Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የመፍቻ ትዕዛዝ የደረሰው ወህኒ ቤቱ ሌላ ትዕዛዝ እየተጠባበቀ ነው – ዳዊት ሰለሞን

$
0
0

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ወህኒ ቤቱ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ትናንት እንደደረሰው አረጋግጧል
===============
Habitamuበሽብር ወንጀል ተከሰው ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ ክሱ እንደማይመለከታቸው የተረጋገጠላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮቹን አብርሃ ደስታ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋን ጨምሮ አቶ አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ የጻፈው ባሳለፍነው ሐሙስ ቢሆንም ትናንት አርብ ፖለቲከኞቹን ለያዘው ወህኒ ቤት የፍቺ ወረቀቶቹ እንዲደርሱ ተደርገዋል፡፡

ተከሳሾቹ በከፍተኛው ፍ/ቤት ከቀረበባቸው ክስ በነፃ መሠናበታቸውን ተከትሎ በአቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠይቆባቸው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው በጠቅላይ ፍ/ቤት እየተከታተሉ ቢቆዩም ፍ/ቤቱ ከትናንት በስቲያ “ከእስር ነፃ ሆናችሁ በውጪ ጉዳያችሁን እንድትከታተሉ የመፍቻ ትዕዛዝ ይፃፍላችኋል›› ባለው መሠረት፤ በትናንትናው እለት ትዕዛዙ መድረሱን ለማወቅ መቻሉን አዲስ አድማስ ጋዜጣ ለንባብ አብቅቷል፡፡

በወህኒ ቤቱ አስተዳደር በደል እየደረሰብን ነው በማለት ከ5ቱ ተከሳሾች ሶስቱ ማለትም አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቶ የሸዋስ አሰፋና አቶ አብርሃ ደስታ ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ አቤቱታ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን ወህኒ ቤቱ ለየካቲት 3 ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በቀጠሮው እለት ዳኞች ከማረሚያ ቤቱ መልስ ሳይሆን ነገ መፈቻችሁ ይፃፍላችኋል የሚል ምላሽ ከትናንት በስቲያ የሰጣቸው ሲሆን የመፈቻ ትዕዛዙም ከፍ/ቤቱ ተጽፎ መውጣቱን የተከሳሾች ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ለአዲስ አድማስ አረጋግጠዋል፡፡በመፈቻ ትዕዛዙ ላይ ተከሳሾች ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ከሃገር እንዳይወጡ ለኢምግሬሽን ትዕዛዝ እንዲደርስና ፍትህ ሚኒስቴር እንዲያውቀው የሚል መልዕክት እንደሰፈረበት ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

እስረኞቹን ፍታ የተባለው ወህኒ ቤቱ በበኩሉ በዛሬው ዕለት እነሐብታሙን አለመልቀቁ ታውቋል፡፡የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ከጠዋት ጀምረው እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ ተስፋ በማድረግ በወህኒ ቤቱ በር ላይ መለቀቃቸውን ቢጠባበቁም ወህኒ ቤቱ ከደረሰው ትዕዛዝ በላይ የሚጠባበቀው ትዕዛዝ በመኖሩ እነ ሀብታሙን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

የአመራሮቹ ቤተሰቦች በነገው ዕለትም ወደ ወህኒ ቤቱ በማምራት መለቀቃቸውን እንደሚጠባበቁ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ከጅብ የማያስጥሉ የአህያ ባሎች ሆነው መታየታቸው ረዥም አመታትን ያስቆጠረ እውነታ ቢሆንም የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የሰበር ሰሚን ትዕዛዝ በዚህ ደረጃ ተጥሶ ማየትም የፍርድ ቤቶችን አቅመ ቢስነት ያጋለጠ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡

የፊታችን ሰኞ ፍርድ ቤቱ እነሐብታሙን ከቤታችሁ መጥታችሁ ትከራከራላችሁ ያላቸው በመሆኑም ነገ ወህኒ ቤቱ የሚጠብቀው ቀጭን የደህንነት ትዕዛዝ ካልደረሰውና ካልለቀቃቸው ሰኞ ምን አይነት መልስ እንደሚሰጥና የፍርድ ቤቱም ምላሽ ምን እንደሚሆን ይታያል፡፡
እነሐብታሙ በግፍ እያሳለፉት የሚገኘው እያንዳንዱ የእስር ቀንም የስርዓቱን ወፈፌነት ወለል አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ በድርጊቱ እነሐብታሙ ሳይሆኑ ወህኒ ቤቱና ትዕዛዙ ያልተከበረለት ፍርድ ቤት ሊያፍሩ ይገባል፡፡

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles