የኢኮኖሚ አብዮት የአንድ አገር ኢኮኖሚን አንድ ቡድን ወይንም ከአንድ ብሔረሰብ የተውጣጡ ቡርዣዎች በበላይነት ተቆጣጥረውታል፤ በብቸኛነት በልጽገውበታል፤ በሀብት ናጥጠዋውበታል፣ ወዘተ የሚሉ መነሻዎችን ታሳቢ የሚያደርግ ነው።
እየሰማነው ያለው የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮትም አንድ ቡድን ወይንም ከአንድ ብሔረሰብ የተውጣጡ ቡርዣዎች ኦሮሞን በበላይነት ተቆጣጥረው እያደኸዩ በብቸኛነት የበለጽጉና በሀብት የናጠጡ ቱጃሮች እንዳሉ መነሻ የሚያደርግ መሆን አለበት።
ጥያቄው ኦሮሞን በበላይነት ተቆጣጥሮ እያደኸዩ በብቸኛነት የበለጸገው፤ በሀብት የናጠጠውና ቱጃሮ የሆነው መደብ ነው? ወይንስ ከአንድ ብሔረሰብ የተውጣጡ ትጃሮች ናቸው? የሚለው ነው።
የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት መነሻው ከዚያው ከኦሮሞዎች መካከል የተውጣጡ ግለሰቦች የፈጠሩት ቡድን በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ ቱጃር የኦሮሞ መደብ ሊሆን ይችላል የሚለውን መላ ብንመታ መስደን መፈተሽ እንችላለን። ሆኖም ይህ መላምት ውሀ አይቋጥርም፤ ምክንያቱም ከዚያው ከኦሮሞዎች መካከል የተውጣጡ ግለሰቦች የመሰረቱትና አብዮትን ያህል ነገር ሊወልድ የሚችል ቡርዣ ቡድን ደብዛው የለምና።
የኦሮሞን የኢኮኖሚ አብዮት የወለደው በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ የኦሮሞ መደብ ሊኖር ቢችል እንኳ በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ ቱጃር የኦሮሞ መደብ ሊሆን የሚችለው ወያኔ የፈጠረው ኦህዴድ መደብ ብቻ ነው። ወያኔ የፈጠረው የኦህዴድ መደብ ደግሞ «የኦሮሞን የኢኮኖሚ አብዮት እየመራሁ ያለሁ እኔ ነኝ» እያለ ስለሆነ የአብዮቱ ምክንያት ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም የአብዮቱ መነሻ ምክንያት የአብዮቱም መሪ ሊሆን አይችልምና። ስለዚህ የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት መነሻ ምንክያት በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ የኦሮሞ መደብ ሊሆን አይችልም ማለት ነው።
የኦሮሞን የኢኮኖሚ አብዮት የወለደው በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ የኦሮሞ መደብ ካልሆነ በኦሮሞ ላይ ነግሶ ኦሮሞን እያደኸየ፣ሀብቱን በብቸኛነት በመቆጣጠር በንዋይ የናጠጠ የኢኮኖሚ አብዮት ሊወልድ የሚችለው መንግሥታዊ መዋቅሩን በመቆጣጠር የቅሚያና ዘረፋ ማህበር፤ የግድያና የማሰቃያ ድርጅት የሆነው ወያኔ የወለደው የትግራይ ቱጃሮች አገዛዝ ነው።
ስለዚህ የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት ብቸኛ መነሻው ለሁሉም ሰው ግልጽ እንደሆነው ኦሮሞንና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን በበላይነት ተቆጣጥሮ እያደኸዩ በብቸኛነት የበለጸገው፤ በሀብት የናጠጠውና ቱጃሮ የሆነው ከትግራይ ብሔረሰብ የተውጣጡ ቡርዣዎች የወለዱት በደል፤ የሚፈጥሙት ብዝበዛና የአገር ሀብት ምዝበራ ነው። የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት የወለዱት የትግራይ ቡርዣዎች የፖለቲካውን ስልጣን የተቆጣጥሩ ዘራፊዎችና ነፍሰ በላ ወንጀለኞች ጭምርም ናቸው።
እንግዲህ! ወያኔ «የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት» ሲል ጀመርሁት የሚለን «መርሀ ግብር» መነሻው ወያኔ የፈጠረው የትግራይ የበላይነት የወለደውና ወያኔ ራሱ በኦሮሞ ላይ ነግሶ የአገሪቱን ሀብትና ስልጣን ሁሉ በብቸኛነት በመቆጣጠሩ፤ የትግራይ ቱጃሮች የወያኔን ስልጣን ተጠቅመው በሀብት በመናጠጣቸውና ሌላውን በማደህየታቸው፤ ኢትዮጵያን በመበዝበዝና በመመዝበራቸው በዚህም የተነሳ ሕዝቡ ለረሃብና እርዛ በመጋለጡ የተከተለው መረን የለቀቀ ኢፍትሀዊነት የወለደው ብዝበዛ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ይህ ማለት ወያኔ «የኦሮምያ የኢኮኖሚ አብዮት» ብሎ በጀመረው እንቅስቃሴ ከትግራይ የተውጣጡ ቱጃሮች ኦሮሞንና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን በበላይነት ተቆጣጥረው እያደኸዩ በብቸኛነት እንደበለጸጉ፤ በሀብት እንደናጠጡና የፖለቲካ ስልጣኑን ተገን አድርገው ቡርዣ እንደሆኑ እየነገረን ነው ማለት ነው።
ከትግራይ ብሔረሰብ የተውጣጡ ቡርዣዎች የኢትዮጵያውያን ደም በመምጠጣቸው የኢኮኖሚ አብዮት እንደሚያስፈልግ ወያኔ እየነገረን ከሆነ፤ አብዮቱ የሚሳካው የኢኮኖሚ አብዮቱን የወለዱት መነሻዎች ተጠራርገው ሲወገዱ ስለሆነ የኦሮምያ የኢኮኖሚ አብዮት ሊሳካ የሚችለው ወያኔ ከነግሳንግሱ ሲነቀል ብቻ መሆኑ ግንዛቤ መያዝ ይኖርበታል። የኢኮኖሚ አብዮቱን የመወለድ ወያኔ የአብዮቱ መሪ ሊሆን አይችልም። በራሱ በወያኔ ቋንቋ አብዮቱን የወለደው የአብዮቱ አደናቃፊ ስለሆነ መወገድ አለበት። ስለዚህ ወያኔ እውነተኛ የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት እንዲካሄድ ከፈለገ የኦሮሞን የኢኮኖሚ አብዮት የወለደው ወያኔ መወገድና ከወያኔ ጋር ተጠግተው በዘረፋ የከበሩ የትግራይ ባለሀብቶች ንብረት መወረስ ይኖርበታል። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ታምርም ቢፈጥር የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዮት ሊሳካ ቀርቶ ሊታሰብ አይችልም።
The post የኢኮኖሚ አብዮት ሲባል. . .- አቻምየለህ ታምሩ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.