Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

በትግራይ ድርቅ ህይወት እየቀጠፈ ነው!

$
0
0

* “ከብቶቻችሁን ሸጣችሁ ተገላገሉ” ህወሃት ለነዋሪዎች

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ትግራይ ድርቅ በአስከፊ ሁኔታ ህይወት እየቀጠፈ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ለእንስሳትም ሆነ ለሰው ዕርዳታ መስጠት ገና ባይጀመርም በሚደረገው ዕርዳታ የመስጠት ዕቅድ ውስጥ የዓረና-መድረክ አባላት የሆኑ ነዋሪዎች “ዓረና ይርዳህ” በመባል ከዕርዳታው አሠጣጥ ዕቅድ ውጪ ተደርገዋል፡፡ የህወሃት ካድሬዎች ነዋሪ ገበሬዎችን “ከብቶቻችሁን ሸጣችሁ ተገላገሉ” በማለት መመሪያ እየሰጡ ነው፡፡ አምዶም ገብረሥላሴ በፌስቡክ ገጹ ላይ ያወጣው መረጃ እንዲህ ይነበባል፡-

ድርቅ በትግራይ አስከፊ ሁኔታ ላይ በመድረሱ የቤት እንስሳ ህይወት እየቀጠፈ ነው። በትግራይ አብዛኛው ወረዳዎች የድርቅ አደጋ የተጠቁ ሲሆኑ እጅግ አስከፊ የሚባል ጉዳት ያደረሰባቸው ወረዳዎች ግን አፅቢ ወንበርታ 12 ቀበሌዎች፣ የክልተ አውላዕሎ በርካታ ቀበሌዎች፣ አብዛኛው ራያ ዓዘቦና ራያ አለማጣ ቀበሌዎች፣ የኦፍላ ግማሽ ቀበሌዎች፣ አብዛኛው ሕንጣሎ ወጀራት፣ ከግማሽ በላይ ሳምረ ሰሓርቲ፣ አብዛኛው ጣንቋ አበርገለ ወረዳ፣ የምዕራባዊ ዞን የርካታ ቀበሌዎች ናቸው።

በተጠቀሱት ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት የእንስሳት ምግብ እጥረት አጋጥሞ በርካታ የቤት እንስሳት ለሞት ተዳርገዋል።

የትግራይ ክልል መስተዳድር ምንም ዓይነት የህይወት አድን ስራ መስራት አልቻለም። በጣም የሚያሳዝነው (አገዛዙ) ሃላፊነቱን በመዘንጋት በድርቅ ለተጠቁ አካባቢ ነዋሪ ገበሬዎች “በድርቁ ምክንያት ከብቶቻችሁን ሸጣቹችሁ ተገላገሉ” የሚል መመሪያ መስጠቱ ነው።

በጣም የሚገርመው እስካሁን ለእንስሳም ይሁን ለሰው እርዳታ ማቅረብ ያልተጀመረ ሲሆን በድርቅ የተጠቁ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑት የዓረና አባላት ከጥናቱ ውጭ እያደረጓቸው ይገኛሉ።

ለምሳሌ በኦፍላ ወረዳ ዓረና-መድረክን ወክሎ ለክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረው አቶ ጡዕማይ ስዩም “ዓረና ይርዳህ” በማለት ከእርዳታው ውጭ በማድረግ ከነፍስ ማጥፋት የማይተናነስ ወንጀል እየፈፀሙ ይገኛሉ።

ከድርቅ አደጋ በተጨማሪ በርካታ ቀበሌዎች በበረዶና በጎርፍ አደጋ ሰብላቸው ከጥቅም ውጭ ሆኖባቸዋል። የህወሓት አገዛዝ ለእነዚህ ተጎጂዎች “እርዳታ ስጡኝ” ብሎ ለልመና ለዓለም ማህበረሰብ እጁ ዘርግቷል።

ይሁን እንጂ አስቸኳይ እርዳታው ለፖለቲካዊ ጥቅሙ እያዋለው ይገኛል። የዚህ ወንጀል ሰለባ ከሆኑት በዓብይ ዓዲ-ሃገረሰላም ምርጫ ክልል የዓረና-መድረክ የክልል ምክርቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አቶ ኪሮስ ታደስ እንደሌሎች የደጉዓ ተምቤን ወረዳ ደጎል ወያነ ቀበሌ ነዋሪዎች ሰብላቸው በበረዶ ከጥቅም ውጭ የሆነባቸው ሲሆኑ ለዚህ ጉዳት ለመከላከል ጥናት የሚያደርጉ የወረዳው ሹመኞች የቀበሌው ህዝብ እንደተሰበሰበ “ዓረና ይርዳህ” ተብለው ከነቤተሰባቸው ከሞት የማይተናነስ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተወስኖባቸዋል።

ይህ ስራ በ1977 አስከፊው ድርቅ ወቅት በትግራይ ህዝብ ላይ ሻእብያ የወሰደው አስነዋሪ ውሳኔ በህወሓት እየተደገመ መሆኑ የሚያመላክት ነው።

የትግራይ ክልል መንግስት በድርቅ ለተጠቁ አከባቢዎች የውሃና ሳር ድጋፍ እስካሁን አላደረገምና እየጠፋ ያለው የእንስሳ ህይወትና በጠኔና ረሃብ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ እያለ ያለው ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ማድረግ ይገባዋል።

ከኦሮምያና ዓፋር ክልሎች ተሞክሮ እንዲወስድም እንጠይቃለን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!

IT IS SO…!

(ፎቶ፡ ከቀድሞው ድርቅ ለማሳያነት የቀረበ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

<!–

–>

The post በትግራይ ድርቅ ህይወት እየቀጠፈ ነው! appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles