አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ እንዲሁም የጸረ-ሽብር ግብረ ኃይሉ፣ በኦሮሚያ ክልል የተካሄደው እንቅስቃሴ፣ በአገር ዉስጥና በዉጭ አገር በሚገኙ ጸረ-ሰላም ኅአይሎች የተቄባበረ ነው ሲሉ በተደጋጋሚ ሲከሱ እንደነበረ ይታወቃል።ከዚህም የተነሳ አገዛዙ አቶ በቀለ ቀርባን ጨመሮ በርካታ የዖፌኮ አመራሮችን ያሰረ ሲሆን፤ የሰማያዊ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ የሰማያዊ ልሳን የሆንው ይነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ አቶ ጌታቸው ሽፈራው ታስረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ባደረጉት ስብሰባና ግምገማ፣ በኦሮሚያ የተከሰተው ተቃዉሞ ያስከተለዉን ችግርና መንሴዉን እንደገመገመ በመግለጽ፡የግምገማዉን ዉጤት ይፋ አደርጓል። ግምገማዉን በተመለለተ አስተያየት የሰጡት የኦህዴድ ም/ፕሬዘዳንት እነ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ “እንደሚታወቀው የኦሮሚያ በተለያዩ ምክንያቶች በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ብጥብጥና ሁከት የነበረበት ሁኔታ ነው የነበረው። የብጥብጡና ሁከቱ ዋና መንስኤ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ በግምገማችን ለይተናል” ሲሉ የመንግስት ባለስልጣንናት ሲናገሩ የነበሩት ሙሉ ለሙሉ በመቃረን፣ ችግሩ በዋናነት የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሆነ ገልጸዋል።
በዚህ ጉዳይ የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ የሚከተለውን ዘግቧል