Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በአምቦ የ9 ዓመት ልጅ በህወሃት ታጣቂዎች ተገደለ።

$
0
0

10295666_1080845151937391_5176747592830511208_nበአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ ከሦስት ወር በላይ አስቆጥሯል፡፡

በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በጋራ ሙለታ ግራዋ ወረዳ ዛሬም የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደነበር፤ ዛሬ በአምቦ የአዋሮ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በጥይት መገደሉን የዐይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ተናግረዋል።

በተጨማሪም እዚያው አምቦ ውስጥ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ቃጠሎ መነሣቱን፣ በተጨማሪም ምዕራብ አርሲ ውስጥ በሻሸመኔ ወረዳ አጄ በተባለች የገጠር ከተማ ውስጥ የሚገኝ እሥር ቤት ተሰብሮ እሥረኞች እንዲወጡ መደረጉን የሬዲዮው የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

በተለያዩ የኦሮሞ ከተሞች ቅዳሜም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩና በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭትም መስተዋሉን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

ነቀምት አካባቢ በተኩስ ልውውጥ የታጀበ ግጭት እንደነበረ፣ በምሥራቅ ሸዋ ጉደር አካባቢ ደግሞ ትናንት ምሽት ላይ በተቃዋሚዎች እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል በተነሣ ግጭት የሁለት ሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ ውጥረቱ አሁንም እንደበረታ ነው፡፡

በጉደር፣ በአምቦ፣ በቶኬ ወረዳ ቶኬ ከተማና በጎሮ ሶሌም እንዲሁ ግርግርና ግጭቶች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

ጉዳር ውስጥ ትናንት ምሽት ላይ በነበረ ግጭት የሁለት ሰው ሕይወት ጠፍቷል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በምሥራቅ ሃገርጌ ግራዋም ግጭቶች የነበሩ ሲሆን ደቡብ ኦሮምያ ውስጥም የአባባቢው ነዋሪዎች ለአንድ ባለሃብት ተሰጥቶ የነበረን አንድ ሺህ ሄክታር የሚሆን መሬት እራሣቸው በሽማግሌ መከፋፈላቸውን ናሞ ያነጋገራቸው የአካባቢው ሰዎች ገልፀዋል፡፡

ነገሌ ከተማ ውስጥ ዛሬ ተደርጎ የነበረ ሰልፍ ያለ ግጭት መበተኑም ተገልጿል፡፡

በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች ተመሣሣይ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩም ተሰምቷል፡፡ (መጠነኛ ለውጥ በጎልጉል የተደረገበት መረጃ ምንጭ: አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles