Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ባለሥልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ያገኙታል›› ካሪቱሪ

$
0
0

እርስዎ 10 ሺሕ ሔክታር ጠየቅሁ ቢሉም እኛ የምናውቀው ግን 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደተቀበሉ ነው፡፡ ይህ እውነት አይደለም እንዴ?

ራም ካሪቱሪ፡- የተመዘገበና በየትኛውም ፍርድ ቤት ላረጋግጠው የምችለው ሀቅ አለኝ፡፡ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡
ደስ አይልም ህንዱ ‹‹ምርጫ አልነበረኝም››ሲል ወሰድኩት ማለቱ ነው ከዚያስ ፉከራውን ስሙልኝማ
‹‹መሬቴን ንኩና የህንድን ኃያልነት ታያላችሁ፡፡ ይኼ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ፡፡ ራሴን መከላከል አያስፈልገኝም፡፡ ባለሥልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ያገኙታል››፡፡
ሳይጠይቅ ሰጥተውት ሳይጠይቅ ሊቀሙት ሲያሰፈስፉ እንደነርሱ ‹‹ደደብ››ባለመሆኑ
‹‹የህንድን ኃያልነት ታያላችሁ ይላቸዋል፡፡
የህንድ ግን ኃያልነት በፍቅር ፊልሞቿ ይመስላቸው ለነበሩ ‹‹ደደቦችስ ››ማስፈራሪያው ትርጉም ይኖረው ይሆን፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

The post ባለሥልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ያገኙታል›› ካሪቱሪ appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles