እርዳታ ዘይት ከተጫነበት መኪና በቀጥታ ወደ ነጋዴዎች መጋዘን ገብቶ እየተቸበቸበ ነው። በትግራይ ክልል መንግስት ያመነበት በድርቅ የተጠቃ የህዝብ ቁጥር 1.2 ሚልዮን መሆኑ ይታወቃል።
ለዚህ ህዝብ የመጣው የእርዳታ ዘይት ከመኪናው እየተዘረፈ በሃብታም ነጋዴዎች መጋዘን በማከማቸት እየተቸበቸበ ይገኛል።
የእርዳታ እህል መጋዘን ጠበበ፣ ለኣባይ ግድብ መስርያ እያሉ መዝረፉ ወደ ዘይት ተሸጋግሮ በመቐለ የተወሰኑ ሱቆች እየተሸጠ ይገኛል።
የኣንድ USAID የሚል ጣሳ ባለ 4 ሊትር ዘይት በ220 ብር እየተሸጠ ይገኛሌ።
ይኸው በእርዳታ የመጣ ዘይትና እህል በሙሰኞች እየተዘረፈ ነው።
መጋዘኖቹ በመቐለ ቀዳማይ ወያነ፣ ዓዲሹም ድሑንና ዓዲ ሓውሲ ይገኛሉ።
ይሄ የምትመለከቱት ሱቅ በቀዳማይ ወያነ የሚገኝ ነው።
በሌላ ኣቅጣጫ ደግሞ እርዳታ ባለ ማግኘታቸው በረሃብ ምክንያት በሞት ኣፋፍ የሚገኙ ሰዎች እጅግ በርካታ ናቸው።
ይሄ ማጣራት የፈለገ ወገን ካለ ወረዳ ራያ ዓዘቦ የሚገኝ ሓደ ኣልጋ ቀበሌ ሄዶ ማረጋገጥ ይችላል።
ረሃብ……ረሃብ……ረሃብ…… የሞት ምክንያት እየሆነ ነው።
ውድ ኢትዮጵያውያን በረሃብ ለተጠቁ ወገኖቻቹ ኣስቸኳይ እገዛ ኣድርጉላቸው። እርዳታው ራሳቹ በኣካል ተገኝታቹ ኣከፋፍሉ። ለመንግስት ከሰጣቹት ግን ይሄው ካድሬዎቹ ይበሉታል።
The post የእርዳታ ዘይት ተዘርፎ እየተሸጠ ነው። – አንዶም ገብረ ስላሴ appeared first on Medrek.