Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

 በማር የተለወሰ እሬት ፡   በጳጳስ የተሽፈነ ክህደት፡ ለአቡነ መልኬጼዲቅ የተሰጠ መልስ – ከ አባ መላከ ሕይወት ሲያትል  

$
0
0

 

  • sddefaultአቡነ መልከፄዴቅ፡ የስደተኛው ሲኖዶስ ፀሐፊ፡ “የቅዳሴያችን ይዘት” በማለት በጻፉትና በአሰራችጩት በ140 ገጽ በተካተተው ከቁጥር 45- 48 ገጽ በሰፈረው ድንግል ማርያምን በንቀትና በኑፋቄ ብቻ ሳይሆን ፍጹም ክህደት የተሞላበትን፡ በመቃወም መልስ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው።

አባታችን ፡ እርስዎ ከንጉሱ የዙፋን ችሎት፡ እስከ አሜሪካ ስደት ባለስልጣን! በመሆንዎ በጣም ደስ ይላል በሌላ በኩል ጓደኛ የማይገኝልወት የእድሜም ባለፀጋ በመሆነዎ በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ። በቅድስት ድንግል ማሪያም ወላዲትአምላክ ላይ ግን በጣም እያዘንኩ ልቃዎምት ተገድጄ አለሁ። ማርያም ጥንት አብሶ፡ ከሄዋን የወረስችው መርገመ ስጋ አለባት የሚለውን መጽሐፍዎን አንብቤው አለሁ። በዚህና በሌሎች ቤተክርስትያናችን ቀኖናዎች በአለዎት ስህተት ላይም ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ ሲያጋልጥዎትና ሲያወግዝዎት እርስወም የሰጡትን መልስ ሰምቸአለሁ። ስሜ ሃብተማርያም፡ የአባቴ ገ/ማርያም፡ የእናቴ ወለተ ማርያም፡ ሌሎችም ዘመዶቼ ( ቤተሰቦቼ)በማርያም ስም እየተጠራን እንዴት የማርያም ጠላት (መናፍቅ) እባላለሁ የሚል ሲሆን

1• የእርስዎና የኔ ወዳጅ የሆነ ግለሰብ ጥንተ አብሶ የሚለውን ቃል እንዲያሳትምላቸው ረቂቁን ለመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ሰጥተውት ስለነበር እርሱም ይችን ቃል አስገብቶ ጉድ ሰራቸው ሲል ስለነገረኝ የነበረኝን ጥላቻ ቀንሶልኝ ነበር በአጋጣሚ ግን አሜሪካ ለጉብኝት መጥቸ በነበረበት ወቅት ለወራቶች ከርስዎ ጋር በእንግድነት፡የመቀመጥ እድል ስለነበረኝ የማሪያም ጠላት መሆንወን አረጋገጥኩ።

ምክናያቱም እርስዎ በሚመሯቸው ወይም ወገኖችዎ በአሉበት፡ ዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ገብርኤል፡ ዋሽንግተን ሲያትል ቅ/ገብርኤል፡ ፖርትላንድ ቅድስትማርያም ፡ እራስዎ ያሉበት ኦክላንድ መድሃኔዓለም ፡ በሌሎች አብያተ ክርስትያናት ፡ የድንግል ማርያም ስም ጭራሹን እንዳይወሳ (እንዳይነሳ) በማገድ ስሟ ጭራሹን አይወሳም፡ የማንኛውም አድባራት ገዳማት እና አብያተ ቤተክርስትያን መክፈቻ እና መዝጊያም፡ ድንግል ናት ፡ የእርስዎ ቀኖና (መመሪያ) ግን በወንጌል ተከፍቶ በፕያኖ ይዘጋል። ጭራሹን በ 2003 በአዘጋጁት ከላይ በተጠቀሰው መፀሐፍ ላይ ሐጸ፡ ኑፋቄ ጦርወን ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፡ ቤተክርስትያን ሰንዝረዋል ።

 

ይህውም፡ ቅዳሴ ማርያምን በመንፈስ ቅዱስ አባህርያቆስ አልደረሰውም የኢትዮጵያውያን ድርሰት ነው በማለት ማረጋገጫ ይሆናል ሲሉ የጠቀሱት ህርያቆስ ግብፃዊ ቢሆንም በግብፆች በቅዳሴያቸው ከአለመኖሩም በላይ ከነአካቴው አያውቁትም የቃሉም አሰካክ ኢትዮጽያዊ እንጅ የተተረጎመ አይመስልም ብለዋል።

መልስ!

ይህን ቅዳሴ ማርያም በግብፆች ቢኖርም ባይኖርም ቢያውቁትም ባያውዉትም በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አባህርያቆስ ለቅድስት ድንግል ደርሶታል፡ ለግብጻውያን ያልተሰጠ ፀጋ ለኢትዬጵያን ተሰጥቷል ።

ድንግል ማርያም መንፈስ ቅዱስ ይመፅ ላእሌኪ ፡ ብሎ ገብርኤል በተናገረው መሰረት መንፈስ ቅዱስን ሳትቀበል በእርሷም አማካኝነት በኤልሳቤጥ እና በፅንሷ መንፈስ ቅዱስ ከማደሩ በፊት፡ ሐዋርያትም በፅርሃ ፅዮን( እየሩሳሌም) መንፈስ ቅዱስንም ከመቀበላቸውም በፊት ኢትዮጵያ መንፈስ ቅዱስ ያደርባት ናት። ይህም ይታወቅ ዘንድ ቅዱስ ዳዊት ነቢየ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊሃ ሀበ እግዜአብሔር ! ሲል አረጋግጦላታል። ሀገረ እግዚአብሔር በመሆንዋም የቃለአብ ክርስቶስ ርደቱ፡ ፅንሰቱ፡ ልደቱ፡ ጥምቀቱ፡ አስተርዮቱ፡ ህማሙ፡ ስቅለቱ፡ሞቱ፡ ትንሣኤውና እርገቱ በምድረ እስራኤል እንጅ በምድረ ኢትዮጵያ አይደለም። መድሃኔዓለም ክርስቶስ ለምፅ ያነፃበት፡ እውር ያበራበት፡ሙት ያስነሳበት፡ ውሃውን ወይን ያደረገበት፡ በምድረ እስራኤል እንጅ በምድረ ኢትዮጵያ አይደለም። 4ቱ ወንጌል በአጠቃላይ አዲስ ኪዳን መጻህፍት በምድረ እስራኤል እንጅ በምድረ ኢትዮጵያ አልተፃፈም።

ኢትዮጵያ ግን ሀገረ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያደረባት በመሆኗ አይሁዶች ያልተቀበሉትን ፀጋ እርሷ ተቀብልላለች። ያስተማራት መንፈስ ቅዱስ እንጅ አዲስ ኪዳንን፡ ወንጌልን፡ ከሃዋርያቶች ወይም ከአርድእቶች አንዱ አስተማራት አይባልም የሃዋርያትን አይን አይኗ ፡ የሃዋርያትን ጀሮ ጀሮዋ ፡አድርጋ እንደተቀበለችው ሁሉ ቅዳሴ ማርያምንም፡ አባ ህርያቆስ፡ ጎስአ ልብየ፡ ከአለ በኋላ ወእቀውም ዮም በትህትና ወፍቅር ቅድመዝንቱ ቁርባን ወቅድመዝንቱ ማዕድ ፡በማለት ትህትናውን ፍቅሩን፡ ኦ አበዊነ መምህራን እለመትልወ ሐዋርያት፡ እያለ ከእርሱ በላይ ያሉትን መምህራን ክብር አክብሮ፡ ኦ ማርያም በእንተ ዝ ናፈቅርኪ ወነአብየኪ እስመ ወልደኪ ለነ መብዓ ፅድቅ ዘበዓማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን ፡ በማለት ከእርሷ በተገኘው የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውና ደሙ የመጨረሻ ህይወት ሰጭ መሆንዋን ቁልጭ አድርጎ ቢያቀርብላቸውም፡ ደደብ፡ ደንቆሮ ፡ የተፃፈውን ፡ ማንበብ የማይችል ፡ ዛሬ ደግሞ እንግዳ ድርሰት ደረስኩ ብሎ የአረፋ ጀጀባውን፡ የቆጥ የባጡን፡ይቀባጥራል ከማለት በስተቀር አልተቀበሉትም ። እስራኤል ወንጌልን ሳትቀበል ኢትዮጵያ እንደተቀበለችው ሁሉ ግብፅ፡ አምና ያልተቀበለችውን፡ ኢትዮጵያ ተቀብላ፡ ብዙ ተአምር እየሰራችበት ትገኛለች። ይህውም ይታወቅ ዘንድ፡ እጠቅሳለሁ ።

ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘይፄሊ !   ረሰዮ ህብስተ ሣሙኤል ዘሀቅለዋሊ ! •     የጥቅሱ መጨረሻ።።።።፡፡፡፡፡፡

 

  • ይህም ማለት ፡ የዋልድባው አባት፡ አቡነ ሣሙኤል ፡ በረኸኛው በቅዳሴሽ ፀሎት እየፀለየ ፡ ውሀውን ቢባርከው፡ ውሀውን፡ ወደህብስትነት፡ ቀይሮ ቆርቦ አቆረበ፡ወይም የተራቡትን፡ መገበ ማለት ነው።

 

ለሌሎች ቅዳሴ ያልተሰጠ ክብር ለዚህ መጽሐፍ ተሰጠ። ይህውም ከእሳት ቢጥሉት አልተቃጠለም፡ ከውሃ ቢጥሉት አልተደመሰሰም፡ ከህሙማን ቢጭኑት ፈውሷል፡ ከሙታን ቢጥሉት( ቢጭኑት) አስነስቷል ፡ እየተባለለት ነው ሲሉ የኑፋቄ ሀሳብ ያስቀመጡት፡ የመጹሐፉ ሀይል ሳይሆን ልጇ ወዳጇ አማኑኤል፡ በሰጣት ሀይለ ረድየት መሆኑን ቆም ብለው ያስቡ። በውጭ ሐገር ተደረሰ የተባለውም ፡ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው ብለዋል። ለመሆኑ? ድጓ፡ ዝማሬ፡ መዋስእት የተደረሰው በኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ ሲሁን ሰአታት የተባለውም መጽሐፍ በኢትዮጵያዊው አባ ዘ ጊወርጊስ የተዘጋጀ መሆኑ ግልጽ ነው። እነዚህን መጻህፍቶች የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ ክርስትያን ጠርዛ፡ ደጉሳ ፡በክብር ይዛ፡ ከምትገለገልባቸው በስተቀር በሀገር ውስጥ የተደረሰ ነው ብላ፡ ንቃ ፡ ከበሐር ያልጣለቻቸው መሆኑን አያውቁም ወይ? ለመሆኑ የአንዱን ሐብተ ጸጋ ለሌላው ማስተላለፍ የወንጀሎች ወንጀል ነው። አባህርያቆስ በህይወተ ስጋ ቢኖር በኮፒ ራይት ሊከስወት በቻለ ነበር። የተረት ተረት ቅዳሴ ነው ብለዋል። ለዚህም ኑፋቄዎን ሲያስቀምጡ ቅድስ ኤፍርኤም ሶርያዊ፡ አባህርያቆስ ብህንሳዊ፡ ቅዱስ ያሬድ አክሱም መደባይታብር፡ የቱን ከየት? ከማለትወም በላይ፡ ሲቀጥሉ፡ ።።።።።።

ቅዱስ ኤፍረኤም በ 4 ኛው መቶ ክ/ዘመን   ቅዱስ ያሬድ በ 6 ኛው መቶ ክ/ዘመን   ባህርያቆስ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ስለዘህ አረፍተ ዘመን ከግድግዳና፡ ከግንብ ስለሚከልል የሀገር ርቀትና ክፍለዘመን ይገድባታል፡ ከማለትወም በላይ የቅዱስ ኤፍሬም ቋንቋ ሱርስት ፡ የአባ ህርያቆስ ቋንቋ ኮፕቲክ ፡ የቅዱስ ያሬድ ቋንቋ ግዕዝ፡ በምንም ሊያግባባቸው የሚችል ነገር የለም፡ ደመናትም ከሩቅ ሀገር እስከ ኢትዮጵያ ሊታዘዙላት እንደማይችሉ ፡ችሎታም እንደለላት በማድረግ፡ ንስጥሮሳዊ! ኑፋቄ አስቀምጠዋል። •

መልስ።።።።

  • ቋንቋን በተመለከተ፡ የኤፍሬም ሶርያዊ እና፡ የባስልዮሰ ዘቂሳርያን ታሪክ ይመልከቱ። ስለደመናት መታዘዝን፡ በደመና ስታርግ ቶማስ ከደመናዉ ደንግጦ ሊወድቅ ሲል እንዳይወድቅ እንዳደረገችለትና እርሷንም ደመና ይዟት እዳረገች ይመለከቱ። ሙታንን ስለማስነሳትም ፡ ያች፡ ከአዋልደ፡ ንግስት ውስጥ ሀጢአቷን ስትመዘግብ ቆይታ በዚህ ያለው ይሰረዝልሽ በለኝ ብላ ፡ኤፍሬምን ስትጠይቀው ስለትህትና ይህ ለባስልዮስ፡ እንጅ ለኔ አይቻለኝም፡ ብሎ ወደባስልዮስ እንደላካትና ባስልዮስም፡ ሃጢያቷን ከደመሰስላት በኋላ አንዲት ፡ በመቅረቷ ይህስ ለኤፍሬም እንጅ ለእኔ አይቻለኝም፡ ብሎ ስለትህትናው ወደ ኤፍሬም እንደላካት፡ ኤፍሬምም ለኔ አይቻለኝም ለባስልዮስ ነው፡ ነገር ፡ ግን አሁን ስትደርሺ ሞቶ ስለምታገኝው ሳትጠራጠሪ፡ ከአስከሬኑ( ከመቃብሩ) ጣይው ስለአላት ስትደርስ ሞቶ ሊቀብሩ ሲወስዱት አግኝታ፡ ከአስከሬኑ ላይ እንደጣለችና ድንግል በአስከሬኑ ላይ ፡ሀይለ መንፈስ ቅዱስን አሳድራ ሃጢአቷ ፡እንደተሰረየላት ይህንን ይመርምሩ ይወቁ ። ሁለተኛም ኤፍሬምና ስምዖን ዘአምድ፡ መምህራችን ድሮ ይህን አላስተማረንም፡ አስተምሮናል እንጅ በሚል በሁለቱ ክርክር ከመምህራቸው መቃብር ሄደው ሲጠይቁት ቅድመ ሞትየኒ ሰላም ለርኪ ከመስምኦን ዘአምድ ፡ ወድህረሞትየኒ ሰላም ለኪ ኦ ቅድስት ድንግል ወኩሉ አእፅምትዮ ይብሉኪ ወይዌድሱኪ ከመ ኤፍሬም ሶርያዊ ሲል አስሩን የእጁ ጣቶች እንደፋና አብርታ አስነስታ አስመስክራዋለች። ልጇ መድኃኔዓለም ክርስቶስም ከ1 ሺህ ዓመት በላይ የበሰበሰውን፡ የረገፈውን ፡ የሙሴ አፅም ለምስክርንት በደብረታቦር አስነስቶት የለም እንዴ ? ታድያ የአንድየን እናት እርስዎ ከነጳውሎስ፡ ጨርቅ እንዴት ሊያሳንሷት ይሞክራሉ? መቸምበድፍረት የሚቃወምዎት አለቃ አያሌው ታምሩ፡ ሞተዋል ብለው ጊዜ ጠብቀው የሰነዘሩትን የክህደት መፅሐፍ፡በጳጳስ ላይ ያለ ክህደት፡በማር፡የተለወሰ፡እሬት፡እንዳይሆንብወት፡ይህን፡ የሚያስተባብል መጽሐፍ አዘጋጅተው፡ ካላስተላለፉ እና ይህን ማድረግ ካልቻሉ ፡ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ/ዋህዶ ቤ/ ክርስትያን በህይወትወ እንደማትቀበልዎትና ከህይወት በኋላም ቢሆን ጸሎተ ፍትሀት እንደማታረግልዎት ላረጋግጥልወት እወዳለሁ። •     •    ወስባሐት፡ ለእግዚአብሔር።

Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles