![20111124-WN-09-Ethiopia-Attempts-to-Insulate-Against-Drought](http://www.satenaw.com/amharic/wp-content/uploads/2015/12/20111124-WN-09-Ethiopia-Attempts-to-Insulate-Against-Drought.jpg)
የህጻናቱ ሁኔታ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ሲገልፅ የቆየው ይኸው ተቋም፥ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የህጻናቱን ህይወት ለመታደግ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በቀጣዩ ጥቂት ወራቶች ውስጥ የተረጂዎች ቁጥር ወደ15 ሚሊዮን ያሻቅባል ተብሎ በመጠበቁም ለጉዳት የሚጋለጡ ህጻናት ቁጥርም አብሮ እንደሚጨምር ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በድርቁ ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ህጻናት ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ መድረሱን ያወሳው ድርጅቱ በሀገሪቱ ያለዉ የድርቅ አደጋ ከተገመተዉ በላይ መሆኑንም አመልክቷል።
የህጻናት አድን ድርጅቶች ጥምረት በበኩሉም ልዩ ድጋፍና ክትትልን የሚፈልጉ ህጻናት በቂ ድጋፍ እያገኙ አለመሆኑ ስጋት መፍጠሩን ገልጿል።
ይኸዉ ከ180 በሚሆኑ ወረዳዎች ዉስጥ ተከስቶ ያለዉ የድርቅ አደጋ እስከቀጣዩ አመት መጋቢት ወር ድርስ ቀጣይ በመሆኑም አስከፊ የጤናና የአካል ጉዳት የሚደርስባቸዉ ህጻናት ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ጥምረቱ አሳስቧል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የአለም አቀፉ ማህብረሰብ የገባዉን ቃል ባለመጠበቁ ሳቢያ ቸግሩ እየተባባሰና የተረጂዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን በደጋሚ አስታዉቋል።
Source:: ethsat
The post በድርቁ ምክንያት 400ሺ ህጻናት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው፣ አንድ ሚሊዮን ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ appeared first on Medrek.