውጪ ያሉትን የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ‹‹የራሳቸው ህልውና የሌላቸው የህወኃት ስሪት ተላላኪና ጉዳይ ፈጻሚ …›› በማለት የምንገልጸው ነው፡፡ ይህንንም ‹‹ .. በደቡብና ኦሮሚያ አባላት በብዛት እንመለምላለን…ዝንብ ሆነው ይገኛሉ፣ እናራግፋቸዋለን … እንደገና እንሞላለን…እናራግፋለን›› የሚለው አገላለጻችንን አጠንክሮ ያስረግጣል፡፡

ወገኖቼ ሆይ ይህን እያነበባችሁ ነው እስከዛሬ የዘለቃችሁት…. በእጅጉ አዘንኩላችሁ፤ ….. ደግሜ ዛሬስ – በሌላው በብዛት ‹‹የምትፈለፈሉ›› ዝንቦች ናችሁ ወይስ …? ብዬ ልጠይቅና የቅድሙን ምክሬን አስታውሼ – ለእኔ ማንበቤም ከብዶኛልና እንዲህ ለሚኖሩት እየጸለይኩ፣ለራሴ ‹‹ጉድና ጅራት..›› በሚለው እየቆዘምኩ ወደ መኝታዬ ላምራ፡፡

በቸር ያገናኘን፡፡

14/06/08


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles