ብርሃንደጅ ሃሰን
24 May,2017
በቅርብ ጊዜ በምኖርበት ከተማ አደባባይ መሃል (ሞል) ላገኛቸው ብመኝም በተለያዩ ምክንያቶች ለሁለት ዓመት ያህል ካጣኋቸውና ከምወዳቸው ሁለት ወንድና ሴት ኢትዮጵያኖች ጋር ባጋጣሚ ተገናኘሁ ። ተቃቅፈንና ቆም ብለን ሰላምታ ከተቀያየርን በኋላ ቡና እየጠጣን መጫወት ይሻላል በሚል ተስማምተን ፤ የቡናና የሻይ አገልግሎት ወደ ሚሰጥበት ንግድ ቤት አመራን ። እነሱም ምንተስኖትና ገበያነሽ ይባላሉ ።
ገበያነሽ አገርዋና ሕዝቧ ከልቧ ስለምትወድና የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ሰለምታጠብቅም – ከበርካታ ኢትዮጵያዊያን ጋር ትገናኛለች፤ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ቤትም ተጎበኛልች። በምንኖርበት ከተማ ስለማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ሕይወት ሲነሳ ፤ ገበያነሽ በናሙና ኢትዮጵያ ዊትነት ትታወቃለች። የምታውቃቸ ውና የሚያውቋት ከመብዛታቸው የተነሳ እውነትም ገበያነሽ! ይልዋታል ።
የአገራችንን ሁለገብ ሁኔታ የሞት አፋፍ ላይ መድረሱን ወይም ባልሞትባይ ተጋዳይነት ደረጃ ላይ መሆኑን እጅግ በጣም ከሚያሳስባቸውና ከሚያስ ጨንቃቸው ኢትዮጵያዊያን አንዱ ምንተስኖት ነው ፡፡ የምንተስኖትን የፖለቲካና የማኅበራዊ ንቃተ-ኅሊናውን ስክነት የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ከእሱ ጋር ሲወያዩ በጣም ተጠንቅቀው ነው ።
እዚያ ቡና እየጠጣን -ስለእየግላችንና ስለእየቤተሰባችንን ሁኔታ አውርተን ስንጨርስ ፤ እየተመስቃቀለ ወይም እየተወሳሰበ ስለመጣው የአገራችንን አገራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሁኔታዎችን ጨረፍ ጨረፍ አድርገን ከተወያየን በኋላ ፤የወያኔ/ኢህ አደግ የሥልጣን ዘመን መርዘም ምክንያቶች ምንና ምን ናቸው ? ወደሚለው ውይይት አመራን ።
የወያኔ/ኢህ አ ደ ግ የሥልጣን ዕድሜ የተራዘመው በብዙ ውስብስብና ቀላል ምክንያቶች ስለሆነ ሰፋ ያለ ጽሁፍና ሰፋ ያለ ትንተና የሚያስፈ ልገው አብይ አርእስት ቢሆንም ፤ለግዜው እጅግ በጣም አጠር ባለመልኩ እኔ የሚታየኝን ላስጨብጥና እናተም የሚታያችሁን ትጨምሩበታላችሁ ብያቸው -ለወያኔ/ኢህ አ ደ ግ የሥልጣን ዘመን መርዘም ምክንያት ናቸው ወደ ምላቸው ነጥቦች አመራሁ ። ይኸውም፦
- በአሜሪካና በአጋሩ ምዕራባዊያን መንግሥታት ግዙፍ ዲፕሎማሲያ ዊ ፣ፖለቲዊ ምክር ፣ ወታደራዊና ስለላዊ ሥልጠና፣ወታደራዊ ስንቅ ና ትጥቅ ፣በግዙፍ ዶላርና ፓወንድ ወዘተ.. በመታጀቡ
- የኢትዮጵያ አጎራባች አገሮች መንግሥታትና የቀይባህር ማዶ የአረብ አገሮች መንግሥታት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ይዘው ፤ ወያኔን ደግፈው በመቆማቸው ፤ ወያኔ/ኢ ህ አ ደ ግ ተቃዋሚዎችን አላስጠጋ በማለ ታቸው/ በመከልከላቸው
- የኅብረ ብሄር ብሄረስብ የፖለቲካ መተክል የሚከተሉተሉን የተቃዋሚ የፖለቲካና የሲቪክ ድረጅቶች ኅብረት ፈጥረው በአንድ አገራዊ መርህ – የአጭርና የረዥም ግዜ መርሃግብር ነድፈውና አንድ መአከል ፈጥረው መታገል ባለመቻል
- ፀረ-አንድነት የሆኑ የጎሰኛና የመንደርተኛ ፖለቲከኞች መበራከት ፤ ፀረ-አንድነት የቀኝ ክንፍ ጀብደኛ ወይም (populist) ፖለቲከኞች እዩኝ ስሙኝ እያሉ መምጣት
- በቅርጽ ተቃዋሚ መስለው በይዘት ከወያኔ ጋር ያበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች በመኖራቸው
- የፖለቲካ ድርጅታችው ብቻውን ታግሎና ወያኔ/ኢህ አ ደ ግን አሸንፎ – ለፖለቲካ ሥልጣን እንበቃለን የሚሉ ፖለቲከኞች በመኖ ራቸውና ህብረት እንዳይፈጠር እንቅፋት በመሆናቸው
- ወያኔ/ኢህ አ ደ ግ ኢትዮጵያውያንን በጎሳ ቋንቋና ሥነልቦና አጥር አጥሮ ስለሚግዛና አንዱን ጎሣ ለሌላው ጎሣ ጠላት እንደሆነ አድርጎ በመስበኩና በማስተማሩ – ኢትዮጵያውያን ተማምኖ በጋራ ጠላታቸው በወያኔ ላይ መነሳት ባለመቻላቸው ወዘተ.. ብዬ ስጨርስ “የረሳኸው ነገር አለ” አለኝ ምንተስኖት ። ምን እስቲ ግለጻቸው! ስለው – “ በኢትዮ-ዲያስፖራ ሬዲዮና ኅትመት ሚዲያ የሚሰሩ ሃቀኛ ጋዜጠኞች/የሚዲያ ሞያተኞች የሉንም ፤ ቢኖሩም በጣም ጥቅቶች ናቸው ፤አብዛኞቹ ለወያኔ ዕድሜ መርዘም አስተዋጽዎ ያደረጉና የሚያደርጉ ናቸው ” አለኝ ። እንዴት እስቲ አስረዳኝ ! ስለው -እንደሚከተለው ገለጸው ።
(1 ) “አንድ የአገርና የኅዝብ ጉዳይ የሚመለከት/መልዕክት ያለው ጽሁፍ ሲላክላቸው ፤ጽሑፉን አንድ የገንዘብ ድጎማ የሚያደርግላቸው ወይም የተወዳጁትን የፖለቲካ ፣ የሲቪክ፣የሃይማኖት ወዘተ..ድርጅት ወይም ድርጅት መሪ የሚነካ ከሆነ ጽሑፉን አደባባይ እንዳይወጣ ያፍኑታል (2) አንድ ጽሁፍ ሲላክላቸው ጽሑፉን የሚለኩት በጽሑፉን ይዘትና መልዕክ ት ሳይሆን በጸሃፊውን ማንነት ነው ። ጽሁፉ -በፕሮፌሰር ፣ በዶክተር ፣ በፖለ ቲካና በሕዝባዊ መድረክ በሚታወቅና አንድ ትንሽ መጽሃፍ ጽፎ በአንድ ድረገጽ በለጠፈ ሰው ወዘተ.. የተጻፈ ከሆነ ወዲያውኑ በድረገጻቸ ው ይለጥፉታል ። በአገር ጉዳይ ላይ ለቃለ መጠየቅም ሆነ ለውይይት የሚጋብዙዋቸው ከሞላ ጎደል እነዚሁ ናቸው (3) በጓደኝነት ፣ በዝምድና ፣ በመንደርተኝነት ፣ በጎሳ ፣ በአምቻና ጋብቻ ወዘተ.. የሚላኩ ጽሑፎችም በደምብ ይስተናገዳሉ (4) ጸሃፊውን የማያውቁት ከሆነና ጽሁፉን ለዓይናቸ ካላማረ አንብ በው የጽሁፉን ቁም ነገር መረዳት ስለሚሰንፉ -ጽሑፉን ለአ ንባቢያን አደባባይ ከመውጣት ያስቀሩታል (5) የወያኔዎች ገበና በደንብ የሚያጋልጥና ወያኔዎችን አጥብቆ የሚተች ጽሑፍ ሲላክላቸው አደባባይ እንዳይወጣ የሚያፍኑ ጋዜጠኞችም አሉ ፤ ለምን አፈንከው/አፈናችሁት ተብሎ ሲጠየቅ/ቁ በብዕር ስም የሚላክ ጽሁፍ አናውጣም፣ቅብጥርሶ የሚ ል ሰበብ ይሰጣሉ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን እውነተኛ ስም በምናዓብ የሚያውቁ ይመስላሉ ፤የፈሪ ዱላ ብዙ ነው ይባል የል! (6) የወያኔ ባለስልጣኖች ለቃለመጠይቅ ሲጋብዙ በጣም ልስልሰው ያስተናግዷቸዋል ። በሕዝብና በአገር ላይ የፈጸሙትን ደባና ወንጀል እንዲናገሩ ጠበቅ አድር ገው አይጠይቋቸውም ፤ ባለሥልጣኖቹ ማስማት ወይም ማስተላለፍ የሚፈልጉትን መልዕክት ብቻ አስጨብጠው ይሄዳሉ ፤ቃልመጠየቅ አድራጊው ጋዜጠኛ የእነሱ ተባባሪ ወይም ጉቦ የሰተጠው በሚመስል መልክ ነጻ ግልቤያ (free ride) ሰጥተው ይሸኛዋቸዋል ። ይህንን በተመለ ከተ አገራቸውና ሕዝባቸውን ወዳድ ኢትዮ-አው ስትራሊያውያን የ(SBS) ሬዲዮ አዘጋጅና ዜና አስራጭ በሆነው ጋዜጠኛ ላይ ብርቱ ቅሬታ ሲያሰሙ ሰምቼያለሁ ። ምክንያቱም የአገራችንን ተጨባጭ ፖለቲካዊ ሁኔታ በተመለከተ በተለይም ከበርካታ ወራት በፊት ተፋፍሞ የነበረውን ሕዝባዊ አመጽ አስመልክቶ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትርፉ ኪዳኔን ለቃለመጠቅ ጋብዞ ሲጠይቃት እሷ የምትፈል ገውን ውሸት ተፍታና ስብካ እንድትሄድ ፈቀደላት ፤ ባትቀበለውም ወያኔዎ ች ከሚፈጽሟቸው ግዙፍ ግፎች ጥቂቶችን እንኳን አንስቶ መጠየቅና ማፋጠጥ (challenge) ማድረግ ነበረበት በሚል ሲሆን ፤
ከዚያ ቀድም ብሎም ከአገር ቤት የወያኔ ባለስልጣኖች ለቃለመጠቅ ጋብዞ ሲጠይቃቸው እነሱን የሚጎረብጥ ወይም የሚቆነጥጥ ጥያቄ/ጥያቄዎች አቅርቦላቸው አያውቅም ፤ለእነሱ ምቹ በሆነና በለሰለሰ የአጠያየቅ ስልት ያስተናግዳቸው ነበር ፤ እነሱም ማለት የወያኔ ባለ ሥልጣኖችም በቃለመ ጠየቁ ስለሚደስቱ ለምን ወደ አገር ቤት መጥተህ አትጎበኘንም እያሉ ሲጋብዙት ይደመጥ ስለነበር ፤የጋዜጠኛው የቅርብ ወዳጆቹ ጭምር ወደ ወያኔ አምባ ሳይገባ አይቀርም ብለው ሲያሙት ሰምቼአለሁ ። ‘አዎን በየትኛውም አገር የፖለቲካ ሥልጣን ከአምባገነኖች ለመንጠቅ የሚደረገ ውን ትግል እየተራዘመ ሲሄድ የአድርባዮች መተክል/principle ጥቅም ስለሆነ የፖለቲካውና የኮኖሚውን የበላይነት ወደ ያዘው ያዘነብላሉ’ (7) በቅርብ ግዜ እንዳለ ተሺ የተባለ የዩቲዩብ ጋዜጠኛ አቻምየለህ ታምሩን ቃለመጠይቅ (intervi ew) ሲያደርግ – አቻምየለህ ኢ ሕ አ ፓ፣ሜኤሶንና ግንቦት 7 የአማራ ጠላት ናቸው ብሎ ሲወነጅልና ሲኮንን ፤ጋዜጠኛ እንዳ ለ ግንቦት 7ን ብቻ ነጥሎ ከውንጀላው ነጻ ለማድረግ – ግንቦት7 ለአማራ ጠላት ስለመሆኑ ማስረጃ እንዲሰጠው አቻምየለህን በጥያቄ ሲወጥር ቅርጸ ምስላቸው ን እያየሁ አዳመጥኳቸው ። ነገር ግን እንዴት (ኢሕ አፓና ሜኤሶን) ጸረ አማራ ሊሆኑ ይችላሉ ? ምክንያቱ ግለጽልኝ ? ዋልልኝ ኢሕአፓ ወይም ሜኤሶን ነበርን ብሎ አልጠየቀውም ።የዚህ ጋዜጠኛ የጋዜጠኝነት ሞያው ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥብቅና እንዳዋለው በገሃድ አሳይቷል ። ያ የአውስትራሊያው የ(SBS) ጋዜጠኛና እንዳለ ተሺ- ከላይ ሃቀኛ ጋዜጠኞች/የሚዲያ ሞያተኞች የሉንም ላልኩት እይታዬ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው ።ማስረጃ በመስጠት አንባቢ ላለማሰልቸት ላሳ ጥረው እንጂ በርካታ ያልሰከኑና በጥቅም የተገዙ ኢትዮ-ዲያስፖራ የሚዲያ ሰዎች እንዳሉ መጥቀስ ይቻል ነበር “ አለ ምንተስኖት ።
ምንዓይነት የጋዜጠኝነት ሞያ ያላቸው ስዎች ቢኖሩን ትወዳለህ? “ሁላችንም እንደምናውቀው የበሰሉና የነቁ የኪነጥበብ ሞያተኞችና ጋዜጠኞች የአንዳን አገር ሕዝብ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ንቃተ ኅሊና ከፍ እንዲል የሚጫወቱት ሚና ቀላል አይደለም ። እ.አ.አ በ 1970 ከነበሩት ጋዜጠኞች እነ-አሳምኖ ገብረወልድና ጳውሎስ ኞኞ መጥቀስ ይቻላል ። አሁን ኢትዮጵ ያና የኢትዮጵዊ ሕዝብ ከሚገኙበት አደጋ ለማዳን ለሚደረገው ተጋድሎ ሃቀኛ የሚዲያ ሞያተኞች ያስፈልጉ ናል ። ማለት (1)ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የአማከለ (centered) ያደረገ (2) ከአድርባይነት ፣ከእወደድባይነት ፣ከተጠላሁ ባይነት ፣ ከአድሎ ፣ክመንደርተኝነት ፣ከጎሰኛነት ወዘተ..የነጹ (3) የአገራችንን የፖለቲካ አቅጣጫ በመገምገም ሕዝብን -የሚያነቁ ፣ የሚያወያዩና የሚያስተምሩ (4) እሰይ/አሚን የሚያሰኝ የትግል ጽናት፣ የፖለቲካ መርሃግብር ፣መርህና መተክል ያላቸውና አንድ የትግል ማአከል ፈጥረን እንታገል ባዮችን የፖለቲካ ድርጅቶች የሚ ያበረታቱ የሚዲያ ሞያተኞች ያስፈልጉናል። ብቃትና ጥራት የሌላ ቸው 20 የሬዲዮ ዜና አቅራቢና የህትመት(print media) ጋዜጠኞች ከሚኖሩን 10 ከድንቁርና የላቁ (Enlightened) የሆኑ ፣በአገራዊና ሕዝባዊ ፍቅር የታነጹ ጋዜጠኞች ወዘተ.. ቢኖሩን ይመረጣል” አለ ምንተስኖት ።
አሁን በዲያስፖራው ዓለም ካሉት የሚዲያ ሰዎች ማንን ታመሰ ግናለህ ? “ከሬዲዮ ጋዜጠኝነት የአዲስ ድምጽ ባለቤት ‘አበበ በለው’ ፣ ከህትመት ሚዲያ ሳተናውና (satenaw.com) ኢትዮፓንሮማ (ethiopanorama.com)” :: ለምን? “ያለ አድሎ ሁሉንም በእኩልነት ስለሚያስተናግዱ” አለ ምንተስኖት ።
ውይይታችን ያለቀ መስሎኝ ከመቀመጫዬ ለመነሳት ስል “ ምኖ ውይይታችንን ሳንጨርስ ለመሄድ ቃጣህ!” አለች ገበያነሽ።
በመቀጠል “የወያኔ ዕድሜ መርዘም አስተዋጾ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ፤በባዕን አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተብዮች አገር ቤት ላሉትን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸውን ፀረ-ወያኔ ሕዝባዊ ሰልፎችና አመጾችን እንዳይሳተፉ ስለሚመክሩ ” አለች ።
ምን ማለትሽ ነው እስቲ አብራሪዩ ስላት “አው እንደ እኛ በባዕዳን አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ላሉት ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸውን ሥልክ እየደወሉ -“አደራህን ሰልፍ ከመውጣት ተጠንቀቅ ፣ አደራሽን ሰልፍ ከመውጣት ተጠንቀቂ ፣ አደራችሁን ሰልፍ ከመውጣ ተጠንቀቁ “ እያሉ ሲያስጠነቅቁ -የሰማ ኋቸው በርካታዎች ናችው ፤ በአደባባይ ግን ፀረ-ወያኔ መስለው ሲለፈልፉ ይደመጣሉ” አለች ገበያነሽ ። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከዚህ ቀደም አንዲት የጴጤ ቆስቴ ክርስትና ከምትከተል ኢትዮጵዊት ሰምቼ ነበር ፤ እንኳን አስታውስሽ ! አልኳት ።
ከዚያም ሶስታችንም ዓይን ለዓይን ተያይተን ለአምስት ደቂቃ ያህል በነጥቡ ላይ ከተወያየን በኋላ ፤ ለቤተሰቦችሽና ለዘመዶችሽ ሥልክ ስትደዊላቸው ፀረ-ወያኔ ትግልን አስመክቶ የምትሰጫችው ምክር ምንድነው ? ብዬ ጠየቅኳት ። “ ደፋርና ታጋይ ታሪክ ይሠራሉ ፣ ታሪካቸውና ስማቸው ዘላለማዊ ነው ፤ ፈሪ ፣ አድርባይ ና ባንዳ ሲሰደቡና ሲዋረዱ ይኖራሉ ፣ ስለሆነም በሁለገብ ፀረ ወያኔ/ኢህአደግ -ሕባዊ አመጾችና ሰልፎች በጽናት ተሳተፉ፣ታገሉ! በውርደት ለረዥም ዓመታት ከመኖር በክብር ለአጭር ዓመታት መኖር ! ሞት ብክብር ! እያልኩ እመክራቸዋለሁ” አለች ።
አንተስ ለዘመዶችህ ምን ምክር ነው የምትሰጣቸው ?ብዬ ምንተሥኖትን ስጠይቀው -“ የቃላት ልዩነት ካልሆነ በቀር ተመሳሳይ ምክር ነው የምሰጣቸው “ አለኝ ፤የኔም ከእናንተ የተለየ አይደለም አልኳቸው ።
የዚህ ዓይነት አትታገሉ ፣ አታምጹ ፣ ወያኔን አታስቸግሩ ፣ዓርፋችሁ ተቀመጡ ወዘ..የሚል ምክር የሚሰጥ/ጡ ሰዎች የመደብ ጀርባ ምን ይሆን ? ከወያኔ ጋር በምን የተነካኩ ይሆኑ ? ወዘተ.. በማለት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ የሰማቻቸውን ሰዎች ሙሉ ስም እንድ ትገለጽልን ገበያነሽን ጠይቀንና ሰፋ ያለ ሰዓት ወስደን በሰዎቹ ማንነት ላይ ከተወያየን በኋላ ፤ ስዎቹ በይሆናል እንዳንፈርጃቸው በማስረጃ የተደገፈ እነሱነት ለማጥናት የሥራ ድርሻ ተከፋፍለን በሳምንቱ በዚያው ሰዓት እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ተለያየን ።
በሳምንቱ በተቀጣጠርንበት ቦታና ሰዓት ተገናኝተን እየበኩላችንን ጥናት አቅርበን ስንወያይና ስናመሳክር የሰዎቹን የመደብ ጀርባ ማወቅ ቻልን ። ይኽውም ፦
የወያኔ ጎሳ የሆኑ ፣ ቤተሰባቸው ከወያኔ ጋር የሥልጣን ድርሻ ያላቸው ፣ ቤት ሠርተው የሚያከራዩ ፣ ቤተሰባቸው ሁነኛ ንግድ ያላቸው ፣ በውክልና የሚያስነግዱ ፣ ከወያኔ ጎሳ ጋር በአምቻና በጋብቻ የተገናኙ ፣ አገር ቤት የሚመላለሱ ፣ በምንኖርበት ከተማ በሚደርጉ ፀረ-ወያኔ ሰልፎች ተሳትፎ የማያውቁ ወዘተ..ሆነው አገኘናቸው ።
ዶክተር አክሎክ ቢራራ በአንድ በእንግሊዝኛ በጻፉት ጽሁፋቸው ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው የሚሰደዱበት ምክንያቶች ፣ በሃለሥላሴና በደርግ አገዛዝ ዘመን አገራቸውን ጥለው የወጡት ቁጥር ከአሁኑ ጋር ካነጻጸሩ በኋላ ፤ በዚህ ወቅት በባዕዳን አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 6 ሚሊዮን እንደሚደርስ ጠቁሞዋል። ከዚህ ቁጥር በግምት 1/3ኛው ማለት 2 ሚሊዮን የሚሆኑትን ኢትዮጵያውያን ቤተሰባቸውን በፀረ ወያኔ ሕዝባዊ አመጽ እንዳይሳተፉ የሚያስጠነቅቁ ቢኖሩና፤ እያንዳንዳቸው በአማካይ አምሥት ቤተዘመድ ቢኖራቸውና ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆኖ በወያኔ/ኢ ህ አ ደ ግ ላይ እንዳያምጹ ቢታቀቡ =2,000 000X 5 = 10,000 000 የሚያህሉ ወያኔን ደግፊው ሕዝብን ተጻርረው ሊሰለፉነው ማለት ነው ፤ ሌሎች ወያኔ ደጋፊዎች እንዳሉ ሆኖ። ይህ ’ባዕዳን አገራት እየኖሩ አገር ቤት ላሉት ዘመዶቻቸውን ወያኔን እንዲወግኑ ይመክራሉ’ በተመለከተ ፤በዲያስፖራው ዓለም የሚኖሩ- አገራቸውና ሕዝባቸውን ወዳድና ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ጽሁፍ በፊት የማያውቁት ፣ ግልጽ ያልሆነና ትኩረት ያልተሰጠበት ጉዳይ ከሆነ ለማሳወቅ ፣ ለመጦቆም ፣ ለማንቃት(aware) ለማድረግና ውይይት እንዲደረግበት በማሰብ ነው ወደ አደባባይ ያመጣነው ።
በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያልተካተቱና የወያኔ/ኢህ አ ደ ግ የሥልጣን ዕድሜ መራዘም አስተዋጾ ያደረጉ ሌሎች ምክንያቶች እንዳሉ ሆኖ ፤ በእኛ በሦስታ ችን እይታ- የወያኔ/ኢ ህ አ ደ ግ የሥልጣን ዕድሜ የተራዘመው በአጭሩ በዚህ ጽሁፍ ባስጨበጥናቸው/ በነጠብናቸው ነጥቦች ምክንያቶች ነው ። ስለሆነም የሁላችን እንቆቅልሽ የሆነው በሽታችንን ብቻ ማወቅ ሳይሆን መደሃኒታችንን መፈለግ ላይ ነው ።
ብርሃንደጅ ሃሰን
The post የወያኔ የሥልጣን ዕድሜ ያራዘሙ ምክንያቶች – ብርሃንደጅ ሃሰን appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.