ታሪክ እንደሚያስረዳን ወይም ከታሪክ እንደምንረዳው በተለያዩ ጊዜዎችና ወቅቶች የውጭ ወራሪዎች(ጠላቶቻችን)በቀይ ባሕር እየዘለቁ ኢትዮጵያን ሲፈታተኑ አንዳንዴም በለስ እየቀናቸው እስከ መሀል አገር የዘለቁበት ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል።ይሁን እንጅ ሕዝቡ እሽ ብሎ በፈቃደኝነት አልነበረም ወራሪዎችንም ሆነ ኢትዮጵያውያንን ብዙ ዋጋ አስከፍሏል ብዙ የሰው ሕይወት የተቀጠፈበትና የሀገር ሀብት የወደመበት ጦርነት ተካሂዷል።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ለሀገራቸው ቀናኤ ያላቸው ጀግኖች ድንበራችን አናስደፍርም አገራችን አናስወርርም በማለት እስከ 1983ዓ/ም ድረስ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ተከብሮ ቆይቷል።ይህ ታሪክ የትግራይን ሕዝብ ያካተተ ታሪክ ነው።ከ1983ዓ/ም ወዲህ ግን የትግራይ ሕዝብ እንደ እንቁላል ከብክቦ ያሳደጋቸው የእናት ጡት ነካሾች ኢትዮጵያ ታሪክ እንደሌላትና ቢኖራትም የመቶ አመት ታሪክ ነው በማለት እነዚህ ህወሃት በሚል የሚጠሩ የሀገር ውስጥ ጣሊያኖች በግድ ኢትዮጵያ ታሪክ የላትም እንድንል ሊያዛቡን ሲከጅላቸው ተስተውለዋል።የትግራይ ህዝብ ተንከባክቦ ያሳደጋቸው ልጆቹ ከሚፈለገው በላይ ሲጓዙ 5ሚሊዮን አማራ ዘሩ ሲጠፋ፤የወሎና የጎንደር መሬት በኃይል ተነጥቆ ወደ ትግራይ ሲካለል በተለይም ወልቃይት እንዳለ ዘሩ እንዲጠፋ ሲደረግ፤የአማራ ሀብት ተዘርፎ ወደ ትግራይ ሲጋዝ፤አጼ ዮሐንስ የተሰውበት ድንበር ተጥሶ ጠላት ለሆነችው ሱዳን አልፎ ሲሰጥ፤አፋሮች፤የኢትዮጵያ ሶማሌዎች በጅምላ ሲጨፈጨፉ፤አሁን የኦሮሞ ሕዝብ ይዞት የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማንኮላሸት የትግራይ ሕዝብ ያሳደጋቸው ውሻዎች እያሳደዱ ሲገድሉት፤በውጭ የሚኖረው የትግራይ ተወላጅ ከጥቂቶች በስተቀር የዚህ አገር አጥፊ ድርጅት ሰላይና ወሬ አቀባይ ሲሆኑ የትግራይ ሕዝብ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ አንዲት ቃል ትንፍሽ አለማለቱ በእጅጉ አስገራሚ ጉዳይ ነው።ይህ ሁሉ አረመኔያዊ ድርጊት ሲፈጸም ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ተገቢ ነገር ነው ወይ?አሁን እኮ 11ኛው ሰአት ላይ ደርሰናል ምን አለበት ልጆቻችሁ ሥልጣን በሰላም ቢያስረክቡ?እናንተስ ለምን ነገ በሰላም በጋራና በአንድነት ለምንኖርባት ኢትዮጵያ ከእኛ ጋር ዛሬ አትመክሩም?በጣም አነጋጋሪና አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ ልትመክሩበት ይገባል።
ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መልስ ዜናዊ አንድ ወቅት ላይ እንኳን ከእናንተ ተወለድኩ በማለት ሲመጻደቅ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ማንቋሸሹና ዝቅ አድርጎ መመልከቱ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ ወርቅ ህዝብ ነውም ማለት ነበር።ባልሳሳት እናንተም በልባችሁ እንኳንም የእኛ ልጅ ሆንክ ማለታችሁ እንደማይቀር ግልጽ ነው።እናቴ በእንቁላሉ በቀጣሽኝ እንዲሉ መሪያችሁ ስድ እንዲሄድ ተደረገ እነሆ አሁን ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ደርሰን እንገኛለን።አማራንና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በጠላትነት ፈርጆ የተነሳው የነገዋን ታላቋ ትግራይ ትግርኝት ሪፐብሊክ መስርቶ ሳያይ የአማራውን የመጨረሻ እጣ ፈንታና የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ፍጻሜ ሳያይ ያለፈው መለስ የራእዩ ተረካቢዎች ራሳቸውን እንኳን ሊመሩ የማይችሉ የዘቀጡ መሆነቸውን እያስመሰከሩ ነው።
ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)ይዞት የተነሳው መፈክር የትግራይ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ የተለየ ተጨቁኖ ሳይሆን ከዚህ በስተጀርባ ያለውን ወይም የነበረውን መመልከት አልቻልንም ነበር።በመሆኑም ነው ዛሬ ኢትዮጵያ የመበታተን አደጋ ላይ የምትገኘው ከሦሥት ሽህ ዘመን በላይ ታሪክ ያላትን አገር እንዲህ በዋዛ ለመበተን የሚደረገው አባዜም ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል እነዚህ እንደተለከፈ ውሻ የሚቅበዘበዙ ከእናንተው አብራክ የተፈጠሩ የህወሃት አባላትና አመራሮች 1/የሰላም መንገድ እንዲመርጡ፤2/ይህን የጅምላ ጭፍጨፋ እንዲያቆሙ፤3/የሀገር ሀብት መዝረፉንና ማሸሸቱን እንዲያቆሙ፤4/ከፍርሃት በመነጨ ንጹሃን ዜጎችን አገር ጥለው እንዲሰደዱ ማድረግና ወህኒቤት አሸባሪ ናችሁ በማለት ማጎር እንዲያቆሙ፤5/ዛሬ በዘጠኙ ክልሎች የአማራ ነገድ አባል የሆነ በጠላትነት ተፈርጆ የጥቃት ሰለባ የሆነው በዚሁ እናንተው ባሳደጋችሁት ህወሃት መሰሪና ቅጥረኛ ድርጅት የሀሰት ፖለቲካ በመሆኑ እውነቱን በማውጣት ከድርጊታቸው ተቆጥበው ከወዲሁ ማስተባበያና ይቅርታ እንዲጠይቁ ብታደርጉ ነገ እኛና እናንተ ያለምንም ቅሬታ በሰላም አብረን እንደ ድሯችን መኖር እንችላለን።ከዚህ ላይ አንድ ለማለት የምፈልገው የትግራይ ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቅ አላልኩም ህወሃትን ነው ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ያልኩት።
ብዙ ጨካኝና አረመኔ የዓለም መሪዎች የአገር ሀብት የሕዝብ ሕይወት አውድመው የካበቱትን ንብረትም ሳቃይጠቀሙበት ተገቢውን ቅጣት እያገኙ በሰፈሩት ቁና ተሰፍረው ተንከታክተው ወድቀዋል።ይህ ፀረ-ሕዝብ ድርጅትም ብዙ ጊዜ እንደማይቆይና በሰፈረው እንደሚሰፈር በሕግ ፊት ቀርቦ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት መተንበይ ነብይ መሆንን የሚሻ አይደለም።ህወሃት ማለት አሁን ሥር የሌለው ዛፍ ወይም የተነቃነቀ ሊወልቅ እንደሚችል ጥርስ ማለት ነው ከሕዝብ የተነጠለው ገና መጀመርያ ህወሃት ከሁለት ሲከፈልና ከምርጫ 97 በኋላ ነው አሁን ሕዝብና ህወሃት ሆድና ጀርባ ናቸው በምንም ተአመር የሕዝቡን ልብ ለማባበል አይችሉም።ካድሬውና ከላይ ያለው አመራር በደህንነት መከላከያና በአጋዚ ጦር ጥበቃ ታጅቦ የማይደፈር ቢመስልም መሐሉ ዳር ዳሩ መሀል የሚሆንበት ቀን እየቀረበ እየመጣ ስለሆነ ሰፊው የትግራይ ህዝብ እነዚህን አውሬዎች ሊነግራቸው ይገባል ባይ ነኝ።
በመጨረሻ የትግራይ ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው ነገር ቢኖር የህወሃት የደህንነት ተቋም ከሚፈጽማቸው በጣም አሳፋሪ ተግባሮች አንዱ የሆነውን ለመግለጽ እወዳለሁ። ሁሉም የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች፤ምእራባውያንና ዐረቦች ያለ ሀብታቸውን ይዘው ለመዝናናት የሚዘልቁት ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ነው።ታዲያ የህወሃት የደህንነት መስርያ ቤት ከሁሉም ክልሎች ቆንጆ የተባሉ ሴቶችን ለእነዚህ ነውረኛ ባለሀብቶችና ለአፍሪካ መሪዎች እንደሚሸጥ ዕቃ ተደርድረው ይቀመጡና እያንዳንዱ የሚፈልጋትን ሴት በመውሰድ እንደሚያማግጥ ከአንድ ታማኝ የሆነ ሰው ስሠማ ራሴን ለማመን ተቸግሬ ነበር እነዚህ ቆንጆ ሴቶችም ራሳቸውን አርክሰው የአለሌዎችን ፍላጎት ስለ አሟሉ ከአፍሪካ ህዝብ በተዘረፈ ገንዘብ ቤት፤መኪና፤የፈለጉትን ጌጣጌጥ መግዛት የሚያስችል ንብረት በአንድ ምሽት ያገኛሉ ማለት ነው።ሌላውን ሳንመረምር ከሚገኘው ገንዘብ ጋር ብቻ ካያያዝነው መለስም ስለስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሲጠየቅ እኛ ከምንከፍላቸው የተሻለ ካገኙ ቢሄዱ ምን ችግር አለበት የሚለውን እንዳንደግም እሰጋለሁ።
በአብዛኛው ወደ ውጭ አገር በተለይም ወደ ዐረቡ ዓለም የሚፈልሱት ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ጠልተው አይደለም ከሴተኛ አዳሪነት ሠርቶ መብላት ይሻላል በማለት እንጅ በርካታ ደላላ ድርጅቶች እውቅና አግኝተው ወጣት ኢትዮጵያውያንን የሚያፈልሱት ይዋል ይደር እንጅ ነገ በሕግ ፊት እንደሚቆሙ ግልጽ ነው።የእነዚህ በመዲናችን ከማንም ዘራፊ የአፍሪካ መሪዎች፤ከምእራባውያንና ከአረብ ጋር የሚዳሩትን ሁኔታ ግን ማጋለጥና ሕዝቡ የተለያዩ ወረርሽኝ በሽታዎች እንዳይለከፍ የኤድስ ሰለባ እንዳይሆን ትኩረት ሰጥተን አንድ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ አለብን እላለሁ።እንግዲህ ህወሃት በዚህ ተግባሩም ምን ያህል አገርን ያረከሰ ወራዳ ድርጅት እንደሆነ በቂ ማስያ ነው።
በሚቀጥለው በሰላም ያገናኘን
The post ይድረስ ለሰፊው የትግራይ ሕዝብ!! – አንተነህ ገብርየ appeared first on Medrek.