Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ሩሲያ ሙሰኞችን “በመሣሪያ” ልትመረምር ነው

$
0
0

በሩሲያ የሞስኮ ባለሥልጣናት ሙስናን ለመዋጋት በሚል ውሸታሞችን በመፈተኛ (lie-detector test) የመንግሥት ሠራተኞችን ልትመረምር ነው፡፡

ሰሞኑን የሩሲያው ኢንተርፋክስ እንደዘገበው በሞስኮ የሚገኙ የመንግሥት ሹማምንት በሙሉ ውሸታሞችን በሚመረምረው መሣሪያ ሞሳኞች መሆን አለመሆናቸው እንደሚመረመር አስታውቋል፡፡

የፖሊግራፍ መፈተኛ የሚባለው በተለምዶ ውሸታሞችን መመርመሪያ ተብሎ የሚጠራው መፈተኛ በወንጀለኝነት የተጠረጠሩ ሰዎች የሚፈተኑበት ነው፡፡ ተፈታኝ ሰው ላይ የሚገጠመው መሣሪያ ግለሰቡ ጥያቄዎች በቀረቡለት ጊዜ መልስ ሲሰጥ የሚከሰተውን የልብ ምት፣ የደም ግፊት፣ አተነፋፈስ፣ የቆዳ መቆጣት፣ ወዘተ ይመረምራል፡፡ በዚህም መሠረት ግለሰቡ ለተጠየቀው የመለሰው እውነት ወይም ውሸት መሆኑን መሣሪያው መጨረሻ ላይ በሚሰጠው ሪፖርት ያረጋግጣል፡፡

መሣሪያው ፍጹም እውነተኛ አይደለም ብለው የሚከራከሩ ውጤቱን መቀበል ያቅተናል ቢሉም መሣሪያው በበርካታ አገራት ወንጀለኞችን በመመርመር አመርቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡ እስካሁን እጅግ ጠቃሚነቱ ጥያቄ ላይ አልወደቀም፡፡

በቅርቡ በወጣው ዓለምአቀፋዊ የግልጽነት ዘገባ መሠረት ከ168 አገራት 119 ደረጃ ላይ የምትገኘው ሩሲያ ሙስናን ለመዋጋት “ግብረኃይል፤ ታስክፎርስ፤ …” ከማቋቋም ሙሰኞችን በሳይንሳዊ መንገድ መመርመር መፈለጓ ይበል የሚያሰኝ ነው በማለት አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡

በተያዘው ዕቅድ መሠረት በሞስኮ የሚገኙ የመንግሥት ሹማምንት የሚቀርብላቸውን ጥያቄ በመመለስ ከሙስና ነጻ መሆናቸው ይፈተናል፡፡ ከዚያም የፈተናቸውን ውጤት እየተቀበሉ ወደ ቀጣዩ የጸረ ሙስና ምርመራ ይሸጋገራሉ፡፡ ጉዳዩን እየመሩ ባሉ የኢኮኖሚ፣ የሳይንስና የጸረ ሙስና ባለሙያዎች መሠረት ይህ አይነቱ ሙሰኛን የመመርመሪያ አሠራር ሙስናን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስተዋጽዖ አለው ይላሉ፡፡

ሙሰኞችን በእንዲህ ዓይነት መሣሪያ መመርመር ውጤት የለውም የሚሉ “የሰለጠኑ የመንግሥት ሌቦች” መሣሪያውን ማምታታት እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡ “የሰለጠኑ ሙሰኞች” ሙስናን እንደ አንድ ሙያ ስለሚያዩት ማንኛውንም ነገር ለማምለጥ የሚቻላቸውን ዝግጅት ያደርጋሉ፤ ስለዚህ የመሣሪያውንም ፈተና ማምለጥ ይችላሉ ይላሉ፡፡

ህወሃት/ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ የሙስና ጉዳይ ከላይ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የበታች አመራር ድረስ እንደ መብት እና የአባልነት ግዴታ የሚተገበር እንደሆነ በራሱ በኢህአዴግ ሲነገር የቆየ ሃቅ ነው፡፡

ከሞቱ በኋላ ከሙስና ነጻ እንደነበሩ በአፍቃሪዎቻቸው እጅግ የሚነገርላቸው መለስ በአንድ ወቅት ራሳቸውን በሙስናው ክበብ ውስጥ በመጨመር “እስከ እንጥላችን ገምተናል” ማለታቸው ይታወሳል፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

<!–

–>


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles