Quantcast
Channel: Amharic News – Medrek
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

አቶ ግርማ ሠይፉ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ኃሳብ ይዘው ቀርበዋል – ግርማ በቀለ

$
0
0

‹‹ የምስራች //›› አዲስና ዘመናዊ መሲህ ፓርቲ እየመጣ ነው፤ እንዳያመልጣችሁ//

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ግርማ ሠይፉ ማሩ

አቶ ግርማ ሠይፉ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ኃሳብ ይዘው ቀርበዋል ፡፡ ግን ከዚህ በፊት –በደምሳሳው እንዲህ ብለው ነበር፡፡
‹‹ የማንም ፖለቲካ ተሳትፎ እስካዋጣው ነው፤ ማንም /እኔ ካላዋጣው/ኝ የመተው መብት አለው/ኝ ››
‹‹ የፓርቲ ፖለቲካ አብቅቶለታል፣ ተቀብሯል፤ ከአሁን በኋላ ‹ፓርቲ › ስለመመስረት ማሰብ አያስኬድም ፤ …››
‹‹ ከኢ/ር ግዛቸው ጋር ለአንድነት ፕሬዝዳንት ተወዳድረው በዝረራ ሲሸነፉ– ይህ ጠ/ጉባኤ ራሴን ለዚህ ቦታ ማጨቴ ትክክል እንዳልሆነ በግልጽ አሳይቶኛል፣ ወደ ታች ወርጄ ከወረዳ ተነስቼ መምጣት እንዳለብኝ ተረድቻለሁ›› ብለው በኋላ ‹‹በአንድነት ውስጥ ምን ሲያደርጉ ቆዩ፣ ለአንድነት መፍረስ/ መቀማት በሂደቱ ምን አድርገው ነበር ?
ሃሳብ የመለወጥን ከትናንቱ ስህተት ተምሮ በሃሳብ ማደግና ባደገው ሃሳብ ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ መደራጀትን ስህተት ነው ማለት አይቻልም፤ እያልኩም አይደለም፡፡ ግን የአስተሳሰብ መዋቅሩን መጠየቅ ፣ መመርመር ተገቢ ነው፡፡
አቶ ግርማ ሠይፉ በፖለቲካ ተሳትፎ ከጀመሩ ወዲህ ባለው ጊዜ — በአዲሊ፣ በቅንጅት ፣ በአንድነት/መድረክ ፣ አልፎም ብቸኛ የፓርላማ ተወካይ ሆነው አይተናቸዋል፡፡ በነዚህ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎም ከላይ ከጠቀስናቸው አባባሎቸ ጋር አጣምረን ስንመረምር ጥያቄዎች ማንሳታችን አይቀርም ፡፡ እንዲህ የሚሉ፡-
• የፓርቲ ፖለቲካ አብቅቶለታል …. የሚለውን ሃሳባቸውን የሚያስቀይር ምን አዲስ ነገር ተገኘ/አገኙ ?
• ቀድሞ ከነበሩበት ፓርቲዎች የተለየና የተሻለ ለውጤት የሚያበቃ ምን አዲስ ዘዴ፣ መፍትሄ አግኝተው/ልን መጡ ?
• የተቃውሞ ጎራውን ‹ድክመት›ና ተደጋጋሚ ክሽፈት ብቻም ሳይሆን እርሳቸው ለፓርቲያቸው መፍረስ/መቀማት ስላደረጉት አሉታዊ አስተዋጽኦ መርምረዋልን ? ከመረመሩ ለሰሩት ስህተት ይቅርታ ለመጠየቅና ከስህተታቸው ለመማራቸው ሊያስረዱን ተዘጋጅተዋል?
• ካሉት ፓርቲዎች ገብተው መታገል አይቻላቸውም ፤ የሚመጥነኝ የለም የሚሉ ከሆነ ካሉት የተለየና የበለጠ ምን ይዘውልን መጡ… ?
• በአዲሱ ፓርቲ ከወረዳ ተነስተው ሊመጡ ነው ያሰቡት ወይስ ከአናት ሆነው ሊመሩት ?
እነዚህ ባልተመለሱበት ‹አዲስ ፓርቲ› 21ዱን ወደ 22 ከማሳደግ የዘለለ ፋይዳው አይታየኝም ፡፡ አካሄዱም በምግብ ቤቶች ‹‹ በአዲስ መልክ ምግብ ጀምረናል›› ከሚለው ማስታወቂያ የተለየ አልሆነልኝም፡፡ ለመሆኑ አቶ ግርማ ሠይፉ ሲተቹት የነበረው ‹‹የአንድነት መንፈስ ወራሽ›› ነው የተባለው ‹‹ነጻነት›› የሚባለው ፓርቲ የት ደረሰ ? ነብስ ይማር አቶ ብሩ ቤርመጅ፡፡
በአጠቃላይ ለአገር መፍትሄ ወይስ ለግል ዝናና ዕውቅና ? ወይስ እኛ የማናውቀው የፓርቲ ፖለቲካ የሚያስገኘው ‹‹ጥቅም ››/ አለ፣ አዋጪ ‹ኢንቨስትመንት› ነውን ? ብለን መጠየቅ አግባብ ነው፡፡ ከሆነም መልካም ግን እርሳቸው ከዝናና ዕውቅና ጋር ተከትሎ የሚመጣውን ሸክም መሸከም አይችሉም እንጂ፡፡ በፓርላማ –ስለሙስሊሞች ለምን አልጠየቁም ሲባሉ፣‹‹…እንደእኔ ተመርጦ መጠየቅ ይቻላል … ›› … ምርጫ 2007 ለምን መግባት እንደወሰኑ ‹‹…. በቂና ብቁ ዕጩና ድምጹን የሚጠብቅ ህዝብ ስላለን፣ በምርጫው አሸንፈን መንግስት ለመመስረት እንደምንችል እርግጠኛ ስለሆንን…›› በማለት የመለሱትን ፣ሙስሊም ኮሚቴዎች ሲፈቱ ለሽፋን ወዳጅ ተጠግተው ከቤታቸው መገኘታቸው፣ የምርጫ 2007 መደምደሚያንም እናስታውሳለን፣ ድምጹን የሚጠብቅ ያለውን ህዝብ አስተባብሮ ‹ፓርቲውን› ለመጠበቅ/መከላከል ሳይችል፣ራሱ ግርማ ከቢሮው መኪናውን ለምኖ ሲያወጣ፣ ለድምጽ መስጫው ቀን ሳይደርስ ሲቀር ታዘብን፡፡
ሁሉም በውስጡ ያለውን አምባገነንነት፣ ስውር የግል ፍላጎት፣ ሴራና ተንኮል ደብቆ፣ ከኢህአዴግ መጠየቅም ሆነ መጠበቅ አያስኬድም፡፡ ዕድሉን ቢያገኝ /ባለማግኘቱ ተረፍን እንጂ/ የተንገሸገሽንበትን ስላለመድገሙ ምንም መተማመኛ የለንም፡፡ ይህን እያልን ከነማን ጋር ወይም እነማንን በአጃቢነት አስከትለው እንደሚመጡ ጠብቀን የምናየው ይሆናል፡፡ግን በቀደም ዕለት አቶ ሺፈራው ሽጉጤ በ‹ድርደሩ› ላይ ‹‹ . . . ተገደን አይደለም፣ የመድብለ ፓርቲ አካሄዳችን ለማጠናከር ፣ . . . አዳዲስ ፓርቲዎችም እንዲፈጠሩ በማድረግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ነው፡፡›› ማለታቸውን በእግረ መንገድ ማስታወስ አይጎዳም፡፡
ስለዚህ ከአመት በፊት ያልኩትን እደግማለሁ‹‹ የታደሳችሁ ‹ሙሴዎች› ሆይ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ባህሩን ገምሳችሁበት ለማሻገር የወረደላችሁን ‹በትር› አሳዩንና እንከተላችሁ፡፡ ያሊያ እናንተን መሳይ ብዙ ሃሳዊ መሲሆች መጥተው አልፈዋል፣በበቂ አሉም፤ በህዝብ ሥም አትነግዱ፣ ህዝብን አታወናብዱ፤ እናም አርፋችሁ ተቀመጡ //›› እንላለን፡፡
በቸር ያገናኘን፡፡ 25/07/09.

The post አቶ ግርማ ሠይፉ አዲስ ፓርቲ የመመስረት ኃሳብ ይዘው ቀርበዋል – ግርማ በቀለ appeared first on ሳተናው: Ethiopian Amharic News | Breaking News 24/7: Your right to know!.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2265

Trending Articles