Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

‹‹ታስሬ ስንቅ አላቀበለችኝም›› በማለት እናቱን የገደለው በእስራት ተቀጣ

$
0
0

ነዋሪነቱ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ቡርቃ ነገያ ቀበሌ ገ/ማህበር ቡሎ መንደር ውስጥ ነዋሪ የሆነው ባሩዲን አብዲላሂ ሀሰን ቀደም ሲል በሰው አካል ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶት ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ማረሚያ ቤት ታስሮ ይቆያል:: በደተጋጋሚ ጊዜ የምበላው ምግብ እንድታመጣልኝ እና እድትጠይቀኝ ሰዎች ብልክባት ምንም ምላሽ ልትሰጠኝ ፍቃደኛ አልሆነችም በማለት ቂም ይዞ ከማረሚያ ቤት የእስር ጊዜውን ጨርሶ እንደወጣ ወላጅ እናቱን ገሎ ለመበቀል ይወስናል:: በውሳኔው መሰረት መሰከረም 1 ቀን 2009 ዓ/ም ወላጅ እናቱ የሆኑትን ወ/ሮ ፋጡማ ሙሳ እንጨት እፈልጥልሻለሁ በማለት መጥረቢያ ይዞ ወደ ጫካ በመሄድ ትንሽ እንደቆየ እናቱን እየፈለጥኩልሽ ስለሆነ ነይና ውሰጅ ብሎ እናትየዋን ያስጠራታል::

ስለ ጉዳዩ ምንም የማያውቁት እናት አገር ሰላም ነው ብለው የመጡት ለልጆቻቸው ምሳ የሚያዘጋጁበት ተፈለጠ የተባውን እንጨት ለመልቀም ጎንበስ እንዳሉ በያዘው መጥረቢያ ማጅራታቸውን መቶ ከጣላቸው በኃላ በተደጋጋሚ በመወጋጋት በአሰቃቂ ሁኔታ ገሎ ከአካባቢው ለመሰወር ሲሞክር የአካባቢው ነዋሪዎች ይዘው ለፀጥታ አካላት ያስረከቡታል:: ወላጅ እናቱን በመግደል ወንጀል ክስ ተመስርቶበት በኮምቦልቻ ወረዳ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ፖሊስ እና አቃቤ ህግ ምርመራ መዝገቡን በጋራ አጣርተው ለማየት ስልጣን ላለው አካል እንዲተላለፍ ያደርጋሉ:: ጉዳዩን የተመለከተው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀለኛው ባሩዲን አብዱላሂ ሀሰን ወንጀሉን መፈፀሙ በአቃቤ ህግ እና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ የካቲት 24 ቀን 2009 ዓ/ም በአስተዋለው ችሎት የቅጣት ማክበጃ እና መቅለያ አንቀፆችን ከመረመረ በኃላ ጭካኔ በተሞላበት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደላቸው በመሆኑ ወንጀሉን በማክበድ እጁ ከተያዘ ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በሃያ አምስት አመት እስራት እንዲቀጣ የተፈረደበት መሆኑን ፍርድ ቤቱን በመጥቀስ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገልፃል::

ምንጭ: ፖሊስና ርምጃው

The post ‹‹ታስሬ ስንቅ አላቀበለችኝም›› በማለት እናቱን የገደለው በእስራት ተቀጣ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Latest Images

Trending Articles



Latest Images