Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ለአቶ ሌንጮ ለታ፡-ለሁላችሁም ለኢትዮጵያ ውድቀት ምክነያት ለሆናችሁ – ሰርጸ ደስታ

$
0
0

ይን መልዕክት ለመጻፍ ያነሳሳኝ አቶ ሌንጮ ለታ በኖርዌይ አደረጉት የተባለው ንግግር በጽኁፍ ወጥቶ ከአነበብኩት በኋላ ነው፡፡ ጽሁፌም አቶ ሌንጮን በቀጥታ እየጠቀሰ ሀሳቤን የምገልጥበት ሲሆን ለአቶ ሌንጮ የምሰጠውን አስተያየት ሁሉም በእሳቸው አድሜም ያሉ ከዛም በኋላ የመጡ ለኢትዮጵያ ዛሬ እንዲህ መሆን ጉልሁን ድርሻ ላላቸው ሁሉ ነው፡፡ ሀሳቤን የማቀርበው ከልብና ከማውቃቸው እውነታዎች እንጂ ማንንም ለመክሰስ ማንንም ለማስደሰት አደለም፡፡

አቶ ሌንጮ በቅድሚያ በእድሜ ቢያንስ አባቴ ስለሚሆኑ የምሰጥዎት አስተያየትም ሆነ ሌላ ሀሳቤ ከወቀ ያለፈ እርሶን ለመክሰስ ወይም ሌሎች ሌንጮ ለካ እንዲህ ናቸው ብለው እንዲያስቡ አደለም፡፡ በእኔ አስተያየት ምክነያት እንዲህ የሚያስብ ከአለ ተሳስታችኋል፡፡ ብዙዎች በ66 አብዮት ተሳታፊ የነበሩ በአስተሳሰብ ብዙ አጥፍተዋል አሁንም ከዚያ አስተሳሰባቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ በተሻለ አቶ ሌንጮ ላይ ለውጥ አያለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሰጋኛል ማለታቸው በራሱ ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ እርግጥም እድሜ ብዙ አስተምሯቸዋልና፡፡ ይህን ያህል ካልኩ ወደ ጉዳዬ ልግባ፡፡ ትኩረቴን የማደርገው ግን አቶ ሌንጮ ነጻ አወጣሀለሁ በአሉት የኦሮሞ ሕዝብ ዙሪያ ነው፡፡

አቶ ሌንጮ፡- ከላይ እንጠቆምኩት በእድሜ ቢያንስ አባቴ ይሆናሉ፡፡ በብዙ ነገር ግን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን በተመለከተ ከእርሶ የተሻለ ግንዛቤው ሳይኖረኝ አልቀረም፡፡ ኢትዮጵያን በእርግጥም ከዘሜን እስከደቡብ ከምስራቅ እስከምዕራብ ተራምጄባታለሁ፡፡ ሕዝቦቿንም ከሞላጎደል መሠረታቸውን እረዳለሁ፡፡ እርሶ እንዳሉት እኛ ኢትዮጵያውያን ዝም ብሎ ጥቁር በሚል የምንጠቀለል አደለንም፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵያ የአለም ሕዝብ ሁሉ ደም ያለባት አገር ነች፡፡ ይህን የምልዎት በሳይንስ በተረጋገጠ መረጃ እንጂ ከራሴ አደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ስዘዋወር ግን አይኖቼ ያዩትን ነው ሳይንስ የተናገረው፡፡ መረጃው ይሄውልዎት ያንብቡት http://www.cell.com/ajhg/pdf/S0002-9297(12)00271-6.pdf.  በአንድ ወቅት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ  (Ethiopia is like a melting pot where the whole world once gathered there and has become the current Ethiopians) ያሉት ትዝ ይለኛል ኤፍሬም በጣም አስተዋይ ነበሩ፡፡ በእርግጥም ታሪኩን ስለሚያቁት ነበር፡፡ ያም ሆኖ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ አፍሪካውያን ይልቅ ለሌሎች ከአፍሪካ ውጭ ላሉ እንቀርባለን፡፡ ለምዕራብ አፍሪካውያን ከእኛ ይልቅ ብዙ አውሮፓውያን በዘር ይቀርባሉ፡፡ ያም ብቻ አደለም የእኛ በሌሎች የሌሉ ዘሮችን ይዘን ያለን ነን፡፡ አብዛኛው አለም ላይ ያለ ሕዝብ ከ80 በመቶ በላይ የአንድ ዘር (ነገድ) ነው፡፡ በእኛ ግን እንደዛ አደለም፡፡ መሠረታዊ የሚባሉ ቢያንስ ሶስት ትልልቅ የሰው ልጆች ዝርያን የያዝን ነን፡፡ አንዱ ፍጹም ኢትዮጵያዊ፣ አንዱ ምስራቅ አፍሪካ ላይ በብዛት ያለ (ማሳይን ኬንያ የሚያካትት) ሌላኛው ግን እውንም የምንታማበት የመካከለኛው ምስራቅ ሌቫንት የተባለ ጥንታዊ የሰው ዘር(አረብ አደለም) ናቸው፡፡ ይህ ከጥቂት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ሕዝቦች በቀር ሌሎቹ አኩል የሚጋሩት አንዱ ከአንዱ ፍጹም የማይለያይበት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ኦሮሞ፣ አማራ፣ አፋረ፣ ትግሬ፣ ሌሎችም እየተባሉ ዛሬ የሚጠሩ ሕዝቦች ከቋንቋ ውጭ እኔ እንዲህ ነኝ ለማለት የሚያስችል ዘር እንደሌላቸው ነው ይህ መረጃ እንደወረደ የሚናገረው፡፡ ኢትዮጵያውያንን ሊያስማማ የሚችል ነገድ ካለ ደግሞ ሀበሻ የሚለው ጥሩ መገለጫ ነው፡፡ ቃሉ ድብልቅ ሕዝብ ከሚለው ነውና፡፡ ይህን እኮ መጻፈ ቅዱስም ይመሰክራል፣ ኢትዮጵያና ፉጥ(ሊቢያ) ሌሎችም ድብልቅ ሕዝቦች የለናል፡፡ በሌላ ቦታ ኢትዮጵያዊ (አበባ) መልኩን ነበር ዥንጉርጉርነቱን ይላል፡፡ የጥንቱ መጻህፍ የሚለው ኢትዮጵያዊ አበባ መልኩን ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚያመለክተው በዙ የታሪክ ጸኀፍት እንደሚሉት ከጊዜ በኋላ የመጣ መደባለቅ ሳይሆን ጥንቱንም እንዲህ ያለን ሕዝቦች ነን፡፡ በእርግጥም ኢትዮጵያ ጥንት ሰዎች ለችግር የሚሰደዱባት አገር መሆኗ ተጨማሪ ደም ተቀበላ ዘሯን እንዳበዛች እረዳለሁ፡፡ ስለዚህ ዘር ከሆነ ሁላችንም የጥቁር ዘሮች ነን ብሎ በጅምላ መጠቅለል ስህተት ነው፡፡ እኛ ጥቁሩን እንወክላለን እንጂ እነሱ አይወክሉንም፡፡ እኛ ሌሎችንም እንወክላለን ግን ሌሎች እኛን አይወክሉንም፡፡ ይህ እውነታ ለሱዳንና፣ ሱማሌና፣ የመንን ጨምሮ ይሰራል፡፡ ይህ ሕዝብ ከሌሎች ይለያልና፡፡ ከኬንያ ማሳይ ነው ከእኛ ወገን የሚመስለን በአንድ ነገድ ቢጎድለንም፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የጎሳና የዘር ፖለቲካ አትበሉ ይልናል እርሶ፡፡ ምን እንበለው; ያለዘራችን ዘራችንን መንዘራችሁ ጭራሽ አሁን አሁንማ መንደር ድረስ አሳንሳችሁን፡፡ ኢትዮጵያዊነት አለም ነው፡፡ ዘርኝነትን እኮ እርሶ በዋነኝነት ተዋናይ በሆኑበት ሂደት ነው የመጣብን፡፡ በታሪክ ርቀት ማንም አያውቀውም በሚል የነገስታቱን ዘመን እጅግ የከፋ ዘረኝነት እንደሆነ ለትውልዱ ቀረጻችሁበት፡፡ እርሶ ዛሬ ትልቅ ሰው ነዎት እውነታው ይሄ ነበር; ፍጹም የጸዳ ነበር እያልኩ አደለም ግን ቢያንስ አሁን በአለው መለክ የሚነሳ ዘረኝነት እንደሌለ እረዳለሁ፡፡ በዘመን ርቀት ስናይ ደግሞ የጥንቶቹ ከኋለኞቹ የተሻሉ ነበሩ፡፡ የሚኒሊክ ዘመን ከኃይለስላሴ ይሻል እንደነበር እናውቃለን፡፡ እናንተ (እርሶ በዋነኝነት የተሳተፉበት) ግን ያን ዘመን ሲዖል አስመስላችሁ ጆሮ ለሰጧችሁ ሰበካችሁት፡፡ ዛሬ ያለውን የመከነ ትውልድ ፈጠራችሁ፡፡ ለመሆኑ በእርሶ ግምትና እምነት የሚኒሊክ ዘመን እውን እርሶ ነጻ አወጣሀለሁ ብለው ዛሬ ለገባበት ወርደት የዳረጉት የኦሮሞ ሕዝብ በኦሮሞነቱ የተበደለበት ነበር ወይስ የበላይነቱን ያሳየበት ዘመን; ትልቅ ሰው ነዎት፡፡ አሁን ብዙ ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ እንጂ እየተሻሻሉ እንዳልመጡ በእድሜዎ በማየትዎ የሚቀጥለውም ምዕራፍ እንደሚያሳስብዎት ነግረውናል፡፡ ልክ ነዎት በዚህ እስማማለሁ፡፡ መጀመሪያ ሚኒሊክ የኦሮሞን ሕዝብ በኦሮሞነቱ ምን አደረጉት; እውነቱን ይናገሩ እስኪ፡፡ ለመሆኑ የኦሮሞ ጀግኖች እነማን ናቸው; የሚኒሊክን ሥርዓት ከመሩት አሮሞዎች በላይ የኦሮሞ ሕዝብ በዚች አገር ሊጠቅሰው የሚችል ታሪክ አለ; ከዚህ ታሪክ የኦሮሞን ሕዝብ ያላቀቀውና ዛሬ ባዶውን ምልክት የሌለው የባዘነ ያደረጋችሁት እርሶና የእርሶ ተከታዮች አደላችሁም; ጀግናውን ጎበናን እያዋረደ የፌስቡክ ተዋጊዎችን የሚያደንቅ ትውልድ ነው የፈጠራችሁት፡፡ እስኪ ለኦሮሞ ሕዝብ ጀግና ተብሎ የሚጠራ ምልክት ማን ነው; በሕይወት ኖረው ለምልክት በእኛው አድሜ ለመሸኘት እድሉ የገጠመን ሰሞኑን የተለዩንን ታላቁን ጃጋማ ኬሎን እኮ እርሶ የፈጠሩት ትውልድ ታመው ሆስፒታል ገቡ የታሪክ ባለውለታችንን በክብር አስታመን እንሸኝ ተብሎ ለተላለፈው መልዕክት አስተዋጽ ማድረጉን ትቶት እንዲሞቱ ሲራገም ነበር፡፡ እስኪ ይንገሩኝ ለኦሮሞ ሕዝብ ዛሬ ማንን ነው የምትጠቅሱለት; ሁሉንም ታላላቅ የተባሉ ጀግኖች እኮ የኦሮሞ ጠላት አድርጋችሁ የፈጠራችሁት ትውልድ ነው ያለው፡፡ አስቂኙ እናንተ የፈጠራችሁት ትውልድ ለቁጥር የሚታክቱ ጀግኖቹን ጥሎ ውርደቱን እየተቀበለ እየኖረ እንደሆነ ሳያውቅ ደግሞ ሌሎች የአከበሯቸውን ጀግኖች የእኛ ናቸው ይላሉ፡፡ እርሶና መሰሎችሆ የፈጠሩት ትውልድ አሁን በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ነው እያለ የሰው ጀግና ለመቀማት ይሟገታል፡፡ እንዲህ ነው የመከነ ትውልድ ማለት፡፡ በዘር ከሆነ ከላይ እንደጠቀስኩልዎት በላይ ዘለቀ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ እርግጥም የኦሮሞኛ ቋንቋ ይናገሩ ከነበሩ ወሎም ሊሆን ይችላል፡፡ በማንነት ግን ከተባለ በላይ ዘለቀ ጎጃሜ ነው፡፡ ታሪኩም ጀግንነቱም፣ ሁለነገሩ ከጎጃም ሕዝብ ጋር የተያያዘ እንጂ ከእናት አባቱም አገር ጋር አደለም፡፡ ይህ ቁም ነገር ሆኖ ሳይሆን እንደው እርሶና መሰልዎችዎ የፈጠራችሁት ትውልድ እንዴት ባዶውን እንደቀረ ላስገነዝብዎት ነው፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ መከራ የሚያይበትን ሂደት በዋነኝነት እርሶ አሉበት፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲክድ ሁሉንም አማራጭ ተጠቅመው ከኢትይጰያዊነት ከአራቁትና እርቃኑን አስቀርተው ዛሬ አልቃሻና ቁጥር ብቻ ከአደረጉት አንዱና ዋነኛው እርሶ ነዎት፡፡

እርግጡን ልንገርዎት ኢትዮጵያወያን ሁሉ ዛሬ ለገቡበት አዘቅት ምክነያት ወያኔ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ነው፡፡ እርሶ ከንጉሱ፣ የደርግ፣ ከደርግ የአሁኖቹ እየከፋ ነው የሚቀጥለውም ያሰጋኛለ ብለዋል፡፡ እውነት ነው፡፡ ግን እኔ ደግሞ አንደ ነገር ልጨምርልዎት፡፡ ከመለስ ሞት በኋላና በፊት ሲታይ ከመለስ ሞት በኋላ  ለማመን በሚከብድ ሁኔታ የከፋ ነገር እናያለን፡፡ ምንአልባትም መለስ ስንቱን ይዘህው ነበር ብለንም እናመሰግን ይሆናል፡፡ መለስ ከሞተ በኋላና በፊት በአዲስ አበባና ዙሪያው የተደረገውን የመረት ዝርፊያ እንኳን ስናይ በዚህ አጭር ጊዜ አስደንጋጭ ቁጥር እናያለን፡፡ አገሪቱ በአጠቃላይ በዘራፊዎች እጅ ገብታለች፡፡ አህዙን መናገር አልፈልግም፡፡ ስልጣንም ቢሆን እንደዛው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው በኦሮሞ ሕዝብ ምክነያት ነው፡፡ እናነተ ሕዝቡን የምታታግሉት እየገደሉት ከአሉት ሳይሆን ጦርን ከማይፈሩት ከጥንቶቹ ጀግኖች ነው፡፡ እነሱን አለምም አላሸነፋቸውም፡፡ ሞተውም ይሄው በጠላትነት የሚያዩዋቸውን ያስበረግጉታል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ነው እያልኩ በድፍረት የምናገረው ሕዝብ እንደሕዝብ እንደማይወቀስ አጥቼው አደለም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ኦሮሞ በሚል በአንዲት ሰንሰለት ታስሮ የእራሱ ውድቀት ሳያንስ ለሌሎችም ውድቀት ምክነያት ሆኗልና፡፡ ትልቁ ሕዝብ ዛሬ በኦሮሞነት ብቻ እንደልብ የሚዘወር የቦይ ውሃ ነው የሆነው፡፡ ዛሬ የኦሮሞን ሕዝብ ለመዘወር የጠለቀ አስተሳሰብ አላስፈለገም፡፡ እነ ተስፋዬ ገብረአብ የሆነ ምናብ ይጽፉለታል በቃው፡፡ እርካታውም ሌሎችን መጥላት እንጅ ጠላቶቹን መታገል አልሆነም፡፡ ጎበናን የሚንቅ መካን አድርጋችሁት ማን ምሳሌው ይሆነው; ሚኒሊክን የሚያህል ንጉሱን አስጥላችሁት በማን ይመካ፡፡ በኦሮሞነት ሁሉም ወደ አርሲ አኖሌ መንደር ተሰብስቦ ሚኒሊክ እንዲህ አደረገህ እና እንዴት ዝም ትላለህ እየተባለ ዛሬም የሚኒሊክ ወዳጆች ብሎ ከሚያስባቸው ከእነአማራና የቀደሙ የኦሮሞ ጀግኖች ነው የሚዋጋው፡፡ ሚኒሊክን የተዋጉት በወቅቱ የነበሩት አርሲዎች እኮ በሚኒሊክ ቂም አልያዙም፡፡ ጦርነት እንደጦርነትነቱ ጥፋት ነበረበት ከዛ ግን ያሸነፉትም ጮቤ የረገጡበት የተሸነፉትም ያፈሩበት አልነበረም፡፡ የተግባቡበትና ኋላም አድዋን የሚያህል ጦርነት ከሚኒሊክ ጋር የተሰለፉበት እንጂ፡፡ ተገደው ነበር ይልናል የዛሬዎቹ፡፡ እውነታው አደለም፡፡ አርሲን እሺ በውጊያው ቂም ይዟል ብንል እስከ ታች ቦረና ድረስ ያሉ ሕዝቦች እኮ ሚኒሊክን እን ታላቅ መሪያቸው ነው የሚያዩት፡፡ ቦረና እኮ ነው ዋነኛው የሚኒሊክ ወዳጅ የነበረው፡፡ ሚኒሊክም ቢሆን ለቦረና ትልቅ ክብር ነበራቸው፡፡ ሸዋ ሙሉ በሙሉ ሚኒሊክን እንደእናት የሚያይ ነው፡፡ ከአማራው ይልቅ ኦሮሞው፡፡ ወለጋም የእነቦረዳ ግዛት እንዲሁ፡፡ ጅማ አባጅፋር የሚኒሊክ ወዳጅ ናቸው፡፡ ዛሬ በኦሮሞ ሥም አኖሌ ላይ የሆነን አንዲት የጦርነት ክስተት የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተደረገ ጦርነት በሚል በታላላቅ የታሪክ አባቶቹ ላይ በጠላትነት አእምሮውን አጠይሞ እየገደሉት ያሉት አልታይ አሉት፡፡ በነገራችን ላይ የአኖሌ ሀውልት የተተከለው ከመለስ ሞት በኋላ መሆኑና እነማን እንዳስተከሉትም እናውቃለን፡፡ እርሶና ቡድንዎ በጥላቻ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን በተለይም አማራ ከሚባለው ሕዝብ እንዲለይ የጀመራችሁትን የበለጠ በጥላቻ እንዲወርደ ማደረግ ነበር አላማውም እንጂ እውን የጥንቱን የአርሲን ጦርነት ታስቦ አልነበረም፡፡ ዛሬ የኦሮሞ ሁሉ እጣ ፈንታ በኦሮሞነት ሥም የሚወሰነው አእምሮውን እንደፈለጉት በቀረጹት ነው፡፡

የኦሮሞ ነጻ አውጭ በሚል እድሜዎን የፈጁበትን ዘመን ዞር ብለው እንዲያዩት እፈልጋለሁ፡፡ ሰሞኑን ለኦሮሞ ሕዝብ ሌላ ድግስ ተደግሶለታል፡፡ እሱም በአዲስ አበባ ሊኖረው የሚገባ መብት በሚል ነው፡፡ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳወረዱትና መሪና ሰው የሌለው መካን እንዳደረጉት አሳረው ያውቁታል፡፡ በኦሮሞነት ሥም የሚወክሉት ሕዝቡ ወደደም ጠላም ጌቶቹ የሚሰጡትን ይቀበላል፡፡ ይህ አይነት ድራማ ትንንሽ በተባሉትም ሕዝቦች አልተሞከረም፡፡ አንድ ወረዳ የሆነው የኮንሶ ሕዝብ ምን ያህል አስጨንቆ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ ሌሎች ብዙ ሕዝቦችም በዛ አካባቢ እንዲሁ አውቃለሁ፡፡ ለምሳሌ የቡርጂ ሕዝብ ሌላው ነው፡፡ ያስተውሉት እየሆነ ያለውን፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ እንዴት ከመሪነትና ከኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ሙልጭ ተደርጎ እንደ ወጣ፡፡  የሚኒሊክን ዘመን እንተወው ያ ዘመን 80 በመቶው የሚሆነው ስልጣን ይመራ የነበረው በኦሮሞውች ነውና፡፡ በሃይለስላሴም በደርግም ቢሆን ኦሮሞ ተሳትፎው ጉልህ ነበር፡፡ አገሪቱ በታሪኳ በብዛት የኦሮሞ ልጆች የመሩት የነበረው የመከላከያው ተቋም ሳይቀር እንዴት ከአሮሞ እንደጸዳ፡፡ ዛሬ ኦሮሞን ሊወክል የሚችል በክልልም በፌደራልም የለም፡፡ አማራ የተባለው አሁንም ቢሆን ለወያኔ ዋዛ አልሆነም፡፡ ወያኔም ትልቅ ሥጋት የሆነባት ይሄው ከመጀመሪያውም በጠላትነት የፈረጀችው አማራ ነው እንጂ አሮሞውን በቀላሉ የምትዘውርበት መዘወሪያው በእጇ ነው፡፡ ጎንደሬዎቹ የኦሮሞን ሕዝብ በደልና የኦሮሞን ነጻነት ታጋዮች በአደባባዮቻቸው ይዘው የወጡበት ክስተት ወያኔን መቀመቅ የከተተ አደጋ ነበር፡፡ ከዛ አዘቅት ለመውጣት የተባበሯትና አሁንም አማራና ኦሮሞን እስከዘለቄታው በጠላትነት ለማኖር የሚሰሩላት ብዙ ኦሮሞዎች ቀድማ ስለነበራት ሕዝብ አንድ ነን እያለ በይፋ ወኔው በተቀሰቀሰበት ወቅት ነበር ለንደንና አተላንታ ላይ የኦሮሞን ሕዝብ ወክለው ድምጽ የሆኑትን የሰማንው፡፡

ሰሞኑን ኦሮሞ በአዲስ አበባ ሁሉም ተቋማት ስልጣን ይኖረዋል፣ የከተማ ቦታ በነጻ ይሰጠዋል ሌሎች ግን አሁን ከሚከፈለው በእጥፍ ይከፍላሉ የሚለውን የከተማውን ደንብ ወሬ ሰምቼ ምን ያህል እዝቡን እንደናቁት ሳስብ አዝኛለሁ፡፡ እርግጥ ነው ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ብዙ ያዘንኩባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለዛም ነው ዛሬ አመታት እየተቆጠሩ ነው እውነቱን እንደወረደ መናገር ከጀመርኩ፡፡ ይህ ደንብ አዲስ አበባን ፊንፊኔ ማለት ለኦሮሞ ትልቅ ነገር እንደሆነ ዛሬ ያለውን የኦሮሞን ስነልቦና የፈጠሩት ገብቷቸዋል፡፡ በተግባር ማን ያቀምሰዋል በሰነድ አዲስ አበባ ላይ መሬት ለኦሮሞ በነጻ ነው ሌሎች 2 እጥፍ ይከፍላሉ፡፡ አዎ ሌሎች ያሉት ራሳቸውን ነው፡፡ አደለም ሁለት እጥፍ አስር እጥፍ ቢከፍሉ ገንዘቡን ሁሉ ዘርፈው ይዘውታል፡፡ ከዛ በሕጉ መሠረት እነሱ አገሩን ሁሉ ገዝተውት ኦሮሞ በባርነት ይቀጥላል፡፡ ለነገሩ አዲስ አበባ ላይ በሊዝ የሚሰጥ ለእነሱ ሪዘርቭ የተደረገ እንጂ ለግል ቤት መስሪያ የሚሆን ቦታ የለም፡፡ ሰው ዛሬ ቤት የሚሰራው ወጣ ብሎ ነው፡፡ ኦሮሞ ደግሞ ኢንቨስት ሊያደርግ የሚችለው ገንዘብ የለውም ስለዚህ አደለም በነጻ ድጎማ ገንዘብ ቢጤ ቢጣልለት ከእነሱ እኩል መወዳደር አይችልም፡፡ ሑሉንም አዘጋጅተው የሚወስኑለትም እነሱ እንጂ የሚለውጠው የሚያሻሽለው የለም፡፡ አዲስ አበባና የአዲስ አበባ መንገዶች በኦሮምኛ ይጠሩለታል ከዛ በቃው፡፡ ለዘመናት እዚህ እንዲደርስ አሁንም አቶ ሌንጮ እርሶ ነበሩበት፡፡ ሕዝቡ እንዲህ እንዲያስብ አደርገውታልና፡፡ ታሪክ እውነት ምናምን የሚባሉ ነገሮችን እንዳያስተውል፡፡ አዲስ አበባ እኮ የጣይቱ ከተማ ነች፡፡ መንገዶቿና ቦታዎቿም ቢሆኑ ሁኔታዎች በፈጠሯቸው እውነታዎች ሥያሜያቸውን አገኙ አንጂ አማርኛ ለመደረግ አልተሞከሩም፡፡ ቀበና፣ የካ፣ ቦሌ፣ ጉለሌ፣ ለመሆኑ ግን እንደው ታስቦ አማርኛ የሆነ ቦታ ይኖር ይሆን;  ይልቅ የዛሬዎቹ ሆነው ቢሆን እስከዛሬ በአዲስ አበባ የኖሩት አንኳን የቦታ ሥም ኦሮምኛ ቋንቋ በ100ኪ.ሜ. ራዲየስ ውስጥ የማይነገርበት አገር ባደረጉት ነበር፡፡

እድሜ ለሚኒሊክ እንጂ ዛሬ ገዳ ምናምን የሚባለው የኦሮሞ ሥርዓትም እንኳን በዩኔስኮ ሊመዘገብ ማንም ባላወቀው፡፡ ገዳን ያቆዩት የሚኒሊክ ወዳጆች ቦረናና በተወሰነ ሸዋ ናቸው፡፡ ሚኒሊክም በተለይ ለቦረና የገዳ ሥርዓት ልዩ ትኩረት እንደነበራቸውና አባ ገዳዎችን በብዙ መልኩ ይደግፏቸው እንደነበር ቦረናዎች ራሳቸው ይናገራሉ፡፡ አሊያማ ኢንግሊዝ ቅኝ ገዝታ ማንነታቸውን ባጠፋችው፡፡ እውነታው እኮ ይሄ ነው፡፡

አቶ ሀብታሙ አያሌው ይችን አገር ለኦሮሞ አሳልፈን እንሰጣታለን ታርፉ እንደሁ እረፉ ተባልን ይለናል፡፡ ይህ ምንን ነው የሚነግረን ለመሆኑ፡፡ ለመሆኑ አገሪቱን የመሠረቷት እንማ ነበሩ; በአማራና ኦሮሞ መካከል ትልቅ የጠብ ግድግዳ እንዳቆሙ ስለተማመኑ እኮ ነው እንዲህ የሚሉት እንጂ ለኦሮሞ መሠጠት ለአማራው ለምን ሥጋት የሆንበት ነበር፡፡ እርግጥም ነው አሁንም አቶ ሌንጮ ወደእርሶ እመለሳሁ፡፡ እርሶ በእነዚህ ታላላቅ ሕዝቦች መካከል አሁን ሰዎቹ የሚሉት ሊሉ በሚያስችላቸው ደረጃ ጥላቻ እንዲፈጠር ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበሩ፡፡ አሁንም ግልጽ አደሉም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ከአባቶቹ ታሪክ ተላቆ ባዶውን ስለቀረና የአባቶቹን አገር ለጠላቶቹ ስለሰጥ ጀግኖች አባቶቹንም ስላአዋረደ ዛሬ ሌላውን ለማስፈራሪያ ዋይ የሚሉበት መሣሪያ እቃ አድርገውታል፡፡ ይህ እጅግ ያማል፡፡ ለኦሮሞ አሳልፈን እንሰጣታለን!!! ይህ አይጃኢብ የሚያሰኝ ነገር ነው!

በመጨረሻ አቶ ሌንጮ እስከሁንም የዘር ፖለቲካ አደለም ብለው ሊከራከሩን አይሞክሩ፡፡ ዘር ከተባለ አሮሞ ከአማራ የተለየ ዘር የለውም፡፡ ውስጥ ለውስጥ ያለ የዘር ልዩነት ከተባለ ደግሞ የወለጋ አሮሞና የሀረር ኦሮሞ በዘር ከሚገናኘው ይልቅ ጎጃምና ወለጋ ይቀራረባል፡፡ ማንነት ከተባለ ደግሞ ሁሉም እንደየ አካባቢው የየራሱ ማንነት አለው፡፡ ኢጆሌ ባሌ፣ ኢጆሌ ጂማ፣ ኢጂሌ ነጆ፣ ኢጂለ ሻምቡ እያለ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚጠራበት የየራሱ ማንነት አለው፡፡ አማራ በሚል የታጨቊም እንዲሁ ነው፡፡ ሸዋን እንኳን ብንወስድ፣ በንዜ፣ መርሀቤቴ፣ ቡልጋ ምናምን እየተባለ ማንነቱን ይለያል፡፡ እነዚህ ሥያሜዎች ከዘር ጋር አይገናኙም ከአገር ከወንዝ፣ አብሮ ከሚጋሩት ማህበራዊ እሴቶች እንጂ፡፡ ኢጆሌ ጂማ ማለት ጂማ የተወለደ ሁሉ ነበር ድሮ፣ ዛሬ ኢጆሌ ኦሮሞ በሚል ውበቱን ሁሉ ወደ ዘር የቀየረው የእናንተ ፖለቲካ ነው፡፡ የዘር ሳይሆን የዘረኝነት ብዬ አረጋግጥልዎታለሁ፡፡ የድሮ ኢጆሌዎች ህብረት በአገር ልጅነት ነበር፡፡ ብዙ አብረው የሚጋሯቸው ነገሮች አሉ፡፡ ኢጆሌ ባሌ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ ሁሉም ነበር፡፡ ዘፈኖቻችን ሳይቀሩ ዛሬ ላይ እንዴት ጆሮ እንደሚያሳክኩ፡፡ ብሄር ብሄረሰብ የተዋረድንበት፣ ማንነታችንን ያጣንበት፣ በአካባቢያችን አብረን የምንኖረውን ኦላ እንለዋለን ያጣንበት፡፡ ዛሬ በውጭ ኢትዮጵያዊ ሲገናኝ የአገር ልጅነት የሚል የለም፡፡ የአገር ልጅነት የሚጀምረው ድሮ ከቀዬው ነው ከዛ ወደ ትምህርት ቤት፣ ከዛ ውጭ ሲወጣ ሁሉምንም ደግሞ በኢትዮጵያዊነት የሚጠቀልል መንፈስ ነበር፡፡ ይህን ሁሉ ነው ያሳጣችሁን፡፡ በአንድ አላማ ለመቆም አልቻልንም፡፡ የኦሮሞ ባንዲራ ይዘው በኢትዮጵያዊነት የመደራጀትም ሆነ የማደራጀት ሞራሉ አለኝ ቢሉኝ እኔን አሁም እባክዎ ነው የምለው፡፡ በቋንቋ አደለም የተለያየንው የተለያየንው በመንፈስ ነው፡፡ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ለማራቅና ወደፊት ታሪኩንም የማያውቅ ትውልድ ለመፍጠር ታስቦ ቁቤ ማስተማሪያ ሲደረግ እርሶ ነበሩበት፡፡ ሰሞኑን እሱንም እንቀይራለን ሌላ መልክ መያዝ አለበት የሚሉ መጥተዋል፡፡ እርሶና ቡድንዎ አማራ የሚባውን ከፍ ሲልም እርሶና ተከታዮችው ሀብሻ (ማን ምን እንደሆነ ከላይ የተውኩትን ጽኁፍ ያንብቡት) የሚሉትን ሕዝብ ለመጥላትና ለማስጠላት የግዕዝ ፊደልን የጠላት አደረጋችሁት፡፡ ብዙ ስታዳክሩት ከረማችሁና ሰሞኑን ደግሞ የኮሽ አገር ምናምን የሚል ወሬ ተጀምሯል፡፡ በራሳችን ባንቀልድ ጥሩ ነው፡፡ ኩሽ የምትሉት ሕዝብ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሀበሻ የተባለው ሕዝብ ነው፤፡ ኩሽ በእኛ ከአለው ደም አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡ የቅርቡን ታሪክ መሠረቱን አጥፍቶ የማይታወቅ ታሪክ ማውራት ያሳዝናል፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ አባ ባህሬ ድንቅ አድርገው ጽፈውት ነበር፡፡ ኦሮሞ ያንን እንዲያነብ አልተፈለገም፡፡ ኦሮሞ እንዲያነብ የተፈለገው የቡርቃው ዝምታ ዘረኛ ልብወለድ ነው፡፡ 72 ዓመት ተከታታይ 9ገዳ አንድም ሳያስታጉሉ ታሪኩን የጻፉለት አባ ባህሬ ዛሬ በኦሮሞዎች ዘንድ እንደ ልዩ ጠላት ተስለዋል፡፡ ለመሆኑ አባ ባህሬ የጻፉት ያነበበ አንድ ኦሮሞ ይኖር ይሆን;  የዘመኑም የዲንኤ ጥናት፣ የአባ ባህሬም ድንቅ ሥራ፣ ለዘመናት ተሻግሮ እዚህ የደረሰው እንደነ ኢሬቻና ራሱም ገዳ እንሚጠቁሙን ኦሮሞ በአንድ ወቅት በሰሜን ከነበሩ ሕዝቦች ጋር የሚኖር የኦሪት እምነት ተከታይ ሰዎች በመለያየታቸው ምክነያት ተለየቶ የራሱን ባህልና ስርዓት እየተከተለ መጥቶ እንደገና ከዘመናት በኋላ እንደተቀላቀለ እናስተውላለን፡፡ ይህ በኦሮሞም ብቻ አደለም በሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሆነ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ሌላ ጊዜ እመለስበት ይሆናል፡፡ ለጊዜው አቶ ሌንጮ እውን ከአሳሰበዎት አሁን አንደካሳም እንደንስሀም እንዲሆንልዎት ከልብ በሆን ኢትዮጵያያዊነት እንጅ እርሶ ማንነት በሚሉት ዘር ከሆነ ያሉት በቃን አልተቀየሩም፡፡ ከተቀየሩ ግን እውነታውን ይጋፈጡ፡፡ ሥጋትዎና ያዩዋቸው እውነታዎች ትክክል ናቸው፡፡ ቀላል ነገር ለመቀየር እንኳን እልሆነላችሁም፡፡ እናንተ አሁም በኦነግ ባንዲራ ሥር ናችሁ፡፡ በቀላሉ በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ሥር ሕዝቡን ብትመሩት ምን ያህል እምርታ እንደሚመጣ እናውቃለን፡፡ በአላመ ጽናት ከአለ ይሄን ይጋፈጡታል፡፡ እንዲዘነጉት የማልፈልገው እስከ ደርግ በነበሩ ሥርዓቶች እውነታ ኦሮሞ ጨቋኝ እንጂ ተጨቋኝ አልነበረም፡፡ በመሪነት ማለቴ ነው፡፡ ሕዝቡ እንማኝኛው ሌላው ሕዝብ እንጂ የተለየ ጭቆና አልነበረበትም፡፡ አነስተኛ የነበሩ መስተካክሎች መኖር እንደነበረባቸው ግን አላጣሁትም፡፡ እናንተ ነጻ እናወጣሀለን ያላችሁት ሕዝብ ግን የገዥነት እንጂ የተገዥነት መንፈስ ከእነናንተ በፊት አይሰማውም ነበር፡፡ ዛሬ ግን ወርዶ ምንም አቅም የሌለው መካን እንደሆነ ያስተውሉ፡፡

አመሰግናለሁ!

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርጸ ደስታ

 

The post ለአቶ ሌንጮ ለታ፡-ለሁላችሁም ለኢትዮጵያ ውድቀት ምክነያት ለሆናችሁ – ሰርጸ ደስታ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles