ከኣስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል ፣
———————————————————–
እኔ ዜግነቴ ኢትዮጱያዊ ኣገሬም ኢትዮጱያዊ የተወለድኩበት በትግራይ ጠቅላይ ግዛት በሽሬ ኣውራጃ ፣በላዕላይ ቆራሮ ወረዳ ፣በኣሁኑ ጊዜ በህወሓት ኣማራር ከጥንት የነበረ ስም ተቀይሮ ወረዳ መደባይ ዛና በሚባል ዓዲ ዘኽረሞ በምትባል ጎጥ ተወልጄ የኣፍ መክፈቻ ፣(የእናቴ ቋንቋ ) ትግርኛ ሆኖ የሀገራችን የስራ ቋንቋ ኣማርኛ ሆኖ ከረጅም ምእተኣለም ( ኣመታት) ጀምሮ ኣማርኛ ለሁላችን ኢትዮጱያውያን ሀገራዊ ቋንቋ ሆኖ በሃገራችን በስርኣተ ትምህርት ካሪከለም ተቀርጾለት ኣብዛኛዏቹ ቢሄርና ቢሄረሰቦች እየተገደዱ ቢሆንም የሃገራችን 100% ህዝቦቻ እንደመግባብያም ፣እንደ የስራ ቋንቋ የመግባብያ ቋንቋ ሆኖ ኖረዋል ። ኣሁንም እየሰራ ይገኛል ።
ይህ ስል ግን የህወሓት ኢህኣደግ የኣማራር ቡዱኖች ፣ ኣሁን በህዝብ በሰላምና የኣመጽ ትግል ተገደው (ተገፍተወ ) ለተባለሸ ስርኣታቸው እድሜ ለመራዘም ብለው የኦሮምኛ ቋንቋ በሃገር ደረጃ ካሪከለም ተቀርጾለት ሁለተኛ የሀገራችን የሰራ ቋንቋ ሊሆን ነው እያሉ የጭንቀት ዲስኩር እያሰሙን ነው ያሉ ። በእኔ እምነት ይተገደውና ተገፍተው የኦሮም ከ42 ሚሌን በላይ ህዝብ የሚጠቀምበት ኦሮምኛ ቋንቋ ሃገራዊ ቋንቋ ለማድረግ ሃገራዊ የትምህርት ካሪከለም ይወጣለታለ መለታቸው በህዝቦች ትግል ተገፍተው ቢሆንም ጥሩ የትግል ውጤት ኣድርጌ እቀበለዋለሁ ። የሌሎች ቢሄሮችም ቋንቋቸው በሃገራዊ የትምርት ካሪከለም ገብቶ ሁሉም ዜጎች ቢማ ያስፈልጋል ያለፉት ስርኣቶችም ባለፈው ምእተኣመትም በሃገራችን ቡዙ ቋንቋዏች በትምህርት ስርኣት ካሪከለም ተቀርጾ በሀገራችን ያሉ ቢሄሮች ወይ ጠቅላይ ግዛቶች እየተማሩበት ቢመጡ ንረው ኣንደኛ ኣሁን ያለው በቋነቋ በቢሄር መከፋፈል አይከሰትም ነብር ። ሁለተኛ ሃገራችን ኢትየጱያ ባለቡዙ ሃገራዊ ቋንቋ ባለቤት በሆነች ነበር ። ምክንያቱም በሃገራችን ያሉ ቋንቋዎች እጅግ ቡዙ በመሆናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ4 ሚሊዮን እስከ 42 ሚሊዮን የህዝብ ብዛት ያላቸው ቢሄሮች ቋንቋቸው ወደ ሀገራዊ ቋንቋ ከፍ ብሎ በቋንቋቸው እንዲማሩ እንዲፈረዱ እንዲከራከሩ ፣በሀገር ደረጃ ካሪከለም ተቀርጾለት ተምሮ በሁለም ቋንቋዎች ለመስራት ቢችሉ ንረው ካለፉት ነገስታት ጀምሮ እስከኣሁን ያለው ኣንባገነን ስርኣት ለቋንቋቸው ፣ተሪካቸው ፣ባህልና ልምዳቸው ኣስተሳሰባቸው ፣ኣኗኗሯቸው ፣ ጂኦግራፊያዊ ኣቀማመጣቸው በቋንቋ ሳይሆን ለኣስተዳደራዊ ኣመችነታቸው ፣ መብታቸው በመነጠቃቸው ኣለኣስፈላጊ መስዋእት ሊከፍሉ ኣይገደዱም ነበር ።
ኣሁንም ህወሓት እና ኣጋሮቹ ስልጣን ከያዙም በኃላ ሀገራችን በቋንቋና በባህል የተመሰረተ የፈደራሊዝም መዋቅር በመዘርጋት ድሮ በኣለፉት የመሳፍንቶች የዘውዳውያን የደርጋውያን ኣገዛዞች በነበሩበት እንኳን ማንም ዜጋ በማናቸውም ክልል ባገኜው የስራ መስክ ተሰማርቶ ይሰራ ነበር በኣሁኑ ከፋፋይ ስርኣት ግን ከክልል ወደ ክልል ሄዶ በሙያው እንዳይሰራ ፣በንግድ ስራና ኤንቨስትመንት ተሰማርቶ እዳይ ሰራ ወይ እዳይሸቅል ፣ ፣ እንደባእድ ተፋጦና ተራርቆ እንዲኖር ኣድርጎውታል ፣ ሌላ ቀርቶ ድሮ ማህበራዊ ንሮ ለመመስረት (ጋብቻ ለማድረግ ) ቢሄር ወይ ጎሳ የማይለይ የነበረ በኣሁኑ ጊዜ ጭራሽ ቀርቷል ። ቢጋቡም መተማመን የለም። ኣሳዛኝ ነገር ። በተለይ በኣሁኑ ጊዜ በመላው የሃገራችን ክልሎች ከተማዎች የንግድ ስም በኦሮሞ ኦሮምኛ ፣ በትግራይ ትግርኛ በሌሎቹም በቋንቋቸው ካልተጻፈ በህግ ኣስከባሪዎች ይፈርሳል ንግድ ፍቃዱ እስከ እርምጃ መውሰድ ተጀምርዋል ።
ያለዘመናት የሀገራችን የስራ ቋንቋና የሃይማኖት የመግባብያ መጠቀምያ ሆኖ የኖረ ቋንቋ በተለይ በትግራይ በኣማርኛ መጻፍ መናገር በጠላትነት ያስፈርጃል ( እንዲታይ ያደርጋል ) ። እንዳውም በማህበራዊ ሚድያ በኣማርኛ ስንጽፍ ፣በሬድዮ በኣማርኛ ስንነጋገር በተለይ ደግሞ በትግራይ ያለው ስርኣት ወይ የህወሃት የተበላሸ ኣሰሀራር በትግርኛ ስለ ሀገረጉዳይ በኣደባባይ ሲናገሩ ፣በኣማርኛ የተቃውሞ መልስ ወይ ክርክር ያደረገ ሰው ።የትግራይ ውሽጣዊ ሚስጢር ለትምክህተኞች እና ጠባብ ጠላቶኞቻችን ኣጋልጠው ሚስጢር ኣወጡብን በማለት በማህበራዊ ሚዲያ በጽሁፍ ስማችን ሲያጠፉን ይታያሉ ።
የተከበራቹ ወገኖቼ ከላይ ያስቀመጥኩት መንደርደራያ ሃሳብ ያለ ኣንዳች ምክንያት ኣይደለም ። እኔ በመጀመሪያ መግብያ ጽሁፌ እንደ ገለጽኩት ንጹህ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነኝ ።ጽህፈትም ከኣማርኛ የማይተናነስ ችሎታ ኣለኝ ።
ነገር ግን እኔ ባለፉት 26 ኣመት የምጽፋቸው የምናገራቸው ኣብዛኞቹ ኣማርኛ ናቸው ። ኣማርኛ የምጽፈውና የምናገረው ያለ ኣንዳች ምክንያት ኣይደለም ። እኔ እምነረው በትግራይ ክልል ነው ። ትግራይ በመሆኔ የህወሓት ኢህኣደግ መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙት ገበና እጅግ ቡዙ በመሆኑ በይፋ ወጥቶ ለመላው የኢትዮጱያ ህዝቦች መጋለጥ ኣለበት ። በመሆኑም እኔም ሌሎችም በፌስቡክ ፣በውጭ ሬድዮ ጣብያዎች እምናስተላልፈው በኣማርኛ ነው ።
በኣማርኛ የምጽፈው ዋናው ምክንያት የትግራይ ህዝብ ችግር በኦሮሞ በሱሟል ፣በደቡብ ፣በኣማራ ፣በዓፋር በሌሎች ክልሎችም ችግሮች ኣሉ በነሱ ያለው ሰቆቋም በትግራይም
ኣለ ። ሁሉም ክልሎች ደግም ኣንዱን የሌላው ችግር አውቆና ተገንዝቦ መተሳሰብና መደጋገፍም ኣለበት ። ከጥንት ጀምሮ ደግሞ በኩፉም በቦጎውም ኣብሮ ተቻችሎና ተግባብቶ የኖረነበር።
ባለፈው ገዜ ኣንድ ኣንድ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ጸሓፊዎች አስገደ ትግርኛ ጽፈት እየቻለ የትግራይ ሚስጢር ለጠላቾቻችን ትምክህተኛ ኣማሮችና ጠባቦች ጥገኛ ሆኖ (የጌታ ኣዳሪነት) ስለፈለገ በኣማርኛ በመጻፍ ለጠላቾቻችን ሚስጢር ያቀብላል እያሉ ቆይተዋል ። ባለፈው ሳምንት ደግሞ አዜብ መስፍን የኤፈርትን ሃብት በሚመለከት ከኣይጋ ፎሮም ዌቭ ሳይት ባደረገቹ ኣጭበርባሪ ቃለመጠየቅ በመቃወም የመጀመርያ ምእራፍ የውሼታን ገጽታ በመጋለጥ ጽፌላት ኣለሁ ። የእኔን ተቃውሞ በትግርኛ በመጻፌ ኣሁንም ተቃውሞው እጅግ ኣስቀያሚ በሆነ ቃላት ኤፈርትን በመቃወሜ ቡዙ ብለዋል ።
እኔ በኣማርኛ የምጽፈው 100 ሚሊዮን የሀገራችን ህዝቦች በማናቸውም ክልል ያለው ወገናቸው በሚገባቸው ቋንቃ ማወቅ የግድ ይላቸዋል ። እኔ ኣልችልም እንጅ በትግራይ ወይ በኣማራ ያለው የህወሓት በኣዴን ግፍ በኦሮምኛ ወይ በስሟልኛ ብጽፍ ደስታው ኣልችለውም ።ስለዚህ ለምድነው በትግራይ ለሚፈጽሙት መጥፎ ድርጊት እንዲሸፋፈን የሚፈልጉት ? በኣሁኑ ጊዜ ኣለም በኢንፎርሞሽን ኣንድ ሆና እያለች ደቡቁነ ደቡቅን ምን ኣመጣው ። እነዚህ ሰዎች ለዚህ ህዝብ ስንት ጊዜ ተደብቀው ሊበዘቡዙት ።
ለመሆኑ ማነው ትምክህተኛ?ማንንስ ነው ጠባብ ?
በእኔ እምነት ከኔ ኣስተሳሰብ ውጭ ሌላው ሃሳብ ለዚህች ኣገር ኣይጠቅምም እኔ ከሌለሁ ኣገር ፈረሰች የሚለን የላሸቀና የበሰበሰ ዘረኛ ስርኣት ህወሓት ኢህኣደግ ነው ። ድግሞ የሀገር ሉኣላውነት የካደ የኢትዮጱያ የባህሪ በር ለባእዶች በማስረከቡ ሃገራችን በኢኮኖሚ እንድት ወድቅ ፣ጸጥቷዋ እና ድህንነታ ለኣደጋ ያጋለጠ ከጅ ስርኣት ነው ።
ሀገራችን በቋንቋ በባህል ከፋፍሎ ቢሄር ከቢሄር እያጋጨ የከፋፍለህ
ስርኣት እያራዘመና እያስፋፋ ያለ የህወሓትና ተላላኪ ኣጋሮቹ ናቸው ።
እነዚህ በትግርኛ እየጻፍክ የኣማራ ሎሌነትህ ( ኣሽከርነት ) ለመረጋገጥ ስትል ፣ ብሄራዊ ሚስጢራችን ሸጥክ የሚሉ እነማን ናቸው ?
1ኛ የህወሓት ኣማራር ያሳማራቸው በትምህርታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፣ ያለስድብ ሌላ ኣንድ ቃልም የበሰለ ኣስተሳሰብ የሌላቸው የህወሓት ኣማራር በትግራይ ህዝብ ስም የሀገራችን ኣንጥራ ሃብት ከሚበዘብዘው ትርፍራፊ ተጠቃሚ የሆኑ ለባንዳነት የታጩ ፣ (የተመቹ ) ግብረገብነት የሌላቸው ህዝብ ቢራብ ቢሰደድ ፣ ቢሞት ደንታ የሌላቸው ሆዳሞች ናቸው እንጅ ኣማርኛ ጽፈን ህዝባችን ማስታወቁ ምን ሽግር ነበረው ? ዋና ሽግራቸው የዘመኑ ቴክኖሎጂ እያለ ተደብቆ የማይደበቅ ለመሸፈን መፈለጋቸው ነው ።
2ኛ ከኣንድ ቁጥር የተጠቀሱ የሃገር ከሃዲዎች ጥሩንባ እያስተጋቡ ትግርኛ ካልሆነ በኣማርኛ መጻፋችሁ ክዳት ነው የሚሉ የዋሆች ወገኖች የህወሓት ኣማራር ለ43 አመት መሉ በተደጋጋሚ የኣማራ ትምክህትና ጠብነት ጠላቶቻችሁ ናቸው ። የህወሓት ኣማራር ከሌለ መጠግያ የለህም በማለት በተደጋጋሚ የውሼት ቅስቀሳ (ፕሮፕጋንዳ) በመመረዝ ሂትለር ወይ ናዚ ውሼት ሲደመር ውሸት ሃቅ ይሆናል እንዳለው እንደሚሆን ኣድርጎ ሁሉም ሃገራዊና ኣህጉራዊ መረጃ በመዝጋት የህወሓት መሪዎች ፕሮፕጋንዳ ኣስተላላፊ የሆኑ ሬድዮ ድምጽ ወያነና በዬመንደሩ ያሉ ኤፍ ኤም የሬድዮኖች መሰራጫ እንዲሁም በትግርኛ ተለብዥን ያደነዘዛቸው ቅን ወጣቶች ናቸው ሁለቱ ግን እነዛ ቅጥረኞች ሆን ብለው ኣላማቸው ለማሳካት ሌት ተቀን በመታከት መርዛቸው ሲረጩ ። እነዛ ምንም በማያውቁት ንጹሃን ወገኖች ጭንቅላታቸው በውሼት (ብሬን ዋሽ ) የተሞሉ ወጣቶች ናቸው ።
እንግዲህ ይህካልኩ እባካችሁ የትግራይ ቅን የወጣት ማህበረሰብ በተለይ ደግሞ የተማራቹ ንጹሃን ወገኖች የተማራቹ ሁሉም በመገናዘብ ለውድ ሃገራችሀሁ ጠቅማችሁ ለራሳችሁም ለመጥቀም ነው ።በመሆኑ በኣሁኑ ጊዜ በነዚህ ግራዚያኒዎች ወላጆቻችሁ ለፍትህ ለነጻነት ለኣንድነ ሲሉ በሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ፋሽሽት ድርግ ለማስወገድ ሂወት ገብረዋል ኣካላቸው ጎድለዋል የተሰውለትና ኣካላቸው የጎደሉበት ኣለማ በነዚህ ሀገር ሸያጮች ተነጥቀዋል ። እንደገና ደግሞ ለናንተ ኣዲስ ትውልድም በውሼት ኣደንዝዘው መሳሪ ሊያደርጋችሁ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ። በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ በቁም ሙታችሁ እያለችሁ ኣለን ማለቱ ይቅር ።
በትግራይ ያለ ሽግር በሃገር ደረጃም ያለ ነው ሽግር በኣማርኛ መጻፋችን ኣትቃወሙ በትግራይ በሌሎች ክልሎች ያለው ችግር በህብረት ለመፍታት ያስችለናል ።
በሌሎች ተቃዊሚዎች ነን የሚሉ ለትግራይ ህዝብ በጠላትነት የሚፈሩጁ የማህበራዊ ሚዲያ ጸሃፊዎች የህወሓት ኣማራርና የሸኣብያ ቅጥረኞች የሚያሳራጩት መርዝ ነው ። በሌላ በኩሉ በስመ ተቃውሞ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ነጣጥለው ለማየት የተሳናቸው የህወሓት ኢህኣደግ ኣማራር ያስቀዬማቸው ግለሰዎች እና ቡዱኖች እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያና ሬድዮ ጣብያዎች መገዛት የለብንም እነዚህም ለዚህ ስርኣት እድሜ ኣስቀጣዮች ናቸው ከማለት ሌላ ትርጉም ኣንስጠው ።
እናንተ ለሆዳችሁ ለማደር ብለችሁ ኣገርን ለመገነጣጠል የምትታክቱ ያለቹ ተላላኪ ተጠቃሚዎች ቆም ብላችሁ በማሰብ ለጆቻችሁ ጥሩ ሁኔታ ብትፈጥሩና ወላጆቻቸው የጣልያን ባንዳ እንደነበሩ የባንዳ ልጆች ከመባል ኣድኗቸው ( ይማራችሁ) ። ለህሊናቹ ተገዙ ።
ከኣስገደ ገብረስላሴ ወልደሚካኤል ፣
18 / 10 /2009 ዓ ም
The post ይድረስ እኔ በምጽፋቸው ገንቢ ይሁኑ ኣፍራሽ ኣስተያየት ሰጭዎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች (ጸሃፊዎች ) በሙሉ ፣ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.