Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

ይድረስ ለአቶ በቀለ ገርባ ፣ለአቶ ጁሃር መሀመድ እና አጋሮቻችሁ  ለመተባበር መተማመን ይቅደም!

$
0
0

ሙላት በላይ

ምንም እንኳን እኔ የአማራዉ፣ የኦሮሞዉ፣ የትግሬዉ ፣ተወላጅ ባልሆንም  እንደ ኢትዮጵያዊነቴ የኦሮሞ ምሁራን ለአማራዉ የአቀረቡት የትብብር ጥያቄ ልቤን ሰለነካዉ ለዉጤቱ ስምርት የሚስማኝን ለመግለጽ ነዉ፡፡

ወያኔ ወደ በረሃ የገባሁት አማራን እና የክርስትናን ሃይማኖትን አጥፍቼ ኢት ጵያን ለማፍረስ ነዉብሎ አቅዶ እና በፕሮግራም ነድፎ እየሠራበት መሆኑን ኢትጵያዊዉ ሁሉ የሚያዉቁት ሐቅ ነዉ ፡፡

ወያኔ በእቅዱ መሠረት አየአጠፋዉ ያለዉ አማራዉን ቢሆንም በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊዉን እየጎዳ መሆኑ ለማንም ግልፅ ነዉ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ሊለዉ የሚገባዉ ወያኔ አማራን ለማጥፋት በኦሮሞ ጀርባ ተጠልሎ የሌላዉን ብሔረሰብ እና የአማራዉን ሆድ አደሮቸ  እጀታ፤ ሕዝቡን መጥረቢያ አድርጎ በመጠቀም የአማራዉ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እንዲጠፋ እየተሠራ መሆኑን በዓይናችን እየአንነዉ፡፡ ለዚህም መረጃ የሚሆነዉ፤

1.በ1980 ዓ ም በወለጋ አሶሳ አዉራጃ ባምቤሊ ወረዳ ሸርቆሌ ከትምህርት ቤት ዉስጥ አሽጎ ከ400 በላይ አማራ በሳት መጋየቱ፤

2.በ1982 ዓ ም በወለጋ አሶሳ ከ500በላይ አማራ በሳት መጋየቱ፤

3.ከ1992 እስከ1993 ዓ ም ኦሕዴድ የኦሮሞን ሕዝብ በመቀስቀስ በገጀራ በጥይት አማረዉ መጨፍጨፉ፤

4 በ2001 በበደኖ ወረዳ በብዙ ሽህየሚቆጠሩ አማሮች መገደላቸዉና  መባረራቸዉ፤

5.በ2006 በምዕራብ ሸዋ ዞንአምቦ ወረዳ በኦሕዴድ ካደሬዎች በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ አማሮች መገደል እና መባረር፤

  1. በ2006ዓ ወለጋ በጊምቢና በቄለም አዉራጃ በሽህ የሚቆጠሩ አማሮች መገደልና ከ8ሽህ በላይ ከመኖሪያ ቦታቸው መፈናቀላቸዉ ፤ ለዚህም ግንባርቀደም የኦሮሞ ተወናዋኞች አቶ ሽፈራዉ ሽጉጤ፡ አቶ ዘዉዱ እንዳለ: እንስፔክተር ኃይሉ ድሪባ፡ አቶ ጋሻየ ገቼ ፡መቶ አለቃ ገነነ በየነ ወዘተ ናቸዉ፡፡

ኦሮሞች ከአማራ ጋር ተባብሮ አሁን እየጨፈጨፈአችሁ ያለዉን ወያኔን ማጥፋት ሲገባችሁ የኦነግናሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች አምራር  የወያኔን ኑሮ ለማራዘም የወያኔን ሃሳብ በመቀበልና ያለመዉን ለማሰፈጸም ተባብራቸኋል፡፡ ለዚህም መረጃ የሚሆነዉ አሮሞዉ ከአማራዉጋር ተባብሮ ለመኖር ሳይሆን  መነጣጠልን  ከትዉልድ ወደትዉልድ ለማስተላለፍ በቃል ከሚነገረዉ በጽሁፍ ከሚጻፈዉ አልፎ የአኖሌን ሃዉልት በመትከል በናታቸዉ ጉራጌ የሆኑትን አጼምኒልክ ያልሠሩትን   እንደሠሩና የአማራ ብቻ ተወላጅ እንደሆኑ አድርጎ በመቀስቀስ ለወያኔ ተባባሪነታችሁን አረጋግጣችኋል፡፡ ከዚያም በመቀጠል አቶ ጁሃር መሀመድ አማራ ማለት ክርስቲያን ነዉ በሚል የኦሮሞ ክርስቲያኖቸን ጨምሮ ክረስቲያን በመሆናቸዉ ለማጥፋት አማራን አንገቱን እቆርጣለሁ የሚለ መፈክር አሰምቷል ፤ አቶበቀለ ገርባም አማራ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያደረሰዉ  በደል አብሮለመኖር አያስችልም ሲሉ ተሰምተዋል፤

አሁን ደግሞ ወያኔን ለማጥፋት ከአማራዉ ጋር መተባበር ያስፈልጋል ፤ስለ አንዲት ኢትዮጵያ ማሰብ ፣አለብን በማለት ተባብሮ ወያኔን ማጥፋት  እንዳለብን ጥሪአቅርባችኋል፤ የምትሉት  እዉነት ከሆነ እሰየዉ የሚያሰኝ ነዉ፡፡ መተባበርን የሚጠላ ከወያኔ በስተቀር ያለ አይመስለኝም፤ ነገሩም ሀቅ ነዉ፡፡ ወያኔ የጎዳ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራን ብቻ አይደለም የሚሉ፤ የአማራዉን ጉዳት በማቃለል  አማራዉ ችግርን ተደራጅቶ  እንዳይታገል ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚጥሩ የወያኔ አጋሮች እንዳሉ የታወቃል፤እያንዳንዱ ኅሊና ያለዉ ሰባዊ ፍጡር ሁሉ ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ያስችል ዘንድ በአማራዉ ሕዝብ ላይ እና በሌላዉ  ነገድ ላይ የተፈጸመዉን  በደል አነጻጽረን እንይ ፤

1.ወያኔ አንደኛ ጠላቴ አማራነዉ፤ የወነበድኩተም አማራን ለማጥፋት ነዉ ብሎ በፕሮግራም ነድፎ ለማጥፋት አልሞ ሲነሳ በሌላዉ አላልመም፤ ለዚህ ማረጋግጫ ማነፌቶዉን ማንበብ ነዉ፡፡

2.አማራዉ በኢትዮጵያ እኔ ከምሰጥህ ዉጭ አትኖረም ተብሎ በአንድ ጊዜ ከጉራፈርዳ  ወረዳ ብቻ  ከሰባ ሽህ ሕዝበ በላይ ሲባረር፤ ለሃያአምሰት አመታት በሽህ የሚቆጠር አማራ ሲገደል ሲገረፍ ፤ንብረቱን ሲዘረፍ ሲባረር በሌላዉ ብሔረሰብ ላይ ይህ አልተፍጸመም፡፡

3.የአማራዉን ከልል ለም መሬት የሆኑትን ከአምስት በላይ ወረዳዎችን ለራሱ ሲወስድ በሌላዉ ይህ አልተፈጸመም፤

  1. በአማራዉክልል

ሀ. የወላድ ማምከኛ የወሊድ መቆጣጠሪያ ነዉ ተብሎ   ለወላድ ሴቶች ተሰጥቶ ትውልዱየለሸ ሆኗል፤

ለ. ቀኑ ያለፈበት የማይሠራ መድኃኒት ለሃያ አምስት ዓመታት ያለማቋረጥ ታድሏል በሌላዉ ይህ አለትፈጸመም ፤                  ሐ. የኤድስቫይረስ በመርፌ ሆን ተብሎ ለዐማራው ሲሰጥ  በሌላዉ  ይህ አልተፈጸመም.

መ. አማራዉን የማጥፋት ዘመቻ በድል እያአጠናቀቁ ለመሆናቸዉ መለስ ዜናዊ፤ ሳሞራ የኑስ. ስብሃት ነጋ በፌስታና በኩራት እየተንጎራደዱ አማራን እነዳይነሳ አድርገን ገድለን ቀብረነዋል፤ አከርካሪዉን ሰብረነዋል በማለት የአገሪቱ መሪዎች አረጋግጠዋል ፤ በሌላዉ ይህ አለተፈጸመም፤አልተነገረም፡፡

ሠ. በ1999 ዓም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ የአማራዉ ሕዝብ ቁጥር በ2.5 ሚሊዮንቀንሶ  በመገኘቱ ምክንያቱ ምንድን ነዉ ተብሎ መለስ  ሲጠየቅ፤ በፈገግታ ደስታዉን በመግለጽ ‹በኤድሰ ያለቀ ነዉ› በማለት አረጋግጧል ፤ በልላዉ ይህ አልተፈጸመም፤ ማረጋገጫም አልተሰጠም፤ይህ ከላይ ከ ‹ሀ› እስከ ‹ሠ› የተዘረዘረዉ በአማራው ላይ ብቻ የተፈጸመ የዘር ማጥፋትና  የዘር ማጽዳት ወንጀል ለመፈጸሙ አገሪቷን እየመራን ነዉ የሚሉት ቁነጮ ምሪዎች አፋቸዉን ሞለተዉ የመሰከሩለት ነዉ፡፡ መለስ አማራ ማለት ኢተዮጵያ፤  ኢትዮጵያ ማለት አማራ ነዉ ፤ በሚል ቁንጽል አስተሳሰቡ መነሻነት አማረን ለማጥፋት ሌላዉን ብሄረሰብ አደራጅቶ ማዘመት ብሎ በአማራዉ ላይ አዘመተ፤ በዚህም በኦነግ እና ኦሕዴድ ፈታዉራሪነት የአማራዉ እለቂት እና በሌላዉ ብሔረሰብ የመጠላት ዉጤት አያሳየ ሲመጣ እቀዱ ለመፈጸሙ ደስታዉን እነዲህሲል ገለጸ፤  ‹አማራዎች ሲመነጠሩ ሌላዉ ኢትዮጵያዊ የሚቆጣዉ ኢትዮጵያን የማፍረሱ ዓላማ ሲፈጸም ወለል ብሎ ሰለታያቸዉ እንጂ፤ አማራ ስለሆኑና ለአማራዉ አድልተዉ እንዳልሆነ አማራዉ ይረዳል› መለስ ዜናዊበማልት የሱን እቅድ ዉጤት አጠቃሎ መግለጡ ይታወሳል፤  በተጨማሪም አማራዉ በኢተዮጰያዊነቱ አንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በደልተፈጽሞበታል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ወኪል ነን የምትሉ ሁሉ ከአማራ ጋር የእንተባበር ጥሪ ስታስተላልፉ  ለመተባበር መተማመን  ቅደሚያ ሊሰጠዉ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ በአሳለፍነዉ ዘመን ወሰጥ እንተባበር እና ተባብረናል የሚሉ ቃላት ቢያንስ ከአምሳ ጊዜ በላይ ተነግረዋል፤ በየሳልስቱም ተሰባብረዋል፡፡ ወያኔም  ለዚህ ቋንቋ ጀሮ ጠገብ ሆኗል፤ ስለዚህ ከአማራ ጋር እንተባበር የምትሉ የኦሮሞ ምሁራን ከልባችሁ ከሆነ በተግባር ለመፈጸም ያስችላችሁ ዘንድ፤ አማራዉ ከናንተ ቢያንስ ለተፈጸመበት በደል የእምነት ቃል ይፈልጋል፤  ካልሆነ አማራዉ እነዴት ሊያምን ይችላል?  ምክንያቱም እናንተ እንትባበር እያላችሁ በንግግራችሁ ጎን ለጎን ታህሳስ 3ቀን 2015  በምዕራብ  ሸዋ ዞን አማራዎች ሴቶች ጡታቸዉን ወንዶች ብልታቸዉን   በፒንሳ  እየተጠመዘዘ የቁም ስቃይ እያዩ ተገድለዋል፤ ተባረዋል፤ ለኦሮሞ ትብብር ፈላጊ ምሁራን አማራዉ ከሁሉ በበለጠ በሱ ላይ የተፈጸመዉን ጉዳት እርም ብሎ በመተዉ ሊተባበር የሚችለዉና በመተባበር ወያኔን ለመጣል የሚሰለፈዉ  በናንተ በኩል የሚከተሉት ሀሳቦች በእምነትና በሀዘን ሲቀርቡለት ነዉ፡፡

ሀ. በወያኔ ዘመን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አማራን ለማጥፋት ከወያኔ ጋር አጋር ሁናችሁ መቆየታችሁን                            ለ. በአማራዉ ላይ ከሌላዉ ብሄረሰብ በተለየ የዘረማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ በወያኔ የተፈጸመበት መሆኑን ሐ.ከእነግዲህ በወየኔ አስተባባሪነት በቅጥረኛ ኦሮሞዎች ታዘዉ አማራን የየሚያጠፉትን የአማራዉ ጠላት ጠላቴ ነዉ ብላችሁ የወያኔ ባንዳ የሚሆኑትን ኦሮሞዎች እያጋለጣችሁ ለሌላዉ ብሄረሰብ በማሳወቅ ከናንተ ዉጭ መሆናቸዉን የምታጋለጡ መሆናችሁን ፤የአሰባችሁትንና ዓላማችሁን በመጨመር መግለጫ  ብታወጡ አማራዉጥሪያችሁን በደስታ ይቀበለዋል የሚል ዕመነት አለኝ፤  ካለሆነ ግን አማራዉ የሚተርተዉ ተረት አለ፤ አሱም ‹የጠገብ ጂብ ሰድጄ፤ የተራበጅብ አልተካም› የሚል፤

ከመግለጫዉ በተጨማሪ የወያኔ ተቃዋሚ ነኝ የሚሉትን የአማራ ምሁራን፤ የአማራዉን ንቅናቄ ኃይል  የሲቪከ ድርጅት ወዘተ ጠርቶ በጋራ ዉይይት ማካሄዱ መተማመንን ይፈጥራል የሚል ዕምነት አለኝ፤ ስለዚህ የሰከረዉ ዓሣ ወያኔ ሳመልጣችሁ ተግባራዊ እነድታደርጉ የአማራዉምሁራን ንቅናቄወችና ድርጅቶች ለጥሪያአቸዉ ቀናና ፈጣን መላስ ሰጥችሁ በወያኔ ላይ በሁሉም ክልለና ቦታ  ዘመቻ በማካሄድ የሠፊዉን ሕዝብ ቀንበር  ሰባብራችሁ እንደምት ጥሉት   ተስፋ አለኝ፡፡ ከተስፈኞቹ አንዱ

The post ይድረስ ለአቶ በቀለ ገርባ ፣ለአቶ ጁሃር መሀመድ እና አጋሮቻችሁ  ለመተባበር መተማመን ይቅደም! appeared first on Medrek.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles