“የትግራይ ህዝብና ህወሓት ኣንድና ኣንድ ናቸው” የሚሉት ሁለት ኣካላት ቢሆኑም ነገር ግን ኣንድ ዓይነት ዓላማ የያዙ የስልጣን ጥመኞች ናቸው። እነዚህም፦
፩) ኣምባገነኑ የህወሓት ስርዓት ” እኔ ከሌለሁ የትግራይ ህዝብ ጠላቶችህ ያጠፉሃል” በማለት ህዝቡ ለህልውናው ብቻ ብሎ ህወሓትን ከውድቀት እንዲጠብቀው በማሰብ ” የትግራይ ህዝብና ህወሓት ኣንድ ናቸው” ይላል።
፪) በኣምባገነናዊ ባህሪ ከህወሓት የሚመሳሰሉ ፅንፈኛ የስልጣን ጥመኞችና ዘረኞች በህወሓት መንገድ ተጉዘው ራሳቸው በህወሓት ቦታ ማግኘት የሚሹ ተጠባባቂ ኣምባገነኖች ሲሆኑ ፀረ የትግራይ ህዝብ በሚያካሂዱት ቅስቀሳ የዘር ጭፍጨፋ ቢያጋጥም እንደ ህወሓት እያዩ እንዳላዩ ለማለፍ ዝግጁ የሆኑ ናቸው።
እነዚህ ሰዎች በተዘዋወሪ መንገድ የህወሓት የፕሮፖጋንዳ መሳርያ በመሆን ህዝብ ራስ በራሱ እንዳይተማመንና አምባገነኑ ስርዓት እንዳይሸነፍ የራሳቸው ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
ሃቁ ግን ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ጨቋኝና ተጨቋኝ፤ ገዢና ተገዢ፤ ኣምባገነን መንግስትና ተረግጦ የሚኖር ህዝብ ናቸው።
የህወሓት/ኢህኣዴግ ኣባላት ሊያውቁት የሚገባቸው ነገር ቢኖር፡ የትግራይ ህዝብና ኣምባገነኑ የህወሓት ስርዓት ተቃራኒ ኣካላት መሆናቸውና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመተካት ከተቀሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በማበር ታግሎ እውን እንደሚያደርገውም እሙን ነው።
በትግራይ ህዝብ ላይ ሌላው ኢትዮጵያዊ በጥላቻና በዘረኝነት ኣነሳስተው ወገን ለወገን ዘር መሰረት ያደረገ ደም መፋሰስ የሚፈልጉ፣ ወይም ጨፍጭፈው ሊገዙት የሚፈልጉ፣ በህወሓት/ኢህኣዴግ ወንጀል ህዝብ ተጠያቂ ለማድረግ ለሚፈልጉ ፅንፈኛ ዘረኞችና ተተኪ ኣምባገነን ለመሆን የሚቋምጣቸው ኣካላትም ኢንዲሁ ይታገላቸዋል።
የትግራይ ህዝብ ደርግን ኣምርሮ ሲታገል በትግርኛ ተናጋሪ ኣምባገነን ለመተካት ኣልነበረም። ከህወሓት በኋላ መምጣት ያለበት ስርዓት ዲሞክራሲያዊ መሆን ኣለበት።
ሁለታቹ ኣካላት ነገራቹ ከትግራይ ህዝብ ኣውርዱ።
ነፃነታችን በእጃችን።
it is so.
The post ሁለቱ አምባገነኖች – አምዶም ገብረ ስላሴ appeared first on Medrek.