Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአእምሮ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል -ዳዊት ሰለሞን

$
0
0

ዳዊት ሰለሞን

Andargachew 76
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከቤተሰቦቹ ጋር

የአውሮፓ ፓርላማ የሞት ፍርድ የተላለፈበትንና በእስር ላይ የሚገኘውን እንግሊዛዊ ዜግነት ያለውን የፖለቲካ አክቲቪስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የኢትዮጵያ መንግሰስት እንዲፈታ መጠየቃቸውን በአድናቆት የተመለከተው ሪፕራይቭ የተሰኘው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የእንግሊዝ መንግስት ዜጋውን ለማስለቀቅ የአውሮፓ ፓርላማ አባላትን ያህል ለመጠየቅ አለመንቀሳቀሱን ተችቷል፡፡

የትናንቱን የፓርላማ ውሳኔ የጠቀሰው ድርጅቱ የሶስት ልጆች አባት የሆነው አንዳርጋቸው ከፍተኛ ስም ያለው የመንግስት ተቃዋሚ አባል እንደነበርና በ2014 ወርሃ ሰኔ ታፍኖ ወደ ኢትዮጵያ መወሰዱን ያስታውሳል፡፡በ2009 ፍርድ ቤት ሳይቀርብ ከፍተኛው የሞት ቅጣት የተላለፈበት አንዳርጋቸው ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ ጠበቃ የማግኘትና በቤተሰቦቹ የመጎብኘት መብቶቹ እንደተጣሱበት ዘርዝሯል፡፡አንዳርጋቸው የሚገኝበት ሁኔታ ባልታወቀበት መንገድም ማሰቃየት ሳይፈጸምበት እንዳልቀረ ስጋት መኖሩን ጠቁሟል፡፡

የአውሮፓ ፓርላማ ባቀረበው ሪዞሊሽን ባለፈው አመት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን አስተያየት መጥቀሱን ያወሳው ሪፕራይቭ ፓርላማው ‹‹የሰብአዊ መብት ካውንስሉ ያቀረበውን ምክር የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ወደተግባር በማውረድ የፖለቲካ አክቲቪስቱን እንግሊዛዊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በአስቸኳይ እንዲለቅ››ጠይቋል ብሏል፡፡

የፓርላማው ሪዞሊሽን በዚህ ጉዳይ ላይ ከእንግሊዝ መንግስት በተሻለ የኢትዮጵያን መንግስት በመጫን አንዳርጋቸውን እንዲፈታ ሲጠይቅ የእንግሊዝ መንግሰስት ግን ዜጋውን በተመለከተ ሲጠይቅ የቆየው ጠበቃ የማግኘት መብቱ እንዲከበርለትና የክሱ ጉዳይ ስነስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ብቻ ቢሆንም ‹‹ መንግስት እነዚህን ጥያቄዎች እንኳን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም››ብሏል፡፡

ከአውሮፓ ፓርላማ ጥሪ የቀረበው ስለአንዳርጋቸው የአእምሮ ሁኔታ አዲስና አሳሳቢ የኤክስፐርቶች ሪፖርት በያዝነው ሳምንት በወጣበት አጋጣሚ ነው፡፡ የደቡብ ለንደን ኤን ኤች ኤስ ትረስት ኃላፊ ዶክተር ቤን ሮቢንሰን እንደሚሉት የአንዳርጋቸው የአእምሮ ጤንነት እያሽቆለቆለ የመጣው በኢትዮጵያ ከታሰሩ ጀምሮ ነው፡፡ዶክተሩ ‹‹አሁን አንዳርጋቸው ከሚገኙበት ሁኔታ ማስወጣትም ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም››ብለዋል፡፡

ሪፕራይቭ የሞት ቅጣትን ለማስቀረት የሚያደርገውን ንቅናቄ የሚመሩት ማያ ፎ ‹‹የአውሮፓ ፓርላማ ለኢትዮጵያ እንደ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉን ከአገዛዙ የተለየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ማፈን፣ማሰቃየትና የሞት ፍርድ ማሳለፍ ህገ ወጥና ተቀባይነት የለሌለው መሆኑን መንገሩ ትክክል ነው፡፡የአውሮፓ ፓርላማና የተባበሩት መንግስታት ዜጋው ከታሰረበት የእንግሊዝ መንግስት በላይ ሲያደርጉ ማየት አስገራሚ ነው፡፡እንግሊዝ በአስቸኳይ አቋሟን በመቀየር አንዳርጋቸው እንዲለቀቅ መጠየቅ ይኖርባታል››ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles