“አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም? ለመሆኑ አማራ ማነው?” የሚል ውይይት ተነሥቶ ሳይ፥ ታሪክን መሠረት በማድረግ የማውቀውን በጽሑፍ አቅርቤ ነበረ። ድርሰቴን ያነበበው ሁሉ አስተያየቴን ቢቀበለውም፥ “ደመ ንጹሕ አማራ ነን” የሚል እምነት ያላቸው አንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ቅሬታ ያዘለ አስተያየት አንሥተዋል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ ያነበቡ አይመስለኝም። ባያነቡም በግምት እንዲደርሱበት አንድ ነገር በማንሣት ልጋብዛቸው።
የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመኑ በሺ ዓመታት የሚቆጠር ነው። ይህ ማለት ብዙው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ መንግሥት ሥር በሺ የሚቆጠር ዓመታት አብሮ ኖሯል ማለት ነው። በረይቱማና ቦረንም ወደ ማህል ኢትዮጵያ መፍለስ የጀመሩት በአጼ ወናግ ሰገድ ዘመን (1500-1533) ቢሆንም፥ ፍልሰታቸው ከሀገር ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ ነበር። እንግዲህ፥ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ደማቸው ሳይደባለቅ “በንጹሕ” በጉርብትና ኖረዋል እንላለን? እንዴት ሆኖ! ለምሳሌ፥ በደርግና በወያኔ ጭካኔ ምክንያት መሰደድ ከጀመርን አምሳ ዓመት አልሞላውም። በዚች በአጭር ዘመን እንኳን ከአስተናጋጆቻችን ሕዝቦች ጋር ሳንነካካ “ንጹሕ ደም” ያቆየን ሁላችንም አይደለንም። ===-–[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——====
The post ታሪክ አይፈራም – ጌታቸው ኃይሌ appeared first on Medrek.