ከኦሮሚያ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ያለ ቢመስልም ትናንትና ዛሬ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም ከትላንት ምሽት ጀምሮ ተማሪዎች የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተከሰተው የሕዝብ አመጽን ተከትሎ ይህን ለማረጋጋት ሁሉን ነገር እየፈነቀለ የሚገኘው ሕወሓት የሚመራው መንግስት የአምቦ ዩኒቨርሲቲን ከትናንና ምሽት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ መቆጣጠሩን ተከትሎ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ተሰምቷል ::
ዩኒቨርሲቲውን ፌደራል ፖሊስ ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ ከተቆጣጠረው በኋላ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል:: አንዳንድ ሴት ተማሪዎች መኝታ ክፍላቸው በፖሊስ ተሰብሮ በመግባት አሳፍሪ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሴት ተማሪዎች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን እና ግቢው መወረሩን ተከትሎ ተማሪዎች ወደየቤታቸውና ወደየመጡበት ከተማ እየሄዱ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ እንደሚመስል ገልጸዋል:፡
The post ተቃውሞው ዛሬም በምዕራብ ሸዋ አንዳንድ አካባቢዎች ተቀጣጥሎ ይገኛል appeared first on Medrek.